TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የአሜሪካ ሙዚየም ከግብፅ ተሰርቆ የተወሰደውን ጥንታዊ የወርቅ መቃብር መለሰ። በአረብ የፀደይ አብዮት ወቅት ተዘርፎ በኒው ዮርክ ሜትሮፖሊታን የሥነ-ጥበብ ሙዚየም የተገኘው የግብፅ የወርቅ የሬሳ ሣጥን ለሀገሪቱ መመለሱ ተገለጸ፡፡

በወርቅ የተንቆጠቆጠውን ጥንታዊ የሬሳ ሣጥን እኤአ በ2017 በ4 ሚሊዮን ዶላር ሙዚየሙ የገዛው ሲሆን ቅርሱ በሕገ-ወጥ መንገድ በግለሰቦች መዘዋወሩ ተደርሶበት በቁጥጥር ስር ውሎ ቆይቷል፡፡ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ በተገኙበት ቅርሱ ለሀገሪቱ መመለሱ ነው የተገለጸው፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ የግብፃውያን ብቻ ሳይሆን ሁላችንም እንደ አንድ ዓለም አቀፍ ቤተሰብ ልንጋራው የሚገባ ነው ብለዋል፡፡ እንደ ምርመራው ከሆነ ይህ የወርቅ የሬሳ ሣጥን በተመሳሳይ መንገድ ከተሰረቁ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ጥንታዊ ቅርሶች መካከል አንዱ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኒው ዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 74ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን በኢጋድ የሚንስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበርነታቸው የአባል ሃገራት ሚንስትሮች ጋር መክረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ASOSA

በአሶሳ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ 145 የክላሽ ጥይት ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ም/ኢ/ር ደረጀ ኢታና እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት በአሶሳ ከተማ ወረዳ አንድ ቀጠና አንድ አካባቢ አንድ መቶ አርባ አምስት የክላሽ ጥይቶችን ይዘው ለመሸጥ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ በህብረተሰቡ ጥቆማ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው ችሏል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-26-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕና ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ! #ኒውዮርክ #US
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጊፋታ2012

የዘንድሮ የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታ በተለያዩ ፕሮግራሞች ለማክበር ዝግጅቱን እንዳጣናቀቀ የዞኑ ባህልና ቱሪዝም እሴት መምርያ ኃላፊ አቶ ፀጋው ስምኦን ገልፀዋል። እንደ አቶ ፀጋው ገለፃ ከሆነ የወላይታ ዞን መለወጫ በዓል የብሔሩን ባህልና እሴትን ለትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸው የዘንድሮ የጊፋታ በዓልን በተለያየ መልኩ ለማክበርም ዝግጅቶች መደረጋቸውንም ሃላፊው ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/TIKVAH-09-26

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋሞ ዞን ፖሊስ ያስተላለፈው የጥንቃቄ መልዕክት፦

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለመላው የጋሞ ዞን እንኳን ለ2012 ዓ.ም የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና እርስ በእርስ በመደጋገፍ በጋራ የምናከብረው በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡ የመስቀል በዓልን ያለምንም የፀጥታ ስጋት ለማሳለፍ የዞኑ ጸጥታ አካል ከሚመለከታቸው ባለድርሻአካላት ጋር በመሆን ትኩረት በመስጠት እየሰራ በመሆኑ ህብረተሰቡ የተለመደውን እገዛ ወይም ትብብር አጠናክሮ በመቀጠል ከታች በተቀመጡ ስልኮቻችን መረጃዎችን በማድረስ ለወንጀል መከላከሉ ስራ አጋርነቱን እንዲያረጋግጥ ያሳስባል፡፡

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በበዓል ወቅት ሊፈጠሩ ከሚችሉ፡-

• ከበዓል ግብይትጋር ተያይዞ ከሀሰተኛ የብር ኖቶች /ፎርጅድ ገንዘብ/ ዝውውር ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው፣

• ከበዓል ዝግጅት ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ ከሚችሉ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ህብረተሰቡ ለራሱ እና ለንብረቱ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅበት፣

• በሚኖረው ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከታሪፍ በላይ ማስከፈልና አላስፈላጊ መጉላላት በትራንስፖርት ተጠቃሚው ላይ እንዳይደርስ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ክትትል ያደርጋሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለሚፈጠሩ ችግሮች የፖሊስ የመረጃ ስልኮችን በመጠቀም በፍጥነት ጥቆማ በማድረስ ህገ-ወጥ ተግባራትንና ወንጀሎችን በጋራ መከላከል እንደሚገባ እያሳሰበ የመረጃ ስልኮቹ እነሆ በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

የመረጃ ስልኮች፦

የጋሞ ዞን ፖሊስ መረጃ 0468810025
የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ መረጃ 0468814298
ሼቻ ክፍለከተማ ፖሊስ መረጃ 0468810095
ሲቀላ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መረጃ 046881 2637
አባያ ክፍለ ከተማ ፖሊስ 046881 4312
ነጭ ሳር ክፍለ ከተማ ፖሊሰስ 0468813381
#BREAKING ፈረንሳይን ከ1995-2007 በፕሬዘዳንትነት የመሩት የቀድሞው የፈንሳይ ፕሬዘዳንት ዣክ ሺሃክ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የወላይታ ብሄር የዘመን መለወጫ ''ጊፋታ'' ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በወላይታ ሶዶ ከተማ የወላይታ ብሄር የባህል ፤ቋንቋና ታሪክ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ይገኛል።

Via #OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AAWSA

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለመስቀል በዓል የውሃ ችግር አይኖርም ብሏል። ባለሰልጣኑ የመስቀል በዓልን አስመልክቶ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢፈጠር አፋጣኝ መልስ ለመስጠት በ16 ውሃ ማጠራቀሚያዎች ውሃ ማከማቸቱን አስታውቋል።

ይህንኑ የዝግጅት ስራ ንፋስ ስልክ፣ አራዳ፣ መካኒሳ እና መገናኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኙ 16 የእሳትና ድንገተኛ ግብዓት ማከማቻዎች በአግባቡ መስራታቸውን ፈትሼ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ ቅርንጫፎቹም ደመራው በሚለኮስበት መስቀል አደባባይ በአንድ ኪ.ሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እና ችግሩ ቢከሰት በፍጥነት ለመቆጣጠርና ለማጥፋት በሚያስችል ፍጥነት ተደራሽ የሚሆኑ ናቸው፡፡

በዕለቱ በ16ቱም ማጠራቀሚያ ጣቢያዎች ውሃ አቅርቦቱ እንዳይስተጓጎል ብሎም የተሻለ ግፊት እንዲኖረው የሚቆጣጠር ኮሚቴ መቋቋሙንም አስታውቋል፡፡ ባለስልጣኑ ባደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ ሦስት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ማጠራቀሚያዎችን ጠግኖ ለስራ ዝግጁ አድርጊያለሁ ብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#share #ሼር

በኖማም ሆነ በተለያዩ ህመሞች የፊት ገፃቸው ለተበላሸ ሰዎች ቼሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ ከፌሲንግ አፍሪካ ጋር በመተባበር እንግሊዛውያን የቀዶ ህክምና ዶክተሮችን አስመጥቶ ነፃ ህክምና ሊያደርግ እንደሆነ ተሰምቷል። የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አቶ ፋሲል አየለ ለሸገር ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በምግብ እጥረት ሳቢያ የፊት ገፅታን በሚያበላሸው የኖማ ህመም፡ በእሳት አደጋም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት ያጋጠማቸው ሰዎች #መናገሻ በሚገኘው ቼሻየር ሰርቪስ ተሃድሶ ማዕከል ከዛሬ ጀምሮ እየቀረቡ መመዝገብ እንደሚችሉ ጥሪ ቀርቧል። እስከ መስከረም 26 ድረስ ነፃ የቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል። እንግሊዛውያን ዶክተሮቹ 25 ሲሆኑ 50 ሺህ ብር ያህል የሚጠይቀውን ህክምና ነው በነፃ የሚሰጡት።

Via ሸገር ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በወላይታ ሶዶ ከተማ የተከሰተ ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ። ህብረተሰቡ በዝናብ ወቅትና በበዓላት ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ሲጠቀም ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አሳስቧል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ህያሁን ሞጋ እንደገለጹት አደጋው የተከሰተው ትናንት ምሽት 7፡00 ሰዓት በመሃል ክፍለ-ከተማ በተለምዶ 21 ማዞሪያ በሚባል መንደር ነው፡፡ በአደጋውም የእንጨት ውጤቶች ማምረቻ፣ ቶርኖ ቤት እና አንድ መለስተኛ ሻይ ቤት በውስጣቸው ከያዟቸው ንብረቶች ጋር መውደማቸውን አስረድተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-26-3
#ሰበታ

በህገ ወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎች በሰበታ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። የሰበታ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ የጦር መሳሪያዎቹ ኮድ 3 አ.አ በሆነ ተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቀው ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እያሉ ነው በቁጠጥር ስር የዋሉት። ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹም የፀጥታ አስከባሪ አካላት ባደረጉት ክትትል እና ፍተሻ በቁጥጥር ስር ሉውሉ መቻላቸውም ነው የተገለፀው።

የሰበታ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ እንዳስታወቀው፥ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር የዋሉት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች 40 ክላሽንኮቮች ናቸው። በአሁኑ ወቅት የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት እንዳሉ በመግለፅ ህብረሰተቡ አጠራጣሪ ነገሮችን በሚመለከትበት ጊዜ ለፀጥታ አካላት እንዲያሳውቅም ጥሪ አቅርቧል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ግብጽ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ያቀረበችው ሃሳብ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ሉዓላዊ መብት የሚጋፋ ነው" – የምስራቅ ናይል ቴክኒካል አህጉራዊ ጽ/ቤት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአ/አ መፍትሄ ያልተገኘለት የመብራት መቆራረጥ!

በአዲስ አበባ የመብራት መቆራረጥ መፍትሄ ያልተገኘለት ችግር ሆኗል። በከተማው የተለያያየ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለቀናት አለፍ ሲልም ለሳምንታት መብራት እንደሚቋረጥባቸው ይናገራሉ። በትራንስፎርመር ብልሽት የተነሳ ለበርካታ ቀናት መብራት ተቋርጦብናል፤ በአንድ ቀን ውስጥ ከ3 እና ከ4 ጊዜ በላይ መብራት እየጠፋብን ነው የሚሉ ቅሬታዎችን ነዋሪዎች ያቀርባሉ።

ሰሞኔን ጃል ሜዳ አካባቢ የተቃጠለ ትራንስፎርመር ያስከተለው የኃይል መቋረጥ የአካባቢውን ነዋሪዎች የእለት ተእለት ኑሮ ከማወኩ በተጨማሪ የአንድን ጤና ጣቢያ ስራ እየፈተነው እንደሆነ ተሰምታል። በዚሁ ጤና ጣቢያ የሚሰሩ አንድ ባለሞያ የሃይል መቋረጡ በማቀዝቀዣ ውስጥ መቆየት የለባቸው መድሃኒቶች እንዲበላሹ ምክንያት ሆኗል ብለዋል። በኦፕራሲዮን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ታካሚዎችና ወላድ እናቶችም በዚሁ በመብራት ችግር አጋግሎት ማግኘት አልቻሉም።

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በቀለ ክፍሌ የትራንስፎርመር ብልሽት በሚያጋጥም ጊዜ በቶሎ ጥገና ለማድረግ አስቸጋሪ እንደሆነ ተምገልፀው ከሰሞኑን ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየው የመብራት መቆራረጥ ከወትሮ የተለየ ምክንያት የለውም ያረጁ የኤሌክትሪክ መስመሮች በተደጋጋሚ በሚያጋጥማቸው ብልሽት እና ትራንስፎርመሮች ከአቅም በላይ ሆነ ሃይል ስለሚሸከሙ የሚከሰት እንደሆነ ነው ያስረዱት። ያረጁ መስመሮችን ወደተሻሻለው መስመር የመገልበጥ ስራ ሲከወን ነበር ለዚሁ ተግባር ተብሎ ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

Via ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተመልከቱ⬆️

በሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ወረዳ አብዬ ቀበሌ የሚኖሩ ዜጎች ላለፉት 8 ወራት በመብራት #እጦት እየተቸገሩ ይገኛሉ። እስካሁን መፍትሄ አላገኘንም የሚሰማንም አጥተናል፤ የሚመለከተው አካል ችግሩን ተመልክቶ መፍትሄ ይስጠን ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🤔ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአምስት ቀናት ውስጥ ያስመዘገበው ውጤት፡ -

ቻን 2020

ኢትዮጵያ 0 – 1 ሩዋንዳ

ሴካፋ ከ20 ዓመት በታች

ኢትዮጵያ 0 – 4 ታንዛንያ
ኢትዮጵያ 1 – 2 ዛንዚባር
ኢትዮጵያ 0 – 4 ኬንያ

TIKVAH-SPORT ከቅዱስ እና ጎይቶም ጋር🏷https://yangx.top/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ለማዞር የግብይት አማካሪ የመቅጠር ስራ መጀመሩ ተገለፀ!

ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል የማዞር ሂደትን የሚቆጣጠር ብቃት ያለው እና ገለልተኛ የሆነ የግብይት አማካሪ ለመቅጠር ስራ መጀመሩን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የግብይት ሂደት አማካሪው አለም አቀፍ ተቋም ሆኖ በዋናነት የኢትዮ ቴሌኮምን ወደ ግል ይዞታነት የማዘዋወር ሂደትን የሚቆጣጠር እና የሚያማክር ድርጅት ነው ተብሏል።

አዲስ የሚቀጠረው አማካሪ ተቋም ዋና ተግባሩ የሚሆነው የዋጋ ትመና መስጠት ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም በምን ያህል ገንዘብ ወደ ግል ይዞታነት መዛወር እንዳለበት፣ ምን ምን አይነት ድርጅቶች መሳተፍ እንዳለባቸው ለመንግስት ምክረ ሃሳብ ያቀርባል። በዚህ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተቁሙ እንደሚመረጥና ወደ ስራ እንደሚገባም ነው ሚኒስቴር ዴኤታው የገለፁት።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ በአዲስ መልክ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሠጥ የተደራጀውን የራስ መኮንን ፓርክ መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡ ከ4300 ካ.ሜ በላይ ስፋት ያለው የራስ መኮንን ፓርክ የአረንጓዴ ቦታን ጨምሮ የህፃናት መጫወቻ ስፍራ እና ለአከባቢው ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከልን ያካተተ ነው፡፡

Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ልዮ ልዮ የጦር መሳሪያዎችን ከእነ ተጠርጣሪው ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ጎሮ ብርሃኑ ሆቴል አካባቢ አንድ ግለሰብ ነጋዴ መስሎ በመቅረብ አንድ ሙሉ ግቢ ከእነ መኖሪያ ቤቱ በመከራየት በቤት ውስጥ 7 ባለ ሰደፍ ክላሽን ኮቭ ጠመንጃ ከ265 ጥይት ጋር ፣ 2 ማካሮቭ ሽጉጥ ከ22 ጥይትና፣ ሦስት የሽጉጥ ካርታዎችን ሸሽጎ መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ሰላማዊ ሰው በመምስል መኖሪያ ቤት፣ መጋዘን እና የንግድ ቤቶችን በመከራየት የሀገርንና የህዝብን ሰላም የሚጎዳ ወንጀል ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦች መኖራቸውን አከራዮች ተገንዝበው ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡ የጦር መሳሪያዎቹ መስከረም 14 ቀን 2012 ዓ/ም በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዛቸውን ኮሚሽኑ ገልፆ የሠላም ጉዳይ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ መሰል ጥቆማዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብሏል፡፡

ምንጭ፦ የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia