TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 " ዛሬ ጠዋት 32 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል " - የወላጆች ኮሚቴ ➡️ " የታይላንድ መንግስት ያልተቀበላቸው ወደ 300 ልጆች ማይናማር ካምፕ ውስጥ አሉ። 32 ልጆች መጥተናል " - ተመላሽ ኢትዮጵያዊ ከማይናማሩ እገታ ወጥተው ታይላንድ ካምፕ ከነበሩት ኢትዮጵያውያን መካከል 32 የሚሆኑት ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የወላጆች ኮሚቴና ተመላሾቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።…
" 45 ኢትዮጵያን ቦሌ ኤርፓርት ደርሰዋል " - ከማይናማር ተመላሾችና ቤተሰቦቻቸው
በማይናማር ታግተው ከቆዩ በኋላና ከእገታ ቦታ ወጥተው ከሳምንታት በፊት ወደ ታይላንድ ተሻግረው የነበሩ 45 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ጠዋት ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ።
ገና ታይላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሰጡን ቃል፣ 45 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ፣ ከእነዚህም መካከል 8 ሴቶች፣ ቀሪዎቹ ወንዶች እንደሆኑ ትላንት ምሽት ተመላሾቹ በረራ ሲጀምሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ዛሬ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ቤተሰቦቻቸውና ተመላሾቹም፣ 45 ኢትዮጵያውያን ከጠዋቱ 1 ሰዓት ገደማ አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፓርት መድረሳቸውን ገልጸዋል።
ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ/ም በተመሳሳይ መልኩ 32 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርም፣ “ 43 ኢትዮጵያውያን ደግሞ ዛሬ ምሽት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ” ሲል በእለቱ አስታውቆ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ይመጣሉ የተባሉት 43 ኢትዮጵያውያን መጡ ? ሲል ትላንት የጠየቃቸው የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ “ ነገ ጠዋት ይገባሉ ” የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።
‘‘ KK ’’ ከሚባለው ቦታ የወጡና ወደ ታይላንድ ለመሻገር ድንበር ላይ ያሉ ከ450 የሚልቁ፣ በሌላ ቦታ ጭራሹን የከፋ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው የተባሉ 14፣ ሌሎች በችግር ያሉ ዜጎችን ካሉበት ችግር ለማውጣት ምን እየተሰራ ነው ? በሚል ላቀረብነው ተጨማሪ ጥያቄ ዝርዝር ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ከቀናት በፊት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጃፓን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ወደ ታይላንድ በማሻገር ወደ አገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ እንደሆነ መግለፁ አይዘነጋም።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

Photo
#የኢትዮጵያውያንድምጽ🔈
“ ' KK' ከሚባለው ቦታ የወጣን ኢትዮጵያውያን አሁንም ድንበር ካለ ካምፕ 3 ህንፃዎች ከእያንዳንዱ ህንጻ 150 ገደማ ሰዎች አለን ” - ኢትዮጵያዊት በማይናማር
በማይናማር የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ የታይላንድ መንግስት፣ ሀገራት ዜጎቻቸውን ለመውሰድ እስካልሆኑ ድረስ የማይናማርን ድንበር አቋርጠው ወደ ታይላንድ እንዳይገቡ በመከልከሉ አሁንም የድረሱልን ተማጽኖ እያሰሙ ነው።
አንዲት የኢትዮጵያውያኑን ሲቃ የገለጸች ኢትዮጵያዊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለች ?
“ ኢትዮጵያውያን የሚገኙባቸው የቴሌኮሙኒኬሽን ማጭበርበሪያ ማዕከላት (Telecommunication Fraud Centers) Myanmar, Laos, Cambodia ናቸው። በእያንዳንዱ ቦታም በርካታ ፓርኮች (scam cities) አሉ። በእያንዳንዳቸው ፓርኮችም በርካታ ካምፓኒዎች ይገኛሉ።
በእነዚህ ቦታዎች የ29 ሀገራት ዜጎች ሲገኙ፣ ከቻይናውያን በመቀጠል ኢትዮጵያውያን እና ህንዳውያን የመጀመሪያውን ቁጥር ይይዛሉ።
በመጠኑ ቢለያይም በሁሉም ቦታዎች ጭካኔ የተሞላበት አካላዊ ጥቃት ይፈጸማል።
ከእነዚህ መካከል ሚሊተሪ የደረሰባቸውና ነጻ የወጡ ምያንማር - ታይላንድ ድንበር አካባቢ በምያንማር ግዛት የሚገኙ የተወሰኑ ፓርኮች ናቸው።
'Shuigou Valley Town' በሚባል ቦታ KK ፓርክ ላይ ‘kk1’፣ ‘kk2’፣ ‘kk3’፣ ‘kk4’ እንዲሁም ‘ማይዋዲ’ ላይ ሲሰሩ የነበሩ ስደተኞች በሚሊተሪ ድጋፍ ከካምፓኒዎች ወጥተው በካምፕ ይገኛሉ።
ከ‘kk’ እስከ ‘kk4’ (‘KK’ ከሚባለው ቦታ) የወጣን ኢትዮጵያውያን አሁንም ድንበር ላይ ካለ ካምፕ 3 ህንጻዎች ከእያንዳንዱ ህንጻ 150 ገደማ ሰዎች አለን።
(በእነዚህ ህንጻዎች የሌሎች ሀገር ዜጎችም ያሉ ሲሆን፣ የጠቀስኩር ቁጥር የኢትዮጵውያን ብቻ ነው። አጠቃላይ ከ ‘KK’ ብቻ ከ400 በላይ ኢትዮጵያውያን ወጥተናል። እኔ የሌለሁባቸው በሁለቱ ህንጻዎች ያሉትን ወገኖች ትክክለኛ ቁጥራቸውን አልያዝኩም።)
በአጠቃላይ የ29 ሀገር ዜጎች አብረውን የወጡ ሲሆን፣ ወደየሀገር ለመመለስ ግን የየዜጎቹ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ኤምባሲዎች እንደሚሰጡት ፈጣን ምላሽና የማሳለጥ ስራ ይወሰናል።
ለምሳሌ ህንድና ቻይና ባንኩክ መሄድ ሳይጠበቅባቸው ዜጎቻቸውን ማሶት ከምትባለው ምያንማር - ታይላንድ ቦርደር የሆነች የታይላንድ ከተማ ድረስ አውሮፕላን በመላክ አንስተው ዜጎቻቸውን እየመለሱ ነው።
እኛ ጋር የነበሩ 570 ህንዳውያን ትላንት ሚሊተሪ አውሮፕላን ተልኮላቸው ወደ ሀገራቸው ተጉዘዋል። ቻይና በበኩሏ በቀን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ከማሶት ቀጥታ በረራ ወደ ቻይና እየመለሰች ሲሆን፣ ማርች 14 አጓጉዛ ትጨርሳለች።
ኢትዮጵያውያን ዜጎች ግን ከዚህ በፊት ታይላንድ የገቡት ወደ ሀገራቸው ሳይመለሱ 40 ቀን በመቆየታቸው እኛም ራሱ ወደ ታይላንድ እንድንገባ እንኳ አልተፈቀደም። መጥቶ የጎበኘን፣ ሂደት የጀመረልን ተቋምም የለም።
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያን መንግስትን የወላጆች ኮሚቴ ሲጠይቀው፣ ‘ልጆች ያሉበት ቀጠና ከታይላንድና ምያንማር ቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ገብቶ ለማውጣት ተቸግረን ነው" ይል ነበር።
አሁን ደግሞ 'ና ውሰድልኝ' ሲባል በጥቃቅን ሰበብ እያምታታ የዘገየበት ምክንያት አልገባንም። ሰሞኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ‘ተላከ’ የተባለው ቡድንም አልጎበኘንም፣ ምናልባት እየሰራ ሊሆን ይችላል እስካሁን ግን ያወቅነው ነገር የለም።
የታይላንድ መንግስት ‘የዜጎች ሀገር ኤምባሲና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹን ለመውሰድ ዝግጁነቱን እስካልገለጸ ጽረስ ድንበሬን አቋርጠው እንዲገቡ አልፈልግም’ በማለቱ አሁንም ድንበር ላይ እንገኛለን።
ይህ ሚሊተሪም አስቸጋሪ ስለሆነ ሀገራችን በቶሎ ካልገባን በቀን 300 ሚሊዮን ‘ኪያት’ እያወጣ እየመገበ ለመቀጠል እንደሚቸገር በመግለጹ ወደ ካምፓኒዎች እንዳይመልሰን የሚል ስጋት ላይ ነን።
በአጠቃለይ ከላይ ከተጠቁሱት ውጪ በርካታ ቦታዎች በተለይ ወደ ማያንማር ገባ ያሉት አሁን ድረስ በሚሊተሪ ተደራሽ ያልሆኑ ሰዎች ያልወጡባቸው አሉ።
ከእነዚህ መካከልም አንድ በልዩ ሁኔታ ላጋራ ምፈልገው ‘ናሽናል ፓርክ’ የሚባል ቦታ ስላሉ ኢትዮጵያዊያን ነው። እዚህ ቦታ 14 ኢትዮጵያዊያን አሉ። ከ14ቱ 2ቱ ከባድ ድብደባ እና የኤሌክትሪክ ሾክ የተፈጸመባቸው ናቸው።
ስልክና ፓስፖርት ተቀምተው ተገደው በቀንና በሌሊት እየሰሩ ይገኛሉ።
እዚሁ ቦታ ሲሰሩ የነበሩ ኬንያውያን ትላንት ተመርጠው ወጥተው ወደ ሀገራቸው እንዲሸኙ ወደ ካምፕ ተልከዋል። ይህም የሆነው ቀድማ የወጣች ኬንያዊት ለኤምባሲያቸው በሰጠችው ጥቆማ ኢምባሲው ከሶ ‘ዜጎቼን መልሱልኝ’ በማለቱ ነው።
14 ኢትዮጵያውያን ግን አሁንም ድረስ እንደታፈኑ ናቸው።
ሚሊተሪው ቦታው ድረስ ስላልሄደ ተቋማት ከ‘Scam city head office’ ጋር በሚያደርጉት ንግግር ነው የግቢው ፖሊስ ሊሸኛቸው የሚችለው።
በአሁን ወቅት እዛ ፓርክ ኢትዮጵያውያን ብቻ ይገኛሉ። እኛን እንድናስወጣቸው በጽኑ ይለምኑናል።
እኔም ሎኬሽናቸውን ይዤ እኛን ያወጣንና አሁን ጥበቃ እያደረገልን ያለውን ሚሊተሪ ለማናገር ሞክሬ ነበር። 'It is too far, we have nothing to do’ አለኝ። ያሉበት ቦታ አሁን ካለንበት ከ‘kk’ ወደ 20 ኪሎ ሜትር ይርቃል።
የእነዚህን ሰዎች ስም ዝርዝርና ፓስፖርት ፎቶ ያዘጋጀሁ ሲሆን፣ ሊያግዛቸው የሚችል አካል ካለ (ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የታይላንድ ቆንስላ፣ የጃፓን ኤምባሲ፣ የወላጆች ኮሚቴ) ማጋራት እችላለሁ። አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ናቸው።
በፍጹም እነሱን ትቼ የመውጣት ሞራሉም የለኝም። የሚያግዛቸው ተቋም (የታይላንድ ቆንስላና የጃፓን ኢምባሲ) በመፈለግ ላይ ነኝ። ሁላችንም ተረባርበን ወጣቶቹን እናስወጣቸው አደራ” ስትል ተማጽናለች።
ከማይናማሩ እገታ ወጥተው ወደ ታይላንድ ተሻግረው የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን ትላንት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የተጀመረ ሲሆን፣ በተለይ በማይናማር ያሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን አሁንም በችግር ላይ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እየገለጹ ይገኛሉ።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከቤቷ የማብሰያ ክፍል በኩል ካለው በረንዳ 5ኛ ፎቅ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወድቃ ለህክምና እርዳታ ወደ ያኔት ሆስፒታል እየተወሰደች ባለበት ወቅት ህይወቷ አልፏል " - ፖሊስ
በሟች ወጣት ቀነኒ አዱኛ አሟሟት ዙሪያ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሰንሻይን ቤቶች ፊት ለፊት ከሚገኘው ውዳሴ ህንፃ ላይ ነዋሪ የነበረችው ሟች ቀነኒ አዱኛ መጋቢት 01 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 10፡00 ሠዓት አካባቢ ከቤቷ የማብሰያ ክፍል በኩል ካለው በረንዳ 5ኛ ፎቅ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወድቃ ለህክምና እርዳታ ወደ ያኔት ሆስፒታል እየተወሰደች ባለበት ወቅት ህይወቷ እንዳለፈ ፖሊስ ገልጿል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃው ከደረሰው በኋላ የምርመራ ቡድን በማዋቀርና ቦታው ድረስ በመሄድ ተገቢውን የቴክኒክና የታክቲክ መረጃዎችን ያሰባሰበ መሆኑንና የሟችንም አስከሬን ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለተጨማሪ ለምርመራ እንዲሄድ ማድረጉን አመልክቷል።
ሟች ቀነኒ በወቅቱ ከበረዳ ላይ በወደቀችበት ሰዓት ፖሊስ በቤቱ ውስጥ የነበረውን ባለቤቷን ድምፃዊ አንዷለም ጎሳን በቁጥጥር ስር በማዋልም ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።
በቀጣይ የመጨረሻውን የምርመራ ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ያስታወቀ ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ከፖሊስ የወንጀል ምርመራ ውጤት በፊት የሚናፈሱ መረጃዎች ተገቢነት የሌላቸው ናቸው ብሏል።
ከዚህ ባሻገር የሚናፈሱት መረጃዎች በምርምራ ሒደቱ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅህኖ በመገንዘብ የተሳሳተ መረጃ የሚያስተላልፉ እና የሚያሰራጩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

" የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ቀድመው ተገቢውን ሃላፊነታቸው ካልተወጡ የትግራይ ህዝብ መወጣት ወደ ማይችለው ዳግም አስከፊ ጦርነት ይገባል " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስት እና የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ድጋፍ ጠይቋል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ መጋቢት 3/2017 ዓ..ም ባወጣው መግለጫ ፤ የፌደራል መንግስት በፀጥታ ሃይል ስም በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት አካላት የአንድ ቡድን ተላላኪዎች እንጂ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ የማይወክሉ መሆናቸው ተረድቶ አስፈላጊ እገዛ እንዲያደርግ ጠይቋል።
የፌደራል መንግስት ህገ-ወጥ አካሄድ በተከተለ ቡድን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈርሶ ዳግም ወደ ጥፋት እየተገባ ዝም ብሎ መመልከት አይገባም ሲል አክሏል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ባስተላለፈው ግልፅ መልእክት ፤ " ቡድኑና አሽከሮቹ ወንጀሎቻቸው ለመደበቅ ሲሉ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሲያፈርሱ በዝምታ ማየት ትቶ አስፈላጊ ጫና ማድረግ አለበት " ብሏል።
የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ቀድመው ተገቢውን ሃላፊነታቸው ካልተወጡ ግን የትግራይ ህዝብ መወጣት ወደ ማይችለው ዳግም አስከፊ ጦርነት ይገባል ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስጠንቅቋል።

" የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ቀድመው ተገቢውን ሃላፊነታቸው ካልተወጡ የትግራይ ህዝብ መወጣት ወደ ማይችለው ዳግም አስከፊ ጦርነት ይገባል " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስት እና የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ድጋፍ ጠይቋል። ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ መጋቢት 3/2017 ዓ..ም ባወጣው መግለጫ ፤ የፌደራል መንግስት በፀጥታ ሃይል ስም በመንቀሳቀስ…
#Tigray
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ መግባትን ጨምሮ " የትኛውንም ዓይነት ድጋፍ ለማድረግ " በቂ ምክንያት እንዳለው ተናግረዋል።
አቶ ጌታቸው የፕሪቶሪያው ስምምነት አካል የሆኑት የፌደራል መንግሥት እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ " በትግራይ ያለው ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱን እና የፕሪቶሪያ ስምምነት መፍረስ የሚያስከትለውን ትልቅ ችግር ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው " ብለዋል።
ይህን ያሉት ከክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። #ቢቢሲ

#Tigray የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ መግባትን ጨምሮ " የትኛውንም ዓይነት ድጋፍ ለማድረግ " በቂ ምክንያት እንዳለው ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው የፕሪቶሪያው ስምምነት አካል የሆኑት የፌደራል መንግሥት እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ " በትግራይ ያለው ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱን እና የፕሪቶሪያ ስምምነት መፍረስ የሚያስከትለውን…
#ትግራይ
" እነዚህ ሰዎች አብደት ላይ መሆናቸውን ሊነገራቸው ይገባል " - አቶ ጌታቸው ረዳ
🚨 " እኔ ልለው የምችለው ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ አስከፊ ነው !! "
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር።
በዚህም ቃለ ምልልስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
➡️ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ መግባትን ጨምሮ የትኛውንም ዓይነት ድጋፍ ለማድረግ በቂ ምክንያት አለው።
➡️ የፌደራል መንግሥት እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በትግራይ ያለው ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱን እና የፕሪቶሪያ ስምምነት መፍረስ የሚያስከትለውን ትልቅ ችግር ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
➡️ የሠራዊቱ አመራሮች የታገዱት ከመንግሥት ውሳኔ ውጪ መላ ሕዝባችንን እና ወጣቱን ወደ ግርግር፤ የፀጥታ ኃይላችንን ወደ እርስ በርስ ግጭት ብሎም ሕዝባችንን ወደማይወጣበት አዘቅት የሚያስገባ አደገኛ እንቅስቃሴ ባለመቆሙ ነው።
➡️ አመራሮቹ " ውሳኔ " ያሉትን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉንም እርምጃዎች መውሰድ በመጀመራቸው እንደታገዱ ሆነዋል።
➡️ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ሰብረው እየገቡ ነው፣ ጊዜያዊ የአስተዳደር ኃላፊዎችን እያነሱ ነው፣ ይህ ደግሞ በሕዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በይበልጥም በራሱ በሠራዊቱ ውስጥ ውዥንብር ፈጥሯል።
➡️ ጥያቄው " ፕሬዝዳንቱን ወይም የካቢኔ አባላትን ከሥልጣን የማንሳት እና አለማንሳት " አይደለም፤ ከሁሉም በላይ በፕሪቶሪያ ስምምነት የተገኘውን ትንሽ ሰላም የማስጠበቅ ነው።
➡️ የውጭ ኃይሎች በዚህ ውስጥ ተሳታፊ ናቸው ብለን የምናምንበት ምክንያት አለን። አሁንም ይህ ውሳኔ ይቆማል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
➡️ የዓዲግራት ከንቲባ ቢሮ ይዘዋል። ይህን ለማድረግ ያቀዱት ዓዲግራት ላይ ብቻ ሳይሆን መቐለ ላይ ማድረግም ይፈልጋሉ።
➡️ የትግራይን ሕዝብ ኃይል በመጠቀም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን በሕገወጡ የህወሓት አንጃ ስም መያዝ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው እና ወደ ተጨማሪ ጥፋት የሚያመራ ነው።
➡️ እብደታቸውን ለማስቆም የቻልኩትን ሁሉ ለማድረግ እየሞከርኩ ነው ያለሁት። እብደቱን የማስቆም አቅም አለኝ ወይ ? የሚለው የተለየ ጉዳይ ነው፣ ነገር ግን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ ገብቶ እነዚህ ሰዎች አብደት ላይ መሆናቸውን ሊነገራቸው ይገባል።
➡️ " የወረዳ ምክር ቤቶች እንደገና ሊዋቀሩ ይገባቸዋል " የሚል ጥያቄ ይነሳል በሕግ እና በመመሪያ መፍታት እንደምንችል በግልፅ ተናግሯል።
➡️ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ከተናገራቸው እጅግ በጣም አስቂኝ ነገሮች ውስጥ አንዱ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሕግ እና ሥርዓትን ለማስከበር በሚያደርገው ውሳኔ ላይ እንቅፋት ሆኗል" የሚል ነው። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች በሕገወጥ የወርቅ እና የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ወደ እስር ቤት ማስገባት የሚለውን ሃሳብ ሲቃወሙ ቆይተዋል። በትግራይ ሕዝብ ላይ ለተፈፀመው ዘግናኝ ወንጀል ምንም መፍትሔ ሳያበጁ እና አሁን በየመንደሩ ማህተም መንጠቅ ሕግ እና ሥርዓትን እንደማስከበር ተደርጎ መወሰዱ ከንቱ ነው።
➡️ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ግጭት እንዲፈጠር አልፈልግም። የሚፈጠር ከሆነም የትግራይ ሕዝብ የገፈቱ ቀማሽ እንዲሆን አልፈልግም። የትግራይ ሕዝብ በዚህ ዓይነት ውዥንብር ውስጥ እንዲገባ አልፈልግም፣ አንዳንድ ባልደረቦቼ ይህንን ሀሳብ ውስጥ ያስገቡ አይመስሉም፣ ወይም የትኛውንም ክፍተት ለመጠቀም ያሰቡ ይመስላሉ፣ እና እኔ ልለው የምችለው ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ አስከፊ ነው።
#ትግራይቴሌቪዥን #ቢቢሲ

#SafaricomEthiopia
🤙🏽ከሳፋሪኮም ወደ የቴሌ የሚያስደውሉ የድምፅ ጥቅሎች በመጠቀም ከ07 ➡️ 09 መስመር በሽ በሽ ብለን እንደዋወል! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#MPESASafaricom
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether

" ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ሁኔታ የተፈጠረው ' የፍቅር ጥያቄዬ ምላሽ አላገኘም ' በሚል ነው " - ፖሊስ
በአዲስ አበባ ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ካርል አደባባይ አካባቢ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን እንዳጠፋ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ አማርኛ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
" ክስተቱ ያጋጠመው ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም. ጠዋት ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ለሁለት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ድረስ ባላው ጊዜ ውስጥ ነው።
ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ሁኔታ የተፈጠረው ' የፍቅር ጥያቄዬ ምላሽ አላገኘም ' በሚል ምክንያት ነው።
አቶ ሽፈራው ረጋሳ የተባለ የባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ ለሥራ ባልደረባው የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ምላሽ ባለማግኘቱ ግለሰቧን እና ከግለሰቧ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው በሚል የጠረጠረውን ሌላ ባልደረባውን በመግደል ራሱን አጥፍቷል።
ግለሰቡ የፍቅር ጥያቄ ያቀረበላት ወይዘሪት ሃና ተስፋዬ የተባለች 32 ዓመት ወጣት እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለ የሥራ ባልደረቦቹን ነው በጥይት ተኩሶ የገደለው።
ወንጀሉን የፈፀመው የጥበቃ ሠራተኛ ካልተራው ሌላ ሠራተኛን ተክቶ በመግባት እና ከምሽት የጥበቃ ሠራተኞች የጦር መሳሪያ በመቀበል ነው ግድያውን የፈጸመው።
ግለሰቡ ግድያውን የፈጸመው ወደ ዕለታዊ ሥራቸው እስኪገቡ ድረስ በመጠበቅ ነው።
መጀመሪያ አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለውን ግለሰብ በሁለት ጥይት መትቶ ገድሏል።
ባልደረባውን ተኩሶ ከገደለ በኋላ ሌላኛዋን የጥቃቱ ሰለባን ከመግደሉ በፊት ከድርጊቱ እንዲቆጠብ መጠየቁን ነገር ግን ፈቃደኛ አልነበረም።
ግለሰቡ መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ እና እጁን እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦለት የነበረ ሲሆን፣ በዚህ መካከልም ወደ ባንኩ አንደኛ ፎቅ በማምራት የፍቅር ጥያቄውን አልተቀበለችም ያላትን በተመሳሳይ ሁኔታ በጥይት መትቶ ገድሏል።
በሁለቱ ግድያዎች መካከል እስከ 15 ደቂቃ የሚሆን የጊዜ ክፍተት ነበር።
ግለሰቡ ሁለቱን ባልደረቦቹን ከገደለ በኋላ በያዘው መሳሪያ የእራሱንም ሕይወት አጥፍቷል።
በክስተቱ በአጠቃላይ የሦስት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።
ሁለቱ ሟቾች ወ/ሪት ሃና ተስፋዬ እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው የሚጠቁም ፎቶግራፎች ተገኝተዋል። ፖሊስ በምርመራው ስለግንኙነታቸው ያጣራል።
ከዚሁ ክስተት ጋር በተያያዘ ፖሊስ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ሂደት ይቀጥላል። "
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

#ትግራይ " እነዚህ ሰዎች አብደት ላይ መሆናቸውን ሊነገራቸው ይገባል " - አቶ ጌታቸው ረዳ 🚨 " እኔ ልለው የምችለው ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ አስከፊ ነው !! " የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር። በዚህም ቃለ ምልልስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ምን አሉ ? ➡️ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ መግባትን…
#Update
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ያቀረበውን ጥሪ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ተቃወመ።
የተጀመረው " ህግ የማስከበር እርምጃ " ያለው ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ እገዛ እንዲያደርጉ ያቀረበው ጥሪ " ይፋዊ ክህደትና የፕሪቶሪያ ስምምነት የሚያፈርስ " ሲል ውድቅ አድርጎታል።
" ህወሓት ፤ ህዝብና ሰራዊት ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጡትን ተልእኮዎች ለመፈፅም የሚያስችል የአመራር ማስተካከያ ይደረግ እንጂ ይፍረስ አላልኩም ብሏል " ሲልም ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ማህበረሰብ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በመተግበር የትግራይ ዘላቂ ሰላምንና መልሶ ግንባታ እውን እንዲሆን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧክ።
" መላው ህዝብ በትግራይ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እንዲከበር ፣ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥና ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን ግዴታው ይወጣ " ሲል ህወሓት አሳስበዋል።
በተያያዘ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሲያወጣቸው የነበሩ መግለጫዎች ወደ ህዝቡ ሲያሰራጩ የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምፂ ወያነ " የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ " የሚጠይቀውን መግለጫ ሳያስተናግዱት ቀርተዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች ፤ ለ104.4 የመቐለ ኤፍኤምና ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን አዲስ ስራ አስኪያጆች መመደባቸው ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#ኮሬ 🚨" ማንም ከህግ በላይ መሆን አይችልም ህገ መንግስት ይከበር "- የታጣቂዎች ግድያ ከዘጠኝ አመታት በላይ ያማረራቸው ዞን ነዋሪዎች ➡️ " መንግስት ይህን ሕዝብ ስለማወቁ እጠራጠራለሁ " - የኮሬ ዞን የቀድሞ አመራር ሰሞኑን የንጹሐን ሕይወት በታጠቁ አካላት ጥቃት ማለፉን የኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ የጀሎ ቀበሌ ነዋሪዎች እንደተረዳ የኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል። ዞኑ…
" የቤተክርስቲያን ማሳ እያረሱ በነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ የአንድ አርሶ አደር ሕይወት ጠፍቷል " - የኮሬ ዞን ጎርካ ነዋሪዎች እና የሃይማኖት አባቶች
ባሳለፍነዉ ቅዳሜ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ " ጃሎ " ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በታጠቁ ሃይሎች በተፈፀመ ጥቃት የሁለት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ይታወቃል።
ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ በወረዳዉ " ዳኖ ቡልቶ " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን እርሻ ላይ በነበሩ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ላይ በተፈፀመ ሌላ ድንገተኛ ጥቃት እስካሁን የ1 ሰዉ ሕይወት ማለፉን ቄስ ጴጥሮስ ቶንሴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ሟቹ አርሶ አደር በድሉ በቀለ የዳኖ ቡልቶ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አባል ነው። የሁለት ልጆች አባትም ነበር። ቤተክቲያኒቱ አዉጃ በጠራችዉ የደቦ እርሻ ስራ ላይ ባለበት ከምዕራብ ጉጂ ዞን በኩል ካለ አዋሳኝ ጫካ ዉስጥ እንደመሸጉ በሚነገር የታጠቁ ሃይሎች በተከፈተ ድንገተኛ ጥቃት ሕይወቱ አልፏል " ሲሉ ገልፀዋል
" አሁንም ጩኸታችን ዛሬ ለሞተዉ ወጣት የቤተሰብ አስተዳዳሪ ብቻ ሳይሆን ላለፉት ስምንትና ዘጠኝ ዓመታት በገዛ ማሳቸዉ ላይ በከንቱ ደማቸዉ ለፈሰዉና አሁንም እየፈሰሰ ላለዉ የኮሬ አርሶ አደር ነዉ " የሚሉት ቄስ ጴጥሮስ " መንግስትና የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፃቸን ይስማ " ብለዋል።
አቶ ይፍሩ ዮናስና ደበበ የተባሉ የአካባቢዉ ነዋሪ በጥቃቱ የሞተዉ አርሶ አደር የአካባቢያቸዉ ነዋሪና የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አባል እንደነበር ተናግረዋል
" የኮሬን ሕዝብ መንግስት ያዉቀዋል ? የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ የማያቋርጥ ተደጋጋሚ ጥቃት ይፈፀምብናል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የመንግት አካላትን ሃሳብ ለማካተት ወደ ኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ እና የጎርካ ወረዳ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ አየለ የእጅ ስልኮች ደዉሎ ነበር።
በሰዓቱ ጥቃት መፈፀሙን አረጋግጠው በቀጠናዉ አሁንም ዉጥረቶች ስላሉ በ መረጃ ለመስጠት አመቺ እንዳልሆነላቸው ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW

በቀጣይ 10 ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ ዝናብ ሊያገኙ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ፤ በቀጣይ 10 ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ ዝናብ ሊያገኙ እንደሚችሉ ገልጿል።
በጥቂት አካባቢዎች የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል።
- በደቡብ፤
- በደቡብ ምዕራብ፣
- በመካከለኛዉ፣
- በሰሜን ምስራቅ፣
- በምስራቅና በስምጥ ሽለቆና አጎራባች አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡
የበልግ አብቃይ አከባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊያገኙ ይችላሉ።
በዚህ ወር በመደበኛነት ትኩረት ከሚሹ የአየር ሁኔታ ክስተቶች መካከል ቀን ላይ የሚኖረው የሙቀት መጠንና ሌሊት ላይ የሚታየው ወበቅ አንዱ ነው።
በሚቀጥሉት 10 ቀናት ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሙቀት ጋር በተያያዘ ፦
° በጋምቤላ፣
° በአፋር፣
° በሶማሌ፣
° በቤንሻንጉል ጉሙዝና በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እሰከ ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ.
በደቡብ፤ በመካከለኛና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ በልግ አብቃይ አከባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እርጥበት የአፈር ውስጥ የውኃ መጠንን ስለሚያሻሻል የሰብሎች የማሳ ዝግጅት ለማከናውን፣ ለቋሚ ተክሎች፣ ለግጦሽ ሳርና ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ጥሩ እድል ይኖረዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች ዘር ለመዝራት የዘገዩ አካባቢዎች የሚጠበቀውን እርጥበት ለመጠቀም በቂ ዘር ለመዘራት የሚያሰቸል ዝግጅት ከወዲሁ ማድረግ ያስፈልጋል።
#EPA