TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
" በአንድ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ 3‚700 ብር ድጎማ ቢያደርግም ዋጋው ግን በእጥፍ ጨምሯል " - አቶ አገሬ ጥጋቡ

ድጎማ የተደረገበት የ2017/18 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ዋጋው በእጥፍ መጨመሩን በአማራ ክልል የዳሞት ኅብረት ሥራ ዩኒየን አስታወቀ፡፡

የዩኒየኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ አገሬ ጥጋቡ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ የፌዴራል መንግሥት በአንድ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ 3‚700 ብር ድጎማ ቢያደርግም ዋጋው ግን በእጥፍ ጨምሯል፡፡

የዋጋውን ልዩነት ከዓምናው ጋር በማነፃፀር፣ አንድ ኩንታል ዳፕ ማዳበሪያ 3‚700 ብር እንደነበር አስታውሰው፣ ዘንድሮ ግን 7‚835 ብር መግባቱን፣ አንድ ኩንታል ዩሪያ ደግሞ ዓምና 3‚650 ብር እንደነበር፣ ዘንድሮ ደግሞ 6‚113 ብር መድረሱን አስረድተዋል፡፡

ለዩኒየኑ ከቀረበው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 80 ሺሕ ኩንታል ዳፕና 72 ሺሕ ኩንታል ዩሪያ መሆኑን፣ በዕቅዱ መሠረት የሚያስፈልገው አንድ ሚሊዮን 76 ሺሕ ኩንታል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከውጭ የተገዛበትን ጨምሮ የዩኒየኑ ትርፍ ሳይጨምር ዳፕ በኩንታል 11‚000 ብር መገዛቱን ገልጸው፣ ዩሪያ ደግሞ እስከ 10‚000 ብር እንደሚደርስ ነው ያስረዱት፡፡

በክልሉ ባለው የፀጥታው ችግር ምክንያት በእጀባ እስከ ምዕራብ ጎጃም ለዳሞት ኅብረት ሥራ ዩኒየን እስካሁን የደረሰው 152‚000 ኩንታል ማዳበሪያ እንደሆነ ገልጸው፣ ከዓምናው ጋር ሲነፃፀር መዘግየቱን ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ በአገር አቀፍ ደረጃ 1.3 ቢሊዮን ዶላርና 156 ቢሊዮን ብር ለማዳበሪያ ግዥ በጀት የተመደበ መሆኑን ጋዜጣው በዘገባው አስታውሷል።

@tikvahethiopia
Apply to Jasiri’s fully funded Talent Investor program

Requirements:
- Ready to dedicate themselves to entrepreneurship, including a three month residential intensive in Rwanda
- Skilled and knowledgeable in their professional field and are able to spot opportunities in their sector
- Committed to starting a new innovative venture from scratch
- Collaborative and eager to connect with other ambitious co-founders

Apply now
👉 https://bit.ly/40Ai4oR

For more information @Jasiri4Africa
ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማንበብ እንዲማሩ የሚያግዝ አዝናኝ እና አሳታፊ ጨዋታ!

ኪዩሪየስ ሪደር ልጅዎ የተለያዩ ሀገርኛ ቋንቋዎችን ልክ እንደ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማልኛ እና ትግረኛ በቀላሉ ማንበብ እና ማወቅ እንዲችሉ በጨዋታ እና በተረት መልክ እያዋዛ ፊደላትና ቃላቶችን የሚያስተምር መተግበሪያ ነዉ!

ከ”Play Store” ካወረዱ በኋላ ቋንቋ በመቀያየር ልጅዎን ከተለያዩ ሀገርኛ ቋንዎች ጋር ያስተዋውቋቸው!!

እነዚህን ሊንኮች በመጠቀም መተግበሪያውን በነጻ አሁነኑ አውርደው ከልጅዎ ጋር ይማሩ!

ይሄን ይንኩት 👉🏼 አማርኛ
ይሄን ይንኩት 👉🏼 ኦሮምኛ
ይሄን ይንኩት 👉🏼 ሶማልኛ
ይሄን ይንኩት 👉🏼 ትግረኛ


#ለልጅዎ #ከፊደል_ይጀምሩ
" ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር " - ፕሬዜዳንት ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው " ሲሉ ወረፏቸው።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው " ብለዋል።

ትራምፕ ዩክሬን ከአሜሪካ ያገኘችውን ድጋፍ በውድ ማዕድናት እንድትከፍል እንደሚፈልጉ ተናገሩ
ትራምፕ " ትሁቱና ውጤታማ ኮሜዲያን ዘለንስኪ አሜሪካን 350 ቢሊየን ዶላር በማስውጣት መጀመር ያልነበረባቸው እና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል " ብለዋል።

" ዩክሬን ጦርነቱን ያለ አሜሪካ እና ትራምፕ በፍፁም መቋቋም አትችልም " ሲሉም ገልጸዋል።

ዜለንስኪ ከላክንለት ገንዘብ ግማሹ " የጠፋ " መሆኑን አምኗል ያሉት ትራምፕ " ምርጫ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም፣ በዩክሬን የሕዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት በጣም ዝቅተኛ ነው " ብለዋል።

" ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር " ሲሉም ገልጸዋል።

" ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል፤ ካልሆነ ግን የሚያተርፈው ሀገር አይኖርም " ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አክውም " ዩክሬንን እወዳለሁ፣ ነገር ግን ዘለንስኪ አስከፊ ስራ ሰርቷል፣ ሚሊዮኖችም ያለምክንያት ሞተዋል እየሞቱም ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ " ዶናልድ ትራምፕ የሀሰት መረጃ ውስጥ እየኖሩ ወይንም በሀሰት መረጃ እየተነዱ ነው " ብለዋል።

ዩክሬን ከሩስያ ጋር ጦርነቱ ውስጥ እንዳለች ይታወቃል።

መረጃው የአል አይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
" ምርጫ ማሸነፌ እንደወንጀል ታይቶ 1 ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያለአግባብ ታስሪያሁ " - አቶ አማንያስ ጉሹና

ከሰሞኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤዉን አካሂዶ ነበር።

በዚህም ጉባኤ ላይ የኢዜማው ተመራጭ ጉባኤ እንዳይሳተፉ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ የዘይሴ ብሔረሰብ ተመራጭ የሆኑት አቶ አማንያስ ጉሹና " ያለአግባብ 4 ወራት ከታሰርኩ በኋላ ያለመከሰስ መብቴ ተነስቶ ለተጨማሪ 7 ወራት በእስር ላይ እንዲቆይና በምክር ቤት ጉባኤ እንዳልሳተፍና ከመንግስት ስራም እንዲሰናበት ተደርጌያለሁ " ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አቶ አማንያስ ፤ " ብሔረሰቡ ያለዉን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የመዋቅር ጥያቄ በተለያዩ ጊዜያት ሲጠይቅ የቆዬ ቢሆንም ተገቢዉን ምላሽ ባለማግኘቱ በ6ኛ ሀገራዊ ምርጫ የኢዜማ ፓርቲን በመምረጡ ከምርጫዉ ማግስት ጀምሮ በፓርቲው በአባላትና አመራሮች ላይ የእስርና የማሳደድ ተግባር በይፋ ማካሄድ ተጀምሯል " ብለዋል።

" በአሁኑ ሰዓት ከ2 መቶ በላይ የፓርቲዉ አባላትና አመራሮች በጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት እየተመላለስን ነዉ " ሲሉ አስረድተዋል።

" ተወዳድረን ምርጫ ማሸነፋችን ሃጥያት ባልሆነበት በገዢዉ ፓርቲ አመራሮች በግልም ሆነ በብሔረሰቡ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እየደረሰብን ነዉ " የሚሉት አቶ አማንያስ " ለአብነትም የደቡብ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን ባካሄደዉ 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የዜይሴ ብሔረሰብ ያለተወከለበት እና ከሌሎች ብሔሮች ጋር በክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሌሎች ተሳታፊዎች ጋር ያልተሳተፈበት ጉባኤ ነዉ " ሲሉ ወቅሰዋል።

