TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
“ ድግግሞሹ ቀንሷል፤ እንደድሮው አይደለም። ግን የነበረውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል ነው ” - አታላይ አየለ (ፕ/ር)

ከዚህ ቀደም ካጋጠሙ ክስተቶች አንጻር በከፍተኛ ሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመተሃራ በቅርበት ላይ አርብ ሌሊቱን ተከስቶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ አርብ ሌሊት መተሃራ አካባቢ 6.0 ሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉን ተመራማሪ ጠይቋል።

በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥበጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር)፣  በሰጡት ምላሽ፣ “ አዎ። ልክ ነው ተፈጥሯል። ሌሊት 5 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ገደማ ከምሽቱ ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

“ ነገር ግን ሰው አልሰማውም እንደድሮው ” ሲሉ አክለው፣ “ እንደዚያ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከመሬት ወለል በታች ጥልቅ ስለሆነ ነው እንጂ እንደዛ ባይሆን ኑሮ በጣም ብዙ ጉድ ይሆን ነበር ” ብለዋል።

የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 6.0 የተመዘገበ ነው መባሉ ልክ ነው ? ስልን ላቀረብንላቸው ጥያቄ፣ “ እውነት ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህ የሚያመላክተው ስኬሉ እየጨመረ እንደመጣ ነው፤ ሰሞኑን ትንሽ ቆም ሲል ጠፋ የሚል ተስፋ ተሰንቆ ነበር፤ አሁንም እንቅስቃሴው አለ ማለት ነው ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄም ለተመራማሪው አቆርበናል።

“ እንደዛ ሆነ ማለት ይቀንሳል ማለት አይደለም። እየቀጠለ ነው ያለው ነገርየው። ሙሉ ለሙሉ ቆመ፣ ሞተ ለማለት አያስደፍርም። እንቅስቃሴው እንዳለ ነው ” ብለዋል።

“ ከመስከረም ጀምሮ እስካሁን አቅም በፈቀደ ሁሉም ሰው ጥንቃቄ እንዲያደርግ ለማድረግ እየተሞከረ ነው። አሁንም ያው ከመሬት ወለል በታች ጥልቅ መሆኑ ነው የበጀን ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ ድግግሞሹ ቀንሷል፤ እንደድሮው አይደለም። ግን የነበረውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል ነው። ጨርሶ ቆመ ማለት እንደማይቻል ነው ዋናው መልዕክት ” ሲሉ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ሌሎች ምን እንማር ? "

በትግራይ ክልል የነበረውን ግጭት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሂደትን በተመለከተና ከስምምነቱ " ሌሎች ምን እንማር ? " በሚል ርዕስ ዛሬ በአፍሪካ ህብረት ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በዚህ ውይይት ላይም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ እና ሌሎች ተገኝተዋል።

የፕሪቶሪያውን ስምምነትና አፈፃፀም የተመለከተውን ሪፓርት ደግሞ ተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፉኪ ማህማት፣ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድን ሰብሳቢ ኡሊሲንጎን ኦባሳንጆ እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮች አቅርበዋል።

ከአንድ ሰአት በላይ የዘለቀ ውይይት ከተካሄደ በኋላ አቶ ጌታቸው ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት " የዛሬው መድረክ እስካሁን የሄድንበት ርቀት መገምገም ነው። ከጀመርነው ፍጥነት አንፃር ገና ያላለቁ ነገሮች አሉ። ግን በተሻለ ፍጥነት መጨረስ የምንችልበት እድል ለማግኘት ነው የመጣነው " ብለዋል።

አክለውም ሰላምን ከመስበክ ፣ ሰላምን ከመተግበርም ሆነ ከምንም ነገር በላይ ግን ተፈናቃዮች ወደወትሮ ህይወታቸው የሚመለሱበትና ህገመንግስቱ በሚያስቀምጠው መሰረት የፕሪቶሪያ ውል ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ የሚሆንበት ጉዳይ ላይ ነው ሀሳብ የተለዋወጥነው። በቀጣይም በዚህ መሰረት የምንቀጥል ይመስለኛል" ብለዋል።

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ፎቶ ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ (መስፍን ሰለሞን)

@tikvahethiopia
“የባለስልጣናት ያልተገሩ ንግግሮችና የመንግስትም ተቀዳሚ ተግባሩን ፍጹም መርሳት ሕዝብን ለእልቂት እየዳረገ ነው”- ፓርቲው

እናት ፓርቲ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ባወጣውና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ፣ “መልኩንና ቦታውን እየቀያየረ መላ ኢትዮጵያውያንን የደኅንነት ዋስትና ያሳጣው ሀገራዊ እልቂት አሁን አሁን ወደ ሀገራዊ ቀውስነት እያደገ ነው ለማለት ያስደፍራል” ሲል ተችቷል።

አክሎ፣ “ለዚህ ደግሞ ብዙ የተጠራቀሙና ያልተፈቱ የችግር ቋጠሮዎች ቢኖሩም በዋናነት ባለስልጣናት የሚያደርጓቸው አደገኛ የእልቂት ጠመቃ ንግግሮች ዋነኞቹ ናቸው” ብሏል።

“መንግስት በተደጋጋሚ ቢነገር ችላ ያለውን የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ አለመስራት አሁን ያለንበት ሁኔታ ምን አልባት ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ እያደረሰው ይገኛል” ሲል ወንጅሏል።

በዚህም ሰሞኑን በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ቀበሌዎች በአንድ ግለሰብ ግድያ ምክንያት የተስተዋለውን “ቀውስ” ያወሳው ፓርቲው፣ ግድያውን አውግዞ፣ “ድርጊቱም በውል ተጣርቶ አጥፊዎች ከሕግ ፊት እንዲቀርቡ እናሳስባለን” ሲል ጠይቋል።

የስፍራው ነዋሪዎች ዘርፈ ብዙ በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ነዋሪዎች እንደገለጹለት ያተተው መግለጫው፣ በጅማው “ቀውስ” “በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለዋል። ወፍጮ ቤቶች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ሱቆች እየጋዩ ነው። ‘ይህም ማንነት ተኮር ነው’፣ ‘አማራ ነው ያሉትን ንብረት እየመረጡ ነው የሚያቃጥሉት’ ብለዋል” በሚል ተጠናቅሯል።

“ብዙ ሺህ ሰው አካባቢውን ለቆ ከፋ ዞን ተጠልሏል። በተለይ የአቅመ ደካሞች፣ ሕጻናትና ነብሰ ጡሮች ስቃይ አሳዛኝ ነው፤ በሽሽት ላይ ሳለች የወለደች እናት እንዳለችም ይናገራሉ” በማለት የነዋሪዎቹን እሮሮ ጠቃቅሷል።

የከፋ እለቂት ሳይደርስ መንግስት ድርሻውን እንዲወጣ፣ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ እንዲደረግ፣ ገዳዮችና አሳዳጆች ለፍትህ እንዲቀርቡ፣ ‘የሰባብረናቸዋል’ ዓይነት ንግግሮች እንዲቆሙና ማስተባበያዎች ይቅርታ እንዲጠየቅባቸው ፓርቲው በመግለጫው ጠይቋል።

(የፓርቲው ሙሉ መግለጫም ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ። 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአህጉሪቱ መዲና በሆነችሁ በአዲስ አበባ ዛሬ በይፍ መካሄድ ጀምሯል። ጉባኤው ከ35 በላይ የሀገር መሪዎች፣ አንድ ንጉስ፣ 19 ቀዳማዊት እመቤቶች፣ ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሁለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአዲስ…
#AU

38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ተጠናቋል።

በጉባዔው ላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም የሕብረቱ ተቋማት እና አደረጃጀቶች አመራሮች ተሳትፈዋል።

በጉባኤው ፦
➡️ የአፍሪካ ሕብረት ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣
➡️ የማካካሻ ፍትህ፣
➡️ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ለማግኘት እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች፣
➡️ አህጉራዊ ሰላምና ደህንነት፣
➡️ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አፈጻጸምና አህጉራዊ የንግድና ኢኮኖሚ ትስስር፣
➡️ ግብርናና የአየር ንብረት ለውጥ፣
➡️ ሰብዓዊ መብቶች፣
➡️ ስርዓተ ጾታና ወጣቶችን ማብቃት እንዲሁም የተቋማትና አደረጃጀቶች ምርጫ ውይይት ከተደረገባቸው ዋንኛ አጀንዳዎች መካከል ይገኙበታል ተብሏል።

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ተቋማት አመራሮች ጋር መክረዋል።

ባለፉት ቀናት እጅግ በርካታ አህጉር አቀፍ መሪዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎችን ፣ እንግዶችን ስታስተናግድ የቆየችው የአፍሪካና የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ እንግዶቿን እየሸኘች ትገኛለች።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
ብርሃን ልዩ ካርድን በመጠቀም በተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ ኤቲኤም ማሽኖች ገንዘብዎን ወጪ ያድርጉ፣ በፖስ ማሽኖች ክፍያዎችን በቀላሉ ይፈጽሙ!
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
#berhanatm #berhanpos #payment #cashout #liyucard #berhanliyucard #berhanbank
#bank #finance #Stressfreebanking #bankinethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AU #ADDISABABA

38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታውቋል።

የፀጥታና ደኅንነት ጥምር-ኃይሉ "  የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት የበለጠ በማጠናከር የኅብረተሰቡ እንቅስቃሴ ሳይገታ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ በማድረግ በቅንጅት በመሥራቱ ጉባኤው በስኬት ተጠናቋል " ሲል ገልጿል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " የህብረቱ ጉባኤ ለከተማችን ድምቀትና የኢኮኖሚ መነቃቃት ከመፍጠሩ ባሻገር የቱሪዝም መስህቦችን እና የከተማችንን መልካም ገጽታዎችን እንዲሁም የህዝባችንን ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል " ብለዋል።

" ጉባኤው እጅግ ደማቅ እና ከወትሮው የተለየ ሁኔታ የተካሄደ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

እንግዶች ወደየሀገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው።

@tikvahethiopia
“ ይሳቅ ህሩይ የትግራዋይ ነው። ከፋኖ ጋር ሊያገናኘው የሚችል አንዳችም ነገር የለም።  ” - ኢሕአፓ ስለታሰረው አመራሩ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የአዲስ አበባ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ አባሉ አቶ ይሳቅ ወልዳይ እንደታሰሩበት ገልጿል።

ፓርቲው አመራሬ “በሐሰተኛ ፍረጃ ነው” የታሰሩብኝ ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የፓርቲው ተቀዳሚ ፕሬዜዳንት መጋቢብሉይ አብርሃም ሃይማኖት በሰጡት ቃል ፥ "  የካቲት 6/2017 ዓ/ም ከቤታቸው በፓሊስ ተወስደው ነው የታሰሩት።  ' ፋኖ ይደግፋል '  በሚል ሐሰተኛ ውንጀላ ነው የተወነጀለው " ሲሉ
ገልጸዋል።

የፓርቲው ተቀዳሚ ፕሬዜዳንት በዝርዝር ምን አሉ ? 

“ ሰላማዊ ታጋዮችን በሐሰተኛ መረጃ እያሸማቀቁ እያሰሩ፤ ጋዜጠኞችን እያሳደዱ ሀገር ሰላም ማድረግ አይቻልም። ስለዚህ ሰላም ጠሉ ራሱ መንግስት እንደሆነ ነው እያረጋገጠልን ያለው።

አቶ ይሳቅ ከተባለበት ጉዳይ ጋር የሚያያይዘው አንዳችም ነገር የለም። መንግስት ሕግ ማክበር እንዳለበት የዘነጋው ይመስለኛል። መንግስት ሕገ መንግስቱን አክብሮ ነው የሚያስከብረው፤ ራሱ እየደፈጠጠ መሆን የለበትም።

ይሳቅ ህሩይ የትግራዋይ ነው። ከፋኖ ጋር ሊያገናኘው የሚችል አንዳችም ነገር የለም። ግን ‘የአፍሪካ ህብረትን ለመበጥበጥ፣ መሪዎችን ለመግደል’ የሚል ሐሰተኛ ፈጠራ ሲያቀናብሩ አእምሯቸው እንዴት አቀናበረው ? ብለን እንድንጠይቅ አድርጎናል።

ከዚህ በፊት ዓርዓያ ተስፋማርያም በሚባል ጋዜጠኛ ነኝ በሚል ግለሰብ ይሄው አባላችን ታስሮ በጩኸት ወጥቷል። አሁንም በሐሰተኛ ቅንብር፣ ከመንግስት አካላት ጋር ያላቸው ግንኙነትን በመጠቀም ታስሯል ” ብለዋል።

አመራሩ ከ“ፋኖ” ጋር በተገናኘ የተጠረጠሩት ፌደራል ፓሊስ ጉዳዩን ከምን ጋር አገናኝቶት ነው ? ለሚለው ጥያቄ በምላሻቸው፣ በኮሪደር ልማት አዲስ አበባ ቤት የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ካሳ እንዳልተከፈላቸው በማጋለጣቸው ነው ሲሉ ጠቅሰዋል። 

አክለው፣ “ ያንን ተከትሎ ኢሕአፓን ለማሸማቀቅና ቀጣይ የሚያደርጋቸውን ጠንካራ ሰላማዊ ትግል እንዳያደርግ ሆን ተብሎ ለማስፈራራት የተቀናበረ ቅንብር ነው ” ብለው፣ ፓርቲው በዚህ እንደማይሸማቀቅ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የፌደራል ፓሊስ የምርመራ ጊዜ ማጣሪያ የጠየቀበት ደብዳቤ፣ ከአቶ ይሳቅ ጋር 13 ግለሰቦችን ጠቅሶ " በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሰው " ቡድን ግንኙነት አላቸው በሚል ይወነጅላል።

ፓሊስ፣ “ ምርመራውን በሰውና በሰነድ ማስረጃ በስፋት ለማጣራት ” የ14 ቀናት የቀጠሮ ጊዜ እንዲሰጠው ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረቡን ደብዳቤው ያትታል።

የፓርቲው ተቀዳሚ ከንቲባ በበኩላቸው፣ “ ሰኞ ፍርድ ቤት ለኛ ቀጠሮ ሰጥቶናል የፌደራል ፓሊስ የ14 ቀን ቀጠሮን ውድቅ በማድረግ ‘ተጨባጭ መረጃ ካላችሁ አምጡ’ በማለት” ብለዋል። 

“ ፍርድ ቤቱም ‘እንደዚህ አይነት ሐሰተኛ ቅንብሮች እየተለመደ ስለመጡ ተጨባጭ ነገር ካለ አምጡ አለዚያ ጊዜ ቀጠሮ አልሰጣችሁም’ ብሎ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል ” ነው ያሉት።

13ቱም “ተጠርጣሪዎች” የፓርቲው አካላት ናቸው ? ስንል የጠየቅናቸው ተቀዳሚ ፕሬዛዳንቱ፤ ከአቶ ይሳቅ ውጪ ያሉት 12 ተጠረጠሩ ተብለው የታሰሩ ግለሰቦች ከፓርቲው ጋ ግንኙነት እንደሌላቸው አስረድተዋል።

“ ነጋዴዎች አሉ ምንም ፓለቲካ ውስጥ የሌሉ። በተጨባጭ መረጃ ያለን አንድ ካድሬ ከጠላ ይፈርጅህና ለወራት ታሽተህ ትለቀቃለህ። ዜጎችን ማሸማቀቂያ፣ ማሰቃያ ሆኗል የፍትህ ስርዓቱ ” ሲሉ ወቅሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia