TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ሀሰተኛ ወሬዎችን ተጠንቀቁ‼️

በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ #ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለመረበሽ የሚደረጉ ማናቸውንም ዓይነት እንቅስቃሴዎችን በመለየት በጋራ እንደሚከላከሉ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አካላት ገለፁ፡፡

ተማሪዎቹም ተጨባጭ ባልሆኑና መሠረተቢስ #ሀሰተኛ ወሬዎች ተታለው ሳይደናገጡ ዋና ትኩረታቸው በትምህርታቸው ላይ ሊሆን እንደሚገባም የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ አሳስበዋል፡፡

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ እንደገለፁት የዩኒቨርሲቲውን ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደትን #ለማደናቀፍና ለመረበሽ የሚፈልጉ አንዳንድ ሀይሎች ተማሪዎች ርስበርስ እንዲጋጩ ሆን ተብለው መሠረት የሌላቸው ሀሰተኛ ወሬዎችን በግቢው ውስጥ በመንዛት #ብጥብጥና ግጭት ለመፍጠር የተሞከረው ሙከራ አለመሳካቱን ገልፀው፣ ዩኒቨርሲቲው ያለውን መልካም ስምና ገፅታን በማበላሻትና ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተረጋግቶ እንዳይከታተሉ ለማድርግ በውጭም ሆነ በውስጥ በሚሰሩ የጥፋት ሀይሎች ላይ የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው የተደረሰበትንም ውሳኔና እርምጃ በቀጣዩ ዩኒቨርሲቲው እንደሚያሳውቅ ተነግረዋል፡፡

ተማሪዎችም ከእውነት በራቁና በሚናፈሱ ወሬዎች ሳይደናገሩ ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ እንዲሁም ወላጆችም ባልተጨበጠና ሀላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች በማህበራዊ ድህረ-ገጽ በሚሰራጩ መሰረት በሌላቸው ወሬዎች ሊረበሹ እንደማይገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ #ሲሳይ_ዮሐንስ እንደተናገረው ተማሪዎች እንዳይረጋጉ ሆን ተብሎ በሀሰት የሚነዙ ወሬዎች መኖራቸውን ጠቅሶ በአሁኑ ግዜ የመማር ማስተማሩ ተግባር ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ነው ሲል ተነግረዋል፡፡

ምንጭ፦ Hadiya zone Communication main process
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለገሀር🔝አዲሱ የለገሃር የተቀናጀ ማህበረሰባዊ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ልዩ የሚያደርገው ምንድነው?

አራት ቁልፍ ነጥቦች፦

1. በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ቀደም ሲል ከነበረው ልምድ በተለየ መልኩ ወደ ሌላ ቦታ #ሳይፈናቀሉ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ፤ ድጋፍ በተደረገው 1.8 ቢሊዮን ብር በአካባቢው ከፍተኛ ጥራት ያላቸው መኖሪያ ቤቶች ባለቤቶች ይሆናሉ።

2. በሁለተኛ የልማት ፕሮጄክቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በሽርክና (ጆይንት ቬንቸር) የተገባ ሲሆን፣ አዲስ አበባ 27 በመቶ ድርሻ ትይዛለች።

3. ሦስተኛ፣ ፕሮጄክቱ የለገሃርን ታሪካዊ ገጽታዎች ይዞ፣ አዲስ ከሚሰራዉ ሁለገብ ሰፈር ጋር ጎን ለ ጎን ይቀጥላል።

4. በመጨረሻም ፕሮጀክቱ ስራ ሲጀምር እስከ 25,000 ስራዎችን ይፈጥራል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በ57 ሚሊዮን ብር ወጪ የሦስት መስኖ ፕሮጀክቶች #ግንባታ መጀመሩን የዞኑ መስኖ ልማት ባለሥልጣን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በጋምቤላ ክልል ለታዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ክፍተቶች በየደረጃው የሚገኙ የጋህአዴን #አመራር አካላት #ችግር መሆኑ ተገለጸ፡፡ ከክልል እስከ ወረዳ የሚገኙ የድርጅቱ የአመራር አካላት በጋምቤላ ከተማ ጥልቅ ግምገማ እያካሄዱ ይገኛሉ።

Via~ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ🔝

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ሕዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት #ሊ_ዮንግ ጋር ተገናኝተው ተወያዩ። ውይይታቸው በዋናነት ያተኮረው በኢትዮጵያ ውስጥ የተቀናጀ የግብርና ኢንዲስትሪ ፓርኮችን ለማጠናከር የድርጅቱ ድጋፍ ቀጣይነት ላይ ነው። የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ምርታማነትን በማረጋገጥ፤ እሴትን በመጨመርና የኢትዮጵያዊያንን ኑሮ በማሻሻል የአገሪቱን ኢኮኖሚ መዋቅር ያሸጋግራል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_ዑመር በክልሉ በሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች የመሰረተ ልማትና ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። በጎዴ ከተማ በ300 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባ የንጹህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ፣ የጎዴ አጠቃላይ ሆስፒታል ማስፋፊያ እና በሸበሌ ዞን የ2 ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ ስራን የሚያስጀምር የመሰረት ድንጋይ ነው ያስቀመጡት።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤተ ጎልጎታ ሚካኤል🔝

ከላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መካከል በጥገና ላይ የቆየው ቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ዛሬ #ተመርቋል፡፡

ከላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መካከል የመሰንጠቅና የጣሪያ ማፍሰስ ችግር አጋጥሞት የነበረው ቤተ ግልጎታ ሚካኤል ከአሜሪካ አምባሳደር ፈንድ እና ከዓለም ሞኑመንት ፈንድ በተገኘ 700 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ነው ጥገና የተደረገለት፡፡

የጥገና ሥራው ወደፊትም የሚቀጥል ሲሆን በመጠለያ የሚገኙ ቅርሶችን በመጠገን ወደፊት መጠለያዎቹን
ለማንሣት እንደሚሠራ ከቅርስ
ጥበቃ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ሙሉ ጥገና ለማድረግ እስከ 300 ሚለዮን ብር እንደሚያስፈልግ ከዚህ ቀደም በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡

አምባሳደር ማይክል ራይነር ለቅርሱ እድሳት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ቤተክርስትያኗ ካባ አበርክታላቸዋለች፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ🔝 

በኢትዮጵያ በአለፉት ስምንት ወራት ሁለት #ተቃራኒ የሚመስሉ ሁነቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ፡፡ በአንድ በኩል ዴሞክራሲ፣ የሕግ የበላይነት፣ የኢኮኖሚ ግንባታ ይታያል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አለመረጋጋት፣ የሰላም መናጋት፣ ሕገወጥነት፣ በግልም ሆነ በቡድን መፃዒ #እድሎች እርግጠኛ አለመሆን ይስተዋላል፡፡

🔹VOA ከፕሮፌሰር ፕርሀኑ ነጋ ጋር ያደረገውን ቆይታ ከላይ ባለው የድምፅ ፋይል አዳምጡ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ ዩንቨርስቲ‼️

በአሶሳ ተከስቶ በነበረው #ግጭት የሦስት ተማሪዎች #ህይወት ማለፉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ ሚኒስቴር የሆኑት ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በተያያዘ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ምን ይመስላል በሚለው ጉዳይ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህ የተሰማው፡፡

ዶክትር ሂሩት ባለፉት ቀናት በውስን ዩኒቨርስቲዎች ተፈጥሮ የነበሩ ግጭቶችን አስመልክቶ ስለምክንያታቸም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም አሁን ያለው ሀገራዊ ለውጥ እና ለውጡን ለማደናቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ኢላማ መሆን፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚነሱ ሁከቶች ምክንያት ወይም ከግጭቶቹ በስተጀርባ ያለ ጠብ አጫሪ እንቅስቃሴዎች ምንነትና፣ መንግስት ለእነዚሁ ጉዳዮዮች እየሰጠ ያለው ምላሽ በተመለከተ አንስተዋል፡፡

ዶክተር ሂሩት ሀገሪቱ በለውጥ ሂደት ላይ ያለች፣ ባለፉት ሰባት ወራትም የተወሰዱ በርካታ እርምጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ አድናቆትን ያተረፉ ቢሆንም፤ አሁንም ግን ከቀድሞ በተለየ መልኩ በተለይ ዩኒቨርስቲዎችን ኢላማቸው አድርገው ለውጡን ለማደናቀፍ እንቅስቃሴዎች እያየን ነው ብለዋል።

ምንጭ:- ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አዲስ ሰብሳቢን #ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።

Via-ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ሰራዊት ትጥቅ በመፍታት ወደ ሃገር ውስጥ ገብቷል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ‼️

አሶሳ ዩኒቨርሲቲን ወደ ቀድሞ ሰላሙ #ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ካለፈው እሑድ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሰላማዊ መማር ማስተማሩ ተስተጓጉሏል፡፡ ተማሪዎች እና ተወካይ ፕሬዝዳንቱ እንደነገሩን የግጭቱ መነሻ የሁለት ተማሪዎች አለመግባባት ነው፡፡ ይህም እየተስፋፋ ሄዶ ወደ ቡድን ፀብ ተቀይሮ ነበር፡፡

ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር #ሃይማኖት_ዲሳሳ ችግሩን ለመፍታት ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ከተማሪዎች ጋር ምክክር ተደርጎ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በውይይቱም መግባባት ላይ መደረሱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡

ይሁን እንጂ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ትናንት ጠዋት ላይ ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሽ ሲገቡ እንደገና #ረብሻ ተጀምሮ ነበር፡፡

እንደ ተማሪዎቹ መረጃ የግጭቱ ዋነኛ ምክንያት የተማሪዎች መማክርት በወቅቱ አለመመረጥ ኢ-ፍትሐዊ አሠራር ፈጥሯል የሚል ነው፡፡

ተማሪዎቹ ምርጫው ‹‹ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይ መካሄድ ነበረበት፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት አልተካሄደም፤ እስካሁን ግን መቆየት አልነበረበትም›› የሚል አቋም አላቸው፡፡

አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችግሮችን ተወካዮቻቸው በወቅቱ አለመፍታታቸውም ለችግሩ መከሰት ምክንያት መሆኑን ነው ተማሪዎቹ የተናገሩት፡፡

ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ግን ‹‹በውይይቱ ለከፋ ግጭት የሚዳርግ ችግር አላገኘንም›› ነው ያሉት፡፡

በረብሻው ምክንያት ‹‹34 ተማሪዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸውም ይገኛል ብለዋል
ዶክተር ሃይማኖት፡፡

በተከሰተው ግጭት የሶስት ተማሪዎች ህይወት አልፏል፡፡ የጸጥታ ኃይሎች ግቢውን ወደ ቀድሞ ሰላሙ ለመመለስ እየሠሩ መሆናቸውን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎችም ይህን መመልከታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተረጋግተው ለመኖር እና ለመንቀሳቀስም ስጋት ውስጥ መሆናቸውንና ለሰላማቸው #ዋስትና እንደሚፈልጉ ነው የተናገሩት፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia