የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ተከበረ!
በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባ ገዳዎች ምርቃት የተጀመረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ተከብሯል። በአዲስ አበባ የሚከበረውን ኢሬቻ ለመታደም ከኦሮሚያ፣ ከአዲስ አበባና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በርካታ ሕዝብ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተገኝተዋል። በአሁኑ ሠዓት በዓሉ በሠላም ተከብሮ ታዳሚዎችም ወደየመጡባቸው አካባቢዎች በመመለስ ላይ ይገኛሉ። ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ በዓመት ሁለት ጊዜ በፀደይ በውሃማ አካላት፤ በበልግ ደግሞ በተራራማ አካባቢዎች ላይ የሚከበር የምስጋና በዓል ነው።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#UNIVERSITY
በዘንድሮው ዓመት በመንግስት #ዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ የሚያገኙ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 46 ሺህ 416፣ ሴት 32 ሺህ 865 በድምሩ 79 ሺህ 281 ሲሆኑ ፥ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ወንድ 34 ሺህ 838 ሴት 28 ሺህ 702 በድምሩ 63 ሺህ 540 መሆናቸው ተገልጿል።
በዚህ መሰረትም ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገቡ ተማሪዎች 55 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፥44 ነጥብ 5 በመቶዎቹ ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በዘንድሮው ዓመት በአጠቃላይ ወደ መንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር 142 ሺህ 821 ነው። የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግቢያ አራት መሰረታዊ የትምህርት አይነቶችን ውጤት መሠረት አድርጎ እንደሚወሰን መገለጹ ይታወሳል።
Via ኤፍ ቢ ሲ

ዩኒቨርሲቲ መቀያየር አይቻልም!
በአንዳንድ ማህበራዊ ገፆች ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲ እናቀያይራለን የሚሉ መልዕክቶች እየተሰራጩ ይገኛሉ፤ ይህ ከእውነት የራቀ ነው። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለTIKVAH-ETH እንዳሳወቀው ምንም አይነት የዩኒቨርሲቲ ቅይይር አይቻልም። በማህበራዊ ሚዲያዎችም እየተሰራጩ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ቅይይር መልዕክቶች ሀሰተኞችና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እውቅና የሌላቸው ናቸው።
#TIKVAH_ETHIOPIA

ጥብቅ ማሳሰቢያ!
ማንኛውም ተማሪ #ከተመደበበት ዩኒቨርስቲ ወደሌላ ዩኒቨርስቲ መቀያየር እንደማይቻል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያስታውቃል።

ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል እጅግ በደማቅ ሁኔታ በሰላም ተጠናቋል!
PHOTO: AMANUEL ETICHA & EYASU G.
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
PHOTO: AMANUEL ETICHA & EYASU G.
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢሬቻ በዓል በሰላም መከበሩን ፖሊስ አስታወቀ!
በርካታ ህዝብ የታደመበት እና በመስቀል አደባባይ የተከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ለዚህም ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በርካታ ህዝብ የታደመበት እና በመስቀል አደባባይ የተከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ለዚህም ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ
በአዲስ አበባ የነበረው የኢሬቻ በአል አከባበር ባማረ መልኩና በሰላም ተጠናቋል። ይህን አስመልክቶም የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለከተማዋ ነዋሪዎችና ለበአሉ አከባበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ የምስጋና መልእክት አስተላልፈዋል።
ኢንጂነር ታከለ በሁሉም የከተማዋ ጫፎች የሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ያሳዩት ትብብር የሚደነቅና የሚከበር ነው ብለዋል። በአሉን ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡትን በልዩ ፍቅርና ያላቸውን በማቅረብም ጭምር አክብሮታቸውን ስላሳዩም ለከተማዋ ነዋሪዎች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
የከተማዋ ባለሀብቶችም የበአሉን አከባበር በመደገፍ በአሉ እውን እንዲሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናን አቅርበዋል። በበአሉ ላይ አንድም የጸጥታ ችግር እንዳይፈጠር በበቂ ዝግጅትና በሀላፊነት ስሜት በብቃት ለሰሩ የጸጥታ አካላትም ምስጋናን አቅርበዋል።
ለጸጥታው መከበር ወጣቶች ያሳዩትንም ተሳትፎና ትብብርም የሚደነቅ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ። ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአጠቃላይም አዲስ አበባ ህብረብሄራዊነቷን በጠበቀና ባማረ መልኩ የኢሬቻ በአል በመዲናዋ እንዲከበር ድጋፍ ላደረጉና በጨዋነት ለተባበሩ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናቸውን መግለፃቸውን የከንቲባ ፅሀፈት ቤት አስታውቋል።
Via Mayor Office AA

Engineer Takele Uma Banti...
"Tajaajila Geejjibaa mijeessaa jira, obsaa..! ሸገር BUS፣ አንበሳ BUS"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"Tajaajila Geejjibaa mijeessaa jira, obsaa..! ሸገር BUS፣ አንበሳ BUS"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል መንግስት የማንነት ጥያቄዎችን የመለሰበት መንገድ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን እንደሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ!
የአማራ ክልል መንግሥት የአማራና ቅማንት ሕዝቦች በሠላም፣ በፍቅር እና በአንድነት እንዲኖሩ ዕድል ፈጥሮ እያለ ሰሞኑን በአዲስ መልክ የሕዝቦችን ሠላም እና አንድነት የማይፈልጉ አካላት “የቅማንት ማንነት እና የራስ አስተዳድር ጥያቄ አልተመለሰም” በሚል የፖለቲካ አሻጥር ሠላማዊ ዜጎችን እርስ በርስ በማጋጨት በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-05
Via #AMMA

"የቅማንት #የማንነት እና #የራስ_አስተዳደር ጥያቄ አልተመለሰም" የሚሉ አካላት ትክክል አይድሉም ጥያቄዉ እንደተመለሰላቸዉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ተቀብሎ አጽድቋል፤ ‘ሌሎች ተጨማሪ ሦስት ቀበሌዎች ወደ ቅማንት ይካለሉ’ የሚሉ ጥያቄዎችም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበዋል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የጥናት ቡድን ልኮ ቀበሌዎቹ ኩታ-ገጠም አለመሆናቸዉን አረጋግጧል፤ ስለዚህ ጥያቄያቸው ተገቢ አይደለም ተብሏል” አቶ ወርቁ አዳሙ በፌዴሬሽን ም/ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Addis Abeba Police Commission
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከሀገር መከላከለያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱን ገልጿል፡፡
የጋር እቅድ በማውጣት እና ለእቅዱ ተፈፃሚነት በጋራ በመንቀሳቀስ እንዲሁም ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ አብዛኛውን የሰው ኃይል እና ተሽከርካሪዎችን በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በማሰማራት በዓሉ በሰላም እንዲከበር ማድረግ መቻሉን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
የዝግጅቱ አስተባባሪዎች፣ ፎሌዎች፣ የበዓሉ ታዳማዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎችም ከፀጥታ አካላት ጋር ተባብረው በመስራታቸው በዓሉን በሰላም ማክበር መቻሉን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ለእነዚህ አካላት እና ተልዕኳቸውን በላቀ ትጋት ለተወጡት መላው የፀጥታ አካላት ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል፡፡