TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል። የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97…
#ነዳጅ

የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል።

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።


አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር

አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር

አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር

የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር

አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር

#ነዳጅ #ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ብርሃን_ባንክ
የብርሃን ጉዞጎ ተጠቃሚዎች ብቻ የሚያገኙትን ልዩ ቅናሾች እና ጥቅሞች ያግኙ፣ ይህም ጉዞዎን የበለጠ ተመጣጣኝ እና አስደሳች ያደርገዋል።
👉ደንበኞች በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው ከ10 በላይ አለም አቀፍ የአየር መንገዶች የበረራ ትኬቶችን ዋጋ ማወዳደር ያስችላል።
👉ደንበኞች በሚመርጡት አየር መንገድ የበረራ ትኬቶች ላይ ቅናሽ ዋጋዎች እንዲያገኙ ያስችላል።
👉ደንበኞች በሚመርጡት ሰዓት እና ዋጋ አስተማማኝ የበረራ ቡኪንግ ለመያዝ ያስችላል።
👉በሁሉም የባንካችን ቅርንጫፎች፣ በሞባይል ወይንም በኢንተርኔት ባንኪንግ ክፍያዎችን መፈጸም ያስችላል፡፡
👉ያለ ተጨማሪ ክፍያ ሳምንቱን ሙሉ ለ 24 ሰዓታት የባለሙያ ምክር እና እርዳታ እንዲያገኙ ያስችላል።
ስለ ብርሃን ጉዞጎ (GuzoGo) አገልግሎት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በ0116506355 /0116507425 ወይም በነፃ የጥሪ ማዕከል ቁጥር 8292 ላይ ይደውሉ፤
እንደስማችን ብርሃን ነው ስራችን
#eticket #guzogo #internetbanking #mobilebankingbanking #berhanbank #bank #finance #Stressfreebanking #bankinethiopia
#SafaricomEthiopia

🗺 ሃይኪንግ ላይ ሆናችሁ ዳታ መጠቀም ፈልጋችሁ ታውቃላችሁ? እነሆ አዲስ ቅመም!
💨 የትም ይዛችሁት መሄድ የሚያስችላችሁ እስከ 6 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😋

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት
  
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom #1Wedefit #Furtheraheadtogether
" እገዳው ተነስቷል " - ኢሰመኮ

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በኅዳር ወር 2017 ዓ.ም. ፦
- የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል፣
- የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች
- ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባሉ 3 በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶችን በድጋሚ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከልን ማገዱ ይታወሳል።

ኢሰመኮ ታኅሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚተላለፉ እገዳዎች በሲቪል ምኅዳሩ እና በማኅበር የመደራጀት መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይፈጥሩ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስቧል።

በተጨማሪም ኢሰመኮ በድርጅቶቹ እገዳ ላይ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ምርመራ ያከናወነ ሲሆን የደረሰባቸውን ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ለሚመለከታቸው አካላት ማጋራቱን አመልክቷል።

ኢሰመኮ በተለይ አዲስ በተሾሙት ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በኩል ጉዳዩን በልዩ ትኩረት በመከታተል ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና እገዳ ከተጣለባቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግ ለጉዳዩ መፍትሔ ለማስገኘት ሢሠራ እንደቆየ ጠቁሟል።

ይህ የኢሰመኮ ጥረት ውጤት በማስገኘቱ በ4ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ከዛሬ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የተነሳ በመሆኑን ኢሰመኮ አሳውቋል።


@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፐርፐዝብላክ ° " ሥራ ላይ የነበሩ ሱቆችም የቤት ኪራይ መክፈል ስላልተቻለ ሊዘጉ ነው " - የፐርፐዝ ብላክ ባለአክሲዮኖች ° " በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ስላለ ምንም  አይነት መግለጫ አንሰጥም " - ድርጅቱ የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ባለአክሲዮኖች፣ የድርጅቱ አካላት መታሰራቸውን ተከትሎ ድርጅቱ ላይ ባላቸው ሼር ላይ ሥጋትና ቅሬታ እንዳደረባቸው፣ ለቅሬታቸው አፋጣኝ ምላሽ  እንዲሰጣቸው በቲክቫህ…
“ ድርጅቱ ለኪራይ፣ ደመወዝና ለሌሎች ወጪዎች ክፍያ ባለመፈጸሙ ሠራተኛው ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቋል ” - የፐርፐዝ ብላክ ባለአክሲዮኖች

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ሕብረት ባንክ ካለው ገንዘብ ውጪ በሌሎች ባንኮች ያለውን ገንዘብ እንዲያንቀሳቅስ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቢሰጥም በዐቃቢ ህግ ይጎባኝ ውሳኔው መታገዱን የፍርድ ቤት ሰነድና ባለአክሲዮኖች አመለከቱ።

ሁነቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያስረዱት ባለአክሲዮኖች የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ አካውንት ለሰባት ወራት ተዘግቶ መቆየቱን፣ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለደመወዝና ሥራ ማስኬጃ ክርክር ሲካሄድ ቆይቶ እንደነበር ገልጸዋል።

በክርክር ሂደቱም፣ ፍርድ ቤት ሕብረት ባንክ ከተቀመጠው ገንዘቡ ውጪ በሌሎች ባንኮች ያለው የፐርፐዝ ብላክ ገንዘብ እንዲንቀሳቀስ፣ ለማንቀሳቀስ አስተዳዳሪ እንዲሾም ወስኖ እንደነበር አስረድተዋል።

“ነገር ግን ዐቃቤ ሕግ ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ ጠይቆ የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ አሳግዶታል” ብለዋል።

“ድርጅቱ ለኪራይ፣ ደመወዝና ለሌሎች ወጪዎች ክፍያ ባለመፈጸሙ ሠራተኛው ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቋል” ያሉት ባለክሲዮኖቹ፣ “ድርጅቱ የሚፈርስ እንኳን ከሆነ አግባብ ባለው መንገድ መፍረስ ነበረበት እጅግ ከባድ ሁኔታ ተፈጥሯል” ሲሉ አማረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ሰነድ፣ “መዝገቡ ከቀጠሮ በፊት የቀረበው ይግባኝ ባይ በቀን 10/6/2017 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ ያቀረዝነው ይግባኝ ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የፌ/ከፍ/ፍርድ ቤት በወ/መ/ቁ 326384 የሰጠው ውሳኔ ታግዶ እንዲቆይ እንዲታዘዝልን በሚል ባቀረበው አቤቱታ ነው” ይላል።

አክሎም፣ ይግባኝ ቅሬታ ለመስማት ለ20/06/2017 ዓ/ም የተያዘው ቀጠሮ ተሰብሮ የእግድ አቤቱታውን በመመርመር ዝርዝር ትዕዛዝ መስጠቱን ያስረዳል።

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ አካውንቶች መዘጋታቸው፣ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ እሸቱ (ዶ/ር) አገር መውጣታቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ትርፍ ተሳፋሪዎች ከሌሉ አገልግሎት መስጠት ይከብደኛል " - የአዲስ አበባ የአውቶብስ አገልግሎት ድርጅት

ከወንበሮች በተጨማሪ ቆመው የሚሄዱ ተሳፋሪዎች ከሌሉ መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚቸገር የአዲስ አበባ የአውቶብስ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል፡፡ 

በከተማዋ አገልግሎት የሚሰጡ አውቶቡሶች አብዛኛውን ጊዜ ሰዎችን በብዛት አሳፍረው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

" ተገልጋዮችን ከአቅም በላይ እንዲጨናነቁ ማድረግ ለምን አስፈለገ ? ተጠቃሚ ደንበኞችን የሚመጥን የአውቶብስ ቁጥር ማሟላት ያልተቻለውስ ለምንድን ነው ? " በሚል ከአሐዱ የተጠየቀው የአዲስ አበባ የአውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ምላሽ ያለው ሰጥቷል።

የድርጅቱ የቴክኒክ አገልግሎትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምሩ ፉፋ ፤ " ይህ የተደረገው የአውቶብሶችን መለዋወጫ እና የነዳጅ ወጭን ጨምሮ ሁሉንም አስፈላጊ ወጪዎች በራሱ እንዲሸፍን የተሰጠውን መመሪያ ለመተግበር በወንበር ልክ ብቻ አሳፍሮ መንቀሳቀስ የሚያዋጣ ሆኖ ባለመገኘቱ ነው " ብለዋል፡፡

በተለይ የከተማዋን ረጅም ርቀት የሚጓዙ አውቶብሶች ብዙ ተገልጋዮችን አሳፍረው የመጓዝ ግዴታ እንዳለባቸው የገለጹት አቶ ታምሩ፤ " አውቶብሶቹ በሚያሳፍሩበት አካባቢ ረጃጅም ሰልፎች ቢኖሩም ቆመው የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር ግን አነስተኛ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ደንበኞች 'ቀጣይ ተረኛ አውቶቡስ ይመጣል' ብለው እንዲያምኑ የተገነባው ሀሳብ ጥሩ ቢሆንም፤ ድርጅቱን ኪሳራ ላይ የሚጥል እና አውቶብሶቹ ሲመላለሱ መያዝ ያለባቸውን ሰው ልክ ይዘው እንዳይመላለሱ አድርጓል ሲሉም አክለዋል፡፡

" በብልሽት ምክንያት የቆሙ አውቶቡሶችን መለዋወጫ አሟልቶ ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ ለማድረግ እና ሌሎችም ወጪዎችን ለመሸፈን ቆመው የሚሄዱ ደንበኞችን መጫን ግዴታ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪ በመታወቂያ የሚገለገሉ ደንበኞችን አስመልክቶ አዲስ እየተሻሻለ ያለ አሰራር መኖሩ የተገለጸ ሲሆን ፤ ይህ አሰራርም መደበኛ ተጠቃሚዎች ላይ የተፈጠረውን ቅሬታ የሚፈታ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

እየተሸሻለ ያለው አስራር ተግባራዊ ሲደረግ፤ ሃሰተኛ መታወቂያዎችን የሚጠቀሙ አካላትን ለመለየት ያስችላልም ተብሏል፡፡

Credit - Ahadu / አሐዱ

@tikvahethiopia
" የብቃት ምዘና ፈተናውን በመጋቢት 2017 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት እያደረግን ነው " - ጤና ሚኒስቴር

ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ፦
- Medicine
- Nursing
- Public Health
- Anesthesia
- Pharmacy
- Medical Laboratory Science
- Midwifery
- Dental Medicine
- Medical Radiology Technology
- Environmental Health
- Psychiatric Nursing
- Pediatric & Child Health Nursing
- Emergency & Critical Care Nursing
- Surgical Nursing
- Physiotherapy
- Optometry
- Human Nutrition ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመውጫ ፈተን ያለፉ እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር በኩል ተመዝግበው የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በመጋቢት 2017 ዓ.ም ፈተናውን ለመስጠት በዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውዋል።

የዚሁ ፈተና ምዝገባ ከየካቲት 24 - መጋቢት 7/2017 ዓ.ም የሚከናወን ይሆናል።

ፈተናውን የሚወስዱ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን
http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንዲመዘገቡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ እንደማያስተናግድት ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተመዛኞች በተጠቀሱት ቀናት ተመዝግበው ሲስተሙ የሚሰጣቸውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርገው በመያዝ ሲመዘገቡ በመረጡት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንዲገኙ ተብሏል።

ማሳሰቢያ ፦

1. እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድመው በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ። ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑ ተነግሯል።

2. ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን ማሳሰቢያ ተላልፏል።

3. በጥር 30/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፉና በዚህ የብቃት ምዘና ፈተና ለመቀመጥ የተዘጋጁ ነገር ግን ቴምፖረሪ ዲግሪ ከተቋማቸው ያልደረሰላቸው ተመዛኞች ከትምርት ሚኒስቴር ይህ ጉዳይ ቀጥታ ከሚመለከተው የስራ ክፍል የትብብር ደብዳቤ ማያያዝ የሚጠበቅባችሁ መሆኑ ተመላክቷል።

#MoH

@tikvahethiopia
The Jasiri Talent Investor is back!

We want young dreamers like you. If you believe you are a problem solver who can solve problems through high-impact entrepreneurship, then this opportunity is for you.
Don’t hesitate. Apply today!

👉 https://bit.ly/40Ai4oR

For more information @jasiri4africa
አቢሲንያ ባንክ

4ኛ ዙር እችላለሁ! ማርች 8 እየደረሰ ነው ! ዝግጁ !
የሴቶች የሥራ ፈጠራ፣ የሙዚቃና የቲክቶክ ቪዲዮ ውድድር !

ባንካችን በየአመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 ምክንያት በማድረግ እ.አ.አ ከማርች 3 ቀን እስከ ማርች 31 ቀን 2025 ድረስ በሁለት የተከፈሉ ውድድሮችን አዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ክፍት አድርጓል፡፡

1) የሙዚቃ ተሰጥዖ ውድድር
ባንካችን የሙዚቃ ተሰጥኦ ያላቸውን ሴት ተሳታፊዎችን በማወዳደር በባለሙያና በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የህዝብ ድምጽ የተለዩ አሸናፊዎችን በየደረጃው ይሸልማል፡፡ አንደኛ ለምትወጣው የብር 100,000፣ ሁለተኛ ለምትወጣው የብር 75,000 እንዲሁም ሶስተኛ ለምትወጣው የብር 50,000 ሽልማት አዘጋጅቷል።
በሙዚቃው ዘርፍ ተሰጥኦዬን ያሳያል የምትሉትን ከሶስት (3) ደቂቃ ያልበለጠ የሙዚቃ ሥራ ያለ ሙዚቃ መሣሪያና የድምፅ ማዳመጫ (Earphone) ሳይደረግ በቪዲዮ ሰርታችሁ ከዚህ በታች በተቀመጠው ቴሌግራም መላክ ይኖርባችኋል፡፡ የቴሌግራም አድራሻ------------ 0919857373

2) የቲክቶክ ቪዲዮ ተሰጥዖ ውድድር
እንዲሁም በተመረጡ ቲክቶከሮች መካከል ባንካችን ለሴት ደንበኞቻችን ያዘጋጃቸውን አደይና ዘሃራ የቁጠባ ሂሳቦችን በተለየ መንገድ የማስተዋወቅ ውድድር ይካሄዳል፡፡በዚህም ውድድር አንደኛ ለምትወጣው የብር 100,000፣ ሁለተኛ ለምትወጣው የብር 75,000 እንዲሁም ሶስተኛ ለምትወጣው የብር 50,000 ሽልማት አዘጋጅቷል።

3) የሥራ ፈጠራ ውድድር
የሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታት ባንኩ ባሉት ዲስትሪክቶች የሥራ ፈጣሪ ሴቶችን በመምረጥ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔን ካለመያዣ እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቶችን የምታሟሉ የሥራ ፈጣሪዎች አቅራቢያችሁ ባሉ ቅርንጫፎችና የዲስትሪክት ፅ/ቤቶች በመቅረብ ከየካቲት 19 ቀን እስከ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓም. ባሉት ቀናት ብቻ በፁሑፍ ጥያቄያችሁን እንድታቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን።

በዚህም መሠረት በመርሃ-ግብሩ መሳተፍ የምትፈልጉ ሴት ተወዳዳሪዎች አስቀድማችሁ የአቢሲንያ ባንክ የፌስቡክ ገፅን https://www.facebook.com/BoAeth/ መወዳጀት ይኖርባችኋል፡፡
ዝርዝር የብድር እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ለመመልከት ከታች የሚገኘውን የቴሌግራም ሊንክ መጠቀም የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ https://yangx.top/BoAEth
“ የጤና መድን ክፍያ በሚል ማህበረሰቡ ከ3,000 ብር  በላይ በግዴታ እንዲከፍል እየተደረገ ነው ” - የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች

የጤና መድን ክፍያ በሚል ማህበረሰቡ ከ3,000 ብርና ከዚያ በላይ፣ ለኮሪደር ልማት ከ500 እስከ 20 ሺሕ ብር  በግዴታ እንዲከፍል እየተደረገ መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ ነዋረዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

“ ከትንንሽ ምግብ ቤት ጀምሮ በማንኛውም የንግድ ሥራ የተሰማራ ቤተሰብ የሌለውንም ጨምሮ ነው እያስገደዱና የማይከፍለውን እያሸጉ ያሉት ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ከዚህ ቀደም ትዳር መስርቶ፣ ወልዶ የሚኖር ሰው አባል ሆኖ የአባልነት ክፍያ ነበር የሚከፍለው ለጤና መድን አሁን ግን ትዳር የሌላቸው በንግድ ሥራ የተሰማሩ ወጣቶችን ጭምር አባል ሳያደርጉ ብር ብቻ እያስከፈሉ ነው ” ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ “ ለኮሪደር ልማት በሚል በማንኛውም ንግድ ሥራ የተሰማራ ሰው ተገዶ እንዲከፍል እየተደገ ነው ” ሲሉ ነዋሪዎቹ አማረዋል።

አክለውም ፦

“ ነዋሪውበኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ነው ያለው። በአነስተኛ ንግድ የተሰማራው ነጋዴም ስራ ቆሞበታል። ምክንያቱም ተጠቃሚ የለም።

ህዝቡ ግብር ከፍሎ እንደገና ‘ለኮሪደር ልማት፣ ለጤና መድን’ ሲጨምርበት ከአቅም በላይ ሆኖበታል። ይሄ ነገር ከተጀመረ ቆይቷል። ግዳጁ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል። 

የማህበረሰቡም፣ ‘የኑሮ ውድነት ጫናው ቢኖርብንም በህግ አግባብ የተጣለብንን ግብር በሰዓቱ እየከፈልን ነው የምንሰራው። አሁን ላይ ስራ ተቀዛቅዟል። ተጨማሪ ክፍያ የመክፈል አቅም የለንም’ የሚል ቅሬታ አለው።

የኮሪደር ልማቱን ክፍያ በሚመለከት የከተማ አስተዳደሩ ከከፍተኛ ባለሀብቶች ጋር ውይይት አድርጎ ልማቱን እንደሚደግፉ ተስማምተዋል። ነገር ግን ዝቅተኛ ነጋዴዎች ተሳታፊ አልነበሩም። እነሱም ቢሆኑ ልማቱን ይደግፋሉ ነገር ግን ክፍያው አቅምን ያገናዘበ አይደለም።

በካሬታ ውሃና ሌሎች ሥራዎችን የማጓጓዝ ስራ ከሚሰሩ ልጆች ጀምሮ እስከ ቤት አከራይ ለኮሪደር ልማት መዋጮ እየተጠየቀ ነው። ዝቅተኛው 500 ብር ሲሆን፣ እስከ 20,000 ብር የተጠየቁ አሉ። 20 ሺሕ ብር አከራይ ብቻ ነው የሚከፍለው ” ሲሉ አማረዋል።

ነዋሪዎቹ ቅሬታውን ምላሽ እንዲሰጥበት የባሕርዳር ከተማ አስተዳደርን የጠቆሙ ሲሆን ምን ምላሽ እንዳላቸው የጠየቅናቸው  የከተማው ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ቅሬታውን ከሰሙ በኋላ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ጤና መድን አገልግሎትን የጠየቀ ሲሆን፣ ምላሹ ሲገኝ የሚቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ነዳጅ #ቤንዚን

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተባባሰ የመጣዉን የነዳጅ ምርቶች ሕገወጥ ግብይት ለመከላከልና በየከተማዉ የሚስተዋሉ ረጃጅም ሰልፎችን በማስቀረትና የተጠቃሚዎችን ቅሬታ ለመፍታት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ።

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አቡዱላሂ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ በነዳጅ ምርቶች በተለይ በቤንዚን አቅርቦትና ስርጭት በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ቅሬታዎች እንደሚነሱና ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ስለመኖራቸው ገልፀዋል።

" አንዱና መሠረታዊዉ ምክንያት ከዚህ ቀደም 80 በመቶ የሚሆነዉ የሀገራችንን የነዳጅ ፍጆታ ይሸፍን የነበረዉ በሱዳን ወደብ የሚገባዉ ቢሆንም አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ወደ ጅቡቲ ዞሯል " ብለዋል።

" ወደቡ ላይ ከፍተኛ መጨናነቆች ይስተዋላሉ የጅቡቲዉ ወደብ ከ20 ዓመታት በፊት የነበረን የሀገራችንን የነዳጅ ፍላጎትና አቅርቦትን ለማስተናገድ ታስቦ የተሰራ ስለነበር በቴርሚናሉ ላይ ያለዉ መጨናነቅ መንግስት በከፍተኛ ድጎማ የሚያስገባቸዉ የነዳጅ ምርቶች በተለይም በቤንዚን አቅርቦትና ስርጭት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል " ሰሉ ገልፀዋል።

መንግስት አሁንም ድረስ ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማ በማድረግ ወደ ሀገር ዉስጥ በሚያስገባቸዉ የነዳጅ ምርቶች ላይ አንዳንድ አከባቢዎች ሰዉ ሰራሽ አቅርቦት እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ የግል ጥቅማቸዉን ለማካበት የሚጥሩ አካላት መኖራቸዉን ማረጋገጣቸውን ወ/ሮ ሰሃረላ ተናግረዋል።

በቴክኖሎጂ የታገዘ ቁጥጥርና የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት ሕገወጥ ግብይቱን የመከላከልና በህገወጦች ላይ እርምጃ የመዉሰዱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

" ከአቅርቦቱ ባሻገር ወደ ሀገር ዉስጥ የገባዉን ቤንዚን በአግባቡ በማሰራጨቱ በኩል በየክልሉ የተለያዩ ክፍተቶች አሉ " ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሁሉም ማዕቀፎች ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል መወሰድ በመጀመሩ በርከት ያሉ የንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች ማደያዎችን ጨምሮ በሕገወጥ ግብይቱ ሰንሰለቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ላይ በየደረጃው እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አብራርተዋል።

ለአብነትም በሲዳማ ክልል ብቻ የግብይት ስርዓቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ በመፍጠር ሰዉ ሰራሽ እጥረት እንዲስፋፋ ያደረጉ 9 ማደያዎች ላይ ነዳጅ እንዳያገኙ እገዳ እንደተላለፈባቸው ገልፀዋል።

በሌሎችም ክልልሎች በዚህ ረገድ እየተከናወኑ ያሉ የቁጥጥርና ክትትል ተግባራት በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀዉ አዲሱ የነዳጅ ምርቶች ቁጥጥር አዋጅ ጋር ተዳምረዉ በዘርፉ የሚስተዋለዉን ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንሰዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
#Mekelle

ለመቐለ የውሃ አቅርቦት በሚውል ትራንስፎርመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት አገልግሎቱ መቋረጡን የከተማዋ የውሃና ፈሳሽ አገልግሎት ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የተዘረፈው ትራንስፎርመር ለከተማዋ በቀን 1.9 ሚሊየን ሊትር ውሃ ከጉድጓድ እንዲመነጭ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ነው።

ፓሊስ አደገኛ የስርቆት ተግባሩን " እያጣራሁት ነው " ብለዋል።

የትራንስፎርመር ስርቆቱ የካቲት 24/2017 ዓ.ም ሌሊት ፤ ሐድነት ክፍለ ከተማ አይናአለም ቀበሌ ልዩ ቦታ ' ሻፋት ' ነው የተፈፀመው።

ፅ/ቤቱ በትራንፎርመሩ ስርቆት ምክንያት በቀን 1.9 ሚሊየን ሊትር ውሃ የሚያመነጨው ጉድጓድ ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ወጪ መሆኑ ገልጾ " ህዝቡ የውሃ አቅርቦት አገልግሎቱ እስኪመለስ እንዲታገስ " ሲል ጠይቋል።

ትራንስፎርመሩ ጨምሮ ጠቅላላ የደረሰው ወድመት ከ5 ሚሊዮን ብር ላይ ይገመታል ሲልም አክሏል።

ፖሊስ ከባድ የስርቆት ተግባሩ የቦታውን ሁለት ጥበቃዎች ላይ የአካል ጉዳት በማድረስ መፈፀሙ ጠቅሶ ፈፃሚዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የቀናጀ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

ዘራፊዎቹ በጥበቃዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሳቸው የተነገረ ሲሆን ተጣርጣሪዎቹ ለመያዝ በሚድረገው እንቅስቃሴ የህዝቡ ተሳትፎ እና ጥቆማ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ፓሊስ አመልክቷል።

@tikvahethiopia