" በዚሁ የፖለቲካ ተፅእኖ ምክንያት ሀገሬን ለ17 ዓመታት ካገለገልኩበት የመምህርነት ሙያ እንድሰናበት ተደርጌያለሁ " ያሉት አቶ አማንያስ " ወደ ስራ ገበታዬ እንዲመልሱኝ ደጋግሜ ብጠይቅም 'ያለመከስ መብትህ ሳይነሳ መመለስ አትችልም' የሚል ምላሽ ከትምህርት አስተዳደር መዋቅሮች ተሰጥቶኛል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢዜማ ፓርቲ የሕግና አባላት ጉዳይ ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስዩም መንገሻን በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገራቸዉ ሲሆን " በዘይሴ ብሔረሰብ የሕዝብ ተመራጭ አቶ አማኒያስ ጉሹና ላይ የተፈፀመዉ ጉዳይ ኢ-ሕገመንግስታዊ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በወቅቱ ያለመከሰስ መብታቸዉ ሳይነሳ ታስረዉ መቆየታቸዉንና በአካባቢዉ ያለዉን የሰብአዊ መብት ረገጣና የፖለቲካ ተፅእኖ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፅሑፍ ማሳወቃቸዉንና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ወደአከባቢዉ ማቅናቱንና የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ስለመሆኑ አንስተዋል።

" ከስራ የተሰናበቱበትና ወደ ስራ እንዳይመለሱ የሚደረግበት አግባብ ከፍተኛ የፖለቲካ ተፅእኖ ያለበት ነዉ " ያሉት አቶ ስዩም ፤ የኢዜማ ፓርቲ በአከባቢው ያለዉን የፖለቲካ ጫናና ተያያዥ ጉዳዮችን ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በጽሑፍ አቅርቦ ባለድርሻ አካላት የተካተቱበት ግብረሃይል ተዋቅሮ ቦታዉ ድረስ በመሄድ በሰጠዉ አቅጣጫ መሠረት አቶ አማንያስ በዋስ እንዲፈቱ መደረጉን ተናግረዋል።

አቶ አማንያስ " ወደ ስራ ገበታዬ እንዲመልሱኝ በተደጋጋሚ ብጠይቅም የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤትና የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ' ያለመከሰስ መብትህ እስካልተነሳ ድረስ መመለስ አንችልም ' ተብያለሁ " በሚል ላነሱት ቅሬታ ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽ/ቤትና ከጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
#ትግራይ

🚨“ በአንድ አመት ውስጥ ከ40 በላይ ሰዎች ሞተዋል” - በአይደር ሆስፒታል የዲያሌሲስ ዩኒት

➡️ “ ጳውሎስ ሆስፒታል 400 ብር የሚሸጠውን መድኃኒት እኛ 1200 ብር ነው የምንገዛው ” - የትግራይ ክልል ኩላሊት ህሙማን ማኀበር

በትግራይ ክልል ያሉ የኩላሊት ህሙማን ወገኖች በመድኃኒት እጥረት ሳቢያ የዲያሌሲስ ክትትል ለማድረግ በመቸገራቸው ለሞት መዳረጋቸውን የክልሉ ኩላሊት ህሙማን ማኀበርና አይደር ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

በሆስፒታሉ የዲያሌሲስ ዩኒት አስተባባሪ አቶ ጥዑም መድኅን በሰጡን ቃል፣ “ ህሙማኑ ከውጪ ፋርማሲ ነው መድኃኒት የሚገዙት። ከመንግስት ፋርሚሲ አይገኝም ” ብለዋል።

አቶ ጥዑም መድኅን በዝርዝር ምን አሉ ?

“ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ40 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ብዙዎቹ የሚሞቱት የህክምና ክትትል ባለማድረጋቸው ነው። ክትትል የማያደርጉት ደግሞ የገንዘብ እጥረት ስላለባቸው ነው።

ችግሩ ብዙ ነው። በትግራይ ክልል ደረጃ አንድ የዲያሌሲስ ሴንተር ብቻ  ነው ያለው በአይደር ሆስፒታል። ለዛውም መንግስት ምንም ድርሻ የለውም መድኃኒት አያቀርብም።

በ2013 ዓ/ም ጦርነት ከተጀመረ በኋላ በጣም ሰፊ ችግር ነው ያለው። በጦርነቱ ወቅትም ብዙ ሰዎች ናቸው የሞቱት። አሁንም የመድኃኒት እጥረት አለ ሰላም ቢሆንም።

መድኃኒት በትግራይ አይገኝም። ብዙ ጊዜ ከውጪ፣ በብላክ ማርኬት ከአዲስ አበባ ነው የሚገዙት። ዋጋውም ውድ ነው። ለአንድ እጥበት 3900 ብር ነው ከሌሎች መድኃኒቶች ወጪ ውጪ።

በሆስፒታሉ 44 ህሙማን አሉ ክትትል የሚያደርጉ። ከ44ቱ ወደ 4 የሚሆኑት ‘አንችልም’ ብለው አቁመዋል። 40ዎቹ አሉ። 

ግን በሳምንት ሦስት ጊዜ ኩላሊታቸውን መታጠብ ቢኖርባቸውም የገንዘብ አቅም ስለሌላቸው በሳምንት አንድ ጊዜ፤ ሁለት ጊዜ፣ ቀሪ ስምነቱ ደግሞ የባሰ የገንዘብ እጥረት ስላለባቸው በሁለት ሳምንት ይታጠባሉ ”
ብለዋል።

የትግራይ ክልል ኩላሊት ህሙማን ማኀበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ሐፍቶም አባዲ በበኩላቸው “ አርቲፊሻል ኪዲኒ ዲያላይዘርን ከ8 እስከ 10 ጊዜ ነው እያጠብን ነው ስንጠቀም የነበረው በጦርነቱ ጊዜ” ነው ያሉት።

“ በዚያ ምክንያት የፕሪቶሪያ ስምምነት እስከሚፈረም ድረስ በሁለት ዓመት ከ100 በላይ ህሙማን ሞተዋል። ከ100 በላይ የማኀበሩ ታካሚ ህሙማን ውስጥ 14 ሰዎች ብቻ ነበሩ በእድል የቀሩት ” ሲሉም አስታውሰዋል።

የማኀበሩ ሥራ አስኪያጅ አክለው ምን አሉ ?

“ አንድ ታካሚ ለአንድ ዲያሌሲስ ከ35,000 እስከ 40,000 ነው በወር የሚያወጣው ለዲያሌሲስ ብቻ። ለዚህም አቅም የለውም ሰው። ኮስቱ በጣም ከፍተኛ ነው።

ህክምናው የጀመሩ ህሙማንም አቅም ስለሌላቸው ትንሽ ተከታትለው አቋርጠው ነው የሚሄዱት። ዲያሌሲስ ካቋረጡ ደግሞ የሚጠብቃቸው ሞት ነው።

ከፕሪቶሪያ ስምምነቱ በኋላ ብዙ ሰዎች ሞተውብናል። ሦስት ጊዜ ማድረግ ሲጠበቅባቸው በገንዘብ እጦት በሳንምት አንድ ጊዜ ዲያሌሲስ የሚያደርጉ አሉ። በዚሁ ምክንያት ብቻ እኔኳ የማውቃቸው ወደ 5፣ 6 ሰዎች ሞተዋል።

ኮስቱ እንዳለ ታካሚው ላይ ነው ያረፈው። ታካሚው ካለው ይከፍላል ከሌለው ያው የሚጠብቀው ሞት ነው። መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ለዲያሌሲሱ ድጋፍ ያድርግልን። 

ለምሳሌ ፦ እነ ጳውሎስ፣ እነ ሚኒሊክ ሆስፒታሎች ኮስታቸው በጣም ፌር ነው መንግስት ስለሚደግፋቸው።

እኛ ግን የግል ሆስፒታሎች ከሚከፍሉት በላይ ነው እየከፈልን ያለነው በመንግስት ሆስፒታል ላይ ሆነን። መንግስት መደገፍ ያለበትን ራሳችን ወጪ እያደረግን ነው የምናደርገው።

ጳውሎስ ሆስፒታል 400 ብር የሚሸጠውን መድኃኒት እኛ 1200 ብር ነው የምንገዛው። በመንግስት ሆስፒታሎች የሚገኙትን መድኃኒቶች መንግስት ያቅርብልን”
ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰሜኑ ጦርነት በፊት የመድኃኒት ድጋፍ ሲያደርግላቸው የነበረው ሱዳናዊ ድርጅት በጦርቱ ሳቢያ ውሉና ድጋፉ እንደተቋረጠ፣ ከሁለት አመታት በላይ የህክምና የሚደረገው ከህሙማኑ በሚሰባሰብ ገንዘብ መሆኑን ማኀበሩና ሆስፒታሉ አስረድተዋል።

እስከ ጥር 2017 ዓ/ም መጀመሪያ ድረስ መድኃኒት የሚገዛው ከህሙማኑ በሚዋጣ ገንዘብ እንደነበር፣ አሁን አንድ መድኃኒት አቅራቢ ድርጅት ውል ገብቶ በሆፒታሉ በኩል የመድኃኒት አቅርቦት እንደጀመረ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
“ብዙ ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች ይኖራሉ። ነገር ግን ሁሉም ነገር በትክክል ከተካሄደ ሊበቃን ይችላል” - ምክትል ኮሚሽነር ሒሩት ገብረ ሥላሴ

ከቀናት በፊት አንድ አመት ተጨማሪ የሥራ ጊዜ በፓርላማ የተሰጠው የ3 አመታት የሥራ ዘመኑን ነገ ይጠናቅቅ የነበረው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ3 አመታት ክንውንና የቀጣይ አቅጣጫውን በተመለከተ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም ኮሚሽኑ የተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ በቂ ነው? አጠቃላይ ሥራውስ መቼ ይጠናቀቃል? በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረላቸው ጥያቄ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረ ስላሴ፣ “ብዙ ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች ይኖራሉ። ነገር ግን ሁሉም ነገር በትክክል ከተካሄደ ሊበቃን ይችላል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

"ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች አሉ” ያሉት፣ ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ይህን ይበሉ እንጂ ከቁጥጥር ውጪ ስለሆኑ ነገሮችን በዝርዝር አልገለጹም። 

11 ኮሚሽነሮች እንዳሉና ሥራውን ተባብሮ ለመስራት እንደሚቻል ገልጸው፣ "ተጨማሪ አንዳንድ ሥራዎችን የሚያቃልሉ ነገሮች በመንግስትም ሆነ በሌሎች ከተፈጠሩልን ስራችንን ያጣድፋል" ብለዋል።

“ምክክር በዚህ ሰዓት ውስጥ ተመካክራችሁ በዚህ ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ስጡ የሚባልበት አይደለም። ህዝቦች ቁጭ ብለው ጊዜ ውስደው ተመካክረው የሚወሰኑት ሂደት ስለሆነ በቀላሉ የሚወሰኑ አጀንዳዎች ይኖራሉ። ጊዜ የሚፈጁም ሊኖሩ ይችላሉ” ሲሉም አስረድተዋል።

አክለው፣ “በዚህ ምክንያት በትክክል በዚህ ጊዜ ውስጥ ያልቃል ለማለት ያስቸግራል” ብለው፣ ሆኖም ግን ኮሚሽኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥራውን ለመጨረስ ጥረት እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የተወሰኑ ፓርቲዎች ባልተሳተፉበት የምክክሩ ሂደቱ ሙሉ ይሆናል? በሚል ለቀረበው ጥያቄም፣ ፓርቲዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ ጥረት መደረጉን ገልጸው፣ “ዳተኛ ሆነው” ያልገቡት እንዲገቡ ደግሞ ንግግር እንደተደረገ፣ አሁንም ጥረቱ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። 

ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር) በበኩላቸው፣ በመግለጫው ባደረጉት ንግግር በሕጋዊ ከተመዘገቡ ወደ 70 ፓርቲዎች 57 የሚሆኑት ከኮሚሽኑ ጋር እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ከታጣቂዎች ጋር ንግግር ተደርጎ እንደሆን ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት ማብራሪያ ዋና ኮሚሽነሩ፣ የፋኖ ታጣቂዎችን እንዳነጋገሩ፣ “ሊከፋፍለን ነው” በሚል ስማቸው እንደሚነሳ አስታውሰው ተከታዩን ብለዋል።

ምን አሉ?

“ሀገራዊ ምክክሩ ማንንም መከፋፈል አይመኝም። የሚመኘው፣ መደረግ አለበት ብሎ የሚያምነውም ሁሉም ተሳታፊ እንዲሆን ነው።

እኔ ፋኖ መሆናቸውን አላውቅም አንድ ታጣቂ ቡድን ራሳቸው ደውለውልኝ ‘የምክክር ኮሚሽኑን ሥራ ተገንዝበናል። ‘በዚህ መሠረት ወደ ትግሉ የገባንበትን አጀንዳ ወደ እናንተ አምጥተን ወደ ውይይት የሚቀርብ ከሆነ መሳሪያችንን ለማስቀመጥ ዝግጁ ነን’ የሚል በቀጥታ በግሌ አቅርበውልኛል። ይሄን ሰው በተደጋጋሚ አግኝተዋለሁ። 

እዛ ላሉትም የደኅንነት፣ አካላት በስልክ አግኝቼ እነዚህ ሰዎች በአግባቡ መሠረት ሰላማዊ ጥበቃ ተደርጎላቸው አጀንዳቸውን የሚያመጡበት መንገድ እንዲመቻች ይሄን አስተላልፌያለሁ። 

ይህን ሳደርግ ለሀገራዊ ምክክር ጉባዔ በማሳወቅ ነው። እንጂ የፋኖ ናቸው ብዬ የተናገርኩት አንድም የለም” ብለዋል።

በሌላ በኩል በዛሬው መግለጫ የኮሚሽኑ የ3 አመታት ክንውኖች በኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር) በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፣ ይህንኑ ሪፓርት ከቀናት በፊት አድርሰናችሁ ነበር።

(ተጨማሪ ዘገባ በቀጣይ የምናቀርብ ይህናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

የሳምንቱ ምርጥ ጨዋታ !

ማን ሲቲ በኢመሬትስ ስታዲዩም ከሊቨርፑል ጋር ይጫወታል!
⚽️ ከ60 ጨዋታዎች 26ቱን ሊቨርፑል ሲያሸነፍ 12ቱን ማን ሲቲ ድል ማረግ ችሏል! 22 ጨዋታዎችም አቻ ወጥተዋል!

61ኛውን ጨዋታዎቸውን የሚያደርጉት ሁለቱ ቡድኖች ማን 3 ነጥብ ማሸነፍ ይችላል?

🏆 ሊቨርፑል ከአርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ማስፋት ይችላል?
👉 ይህንን ድንቅ ፍልሚያ ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።

🎊 እስከ መጋቢት 22 ባሉት ቀናት አሁን ካሉበት ጎጆ ፓኬጅ የቀጣዩን ቤተሰብ ፓኬጅ፣ የአንድ ወር ሙሉ ክፍያ ሲከፍሉ፣ ዲኤስቲቪ ደግሞ የሜዳ ፓኬጅን ፓኬጅ በነፃ ከፍ ያደርጎታል
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#ሁሉምያለውእኛጋርነው
#Tigray

ትናንተ የካቲት 12 /2017 ዓ.ም በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ በነዋሪዎችና በአከባቢው በሚገኘው የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ተከስተዋል።

በግጭቱ ምክንያት በ20 የቀበሌው ነዋሪዎችና ቁጥራቸው ባልታወቀ የትግራይ ኃይል አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ያጋጠመ ሞት የለም።

ግጭቱ እንዴት እና በምን ምክንያት አጋጠመ ? 

በአዲስ አለም ቀበሌ ሁለት አስተዳዳሪዎች አሉ። አንዱ የቆየ ሲሆን ሌላው ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾመ ነው።

ሁለቱም ማህተም ይዘው በየፊናቸው " እኔ ነኝ ህጋዊ የቀበሌው አስተዳደር " በማለት ህዝቡን ለሁለት መክፈላቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ " ህዝቡ አማርሮ እንድንታደገው ጠይቆናል አዛዦቻችንም ይህንን እንድንፈፅም ልከውናል" ያሉ 9 የሰራዊት አባላት ወደ ቀበሌው ደርሰው ሁለቱ አስተዳዳሪዎች ማህተም እንዲያስረክቡ ይጠይቃሉ።

" ታስረክባላችሁ አናስረክም " በሚል እልህ በነዋሪዎች እና የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ይነሳል። ነዋሪውም ደንጋይ መወርወር ይጀምራል። የትግራይ ኃይል አባላትም ጥይት ይተኩሳሉ።

በዚህ መካከል በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰው እጁ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ሲገባ ሌሎች 20 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በትግራይ ኃይል አባላት ላይም ጉዳት የደረሰባቸው አሉ። 

የወረዳው አስተዳደር ለክልሉ የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ የካቲት 11/2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ 13 ታጣቂዋች ወደ ወረዳው አስተዳደር በመምጣት የጊዚያዊ አስተዳደር ማህተም እና የፅህፈት ቤት ቁልፍ እንዲያስረክቡዋቸው መጠየቃቸውን እና ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር እንዲቆም ጠይቋል።

ከህወሓት ወደ ሁለት መሰንጠቅ በኋላ የክልሉ ዋና ከተማ መቐለ ጨምሮ በተለያዩ የገጠር እና የከተማ አስተዳደሮች ተመሳሳይ ስልጣን ያላቸው ሁለት አሰተዳዳሪዎች መስማት የተለመደ ነው።

በአንዳንድ ዞኖች ያሉ ወረዳዎች በጊዚያዊ አስተዳደሩ እና የደብሪፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት የተሾሙ አስተዳዳሪዎች ለሁለት ተከፋፍለው ይተዳደራሉ።

የትግራይ መሪዎች በተለይም የህወሓት አመራሮች ከዚህ መሰል ህዝብ የሚከፋፍል አደገኛ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የሚመክሩ አስተያየት ሰጪዎች ፤ የትግራይ ኃይል አባላት አንዱን ቡድን ደግፈው ሌላው ቡድን ማውገዝ ተጨማሪ ቀውስ እና ጥፋት ስለሚያስከትል የገለልተኝነት ሚናቸው እንዱወጡ አበክረው እያሳሰቡ ናቸው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
#ችሎት

" ንብረታችሁ ሊወረስ ነው " በማለት ባለሃብቱን አስፈራርተው በቼክ ገንዘብ ሲቀበሉ በፀጥታ አካላት የተያዙ 4 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ በብሔራዊ መረጃ ደህንነትና በፌደራል ፖሊስ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

አዲሱ የንብረት ውርስ አዋጅ ወደ ስራ ባልገባበትና በፖሊስ ምርመራ ባልተጀመረበት ሁኔታ ላይ ተጠርጣሪዎቹ " የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና የፋይናንስ ደህንነት ሰራተኞች ነን " በማለት አንድን ባለሃብት አስፈራርተው 5 ሚሊየን ብር ጉቦ ተደራድረው የ1 ሚሊየን ብር ቼክ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ተብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ መዝገቦች ፍ/ቤት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ፦

1ኛ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በሞጆ ደረቅ ወደብ የጥበቃ ኃላፊ ኢኒስፔክተር ሰለሞን ካሳ፤

2ኛ በግል ስራ የሚተዳደሩት ተስፋ ሀታኡ ገምቴሳ፣

3ኛ ጁዋር አወል ጀማል

4ኛ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የአይቲ ባለሙያ ረ/ኢ/ር ኩሉሌ ጉዮ ቦሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ናቸው።

አዲሱ የንብረት ውርስ አዋጅ ወደ ስራ ባልገባበት፣ በፖሊስ ምርመራ ባልተጀመረበትና በጋዜጣ ባልታወጀበት ሁኔታ ላይ ተጠርጣሪዎቹ " ደዘርት ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር " ለተባለው ድርጅት ባለቤት አቶ ቢኒያም ሀደር እና ወኪላቸው ስራ አስኪያጅ መሐመድ እስማኤል አሊ ለተባሉት ግለሰቦች ስልካቸው ላይ ይደውላሉ።

ጥር 05 ቀን 2017 ጀምሮ ደግሞ በተለያዩ ቀናት ባለሃብቶቹን በአካል በማግኘት " የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና የመረጃ ደህንነት ሠራተኞች ነን " በማለት ይተዋወቃሉ።

" በአዲሱ ንብረት ማስመለስ አዋጅ መሰረት በንብረታችሁ ላይ እና የባንክ የሂሳብ እንቅስቃሴዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ ንብረታችሁ ይወረሳል፤ የባንክ ሂሳብ እንቅስቃሴ እናግዳለን " በማለት ሲያስፈራሩ እንደነበረ በጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ላይ ተብራርቷል።

በተለይ መንግስት ሃብታቸውን እንዳይወርስባቸው እንደሚያደርጉ በመግለጽ ለዚህ ማስፈጸሚያነት የሚውል 5 ሚሊየን ብር በመደራደር በቅድሚያ 20 ሺህ ብር በባንክ ሂሳብ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል አኑዋር ምግብ ቤት ውስጥ አንድ ሚሊየን ብር የተዘጋጀ ቼክ ከደርጅቱ ወኪል ከሆነው ከአቶ ማሐመድ እስማኤል አሊ እጅ ሲቀበሉ በክትትል ላይ በነበሩ ጸጥታ ኃይሎች መያዛቸውን የፌደራል ፖሊስ መርማሪ አሳውቋል።

መርማሪ ፖሊስ በዚህ መልኩ ተጠርጣሪዎቹ የሙስና ወንጀል የምርመራ ማጣሪያ ስራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል ኢኒስፔክተር ሰለሞን ካሳ በሚመለከት የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ ማስረከቡን ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ፖሊስ አስታውቋል።

በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሪክቶሬት ዐቃቤ ህግ በጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ የምርመራ መዝገቡን ከዐቃቤ ህግ መረከቡን ጠቅሷል።

ዐቃቤ ህግ የምርመራ መዘገቡን ተመልክቶ በተገቢው ሁኔታ ክስ ለመመስረት እንዲያስችለው የ15 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

በተጨማሪም ዐቃቤ ህግ በወንጀል ድርጊት ሊገኝ ከታሰበው የገንዘብ መጠን ወይም የደረሰው ጉዳት አንጻር ሲታይ ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣና ዋስትና የሚያስከለክል መሆኑን ጠቅሶ ፤ የተጠርጣሪው ዋስትናው ታልፎ ክስ እስኪመሰረት ባሉበት በእስር እንዲቆዩ እንዲፈቀድለት ጠይቋል።

ተጠርጣሪው የዐቃቤ ህግ ክስ መመስረቻ ጥያቄን በመቃወም ዋስትና እንዲፈቀድለት ጠይቋል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የመረመረው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የተጠርጣሪውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለዐቃቤ ህግ የዘጠኝ ቀናት ክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል።

መረጃው የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

🚨" ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊየን 293 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ ፖሊስ አባላት ብቻ  ተቀጥተዋል !! "

እንደ ሸገር ሬድዮ ዘገባ ፥ በአዲስ አበባ በየቀኑ በአማካይ 7,183 አሽከርካሪዎች በትራፊክ ደንብ መተላለፍ በትራፊክ ፖሊስ ብቻ ይቀጣሉ።

ይህ በሌሎች የትራፊክ ደንብ ታላፊዎችን የሚቀጡትን አይጨምርም።

ባለፉት በ6 ወራት ውስጥ በተለያዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች ከ1 ሚሊየን 293 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ ፖሊስ አባላት ብቻ  ተቀጥተዋል፡፡

ይህም በየቀኑ 7,183 አሽካርካሪዎች መቀጣታቸውን ያሳያል፡፡

በሌላ በኩል " የታጠፈ የደበዘዘ የተፋፋቀ እና በአጠቃላይ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር አደርጋለሁ " ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ተናግሯል፡፡ 

ባለፈው በጥር ወር ብቻ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ ቁጥጥር ከ2,100 በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በየጊዜው እየተባባሰ ለመጣው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ልዩ ልዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች እንደ ምክንያትነት የሚገለጹ ቢሆንም ለእይታ ግልፅ ያልሆኑ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች መበራከት ለአደጋ ብቻ ሳይሆን የወንጀል ስጋት እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ አስረድቷል፡፡

በየጊዜው የታጠፈ የደበዘዘ እና የተፋፋቀ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ችግሩን መቅረፍ አልተቻለም ያለው ፖሊስ አሁንም ጠንካራ የቁጥጥርና አደርጋለሁ ብሏል፡፡

ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ጥፋቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ 1500 ብር ያስቀጣል፡፡

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia