TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጋምቤላ የጋምቤላ ክልል መንግስት የኢሰመኮን ሪፖርት "ለጠላት የወገነ ነው " ሲል ገልጾ ሪፖርቱን እንደማይቀበለውና እንደሚያወግዘው ገለፀ። የጋምቤላ ክልል፤ "ኢሰመኮ ሰኔ 7/2014 ዓ.ም በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ላይ ተፈጥሮ በነበረው ውጊያ ተከትሎ በክልሉ ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሽያ እና ተባባሪ ወጣቶችን ሲመሩ የነበሩ አመራሮች አማካይነት ደረሰ ባላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ላይ ያወጣውን ሚዛናዊነት…
የጋምቤላ ክልል የኢሰመኮን ሪፖርት እንደማይቀበለው እና እንደሚያወግዝ በገለፀበት መግለጫ ምን አለ ?

- ሚዛናዊነት የጎደለው በመሆኑ ምርመራውን አልቀበለውም፤ በጥብቅም አወግዛለሁ።

- ሪፖርቱ የአንድ ክልል የፀጥታ ተቋምን ከተራ የአሸባሪ ቡድን ተላላኪ ጋር በአንድነት ያየ፤ በክልልና በአገር ላይ ይደርስ የነበረ ከፍተኛ ጥቃት በመቀልበስ ሂደት የህይወት መስዋዕትነት የከፈለውን የፀጥታ ተቋሙን በጅምላ የፈረጀ፤ የተገኘውንም ድል በዜሮ ያባዛ ነው።

- ሪፖርቱ የክልሉን የፀጥታ ኃይል ሞራል የሚያዳክም፤ ፀረ-ሠላም ኃይሉንና መንግሥትን በአንድ ሚዛን ላይ አድርጎ ያየ፤ በአጠቃላይ ለጠላት የወገነ ሪፖርት ነው።

- የመረጃ አሰባሰብና ምዘና ሥነ-ዘዴው ምክንያታዊ አሳማኝነት (Reasonable Grounds) ስልት ያልተከተለ ነው።

- መረጃው ከተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ማለትም ከኦነግ ሸኔና ህወኃት ደጋፊዎች እንዲሁም በተለያዩ ወንጀሎች ሲጠረጠሩ ከነበሩ ግለሰቦች የተወሰደና በአንድ አካባቢ የታጠረ ነው።

- ሪፖርቱ የጋምቤላን ነባር ብሔረሰቦች እና አብረዋቸው ለረዥም ዘመናት ከሚኖሩ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር እርስ በርስ ለማጋጨት #ሆን_ተብሎ የተዘጋጀ ሪፖርት ነው።

- በጋምቤላ ክልል የሚገኘው የኮሚሽኑ ጽ/ቤት ባልደረቦች ተቋሙ የተቋቋመለትን ዓላማና ተልዕኮ በቅጡ ያልተገነዘቡ፣ የግል ፍላጎታቸው የታየበት፣ የክልሉን ህዝብና መንግሥት አለያይቶ ለማጋጨት የተደረገ ሴራ ነው።

-  ሪፖርቱ የክልሉን መንግሥትና ህዝብ ስም ለማጥፋት ሆን ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች የክልሉ መንግሥት የሰጠውን መግለጫዎችና ጥንቃቄ የጎደላቸው የግል ሃሳቦችን እንደ ማጣቀሻ በመጠቀም ስህተት ተኮር የሪፖርት ስልት የተከተለ ነው።

የኢሰመኮ ሪፖርት : t.me/tikvahethiopia/73948

@tikvahethiopia