TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ጊዜያዊ ችግር ተማሪዎች ሳይደናገጡ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስልክ ለተማሪዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት፤ፍሬ በሌለው ምክንያት ወንድም ወንድሙን በመግፋት ለውጡን ወደ ኋላ ለመጎተት እየተሞከረ መሆኑን በስልክ ባስተላለፉት ገልጸዋል።

“አብዛኛው የክፉ ሃሳብ ፍላጎት ባይሳካም ተማሪዎች ያጋጠማችሁንና ያደረባችሁን ጉዳት ተረድቻለሁም” ብለዋል።

“ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ደጅ አድራችኋል፣ ተጎሳቁላችኋል፣ ተርባችኋል፣ ቁር መቷችኋል” ያሉት ዶክተር አብይ ተማሪዎቹ ለኢትዮጵያ አንድነት መስዋትነት እንደከፈሉ ቆጥረው ለአንድነትና ሰላም ቁርጠኛ አቋም እንዲወስዱ ጠይቀዋል።

“ብሶታችሁ ይሰማኛል፤ እኔም እጋራዋለሁ፤ እኔም እንደ እናንተ አይነት ችግር ያጋጥመኛል” በማለት፣ ባሉበት ሆነው በትግስት በመጠበቅ ለሁሉም ትምህርት የሚሆን ተግባር እንዲፈጽሙ አስገንዝበዋቸዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የብሩህ አዕምሮ ባለቤት መሆኑን ገልጸው፤ ተማሪዎቹም ያጋጠማቸውን ፈተና ለማለፍ ብሩህ አዕምሯቸውን መጠቀም እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ጉንዳን መጥፎ ወቅቶችን ለማለፍ ክረምት ሳይገባ በትብብር ምግቡን እንደሚያዘጋጅ ሁሉ፣ ተማሪዎችም ወቅታዊ ችግሮችን ለመሻገር የጉንዳንን መንገድ መከተል እንጂ የመንጋ ወሮ በላ አንበጣ ስልት መከተል እንደሌለባቸው መክረዋል።

ከዓመታት በፊት መለገስ እንጂ መለመን የማታውቀው ሶሪያ በውስጣዊ ቸግሮቿ ምክንያት ዛሬ ዜጎች ኢትዮጵያ ድረስ ለልመና መምጣታቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ተማሪዎች የኢትዮጵያን ወቅታዊ ችግር በማገናዘብና መረዳት የመፍትሄ አካል እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

እባብ መናደፍ ባህሪው መሆኑን ገልጸው፤ ”እኛ ግን ለእባብ አስተሳስብ ያላቸው ገፊ አካላት እባብ በመሆን ሳይሆን የሰው አዕምሮ በመጠቀም ልቀን ማላቅ፣ መርዙን ማስተፋት ይገባናል” ብለዋል።

ተማሪዎቹ አሁን ያሉበትም ሆነ እንሂድ የሚሉበት ቦታ አገራቸው መሆኑን ገልጸውላቸዋል።

በተለይ አማራና ኦሮሞ የተሳሰረና የተቀላቀለ ነው ያሉት ዶክተር አብይ፣ አዋጪው ጉዳይ በማይመች ሁኔታም ቢሆን የገጠመን ፈተና በመቋቋም ህዝቡ አንድና የተዋሀደ ሆኖ አገሪቷን አንድ እንዲያደርጋት ልብ ለልብ በመደማመጥ በቆራጥነት ችግሩን በትዕግስት ማለፍ ይጠይቃል ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአካባቢው ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች ለተማሪዎቹ ምክር በመለገስ፣ ተማሪዎቹ ያጋጠማቸውን ችግር እንደወላጅም ሆነው በጋራ እንደሚፈቱላቸው በመግለጽ ያለምንም ስጋት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሣህለወርቅ ዘውዴ በውጭ አገራት ኢትዮጵያን ለሚወክሉ አምባሳደሮች ሹመት ሠጥተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

1. አቶ ዘነበ ከበደ፣
2. አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ፣
3. ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን፣
4. አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድ፣
5. ወ/ሮ ናሲሴ ጫሊ፣
6. አቶ ሐሰን ታጁ፣
7. አቶ ረታ አለሙ፣
8. አቶ ሄኖክ ተፈራ፣
9. ወ/ሮ አለምፀሐይ መሠረት፣
10. ዶ/ር ትዝታ ሙሉጌታ፣
11. አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ፣
12. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣
13. አቶ ተፈሪ ታደሰ፣
14. አቶ ፍፁም አረጋ፣
15. ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር፣
16. አቶ ሚሊዮን ሳሙኤል፣
17. አቶ መለስ አለም፣
18. አቶ ብርሃኔ ፍስሐ፣
19. ዶ/ር አይሮራት መሐመድ እና
20. አምባሳደር ሳሚያ ዘካርያ በባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ተሹመዋል፡፡

ምንጭ፡- የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያዊያኑ አስክሬን ተገኘ‼️

ከሶስት ዓመት በፊት በፅንፈኛው አሸባሪ ቡድን አይሲስ ሊቢያ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ 34 ኢትዮጵያውያን አፅምን ማግኘታቸውን የሊቢያ ባለስልጣናት አስታወቁ።

የሊቢያ የወንጀል ምርመራ መምሪያ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ ሬውተርስ እንደዘገበው፥ ተይዞ መርመራ ሲደረገበት የነበረ የአሸባሪ ቡድኑ አባል የሰጠውን መረጃ መሰረት በማድረግ በተከናወነ ምርመራ ነው ኢትዮጵያውያኑ የተቀበሩበት የጅምላ መቃበር የተገኘው።

መምሪያው ያወጣው በድሮን የተቀረፀ ቪዲዮም ሲርጥ ተብላ በምትታወቀው የሊቢያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በሚገኝ እርሻ ውስጥ ነው የጅምላ መቃብሩ የተገኘው።

የኢትዮጵያውያኑ አፅም ተገቢው የህግ ስራ ከተከናወነ በኋላም ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ እንደሚላክም ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል‼️

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የትጥቅ ትግል ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ሀይሎች መካከል በርከት ያሉት ወደ ሰላማዊ መንገድ እየተመለሱ መሆኑ ተገለፀ።

የኦዲፒ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለፁት፥ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የትጥቅ ትግል ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች እንዳሉ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ሰሞኑን የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች እና የፀጥታ አካላት እያደረጉ ባለው ጥረት በርከት ያሉ ታጣቂዎች በግል እና በቡድን በመሆን ሰላማዊ ትልግ ለማድረግ እና በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ያለውን ለውጥ ለመደገፍ ወስነው ወደ ሰላማዊ የትግል መስመር እየተመለሱ ይገኛሉ ብለዋል።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ታጣቂዎች ሰላማዊ ትግል ለማድረግ በግል እና በቡድን እያሳለፉ ያለውን ውሳኔ እንደሚያበረታታም አቶ አዲሱ አስታውቀዋል።

ሰላማዊ ትግል ለማድረግ የወሰኑ ታጣቂዎችን በመቀበልም በፍላጎታቸው እና በችሎታቸው መሰረት በተለያየ የስራ መስክ ላይ እንዲሰማሩ እንደሚያደርግም ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ በሞጎር በረሃ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 17 ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ትግል መመለሳቸው ተገልጿል።

