TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በኦሮሚያ ክልል በአንድ ቀን 143 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

በኦሮሚያ ክልል የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በእጅጉ እየጨመረ ይገኛል፤ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 2,051 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ ሶስት (143) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከነዚህ መካከል፦

- 31 ከነቀምቴ
- 22 ከሰበታ
- 16 ከአዳማ
- 13 ከቢሾፍቱ
- 12 ከፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን
- 10 ከምስራቅ ሸዋ ይገኙበታል።

በድጋሚ ነቀምቴ፣ሰበታ፣ ቢሾፍቱ ፣ሞጆ፣ አዳማ በሌሎችም የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ውስጥ የምትኖሩ ነዋሪዎች እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በዚህ አጋጣሚ መልዕክት እናስተላልፋለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#HumanRightsWatch

የሁቲ ታጣቂዎች ኮቪድ-19ኝን ምክንያት በማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከሰሜናዊ የመን አስወጥተዋል እንዲሁም ገድለዋል ሲል ሂዩማን ራይተስ ዎች ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ወደ ሳዑዲ ድንበር የተባረሩት ስደተኞች በድንበሩ ጠባቂዎች ሌላ ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ የተወሰኑ ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች የሚቆጠሩት ወደ ተራራማ አካባቢ ሸሽተዋል ብሏል።

ድምፃቸውን ለመብት ተሟጋቹ ድርጅት የሰጡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ለቀናት ያለምግብ እና ውሃ እንደቆዩ ተናግረው ከዚያ በኋላ ወደ ሳዑዲ መግባት ቢችሉም ንፅሕና በሌለው ሥፍራ ታጉረው እንደከረሙ ተናግረዋል።

ሕፃናትን ጨምሮ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አሁንም በየመን እና ሳዑዲ ተራራማ ድንበር አካባቢ ሊኖሩ እንደሚችሉ ድርጅቱ ገምቷል።

የሂውማን ራይትስ ዎች ጥናት ቡድን አባላት ናዲያ ሃርድማና የሳዑዲና የየመን ኃይሎች ኢትዮጵያውያኑ ላይ የፈፀሙትን ግፍ ወቅሰው የተባበሩት መንግሥታት ለጉዳዩ መፍትሔ እንዲሰጠው አሳስበዋል።

HRW:https://www.hrw.org/news/2020/08/13/yemen-houthis-kill-expel-ethiopian-migrants

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት! ዛሬ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የዎላይታ ህዝብ አመራሮች፣ ምሁራንና አክቲቪስቶች ለፍርድ ቤቱ ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ብይን ለመስጠት ለነገ 9:00 ተቀጥረዋል። Via Hailemichael T Lemma / Elias Meseret @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

ዛሬ የዎላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ፣ ምሁራን እንዲሁም አክቲቪስቶች ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብት የተፈቀደላቸው ቢሆንም አቃቤ ሕግ ይግባኝ ጠይቋል። ይግባኝ የቀረበለት ችሎትም ብይን እንደሚሰጥበት እየተጠበቀ ይገኛል።

Via Hailemichel T Lemma
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዎላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ፣ ምሁራን እንዲሁም አክቲቪስቶች በዋስ ከእስር እንዲፈቱ ተወሰነ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዎላይታ ዞን አመራሮች ከእስር ተፈቱ!

ፍርድ ቤት በዋስ እንዲፈቱ የወሰነላቸው የዎላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ፣ ምሁራን እንዲሁም አክቲቪስቶች ከእስር መፈታታቸውን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ አባላት አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1 ፦

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 406 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- 3 ከመተከል ዞን ጉባ ወረዳ
- 2 ከአሶሳ ዞን አሶሳ ወረዳ
- 1 ከአሶሳ ህዳሴ ኤርፖት

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 587 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 66 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የሁለት ሰዎችም ህይወት አልፏል።

አጠቃላይ በሀረሪ ፦
- 432 በቫይረሱ የተያዙ
- 14 ሞት
- 80 ያገገሙ

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 552 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 109 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ከነዚህ መካከል 27 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው።

አጠቃላይ በትግራይ ፦
- 1,361 በቫይረሱ የተያዙ
- 10 ሞት
- 710 ያገገሙ

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 332 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 26 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከማህበረሰቡ በተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው። በተጨማሪ ትላንት የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4,340 የላብራቶሪ ምርመራ 72 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከነዚህ መካከል

- 15 ከባህር ዳር
- 14 ከሰሜን ሸዋ ዞን
- 7 ከደ/ጎንዳር ዞን
- 13 ከሰ/ወሎ ዞን
- 9 ከምስ/ጎጃም ዞን
- 6 ከደሴ ከተማ
- 4 ከማዕ/ጎንድር
- 5 ደ/ወሎ ዞን
- 3 አዊ ብ/ሰብ ዞን
- 2 ከምዕራብ ጎጃም ዞን
- 1 ከደቡብ ጎንደር ዞን

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 68 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል።

-3 ጅግጅጋ
-1 ሞያሌ

@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 1,086 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 14,688 የላብራቶሪ ምርመራ 1,086 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 394 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 26,204 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 479 ደርሷል ፤ እንዲሁም አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 11,428 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ስንት ሲደርስ ነው መዘናጋቱ የሚቆመው ?

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 1 ብቻ ተብሎ የጀመረው የኮቪድ-19 ኬዝ ዛሬ በአንድ ቀን ከ1,000 በላይ ሰዎች ላይ ተገኝቷል።

ዛሬ የተመዘገበው (1,086 ኬዝ) ወረርሽኙ ሀገራችን ከገባ ጊዜ አንስቶ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው። የዕለታዊ የሟቾ ቁጥርም ከአንድ አሃዝ ወደ ሁለት አሃዝ ከተሸጋገረ ሰንብቷል።

ምን እስክንሆን ነው የምንጠብቀው ?

ኮቪድ-19 ይገድላል
ኮቪድ-19 ቤተሰብ ይበትናል
ኮቪድ-19 ልጆችን ያለ ወላጅ ፤ ወላጆችን ያለ ልጅ ያስቀራል
ኮቪድ-19 የሀገርን ኢኮኖሚ ያናጋል
ኮቪድ-19 የጤና ስርዓቱን አሽመድምዶ ይጥለዋል።

መሸፈን ፣ መታጠብ ፣ መራራቅ ፣ መቆየት - እነዚህን እጅግ በጣም ቀላል የመከላከያ መንገዶች መተግበር አቅቶን የሁል ጊዜ ፀፀት እናትርፍ ?

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃ #2 ፦

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 601 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከፍተኛ ኬዝ ከተመዘገበባቸው ክፍለ ከተሞች መካከል ቦሌ (106) ፣ ኮልፌ ቀራንዮ (120) ፣ ጉለሌ (62) ፣ አራዳ (65) ፣ ንፋድ ስልክ ላፍቶ (50) ይጠቀሳሉ።

በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት በአ/አ 14 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል (10 ሰዎች ከአስክሬን ምርመራ፣ 4 ሰዎች ከጤና ተቋም)

#SIDAMA

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 247 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 29 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፤ 1 ሰው አገግሟል፣ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

አጠቃላይ በሲዳማ ፦

- 517 በቫይረሱ የተያዙ
- 11 ሞት
- 133 ያገገሙ

#SNNPRS

ባለፉት 24 ሰዓታት በደቡብ ክልል በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 33 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- 10 ከጋሞ (3 ጬንቻ፣ 3 ገረሴ፣ 2 ቦርዳ፣ 2 አርባ ምንጭ)
- 5 ከኮንሶ (ኬና)
- 5 ከሸካ (3 ማሻና 2 ቴፒ)
- 4 ከጌዴኦ (ዲላ)
- 3 ከወላይታ (ጉኑኖ፣ ዳ/ወይዴና ሶዶ)
- 3 ከጎፋ (ሳውላ)
- 2 ከስልጤ (አሊቾ ውሪሮ)
- 1 ከጉራጌ (ወልቂጤ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እኔም የዕርቅ ሃሳብ አለኝ!

'እኔም የዕርቅ ሀሳብ አለኝ' በሚል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከእርቀ ሰላም ኮሚሽን ትብብር የተዘጋጀው ባህላዊ የእርቅ ስርዓቶች ላይ ያተኮረ የፅሁፍ ውድድር ላይ ለተሳተፉ ወጣቶች (አዲስ አበባና አካባቢው) የምሥጋና መርኃግብር ዛሬ ተከናውኗል።

ዛሬ የተካሄደው ዝግጅት እርቀ ሰላም ኮሚሽን በውድድሩ ላይ ጊዜያቸውን ሰጥተው፣ አንብበውና ጠይቀው የተሳተፉ ወጣቶችን ለማመስገን እንዳዘጋጀ የኮሚሽኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሕይወት አለማየው ተናግረዋል፡፡

የባህላዊ የዕርቅ ሀሳቡን በጹሑፍ ያቀቡ የተሳተፉ ወጣቶችም የተዘጋጀው ዕድል እንደጠቀማቸውና እንደተለወጡበት የተናገሩ ሲሆን ወጣቱን በሰላምና ዕርቅ አሳታፊ የሆኑ መርኃግብሮች ሊበረታቱና ሊደገፉ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በቀጣይም የጹሑፎቹ ይዘት በባለሞያዎች ከተገመገመ በኋላ የተመረጡ ሥራዎችን በማደራጀት ልዩ የሽልማትና የዕውቅና መርኃግብር ለማዘጋጀት ታስቧል።

አጠቃላይ ከተሳተፉ ከ370 በላይ የግልና የቡድን ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ እና አከባቢዋ የሚገኙት ብቻ በ7 ቡድን ተከፍለው የሚካሄድ ሲሆን ለሌሎች ተሳታፊዎችም ባሉበት የዕውቅና ሰርተፊኬቱ የሚደርሳቸው መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምሥጋና በ'እኔም በዕርቅ ሀሳብ አለኝ' በሚለው ውድድር ለተሳተፋችሁ ወጣቶች!

(TIKVAH-ETHIOPIA)

በየአከባቢያችሁ ያለውን 'ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት' ጠይቃችሁ፣ አንብባችሁ እና ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ከሁሉም ሀገራችንን ክፍሎች በሚያስብል መልኩ ለተሳተፋችሁ ወጣቶች ምሥጋናችን ይድረሳችሁ።

ለሀገር የሚተርፍ ባህላዊ የዕርቅ ሃሳብ በአከባቢያችን ፣ በማህበረሰባችን ፣ በቤተሰባችን እንደሚገኝ በሥራዎቻችሁ ተረድተናል።

ወጣቶች ስለ ሰላምና ስለ ዕርቅ መጻፍ እንዲሁም ለሌሎች የሚተርፍ ሥራ መስራት እንደሚችሉም አሳይታችኋል።

ሀገራዊ ዕርቅና ሰላም ያለ ወጣቶች ተሳትፎ ፈጽሞ አይተገበርም። ወጣቱ የሚታረቅ ብቻ ሳይሆን አስታራቂ እና ሰላምን የሚገነባ እንደሆነ እናምናለን።

በዚህ ሀገራዊ ውድድር ላይ የተሳተፉ ወጣቶችም ምሳሌ ሆነዋልና በቲክቫህ ስም እናመሰግናለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የልብ ማዕከል በኢትዮጵያ በእናተ ድጋፍ የህፃናትን ህይወት በመታደግ ላይ ነው።

ስለ አጋርነታችሁ ከልብ እያመሰገንን አሁንም በርካታ ህፃናት ወረፋ በመጠበቅ ላይ ናቸው እና ድጋፋችሁ አይለየን።

ወደ 6710 ፦

A ብለው በመላክ 1 ብር
B ብለው በመላክ 10 ብር
C ብለው በመላክ 50 ብር
D ብለው በመላክ 100 ብር

በባንክ አካውንቶቻችን ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ : 1000001839806
ዳሸን ባንክ : 0041600483011
አዋሽ ባንክ : 01308236167000

የልብ ማዕከል በኢትዮጵያ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ21 ሚሊዮን አለፉ!

በመላው ዓለም በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 21,095,525 ደረሰ ከነዚህ መካከል 757,779 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። 13,946,466 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸው ታውቋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ ሞት የተመዘገበባቸው ሀገራት ፦

- ብራዚል 1,301 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል

- አሜሪካ 1,284 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል

- ህንድ 1,006 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል

- ሜክሲኮ 737 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ዛሬም መፍትሄ ያላገኘው የቴፒ ጉዳይ!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ እጅግ በርካታ ጊዜ ቴፒ ከተማ ስላለው ሁኔታ ከቴፒ አባላት የሚመጡትን መልዕክቶች ሲያጋራ መቆየቱ ይታወቃል።

ዛሬም በአካባቢው ያለው ችግር አልተፈታም ፤ ባለፉት 5 ቀናት በቴፒ ከተማ የንግድ፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች እንደቆሙ የቲክቫህ ቴፒ አባላት አሳውቀዋል።

መልዕክታቸውን ለቲክቫህ የላኩ አባላት መንግስት አሁንም ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዎጌታ ኤፍ ኤም 96.6 ስርጭቱ ተቋረጠ!

ዛሬ ጥዋት ዎጌታ ኤፍ ኤም 96.6 በመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲዘጋ በመደረጉ ስርጭቱም ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ለማወቅ ችለናል።

በጉዳዩ ላይ የጣቢያው ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ይህ እርምጃ በምን ምክንያት ሊወሰድ እንደቻለ የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል።

ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አሳውቀናል ምላሽም በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia