TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
🔴 “ የተሰጠው መልስ ከእውነት የራቀና በህዝቡ ስቃይ እንደመሳለቅ የሚቆጠር ነው ” - አርሶ አደሮች
➡️ “ አንድ ኩንታል እንደዬአካባቢው ስለሚለያይ ይህን ያክል ነው ብለን ለመግለጽ ያስቸግረናል ” - ግብርና ሚኒስቴር
ሀዋሳ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች የማዳበሪያና በበቆሎ ምርጥ ዘር ዘንድሮ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ ከአምናው እጥፍ በላይ በመጨመሩ ማምረት እንደማይችሉ ሰሞኑን በቲክቫህ ኢትዮጵያ ድምፃቸውን ማሰማታቸው አይዘነጋም።
“ አምና 3,600 ብር ስንገዛው የነበረውን ማዳበሪያ ዘንድሮ 8,400 ብር ለመግዛት ተገደናል። አምና 1,800 ብር የነበረው የአንድ ፕሎት ምርጥ ዘር በቆሎ ዘንድሮ 4,600 ብር ገብቷል ” ሲሉ ነበር ያማረሩት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅቱ ምላሽ የጠየቀው የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ፣ “ ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር የማዳበሪያ ዋጋ ጨምሯል። የጨመርነው ነገር የለም። የትራንስፓርት ብቻ ነው የጨመርነው ” ብሎ፣ የምርጥ ዘር በቆሎ ዋጋም ከትራክተር፣ ከነዳጅ ዋጋ ጋር በተያያዘ መጨመሩን ቢሮው አልደበቀም።
አርሶ አደሮቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በድጋሚ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
“ የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ የሰጠው ምላሽ አጥጋቢ ካለመሆኑም አልፎ ከእውነት የራቀና በህዝቡ ስቃይ እንደመሳለቅ የሚቆጠር ነው። ምላሹ ‘ማዳበሪያ ላይ የተደረገው ጭማሪ የትራንስፖርት ብር ብቻ ነው’ ብሏል።
የትራንስፖርቱ ብቻ ሳይሆን ለማዳበሪያ በአመት 4,000 ብር መጨመር ዝርፊያ እንጂ ጭማሪ አይባልም። የበቆሎውን በተመለከተም ቢሮው፣ የትራክተርና የነዳጅ ጭማሬን በመጥቀስ ነው ምላሽ የሰጠው።
ለህዝቡ ማሳውን የሚያርሰው መንግስት አይደለም ህዝቡ በራሱ ገንዘብ እንጂ። ስለዚህ የማይገናኝ ነገር አገናኝቶ ህዝቡን ማሰቃየት አግባብ አይደለም።
በቆሎ የሚዘራው ከታህሳስ 15 ጀምሮ ነው። የሻመና ህዝብ ለአንድ ፕሎት እስከ 17,000 ብር በላይ አውጥቶ እንዴት ሊገዛ ይችላል ? ምንስ ሊያተርፍ ነው ? በዚህ ኑሮ ውድነት ገንዘቡንስ የት ነው የሚያመጣው ? ነው ወይስ ህዝቡን ነገ በረሃብ መቅጣት ነው የተፈለገው ?
በአንድ በኩል ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ የማይጠቀም አርሶ አደር እንዳይኖር ያስገድዳሉ፣ በሌላ በኩል ዋጋ በማናር እንዳይጠቀም ማድረግ አይጋጭም ? አርሶ አደሩ ዘንድሮ ምርት አያመርትም። መንግስት ችግሩን ይፍታልን ” ሲሉ አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ማዳበሪያ ወደ አርሶ አደሩ ሲከፋፈል ዋጋው ምን ያክል ነው ? አርሶ አደሮች ዘንድሮ የተጋጋነ ዋጋ ጭማሪ እንደተደረገባቸው ገልጸዋል። ጭማሬው ከላይ ነው ከታች ? ኩንታል ማዳበሪያ (ለምሳሌ ዳፕ) ዋጋው ስንት ነው ? ሲል ለግብርና ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቧል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ምን መለሱ?
“ አንድ ኩንታል እንደዬአካባቢው ስለሚለያይ ይህን ያክል ነው ብለን ለመግለጽ ያስቸግረናል። ምክንያቱም በርቀቱ ስለሚወሰን። በትራንስፓርት ነው የሚለያዩት።
ከዚያ ውጪ በሁሉም የአገራቷ ክፍል የሚሰራጨውን ማዳበሪያ ሴንትራሊ ዋጋ አውጥቶ የሚልከው ግብርና ሚኒስቴር ነው። ዋጋ ስናወጣ በግብርና ሚኒስቴር በኩል የሚጨመር ምንም አይነት የፕሮፊት ማሪጅን የለም።
ማዳበሪያው የተገዛበት፣ የትራንስፓርትና ሌሎች እንዲሁም ወጪዎች ተደርገው የአንድ ኩንታል ዋጋ ተሰልቶ ነው ወደ ታች የሚወርደው። መንግስት 84 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል።
ማዳበሪያ ከአምናው አንጸር ሲወዳደር ዋጋ በተወሰነ መንገድ ጨምሯል። ስለዚህ ታች የጨመረ ዋጋ ሳይሆን ማዳበሪያው የተገዛበት፣ ከሪፎርሙ ጋር የተወሰነ የነዳጅ ዋጋ ጭማሬ ስላለ፣ በዚያ ምክንያት የማዳበሪያ ዋጋ ጨምሯል።
ማዳበሪያ በዶላር ከውጪ ነው የሚገዛው። ታች ሊጨመር የሚችለው ትንሽዬ ወይ 100 ብር ወይ 50 ብር የዩኒየን ማሪጅን፣ ወደ ታች ደግሞ ሲወርድ እኛ እስከ ማዕከላዊ መጋዘን ነው የምናቀርበው።
ከማዕከላዊ መጋዘን ወደ መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማኀበር ሲያወርዱ ሁሉም ክልሎች እንደየርቀቱ የትራንስፓርት ዋጋ ልዩነት ይኖራል።
ስለዚህ አንድ ኩንታል ዋጋ ይሄን ያክል ብር ነው ብልህ ሀገራዊ ዋጋን ሪፕረሰንት ስለማያደርግ እንደዬ አካባቢው የተለያዬ ነው የሚሆነው። ግን ሴንትራሊ ለሁሉም የተገዛበትም ድጎማውም እኩል ነው የሚሰራው ” ብለዋል።
በአጠቃላይ ያለውን አቅርቦት ሲያስረዱም፣ “ 24 ሚሊዮን ኩንታል ነው የምናቀርበው። እስካሁን የ13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ግዥ ፈጸመናል ” ነው ያሉት።
(ማዳበሪያን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ የምናቀርብ ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

አፖሎ ከአቢሲንያ ባንክ የቀረበ ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጀታል ባንክ መተግበሪያ ሲሆን በቅድሚያ እርስዎ ተመዝግበው ለወዳጅ ዘመዶችዎ የተመዘገቡበትን መለያ ስልክ ቁጥር በመላክ እነሱንም ያስመዝግቡ። የሽልማቱ ዕጣ አሸናፊ ለመሆን አዲስ አካውንት መክፈትና ከ1000 ብር ጀምሮ መቆጠብ ይኖርብዎታል።
ወዳጅ ዘመዶችዎንም ወደ አፓሎ በመጋበዝ የዕጣ ቁጥሮችን በመሰብሰብ ባንኮክን የማየት ህልምዎን እውን ያድርጉ ። በተጨማሪም አይፎን 16 ፣ ሳምሰንግ S24 እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች በዕጣዎቹ ተካትተዋል። መልካም ዕድል!
አፖሎ ዲጅታል ባንክ መተግበሪያውን ለማውረድ https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo ይጫኑ!
ደንብ እና ግዴታዎች https://yangx.top/apollodigitalproduct/248
#ApolloReferral #መጣሁልሽ #አምሮኛል_መጣሁልሽ #ApolloWinBig #DepositAndWin #JoinApolloGetRewards

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ የካቲት 11 በዓል ምን አሉ ?
" ባለፈው የከፈልነው ይብቃ ፤ ያልፈውን አልፈዋል እንዳይደገም ያለፉት ስህተቶቻችን ማረም ያስፈልጋል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) 50ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል በማስመልከት በትግርኛ ቋንቋ ለመላው የትግራይ ህዝብ " የእንኳን አደረሳችሁ " መልእክት አስተላልፈዋል።
በአገር ውስጥና በመላው ዓለም ለሚገኙት የትግራይ ተወላጆች እና ወዳጆች " ለ50ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል እንኳን አደረሳችሁ " በሚል መልዕክታቸውን ያስቀደሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ ፥ የትግራይ ህዝብ ባለፉት ዘመናት ተጋድሎ ለአገር ሉአላውነት እና ዳር ደንበር መከበር የከፈለውን መስዋእትነት በታላቅ ክብር አስታውሰዋል።
በአገራችን ታሪክ ፓለቲካዊ ልዩነቶች በህግ ወይ በመግባባት የመፍታት የዳበረ ልምድ እንዳልነበረ ጠቅሰዋል።
ይሁን እንጂ ማህበረሰቡ በየብሄሩ እና አከባቢው የሚፈጠሩት ልዩነቶች በእርቅ እና ሽምግልና መፍታት በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫዎች የተዘወተረ ነው ብለዋል።
" ይህ ሆኖ እያለ ፓለቲካው ከባህል አፈንግጦ ሁሉም ልዩነቶች በግጭት ብቻ መፍታት ፓለቲካዊ ባህል ሆኖ ለዘመናት ቆይተዋል አሁንም ፈተና ሆኖ ቀጥለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ፓለቲካዊ ልዩነት በውይይት ፣ በእርቅ እና መግባባት ብሎም በህገ -መፈታት አለበት የሚለው አቋም ከለውጡ በኋላ እንደ መንግስት የተያዘ አቋም ነው ጠቅላአቋመያዝ በዘለለ ሕጋዊ እና ተቋማዊ አሰራር ተበጅቶለት በመተግበር ላይ እንደሚገኝ " ገልፀዋል።
" አሰራሩ ጅምር ላይ መሆኑ ልብ ማለት ይገባል " ያሉ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ጭቆና በምክክር እና ህጋዊ አሰራር መፈታት በማይችልበት ወቅት የነበረው ብቸኛ አማራጭ ጠብመንጃ በማንሳት ዴሞክራሲ እና እኩልነት ለማስፈን ከሌሎች ህዝቦች ጋር በማበር የየካቲት 11 ትግል ለማካሄድ መገደዱን አስታውሰዋል።
" ጠበመንጃ በማንሳት የሚካሄድ የግጭት መንገድ በመሰረቱ የሚደገፍ ባይሆንም በወቅቱ የነበረው ፓለቲካዊ እና ህጋዊ ሁኔታ ግን ጠብመንጃ ለማንሳት የሚያስገድድ ነበር " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ " የካቲት 11 የተቀጣጠለው በጠብመንጃ የታገዘ ፓለቲካዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማቆም ልየነቶች በውይይት ለመፍታት ያለመ በመኖሩ ከሱ በፊት ሲካሄዱ ከነበሩት ትግሎች ሲነፃፀር ይለያል " ብለዋል።
ስለሆነም ማንኛውም ልዩነት በጠብመንጃ ሳይሆን በውይይት እና በህጋዊ መንገድ መፍታት የየካቲት 11 ፍሬዎች መሆናቸው መገንዛብ ያሻል ሲሉ አክለዋል።
" ባለፉት የቅርብ ዓመታት ያጋጠሙን መቃቃሮች ለመፍታት የተከተልነው የግጭት መንገድ ፤ ከየካቲት 11 ዓላማዎች የወጣ መሆኑ ግልፅ ነው ፤ ይሁን እንጂ ከባድ ዋጋ ከፍለንም ቢሆን ወደ ውይይት መመለሳችን የሚደነቅ እርምጃ ነው ፤ ይሁን እንጂ አሁንም ፓለቲካዊ ልዩነት በጠንጃ ለመፍታት የመፈለግ ዝንባሌ መታየቱ አልቀረም " ብለዋል።
" ባለፈው የከፈልነው ይብቃ ፤ ያልፈውን አልፈዋል እንዳይደገም ያለፉት ስህተቶቻችን ማረም ያስፈልጋል " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ በትግራይ አመራሮች መካከል የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለውጤት እንዲበቃ ያላቸው መልካም ምኞት ገልፀዋል።
ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ፣ የተስተጓጎለው ልማት ተጠናክሮ በህዝብ ወደ ተመረጠ መንግስት ሽግግር እንዲደረግ ከልብ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።
የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ህዝብና ልሂቃን በተገለፀው የውውይት መንፈስ ማሰብ ከጀመሩ ፤ ትግራይ ወደ መደበኛ የህገ-መንግስት ስርዓት በመመለስ በሃገረ መንግስቱ ያላትን ተሳትፎ አጠንክራ የምትቀጥልበት ጊዜ በጣም አጭር እና ተጨባጭ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መልካም የየካቲት 11 በዓል እንዲሆንም በፅሁፋቸው ተመኝተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

" የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል ! "
የ17 አመት ታዳጊ በሆነችው አዶናይት ይሄይስ ላይ የአስገድዶ መድፈርና የግድያ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተወሰነበት።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ክልል ልዩ ቦታው 15 ሜዳ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።
የወንጀሉ ሰለባ የሆነችው የ17 አመት እድሜ ያላት አዶናይት ይሄይስ የተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ የፍቅረኛው ልጅ ነበረች።
መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰአት ሲሆን ታዳጊ አዶናይት ይሄይስ መኖሪያ ቤቷ እያለች ተከሳሽ " ለምን አስገድዶ ደፈረኝ ብለሽ ለፖሊስ ክስ መሰረትሽ " በሚል ሰበብ በቢላዋ የተለያየ የሰውነት ክፍሏን 16 ቦታ በመውጋት ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመሄድ ልብሱን በመቀየር ሊሰወር ሲሞክር በአካባቢው ማህበረሰብ እና በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ሊያዝ ችሏል።
ፖሊስም በተያዘው ተከሳሽ ላይ ባደረገው ምርመራ ከ2005 እስከ 2007 ዓ.ም ባልታወቀ ጊዜና ሰዓት ታዳጊዋን " ነይ ሱቅ ልላክሽ " እና ሌሎች ማታለያዎችን እየተጠቀመ በመኖሪያ ቤቱ በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት የቆየ መሆኑንና በወቅቱ እድሜዋ በግምት 10 አመቷ እንደነበረ የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ግለሰቡ የእናቷ የፍቅር ጓደኛ የነበረ ሲሆን ይህንን አፀያፊ ድርጊት ለአንድ ሰው ብትናገሪ እናት እና አባትሽን እገላለሁ እያለ ሲያስፈራት የቆየ ስለመሆኑ የሚዘረዝረው የምርመራ መዝገቡ በተጨማሪም ሟችን " በሞባይል ካሜራ ቪዲዮ ቀርጬሻለሁ በሚዲያ እና በቴሌግራም እለቀዋለሁ " እያለ ለአመታት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት መቆየቱንና በዚህም ታዳጊዋ ከተከሳሽ በመፀነሷ ፅንሱን እንድታስወርድ ማድረጉን የተከሳሽ የምርመራ መዝገብ ያስረዳል።
ፖሊስ ባከናወነው ተጨማሪ የምርመራ ስራ ተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙን አምኖ ቦታው ድረስ በመሄድ መርቶ ያሳየ ሲሆን የምርመራ መዝገቡን በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለዓቃቤ ህግ በመላክ ክስ ተመስርቶበታል።
የወንጀል መዝገቡን ሲከታተል የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ #የሞት_ቅጣት እንዲቀጣ እና የዘወትር ህዝባዊ መብቶቹ እንዲሻሩ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡
#AddisAbabaPolice

#Tigray " ችግሮቻቸውን በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል " - የሃይማኖት አባቶች የትግራይ ክልል አመራሮች በመካከላቸው የተፈጠረው የፓለቲካ ልዩነት በሰላም እና በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው የትግራይ የሃይማኖት መሪዎች አስታወቁ። ችግሮቻቸው ለመፍታት እና ወደፊት ሊያራምዳቸው የሚችል የስነ-ምግባር ደንብ ወጥቶ መፈራረማቸውም ሰላማዊ ውይይቱን የመሩ የሃይማኖት አባቶች ዛሬ…
#Update
" በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።
ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት " ቡድን " ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ " መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው " ብለዋል።
አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል።
ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው ሁለት ክሶች በነፃ ተሰናበቱ።
የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ የሕግ ጠበቃቸው አቶ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ማዕከል ከቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል እና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም በሚል የቀረበባቸዉን ሁለት ክሶች ላለፉት አንድ ዓመት ሲከታተሉ ቆይዋል።
በዛሬዉ ዕለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐዋሳና አከባቢዋ ማዕከል በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል።
ከቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በተጨማሪ ተመሳሳይ ክስ ተመሰርቶባቸዉ የነበሩት የቀድሞ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበራ አሬራም በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW

ቪድዮ ፦ በካናዳ ቶሮንቶ ፒርሰን አየር ማረፊያ አንድ አውሮፕላን በማረፍ ላይ ሳለ ባጋጠመው አደጋ ጥቂት መንገደኞች ላይ ጉዳት ቢደርስም አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች መትረፋቸውን የአየር ማረፊያው ኃላፊ አስታወቁ።
" ምንም ዓይነት የሞት አደጋ ባለመኖሩ በጣም ደስተኞች ነን። ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ጉዳት የደረሰባቸው " ሲሉ የግሬት ቶሮንቶ አየር ማረፊያ ባለሥጣን ኃላፊ ዴቦራህ ፍሊንት ተናግረዋል።
አንድ ሕፃን እና ሁለት አዋቂዎች ክፉኛ መጎዳታቸው ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥራ ዘመን ለአንድ አመት ተራዘመ።
ኮሚሽኑ ዛሬ የሦስት አመታት ሪፓርቱን ለፓርላማ ያቀረበ ሲሆን፣ የፓርላማ አባላት በሪፓርቱ ላይ የተለዩዩ ጥያቄዎችንና አስተየቶችን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ሦስት አመቱን የካቲት 14 ቀን በመድፈን የሥራ ዘመኑ ይጠናቀቅ የነበረው ኮሚሽኑ፣ በፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ የአንድ አመት ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቶታል።
በቋሚ ኮሚቴው የተሰጠው የአንድ አመት ተጨማሪ ጊዜ ውሳኔው የቀረበበት ሦስት የተቃውሞ ድምፅ ብቻ ነው።
በተለይ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ስላለው ሁኔታ የፓርላማ አባላት ያነሷቸውን ነጥቦችና የተሰጡ ምላሾችን በተመለከተ ተጨማሪ ይኖረናል።

ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት አስጀመረ፤ የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ በማፋጠን ላይ!
በኢትዮጵያ ቀዳሚው የቴሌኮም እና ዲጂታል አገልግሎቶች አቅራቢ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) ኔትወርክ ማስፋፊያ አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡
ኩባንያችን የ5ጂ አገልግሎትን በአዲስ አበባ እ.ኤ.አ በ2022 ካስጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ እስካሁን ድረስ፣ ጅማን ጨምሮ በ12 ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በጅግጅጋ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በሆሳዕና፣ በአርባ ምንጭ እና በቢሾፍቱ አገልግሎቱን ዕውን አድርጓል።
ቴክኖሎጂው የኔትወርክ አቅም ከመጨመር ባሻገር አዳዲስ የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ ለኦንላይን ትምህርት፣ ለጀማሪ የንግድ ተቋማት (startups)፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ፣ የስማርት ስልክ አቅርቦት ለማሳደግ እና የዲጂታል ሊትሬሲን ለመጨመር አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል።
የ5ጂ ቴክኖሎጂ የድርጅት ደንበኞችን የዕለት ተዕለት አሰራርን ከማዘመን በተጨማሪ፣ ቁልፍ በሆኑ ዘርፎች ላይ ማለትም ጤናን፣ ግብርናን፣ ትምህርትን፣ ማኑፋክቸሪንግን እና ማዕድንን፣ ትራንስፖርትን፣ ቱሪዝምን፣ መዝናኛን በስማርት ቴኮኖሎጂ በማዘመን ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡
ክቡራን ደንበኞቻችን የ5ጂ አገልግሎት ማስተናገድ የሚያስችሉ ቀፎዎች እና ሲም እንደፍላጎት በአገልግሎት ማእከላችን በማግኘት የእጅግ ፈጣኑን ኔትወርክ ተጠቃሚ በመሆን አስደናቂ ተሞክሮ እንድታገኙ በደስታ እንጋብዛለን፡፡
ለተጨማሪ፡- https://bit.ly/42Z0ygF
አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት፣ አዲስ አኗኗር!