ታጣቂዎቹ ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመመለስ መወሰናቸውን ተከትሎም  የወረ ጃርሶ ወረዳ አቀባበል እንዳደረገላቸው ታውቋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በህገ ወጥ መንገድ 4ሺህ 583 ካሬ ሜትር መሬት ለባለሃብቶች ያስተላለፈው ኃላፊ ለከንቲባ ፅህፈት ቤት በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዋለ። በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አጃንባ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የመሬት አስተዳደር የሰነድ አልባ ዴስክ ኃላፊ ከሶስት የክፍሉ ባለሞያዎች ጋር በመተባበር መሬት ባንክ በኮድ ቁጥር 79 ገቢ የተደረገን ባዶ ቦታ የድርጅት በማድረግና መረጃ በማዛባት ለግለሰቦች ካርታ አዘጋጅቶ በመስጠት የህዝብን ውስን ሃብት ለግል ጥቅም በማዋል መንግስት ሊያገኘው የሚገባውን 12ነጥብ1 ሚሊየን ብር ማሳጣቱም ነው የተገለጸው። ተጠርጣሪው ከተጠቀሱት ባለሃብቶች ጋር በግል በፈጠረው ያልተገባ ቁርኝት ከ1ኛው ባለሃብት 600ሺህና ከ2ኛ ባለሃብት 400ሺህ ብር የሊዝ ዋጋ በማስከፈል በድርጅት ስም የመሬት ባንክ ንብረት የሆነውን 4ሺህ 583 ካሬ ሜትር አጥር የሌለው ቦታ ማስተላለፉ ነው የተገለጸው፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ‼️

የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ እሁድ ታህሳስ 14/2011ዓ.ም ከምሸቱ 2:30 ሰዓት አካባቢ በጥበቃ ሰራተኛ #በተተኮሰ ጥይት ተማሪ ዩሴፍ ገ/መስቀል ህይወቱ ያለፈ ሲሆን አንድ ተማሪ ደግሞ የመቁሰል ጉዳት ደርሶበታል፤ በዚህም ምክንያት የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎችና ማህበረሰብ ትላንት ሰኞ ጧት ሃዘናቸዉን ገልጸዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ ተማሪዎቹ ^ወንጀለኛዉ ግለሰብ ተይዞ ለፍርድ እንዲቀርብ በሰላማዊ መንገድ የጠየቁ ሲሆን የዩኒቨርሲቲዉ አመራረም ተማሪዎቹን አወያይቷል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻዉ ለተፈጠረዉ ችግር የተሰማቸዉን ኃዘን ገልጸዉ ወንጀለኛዉ ተይዞ ለፍርድ እንዲቀርብ ዩኒቨርሲቲዉ የበኩሉን እየሰራ እንደሆነ አስታዉቀዋል፡፡

ተማሪ ዩሴፍ የአምስተኛ አመት የመካኒካል ትምህርት ክፍል ተማሪ የነበረ ሲሆን የቀብር ስነ-ስርዓቱ በትውልድ ቦታው ደቡብ ጎንደር ዞን ሃሙሲት ተፈጽሟል፡፡ የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ለቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እየተመኘ በተማሪው ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡

የመቁሰል ጉዳት የደረሰበት ሌላዉ ተማሪ የሁለተኛ ዓመት የእጽዋት ሳይንስ ተማሪ ሲሆን አሁን በህክምና ላይ የሚገኝና ጤንነቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲዉ ትላንት ከሰዓት በኋላ ያለዉ ሁኔታ ሰላማዊና የተረጋጋ ሲሆን ከዚህ የተለየ የሚሰጡ አስተያየቶችም ከእዉነት የራቀ መሆኑን ዩኒቨርስዉ ይገልጻል።

ምንጭ፦ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅሬታ‼️

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢው ስለተፈጠረው ችግር ሚዲያዎች እያቀረቡትቡት ያለው ዘገባ ከእውነት የራቀ ነው ሊታረም ይገባል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዘን መግለጫ‼️
----------------------
በተማሪ ዩሴፍ ገ/መስቀል ሞት ምክንያት የደብረ ታብር ዩኒቨርስቲ የተሰማውን ጥልቅ #ሀዘን ይገልፃል፡፡

ተማሪ #ዩሴፍ የአምስተኛ አመት የመካኒካል ትምህርት ክፍል ተማሪ የነበረ ሲሆን እሁድ ታህሳስ 14/2011ዓ.ም ከምሸቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ በጥበቃ ሰራተኛ #በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፏል፡፡

የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ለቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እየተመኘ በተማሪው ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ዩኒቨርስቲው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አባ ቶርቤ‼️በኦሮሚያ ክልል “አባ ቶርቤ” (ባለ ሳምንት) በሚል ስም #በህቡዕ ተደራጅቶ የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ ጸጥታ ሃይል አባላትንና ንጹሃን ዜጎችን ሲገድል የቆየው ቡድን ውስጥ አባል የሆኑ ግለሰቦች እየተያዙ ይገኛሉ፡፡ ትላንት ከተያዙት መካከል ጋዲሳ ነጋሳ፣ መርጋ ተፈራ እና አኒሳ ጌታቸዉ #በነቀምት፣ ደምቢ ዶሎ፣ ነጆ እና ሰሜን ሸዋ ሰዎችን #ሲገድሉና #ሲያስገድሉ የነበሩ ሲሆኑ አዲስ አበባም #ባለሥልጣናትን የመግደል #ዕቅድ ነበራቸው፡፡ ተጠርጣዎቹ በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሃይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሏል፡፡

Via~wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

በፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ተሹመው ሲያገለግሉ የቆዩት ዳኛ #ዘርዓይ_ወልደሰንበት በፍቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸው ተሰማ። ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት የመልቀቂያ ደብዳቤውን ያስገቡት ለፌድራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ነው፡፡ በፈቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸውን ከዚህ ቀደም የዳኝነት ሹመታቸውን ላፀደቀላቸው የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ያሳወቁት አፈጉባዔው አቶ ታገሰ ጫፎ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️የሚመለከተው አካል በአሁን ሰዓት #በቡሌ_ሆራ_ዩኒቨርሲቲ እየሆነ ያለውን ጉዳይ በአስቸኳይ እንዲመለከተው ተማሪዎች ጠይቀዋል።
.
.
.
#TIKVAHETHIOPIA
🚫ተማሪዎች ካላስፈላጊ ግጭቶች እና ሁከቶች ራሳችሁን አርቁ። ሰላም እያደፈረሱ ያሉ አካላትን ለፀጥታ ሀይሉ አሳልፋችሁ ስጡ!!🚫
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የODP ማዕከላዊ ኮሚቴ‼️

በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) መካከል ተደርገው የነበሩ ስምምነቶችን ኦነግ ተግባራዊ አለማድረጉ አሁን በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚፈጠሩ ችግሮች ምክንያት እንደሆነ የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል ተደረሶ የነበረው በአንድ ሃገር ሁለት መንግሥት የማይኖርበት እና ትጥቅ የመፍታት ጉዳይ እንዳልተከበረ በምዕራብ ኢትዮጵያ እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች ምክንያት ነው ብሏል የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሞገስ ኢዳኢ ገልጸዋል፡፡

በኦነግ በኩል እንዲከበሩ የሚጠበቁ ሰምምነቶች ደግሞ የመኪና እና የቤት ጥቅማ ጥቅሞች እንዳልተከበረላቸው እና በODP በኩል በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የገቡ አካላት ለምን እንድገቡም ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

"ከደንቢ ዶሎ-ጊንቢ ያለው መንገድ ከተዘጋ ዛሬ 6 ቀኑ ነው፡፡ ከትላንትና ጀምሮ በደንቢ ዳሎ ከተማ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም በርሀብ አለቅን!!"

ይህን መልዕክት ያደረሱት በስራ ጉዳይ ወደ ደንቢ ዶሎ ያቀኑና በአሁን ሰዓት በአንድ ሆቴል ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ናቸው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዓለም ገነት ቆርቆሮ ፋብሪካና በግንባታ ላይ ያለው ፎር ፖይንት ሸራተን ሆቴል ባለቤት አቶ ዓለምፍፁም ገብረስላሴ ላይ የክስ መመስረቻ 10 ቀናት ፈቅዷል።

Via~fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️ በመቱ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ አለመረጋጋት የዛሬው የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቋረጥ ሆኗል። የሚመለከተው አካል ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ እንዲፈልግ ተማሪዎች ጠይቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ነዳጅ የጫኑ ሁለት ቦቴ መኪኖች መነሻቸዉን ጅቡቲ በማድረግ ወደ ሀገር ዉስጥ ገብተው ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ ተሸከርካሪዎቹ ነዳጁን ወደ አዶላ እና ደባርቅ እንዲያደርሱ የተሰጣቸውን ፍቃድ በመጣስ ተመልሰው ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል፡፡ ኮድ 95687/29557 ኢት የሆነ 46ሺ 700 ሊትር ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ወደ ደባርቅ እንዲሁም ኮድ 95829/29334 ኢት ተሳቢ ደግሞ 47 ሺህ 59 ሊትር ነዳጅ ጭኖ ወደ አዶላ ከተፈቀደላቸው መስመር ውጪ ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ በህብረሰቡ #ጥቆማ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ አሳዉቀዋል፡፡ ይሄን መሰል ህገ-ወጥ ደርጊት ለመከላከል መንግሥት ከምን ጊዜውም በላይ ጠንክሮ እየሠራ እንደሚገኝ አቶ ደመላሽ ተናግረዋል፡፡ ህዝቡም እያደረገ ያለውን ንቁ ተሳትፎ ምስጋናቸዉን ገልጸዋል፡፡በቀጣይ ህገ ወጦችን በንቃት በመከታተል ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ የበኩሉን ሃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም መገለጹን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
#tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

"ሰበር አፈትላኪ መረጃ" ተብሎ እና ከላይ ያለውን ምስል አስደግፎ እየወጣ ያለው መረጃ #ሀሰት እንደሆነ ቢታወቅ! "በእርግጥ በምእራብ ኦሮሚያ አንዳንድ ስፍራዎች የፀጥታው ችግር እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ቢሆንም በሂሊኮፕተር የታገዘ መከላከያ ሰራዊት ከኦነግ ጋር #እየተፋለመ ነው ተብሎ በማህበራዊ ሚድያ ከተወሰነ አቅጣጫ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የሀሰት ነው" ብለው አሁን ላይ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ በክልሉ በሀላፊነት ቦታ ያሉ ግለሰብ ዛሬ ከሰአት ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት‼️የሚመለከተው የመንግስት አካል ለወልዲያ እና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች ትኩረት እንዲሰጥ እንጠይቃለን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሸካ ዞን‼️

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል በሸካ ዞን ባለፉት ወራት ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት አገልግሎት አቁመው የነበሩ ተቋማት ወደ መደበኛ ስራቸው መመለሳቸው ተገለፀ።

የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ  በአሁን ወቅት አንፃራዊ ሰላም የሰፈነበት መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ የሺዋስ ዓለሙ አስታውቀዋል።

በፀጥታ መደፍሱ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አሁን ላይ ለማህበረሰቡ አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩ የገለፁ ሲሆን፥ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደቱ መጀመሩንም  አስረድተዋል፡፡

አስተዳዳሪው #የሚዛን_ቴፒ_ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢም ተማሪዎችን ተቀብሎ የዓመቱን የትምርት መርሀ ግብር ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው ብለዋል።

በፀጥታ መደፍረሱ የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ ከመምህራን እና ከሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጋር በመሆን ይሰራልም ተብሏል፡፡

በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ አካባውን ለቀው የነበሩ ነዋሪዎችም ወደ ቀደመው ህይወታቸው እንደተመለሱም ተጠቁሟል።

በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ማህበረሰቡ ከመንግስት ጋር በትብብር እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፥ SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia