TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#UPDATE

የወላይታ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ተቀመጧል። ጉባኤው፦

1.የወላይታ ብሄር የክልልነት ጥያቄ የደረሰበት ደረጃ ይገመግማል።

2.ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

(ኦ ኤም ኤን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ምሽት በኖርዌይ የኖቤል ተቋም የክብር እንግዳ መዝገብ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክብር እንግዳ መዝገቡ ላይ በአማርኛ አስተያየታቸውን ያሰፈሩ የመጀመሪያው ሎሬት መሆናቸውን ከኖርዌይ የኖቤል ተቋም የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም...

• አመራሩ ብሔሩን እየለየ የሚያገለግል ከሆነ አስቸጋሪ ነው። በእያንዳንዱ ክልል የተለያየ ብሔር ብሔረሰብ አለ። መንግሥት እኩል ካላገለገለ አድሎ ከተፈፀመ በአግባቡ አልተገለገልኩም የሚል ጥያቄ ያቀርባል።

• አንዱ ከአንዱ ጋር የሚገፋፋ ከሆነ አንድነት አይመጣም። ሰው ሲሞት ለምን ሞተ ከማለት ይልቅ የየትኛው ብሔር ተወላጅ ብዙ ሞተ እየተባለ ነው። ይህ ቀድሞ መሠራት የነበረበት ሥራ ባለመሥራቱ የመጣ ነው።

• ማንኛውም ሰው የራሱን ማንነት እንዲከበርለት የሚፈልግ ከሆነ የሌላውንም እኩል ማክበር አለበት። እዚህ ላይ ትልቅ ክፍተት ነበር።

• ስለብሔር ማሰብ ላይ ብቻ መተኮር የለበትም። አንዲት ትልቅ አገር መኖሯንም መዘንጋት የለበትም።

• አገርን ከመገንባት ለሌሎች ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩል ክብር እና እውቅና መስጠት ያስፈልጋል።

• ብሔራዊ ማንነት ቢኖረንም ከአገራዊ ማንነት ውጭ መሆን አንችልም። እርስ በእርሳችን እንከባበር የምንለው አገራችንን ለመገንባት ነው።

• ትልቁ ችግር አገራዊ እና ብሔራዊ ማንነት ሚዛናቸውን ጠብቆ አለመሄዳቸው ነው። ለራስ ብሔር ብቻ ማሰብ ትርጉም የለውም።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-10

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ)

(አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
- ዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት "IYF" የተሰኘ የኮሪያ በጎ ፈቃደኛ ቡድን የአስተሳሰብ ማቅኛ "ማይንድ ሴት" ስልጠና ከጋሞ ዞን ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ከ850 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች በትላንትናው እለት በአርባምንጭ ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

2 ኛው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን መድረክ "የአልሙናይ ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ውጤት" በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ ታህሳስ 4፣ 2012ዓ.ም በአዲስ አበባ ሃርመኒ ሆቴል ይካሄዳል። በመድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የክብር እንግዶችን ጨምሮ ከ200 በላይ ታዳሚያን እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሩዋንዳ የኢቦላ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረች!

- ሩዋንዳ የኢቦላ በሽታን የሚገታ  የክትባት ዘመቻን ለመጀመሪያ ግዜ መስጠት ጀመረች። የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዘመቻው ክትባቱ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚዋሰኑ ቦታዎች ለ200 ሺ ሰዎች  ይሰጣል ብለዋል፡፡

የጤና ሰራተኞች፣ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች፣ ፖሊሶች እና ድንበር ተሻጋሪ ንግድ ላይ ለተሰማሩት የህብረተሰብ  ክፍሎች ክትባቱ በቅድሚያ ይሰጣችዋል ተብሏል፡፡

በሩዋንዳ እስከ አሁን ምንም ዓይነት የኢቦላ በሽታ አለመታየቱ ቢገለጽም፤ በጎረቤት  ሀገር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ በሽታ ምክንያት ከባለፈው ነሃሴ ጀምሮ ከ2 ሺ 200 ሰዎች በላይ መሞታቸው ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክንያትም ክትባቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው በምስራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ  በምትገኘው ጎማ  ሲሆን፤ እስከ አሁን ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑ ኮንጎውያን ክትባቱ እንደተሠጣቸው የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።

(BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#FerweyniMebrhatu #CNN

"ፍሬወይኒ መብራሃቱ በአውሮፓውያን አቆጣጠር የ2019 የሲ.ኤን.ኤን የዓመቱ ጀግና ተብላ በመጠራቷ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል። ሴት ልጆች በትምህርት ቤት እንዲቆዩ ያላት ቆራጥነት፣ እንዲሁም ማኅበረሰቧን የተሻለ ለማድረግ ያላት አቋም የሚደነቅ ነው። ኢትዮጵያ በፍሬወይኒ ኮርታለች።" ዶ/ር ዐብይ አህመድ (የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር)
.
.
"የእኛው ፍሬወይኒ CNN የ2019 ጀግና ሆነች!! እንኳን ደስ አለሽ! በተፈጥሯው ጉዳይ ለሚሸማቀቁ: ከትምህርታቸው ለሚስተጏጎሉ: ለሚያቋርጡ:ከሌላው በታች የሆኑ ለሚመስላቸው..የአገራችን ሴቶች ትልቅ ቀን ነው!ተባብረን ዘላቂ መፍትሄ እናምጣ!" ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት)

@tikvahethiopiaBot @tikavhethiopia
የስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለው ፈሳሽ ዕውቅና የለውም ተባለ!

በየመንገዱ የስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ስላለው ፈሳሽ የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን አስታወቀ።

ናኖ ቴክኖሎጂ ማለት ዘረፈ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን በውስጡ የሚይዝ መሆኑም ተገልጿል። የሞባይል ስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ፈሳሽ መፈተሽ እንዳለበት የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አወቀ ሺፈራው ተናግረዋል።

በፍተሻውም ወቅት በስልክ ገጽ ላይ የሚቀባው ፈሳሽ ጨረራ አለው ወይስ የለውም፤ የጨረራ ይዘቱ ምን ያህል ነው የሚለው ፍተሻ እንደሚደረግበት ገልጸዋል።

በፍተሻው ውጤት መሠረት ጨረራ አመንጪ ከሆነ ደግሞ መጠኑ ከዚህ በላይ ከሆነ ጉዳት አለው፣ ከዚህ በታች ከሆነ ደግሞ ጉዳት የለውም የሚለውን በሳይንሳዊ ትንታኔ መሠረት መናገር ይቻላል፤ ይህ ባልታወቀበት ሁኔታ ግን ይህ ነው ብለን መናገር አንችልም በማለት አብራርተዋል። አያይዘውም፣ በተቋማችን አሠራር አንድ ጨረር አመንጪ ቁስ አካል ወደ አገር ውስጥ ሲገባ አስመጨዎቹ ያመጡትን ነገር ወደ ተቋማችን አምጥተው የማሳወቅ ግዴታ እንዳለባቸው ሕጉ ያስገድዳል።

https://telegra.ph/ETH-12-10-2

(ኢቲቪ)

@tikvahethiopiaBot @tikavhethiopia
የወላይታ ዞን ምክር ቤት አራተኛ ዙር ሰባተኛ ዓመት አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ በጠራው ስብሰባ ያወጣው የአቋም መግለጫ!

ህዳር 30/2012 ዓ.ም የወላይታ ዞን ምክር ቤት የወላይታ ብሔር በክልል የመደራጀት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በብሔሩ ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ለክልሉ ምክር ቤት ለጉባኤ ቀርቦ ለምርጫ ቦርድ ተመርቶ ሕዝበ ውሳኔ ባለመደራጀቱ ምክንያት የብሔሩ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

የወላይታ ብሔር እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለ125 አመታት የዘለቀ ነዉ፡፡ የወላይታ ህዝብ በ1983 የሽግግር ወቅት ራሱን ችሎ በክልል ዘጠኝ ተደራጅቶ ነበረ፤ ኋላም በድንገተኛ ውሣኔ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተጨፍልቆ ‹‹ የደቡብ ክልል›› በሚል እንዲዋቀር መደረጉ የቅርብ ሩቅ ጊዜ ትዉስታ ነዉ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ህዝቡ በክልል የመመስረት ፍላጐቱን በተለያዩ አግባቦች ሲያንፀባርቅና ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡ በ1992 ዓ.ም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የብሔሩ ተወላጆችም በቋንቋ አጠቃቀምና ክልል በመመስረት ጉዳይ ላይ ሠላማዊ ሠልፍ አድርገው እንደነበርም ይታወቃል፡፡

More👇
https://telegra.ph/WRS-12-10

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወላይታ ዞን ምክር ቤት...

- "በኢፌዴሪ ህገ - መንግስት አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 3 (ለ) በተጠቀሰው መሠረት እስካሁን የደቡብ ክልል ምክር ቤት የወላይታ ብሔር ክልል የመመስረት ጥያቄ ጉዳዩ ለሚመለከተው የኢትዮጰያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሳያስተላልፍ መቆየቱ ኢ-ህገመንግስታዊ በመሆኑ የተከበረው የዞኑ ምክር ቤት ሁኔታውን ያወግዛል፤ ስለሆነም የክልሉ ምክር ቤት ጉዳዩን ተቀብሎ በቀሪ አስር ቀናት ውስጥ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲያስተላልፍ በአፅኖት ይጠይቃል፡፡"

(የወላይታ ዞን ምክር ቤት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወላይታ ዞን ምክር ቤት...

"የደቡብ ክልል ምክር ቤት በቀሩት አስር ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ አስቸኳይ የምክር ቤት ጉባኤ በመጥራት የህዝባችንን ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ለጉባኤ በማቅረብ ለኢትዮጰያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝብ ውሳኔ እንዲያደራጅ የማይልክ ከሆነ የኢፊዴሪ ፈዴሬሸን ምክር ቤት ጠልቃ በመግባት ለደቡብ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ እንዲጠራ ትዕዛዝ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፤"

(የወላይታ ዞን ምክር ቤት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“በአንድ ሀገር ውስጥ የመናገር ነፃነት ያለ ገደብ ሲሰጥ የጥላቻ ንግግሮች እና ሐሰተኛ መረጃዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ለዚህ ደግሞ መንግስት ገለልተኛ ተቋማትን ማቋቋምና ከዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች በመነሳት ጠንካራ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ነው፡፡" - በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕግ መምህርና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሀሳብን በነፃነት መግለፅ ልዩ ፀሐፊ ፕሮፊሰር ዴቪድ ኬይ

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ተቀበሉ!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን ተቀበሉ። የኖቤል የሰላም ሽልማት ስነ ስርዓት በዛሬው እለት በኖርዌይ ኦስሎ በመካሄድ ላይ ይግኛል። በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን ለጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ሽልማት ከመስጠታቸው በፊት ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ሚንሥትሩ ለሰላም ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማስፈን በርካታ ርምጃዎችን መውሰዳቸው እንዲሁም በካቢኔያቸው አምሳ በመቶ ሴቶችን መሾማቸዉ ተመስግኗል። በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰላም ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ሣኅለ-ወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ማአዛ አሸናፊ ሴቶች መኾናቸውን ሊቀመንበሯ አመስግነዋል።

ሽልማቱም የተሰጠው፦ ሰላም እና ብልጽግና በኢትዮጵያ ለማስፈን ዓልመው መነሳታቸው ሊቀመንበሯ ገልጠዉ የኖቤል ኮሚቴዉ ዕውቅና ሰጥቶታል። በምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ሰላም እንዲሰፍን ጠቅላይ ሚንስትሩ ላበረከቱት አስተዋጽዖም በኮሚቴው ተመስግነዋል።

ኤርትራ እና ጅቡቲ ሰላም እንዲፈጥሩ ጥረት መደረጉ፤ በደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ሰላማዊ መፍትኄዎችን እንደ አማራጭ መወሰዳቸው ተወድሷል። «ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መገኛ ናት» ያሉት የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን፤ «የመጀመሪያው ሆሞ ሴፒያን የፈለሰው ከእርስዎ [ጠ/ሚ ዐቢይ]ሀገር ነው፣ በዚህም እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን» ብለዋል። ኢትዮጵያ በአዉሮጳዉያን ቅኝ አለመገዛትዋ፤ የአፍሪቃ ኅብረት መቀመጫ መኾኗ ከመድረኩ ሲገለጥም ሞቅ ያለ ጭብጨባ ከታዳሚያን ተሰምቷል።

(DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
«ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መገኛ ናት። የመጀመሪያው ሆሞ ሴፒያን የፈለሰው ከእርስዎ [ጠ/ሚ ዐቢይ] ግዛት ነው። በዚህም እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያኖች ነን።» - የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኖርዌይ፣ ኦስሎ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

• የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ ለሰጠኝ እውቅና አመሰግናለሁ፡፡

• ለኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ስምምነት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሰላም ቁርጠኝነት ወሳኝ ነበር፡፡

• ይህንን ሽልማት የአፍሪካ ህዝቦችና የዓለም ህዝቦችን ወክዬ ነው የምቀበለው፡፡

• ከ20 ዓመታት በፊት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሬድዮ ኦፕሬተር ነበርኩ፡፡

• ጦርነቱ በርካታ ቀውሶችን አስከትሎ ነበር፡፡

• በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት ሰላም አልነበረም፤ ሰዎች ተለያይተዋል፤ በርካታ ሰራዊት በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ መሽጎ ነበር፡፡

• ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆንኩ በኋላ የሁለቱ አገራት ህዝቦች ልዩነት መቆም እንዳለበት ወሰንኩ፡፡

• ሁለቱ አገራት ጠላቶች እንዳልሆኑ ይልቁንስ ድህነት የጋራ ጠላታችን እንደሆነ አውቀን ለአገራቱ እና ለቀጠናው ብልፅግና መስራት ጀመርን፡፡

• መደመር አገር በቀል ሀሳብና የጋራ ብልጽግና ላይ ያተኮረ ፍልስፍና ነው፡፡

• የመደመር ጽንሰ ሀሳብ እንደ ዘር ውስጤ የበቀለው በኦሮሚያ ክልል በምትገኝ የትውልድ መንደሬ በሻሻ ውስጥ ነው፡፡

• በመደመር ጽንሰ ሀሳብ ውስጥ እኛና እነሱ የሚባል ነገር የለም፡፡

• ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመቆማችን ለዓመታት ነፃ አገር ሆነን ቆይተናል፡፡

• የአፍሪካ ቀንድ የአሸባሪዎች ቀጠና እንዲሆን አንፈልግም፣ የሰላም ቀጠና እንጂ፡፡

• ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሰላም ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

• ለዴሞክራሲ ግንባታ መንገድ ዘርግተናል፤ በቅርቡ ነፃና ፍትሓዊ ምርጫ እናካሂደለን፡፡

• ለሁሉም ዜጎቿ እኩልነት መረጋገጥ አብረውኝ እንዲሰሩ ለኢትዮጵያውያን ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

(ኢቢሲ)
ዶ/ር ዐብይ ፕሬዚደንት ኢሣያስ አፈወርቂ አወደሱ!

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማታቸውን ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግር ፕሬዚደንት ኢሣያያስ አፈወርቂ አወደሱ። «ይኽን ሽልማት የምቀበለው በኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስም ነው።

በተለይ ደግሞ ለሰላም ሲሉ ከፍተኛውን መስዋእትነት በከፈሉት ስም። በተመሳሳይ ሽልማቱን የምቀበለው በአጋሬና የሰላም ጓድ በኾኑት ፕሬዚደንት ኢሣያያስ አፈወርቂ ስም ነው» ብለዋል። ይኽ ንግግራቸውም ከታዳሚያን ሞቅ ያለጭብጨባ ታጅቧል። የፕሬዚደንት ኢሣያያስ አፈወርቂ «መልካም ፈቃድ፣ እምነት እና ቁርጠኝነት ለኹለት ዐስርተ-ዓመታት በሃገሮቻችን መካከል የዘለቀው መቆራረጥ እንዲያበቃ ወሳኝ ነበር።»

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ጦርነቱ ሲከፈት ወጣት እንደነበሩ የተናገሩት ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ፦ በጦርነት አውድማ «ወንድም ወንድሙን ሲገድል» መመልከታቸውን ገልጠዋል። የጦርነት መራራ ገጽታን፤ የሰላምን ወሳኝነት አጉልተው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት የተነሳ ለኹለት ዐሥርተ-ዓመታት ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦች መገናኘታቸውን፤ «ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ እንደ አዲስ መጀመሩንም» ጠቅሰዋል። የአየር እና የቴሌኮሙኒኬሽን ግንኙነት በኹለቱ ሃገራት መጀመሩንም በንግግራቸው አሰምተዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-10-3

(DW)

@tikvahethiopiaBot tikvahethiopia
የእንኳን ደስ አሎት እና የስጋት መልዕክት...

(ቲክቫህ ቤተሰቦች)

በቅድሚያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተ አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆናቸው ከፍተኛ ክብር፣ ኩራት እና ደስታ ተሰምቶናል። ይህ ሽልማት ለሰላም እና ለዓለም አቀፍ ትብብር ላደረጉት ጥረት በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ለዓመታት የዘለቀው የድንበር የይገባኛል ውዝግብ በሰላም እንዲፈታ ተነሳሽነትን በመውሰዶ የተበረከተ እንደሆነ እናምናለን።

በቀጠናው ላይ ያመጡትን ለውጥ እያደነቀን በአሁን ሰዓት እኛ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በእጅጉ ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ እንደሚያሳስበን፣ በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታም በከፍተኛ ሁኔታ እየተጨነቅን እንደሆነ ለመግለፅ እንወዳለን።

ሽልማቱ በሀገር ውስጥ የሚታየውን ምኑም ያልተጨበጠ ምስቅልቅል ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ እንዲያጠሩ ተነሳሽነትን ይፈጥርሎታል ብለን እናምናለን። ሁሉም ዜጎች በእኩል ተስተናግደው እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎችም ትኩረት እየተሰጣቸው ሀገሪቱ እየሄደች ካለችበት አደገኛ አካሄድ ጊዜው ሳይረፍድ ለመመለስ ትልቅ ተነሳሽነት ይፈጥርሎታል ብለን እናምናለን።

ይህ ሽልማት በሀገራችን ላይ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ የዜጎች በተለይም በአሁን ወቅት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደህንነት እንዲጠበቅ፣ ህዝቡ ሰላም ወጥቶ ሰላም እንዲገባ፣ ወጣቱ እየሄደበት ካለው አደገኛ አካሄድ ቆም ብሎ እንዲያስብ፣ ጥፋተኞች ለህግ እንዲቀርቡ፣ በመንግስት ተገፍተናል የሚሉ አካላት ድምፃቸው ተሰምቶ እኩል ስለሀገራቸው እንዲጮሁ የማድረግ ስራ እንዲሰሩ መነሳሳት ይሆኖታል ብለን እናምናለን።

ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ትሻለች!

በድጋሚ እንኳን ደስ አሎት!

(የቲክቫህ ቤተሰቦች የላኩት መልዕክት)

@tikvahethiopiaBot
የሰብዓዊ መብት አያያዝ ቢሻሻልም የመንጋ ፍትህ ሌላ ፈተና ሆኗል!

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም መሻሻል እየታየበት መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተቋማት ገለጹ። ከለውጡ በኋላ የተለያዩ ህጎች እየተሻሻሉ መምጣታቸው እንደመልካም አጋጣሚ ቢቆጠርም የመንጋ ፍትህ አሁንም ስጋት ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ71ኛ ጊዜ የሚከበረው የሰብዓዊ መብቶች ቀን ዛሬ በአዲስ አበባ ከሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ የሲቪክ ማህበራት ጋር ተከብሯል።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ህብረት ዋና ዳይሬክተር አቶ መስዑድ ገበየሁ እንዳሉት፤ ከለውጡ በኋላ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ተስፋ ሰጭ ጉዳዮች ይታያሉ።

መንግስት ለሰብዓዊ መብት አያያዝ እንቅፋት የሆኑ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻልና ተቋማትን በማደራጀት ብዙ ርቀት ሂዷል ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በሰብዓዊ መብት ጉዳይ የተሰማሩ የሲቪክ ማህበራት እንደጠላት ይቆጠሩ እንደነበር ገልጸው፤ አሁን መንግስት ለውይይት በሩን ክፍት ማድረጉን ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ አሁን ያለው አካሄድ በዜጎች ሰብዓዊ መብት ላይ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊም አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል። መንግስት ለሰብዓዊ መብት ትኩረት ሰጥቶ ተቋማትን ማደራጀቱና ህጎችን ማሻሻሉ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የውስጥ መፈናቀል፤ የመንጋ ፍርድ፣ መንግስት ህግ ለማስከበር የሚያሳየው ዳተኝነት ለዜጎች ስጋት መሆኑን አስረድተዋል።

https://telegra.ph/ETH-12-10-4

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማሻሻያ በሚል ሰበብ ዜጎች መጎዳት የለባቸውም!

"መንግስት ችግሮች ሲፈጠሩ በመዋቅራዊ ለውጥ ላይ ስለሆንኩ ነው በሚል የሚያቀርበው ሰበብ ጊዜ ሊቀመጥለት ይገባል፤ ሁልጊዜ ማሻሻያ በሚል ሰበብ ዜጎች መጎዳት የለባቸውም፤ በመሆኑም መንግስት የመንጋ ፍርድ እንዲቆምና ዜጎች ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲችሉ እኛም የበኩላችንን ሚና እንወጣለን።" - ሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ የሲቪክ ማህበራት

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia