የብርሃን ቤተሰቦች በመሸለም ላይ ናቸው!
እርሶም የብርሃን ቤተሰብ በመሆን፤ ውድድሩን ይቀላቀሉ ተሸላሚ ይሁኑ፡፡
አርብ 4፡00 ሰዓት በቴሌግራም ገፃችን ይጠብቁን
👇👇👇
Telegram Link: https://yangx.top/berhanbanksc
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
#Weeklyquiz #questionandanswer #stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ዛሬ በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች በኩል የፓሊስ ትእዛዝ የጣሱ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራቸው ሰልፈኞች ፥ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ጥር 14/2017 ዓ.ም የወጣውን የውሳኔ ሃሳብ የሚደግፉና እና ሌሎች መፈክሮች አስተጋብተዋል። በራሳቸው ተነሳሽነት ሰልፍ መውጣታቸው የሚናገሩት በብዛት ወጣቶች…
" መንግስታችን እንዳይፈርስ እስከ ሞት ድረስ እንታገላለን ፤የጦርነት ነጋዴዎች ከድርጊታችሁ ታቀቡ " - አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ
ዛሬ በመቐለ " እምቢ ለጦርነት እምቢ ለመፈንቅለ መንግስት !! " በሚል መሪ ቃል የሰሞኑን የወታደራዊ አመራሮች መግለጫ የሚቃወም ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።
በሰልፉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተው ነበር።
በጊዚያዊ ኣስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ በሰልፉ ላይ ተገኝተው " የሰላም ዋስ የሆነው ሰራዊት የቡድኖች መጫወቻ አይሆንም ፥ የጦርነት ነጋዴዎች ይብቃችሁ " ብለዋል።
" የሻዕብያ ተላላኪዎች አቁሙ !" ሲሉ በምሬት የተናገሩት ከንቲባው " መንግስት ለማፍረስ የተሄደው ርቀት አይሳካም ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ይከበሩ ህዝቡም እንዲከበሩ ያግዝ " ብለዋል።
" የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት በሙሉነት እንዲተገበር ፣ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዲከበር እና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ቁርጠኛ መሆን አለበት " ያሉት ከንቲባው " የትግራይ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በሰላም ብቻ መሆኑን በማመን ወጣቱ ትግሉ አጠናክሮ ይቀጥል " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
ዛሬ ከመቐለ በተጨማሪ በሌሎችም ከተሞች ጊዚያዊ አስተዳደሩን ለመደገፍ እና " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው መገለጫ እና ውሳኔና በመቃወም ወጣቶች በበዙባቸው ሰልፎች ተካሂደው ነበር።
በዚህም ፦
- መንግስት ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- የትግራይ ህዝብ ጥቅም በሰላም ብቻ ነው የሚረጋገጠው !
- ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንደግፋለን !
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ይከበሩ !
- የፕሪቶሪያ ስምምነት ይከበር !!
- የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር !!
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!
የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች ተደምጠዋል።
ትላንትና ዛሬ መቐለ ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የትግራይ ኃይል መኮንኖችን የሚደግፉና የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ የሚገኝ ሲሆን ሰልፎቹ የፖሊስን ክልከላ በጣሰ መንገድ ነው እየተካሄዱ ያሉት።
በህወሓት የፖለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እና መከፋፈል ወደ ፀጥታ ኃይል አመራሮች መዛመቱ ህዝቡን ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሏል።
ትግራይ ከአስከፊው እና አውዳሚው ጦርነት ገና በቅጡ ሳታገግምና ችግሮች ሳይፈቱ ወደ ሌላ ቀውስ ውስጥ ሊያስገባ የሚችል ሁኔታ እየታየ መሆኑ በርካቶችን አሳስቧል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

Photo
“ ቪዲዮው ደርሶናል። ምርመራ እያደረግን ነው ” - ኢሰመኮ
የጸጥታ ኃይል ልብስ የለበሰና መሳሪያ የታጠቀ አካል እጁን ወደ ኋላ የፊጢኝ የታሰረን ወጣት ከወደጀርባው በመሆን ጭንቅላቱ ላይ ሲተኩስበት የሚያሳይ ቪዲዮ ከሰሞኑን በማኀበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።
ድርጊቱ ብዙዎችን ያስለቀሰና ያስቆጣ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ “ እንዲያው እንደዚህ ያጨካከነን ምን ይሆን? ” ሲሉ በሀዘን ስሜት ተውጠው ሲጠይቁ ተስተውለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበከሉ፣ ድርጊቱ ደርሶት በሰብዓዊ መብት ጥሰት አኳያ ጉዳዩን ዳሶት እንደሆን በሚል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን ጠይቋል።
ኮሚሽኑ ይህንን ግፍ የተሞላት ድርጊት ተመልክቶት ይሆን ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ “ ጉዳዩ ደርሶናል። እኛ የራሳችንን ኢንቨስቲጌሽን ስለምንሰራ በቪዲዮው ላይ ትንሽ ጊዜ ይወስዳል ” የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።
ድርጊቱ የት ? መቼ ? በማን ተፈጸመ ? ለሚለው እካሁን የተሰጠ ማብራሪያ የሌለ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ በበኩሉ፣ “ መቼ ነው የተፈጸመው ? ማነው የሞተውስ ? የሚለውን ዝርዝሩን በሙሉ እያጣራን ነው የምንገኘው ” ሲል ጠቁሟል።
“ ዲጂታሊ ሰርተን ስናበቃም እዚያው የነበሩ የአካባቢው ሰዎችን ደግሞ ማነጋገር ይኖርብናል” ነው ያለው።
ድርጊቱ የተፈጸመበት አካባቢ ታውቋል ? ለሚለው ጥያቄ ኮሚሽኑ በምላሹ፣ “ ፍንጭ አለን ግን አሁን ለሚዲያ መግለጽ አንችልም። ምክንያቱም እርግጠኛ አይደለንም። እሱን እርግጠኛ ስንሆን እንነግራችኋለን ” ብላል።
ስለዚህ አሁን ምርመራው ተጀምሯል ማለት ይቻላል? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ፣ “ ቪዲዮው ደርሶናል። ኢንቨስቲጌት እያደረግን ነው ” ሲል መልሷል ኮሚሽኑ።
እንዲህ አይነት ግልጽ የወጡ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶትን በተመለከተ አስተያዬት እንዲሰጥ ጠይቀነው ባስረዳበት አውድ ደግሞ፣ “ አሁን ባለው ሁኔታ እንዲህ አይነት ቪዲዮዎች በብዛት እየወጡ ናቸው ሚዲያ ላይ። እኛ ጋም የሚደርሱ አሉ ” ሲል የድርጊቱን ሁኔታ አስረድቷል።
“ አስቸጋሪ ነው። በጣም ብዙ ናቸው እናንተ አንድ ብቻ ስላያችሁ ነው እንጂ። ስለዚህ ይሄ ቪዲዮ ላይ ብቻ አሁን ላይ ኮመንት ማድረግ አልችልም ” ነው ያለው።
“ በአጠቃላይ አገሪቱ ላይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? ለሚለው በየጊዜው የምናወጣቸው ሪፓርቶች አጠቃላይ የሚያሳዩት ገጽታ አለ እሱን መያዝ ነው ” ብሏል።
የሰሞንኛውን ቪዲዮ ምርመራ ሲያልቅ ሙሉ አስተያዬትና ማብራሪያ እንደሚሰጥ ኮሚሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃል የገባ ሲሆን፣ ሁነቱን ተከታትለን በቀጣይ ተጨማሪ መረጃ የምናደረሳችሁ ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

" እስር እና ሰዎችን ወደ መጡበት አገር የመመለስ ሥራ በቁጥር ይጨምራል " - የትራምፕ የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ
በአሜሪካ ሕገወጥ ከተባሉ ስደተኞች ጋር በተያያዘ ከእሑድ ጀምሮ በተጀመረ የአሰሳ ዘመቻ እስካሁን 956 ሰዎች መታሰራቸው ተገለጸ።
ይህም ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ ቁጥር መሆኑን የአገሪቱ የስደተኞች እና የጉምሩክ ተቋም የሆነው ኢሚግሬሽን ኤንድ ከስተምስ ኢንፎርስምነት (አይሲኢ) አስታውቋል።
የፌደራል ተቋማት በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥልጣናቸው እንዲሰፋ መደረጉን ተከትሎ በቺካጎ፣ ኔዋርክ፣ ኒው ጀርዚ እና ማያሚ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞችን የማደኑ ዘመቻ ተካሂዷል።
ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወደንጀለኞች ያሏቸውን ያልተመዘገቡ ስደተኞችን በጅምላ ወደመጡባቸው አገራት እንደሚመልሱ ቃል ሲገቡ ነበር።
የትራምፕ የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ " ሰነድ አልባ ሰዎች በአሰሳ ወቅት ከተያዙ ወደመጡበት አገር ይመለሳሉ " ብለዋል።
" እስር እና ሰዎችን ወደ መጡበት አገር የመመለስ ሥራ በቁጥር ይጨምራል " ሲሉ ተናግረዋል።
" አሁን ትኩረታችን የሕዝብ ደኅንነት እና የብሔራዊ ደኅንነት ስጋትን ማስወገድ ነው " ብለዋል።
ያለፈው ሳምንት አርብ 538፣ ቅዳሜ 593 እና እሑድ 286 ሰዎች ተይዘዋል። በጆ ባይደን የአራት ዓመታት አስተዳደር ዘመን ከአሜሪካ ተባረው ወደ አገራቸው የተመለሱ 1.5 ሚሊዮን ስደተኞች ናቸው።
መረጃው የቢቢሲ እና ኤቢሲ ኒውስ ነው።

🪪 የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) በአገልግሎት ማዕከሎቻችን በነጻ ይመዝገቡ!!
የካርድ ኅትመት አገልግሎት በአዲስ አበባ፣ በሐዋሳ፣ አዳማ፣ ወላይታ ሶዶ እና ነቀምቴ ከተሞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡
👉 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ‘’NID (Fayda) Printing’’ መተግበሪያ ተጠቅመው የካርድ ኅትመትዎን በቀላሉ ይዘዙ!
🔗 በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመረከቢያ ቦታዎችን ለመመልከት፡ https://bit.ly/40efSUZ
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

" ተመዝግበንና ክፍያም ከፍለናቸው ትምህርት በመጀመር ሂደት ላይ ባለንበት ዩኒቨርሲቲዉ አላስተምራችሁም ብሎናል " - የሪሚዲያል ተማሪዎች
➡️ " ዉሳኔዉ የትምህርት ሚንስቴ እንጂ የዩኒቨርሲቲው አይደለም " - የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
" የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሁለት ወራት ፊት በሣምንቱ የዕረፍት ቀናት የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ከፍለዉ መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ባወጣዉ ማስታወቂያ መሰረት የምዝገባ እና የመማሪያ ክፍያ አጠናቀን ትምህርት በመጀመር ሂደት ላይ እያለን ዩኒቨርሲቲው ሌሎች አማራጮችን መጠቀሚያ ጊዜ ባለፈብን በዚህ ወቅት አላስተምራችሁም ብሎናል " ሲሉ ተማሪዎሽ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድርሰዋል።
ቅሬታቸዉን ካደረሱን ተማሪዎች መካከል በመደበኛው የትምህርት ሚንስቴር ምደባ ጅግጅጋ ፣ሰላሌ እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ተመደብዉ እያለ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) በእረፍት ቀናት በክፍያ ለማስተማር ማስታወቂያ ማዉጣቱን ተከትሎ ከቤተሰብ ላለመራቅና በአንዳንድ አከባቢዎች ካለዉ የፀጥታ ችግር የተነሳ ከፍለዉ ለመማር በመወሰን የምዝገባና የትምህርት ክፍያ አጠናቀው የትምህርት መጀመርን ሲጠባበቁ እንደነበር ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲዉ " ኃላፊነት በጎደለው መልኩ 'ትምህርት ሚንስቴር በግል ከፍሎ መማርን ስላልፈቀደ ማስተማር የማንችል በመሆኑ ክፍያችሁን መዉሰድ ትችላላችሁ ' ብሎ የለጠፈዉ ማስታወቂያ እጅግ አሳዝኖናል " ብለዋል።
በተመደብንባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች መሄድ በማንችልበትና ሌሎችም በግል ኮሌጆች ከፍለን የመማሪያ ጊዜዉ ካለፈብን በኋላ የተወሰነዉ ይህ ዉሳኔ ከጊዜ እና ገንዘብ ጉልበት ብክነት ባሻገር በስነልቦናም ጉዳት አድርሶብናል ብለዋል።
ተማሪዎቹ ቅሬታቸዉን ለዩኒቨርሲቲዉና በግልባጭ ለትምህርት ሚንስቴርም ማቅረባቸውን ገልፀዉ የሚመለከተዉ አካል አስፈላጊውን መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌን አግኝቶ በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግሯል።
ዶክተር ቅሬታዉ እንደደረሳቸዉና ዩኒቨርሲቲዉ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገዉ ሁሉ " በሣምንቱ መጨረሻ ቀናት የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ለመስጠት ማስታወቂያ ማዉጣቱንና 400 የሚሆኑ ተማሪዎች ተመዝግበው ክፍያ ላጠናቀቁ ተማሪዎች ትምህርት የመጀመር ሂደት ላይ እያለን ትምህርት ሚንስቴር በሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረት ማስተማር ስለማንችል ማስታወቂያ ለጥፈናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ዩኒቨርቲዉ ለማስተማር ካለዉ ፍላጎት የተነሳ ተማሪዎችን መዝግቦ ወደ መማር ማስተማር ሂደት በመግባት ሂደት ላይ እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዘረዳንቱ የተማሪዎችንና የወላጆችን ቅሬታ ተከትሎ ጉዳዩን ወደ ትምህርት ሚንስቴር በማቅረብ ሂደት ላይ መሆናቸዉን ገልጸዋል።
" በሚንስትር መስሪያ ቤቱ ምላሽ ላይ ተመስርተን ' አስተምሩ ' የሚባል ተስፋ ሰጪ ጉዳዮች የሚገኙ ከሆነ ለተማሪዎቹ ጥሪ እናቀርባለን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።
ጉዳዩን ተከታትለን ተጨማሪ መረጃ የምናደርስ ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

" ከውጭ የሚመጣ ተሟጋች አያስፈልገንም !! " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሂጃብ ጉዳይ ምን አሉ ? " ከውጭ የሚመጣ ተሟጋች አያስፈልገንም። ጉዳዩ በራሳችን ነው የምንጨርሰው። ያለን አንድነት እና መፈቃቀር ሊነካ አይገባም። የአክሱም ህዝብም በዚህች ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዳለው ነው የማውቀው። አንዳንድ በክፋት የተሰማራ ካልሆነ፥ እያያችሁት…
" ታስረው ይቅረቡ " - ፍርድ ቤት
ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የቀረበውን ክስ ፍርድ ቤት ቀርበው መልስ እንዲሰጡ የተፃፈላቸውን ትእዛዝ " አንቀበልም " ያሉ አካላት ታስረው እንዲቀርቡ የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት አዘዘ።
ፍርድ ቤቱ ጥር 19/2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ ፤ ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ ክስ የቀረበባቸው 4 ርእሰ መምህራን የአክሱም ከተማ ፓሊስ አስሮ እንዲያቀርባቸው ፍርድ ቤቱ አዟል።
ፍርድ ቤቱ ታስረው እንዲቀርቡ ትእዛዝ ያወጣባቸው የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የአብርሃ ወ አፅብሃ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ የወርዒ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ የክንደያ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ርእሳነ መምህራን የካቲት 7/2017 ዓ.ም በአክሱም ከተማ ፓሊስ ተይዘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ይህ በእንዲህ እያለ ከሂጃብ ክልከላ ተያይዞ በአክሱም በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተነሳው ውዝግብ ቀጥሏል።
አንዳንድ መረጃዎች አሁንም 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከሂጃብ ክልከላ ጋር በተያያዘ ከሚድ ፈተና ውጪ እንዲሆኑ መደረጋቸውን እያመላከቱ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የሴት ሙስሊም ተማሪዎቹ ከፈተና መቅረት ልክ መሆኑ እና አለመሆኑ ለማጣራት ወደ ትምህርት ቤቶቹ ደውሎ ባገኘው መረጃ መሰረት " የቆየው የተማሪዎች የትምህርት ቤት የአለባበስ ደንብ በሚመለከተው አካል እስካልተቀየረ ድረስ ሂጃብ ለብሰው መግባት አይችሉም " ብለዋል።

" ' ብር (ጉቦ) ክፈሉና እንቀጥልላቹ ' ያለን የቴክኒክ ክፍል ሰራተኛ አለ " - ቅሬታ አቅራቢዎች
በአዲስ አበባ ከተማ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ በቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም ሳይት 3 የብሎክ 734 እና 735 ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በገቡት የቆጣሪ እዳ ውዝግብ ምክንያት ሃይል ከተቋረጠባቸው 1 ወር ከ 5 ቀን መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠቀሱት ብሎኮች ሃይል ያቋረጠው " በሦስት ቆጣሪዎች ያልተከፈለኝ ከ160 ሺ ብር በላይ እዳ አለ " በማለቱ ምክንያት ነው።
ቆጣሪዎቹ የተተከሉት ሳይቶቹ በግንባታ ላይ በነበሩበት ወቅት የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በገባው ውል ሲሆን ቆጣሪዎቹ የተመዘገቡት ደግሞ ከቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር ውል በገባው እና ግንባታዎቹን ባከናወነው የስራ ተቋራጭ (ኮንትራክተር) ስም ነው።
" ይህ በሆነበት ሁኔታ ቆጣሪዎቹን ባልተረከብንበት እና ከእነዚህም ቆጣሪዎች ሃይል ቀጥለን ባልተጠቀምንበት ሁኔታ እዳውን ክፈሉ ተብለናል " ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።
" የመኖሪያ መንደሩ በግንባታ ላይ በነበረበት ወቅት የስራ ተቋራጩ (ኮንትራክተሩ) የተጠቀማቸው እና ግንባታቸው ተጠናቆ ከገባን በኋላም እንዲነሱ ባልተደረጉ ቆጣሪዎች ምክንያት የቆጣሪዎቹን የተጠራቀመ የክፍያ እዳ ክፈሉ ተብለናል ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናችንም ምክንያት ላለፈው አንድ ወር በላይ ለሚሆን ጊዜ ሃይል ታቋርጦብናል" ነው ያሉት።
በሁለቱ ብሎኮች ከ60 በላይ ነዋሪዎች የሚገኙ ሲሆን አብዛኛዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኙ የልማት ሥራዎች ምክንያት የተነሱ እና ከሁለት ዓመት እስከ ሁለት ወር ለሚሆን ጊዜ ገብተው መኖር የጀመሩ ናቸው።
ነዋሪዎቹ ቅሬታቸውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና ለለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ያሳወቁ ሲሆን ጽ/ቤቶቹም ሃይል እንዲመለስላቸው የሚጠይቅ ደብዳቤ በተናጠል ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽፈዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው እና በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ኢ/ር በላይ ሞቱማ ተፈርሞ በ07/05/17 ዓም የወጣው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው ብሎኮቹን የገነባው ኮንትራክተር ቆጣሪዎቹን ከኮርፖሬሽኑ መረከቡን ከግንባታው በኋላም እነዚህን ቆጣሪዎች ከኮንትራክተሩ በመረከብ ለነዋሪዎች አለመተላለፉን እና አሁንም በኮንትራክተሩ የተመዘገበ መሆኑን ይገልጻል።
በዚህም ምክንያት ከቆጣሪው ጋር ተያይዞ የሚመጣ እዳ ሁሉ ኮንትራክተሩን እንጂ ነዋሪዎችን እንደማይመለከት በማስረዳት አስፈላጊውን ህጋዊ ድጋፍ ይደረግላቸው ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ጠይቋል።
የለሚኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በበኩሉ በ 09/05/17 ዓም በጻፈው ደብዳቤ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የጻፈውን ደብዳቤ በመጥቀስ ለነዋሪዎች የመብራት አገልግሎት እንዲያገኙ እንዲደርግ እንገልጻለን ብሏል።
ሁለቱም ጽ/ቤቶች በተናጠል በጻፉት ደብዳቤ ሃይል የተቋረጠባቸው ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ቢጠይቁም አገልግሎቱ ሃይሉን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ላለፉት አንድ ወር በላይ በጨለማ ለመቀመጥ መገደዳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ነዋሪዎች በዝርዝር ባቀረቡት ቅሬታ ምን አሉ ?
" የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተጠራቀመውን እዳ ኮንትራክተሩን ፈልጋቹ አስከፍሉ ወይም የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እዳውን እንዲከፍል አድርጉ እያለን ነው እነሱ በተዋዋሉት እኛ የምንጠየቀው ለምንድነው ?
መንገድ ላይ ያሉ ቆጣሪዎች እንዲነሱ ማህበረሰቡ ከአመት በፊት ጀምሮ አቤቱታ እያቀረበ ነው ያለው አልተሰማንም ቆጣሪዎቹ ሃይል አልተቋረጠባቸውም፣ አላነሳቸውም እኛ ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል አልቀጠልንም።
በዚህም ምክንያት ተዋውለን ለብሎካችን ያስገባነውን ስሪ ፌዝ ቆጣሪ ሃይል አቋረጡብን ለምን ? ስንል የዛኛውን ቆጣሪ እዳ ካልከፈላቹ ተባልን ባልገባነው ውል ባልተጠቀምንበት ሃይል ክፈሉ ተብለን ለምን እንገደዳለን ? እዳው የተመዘገበው በኮንትራክተሩ ነው እኛ ለምንድነው የምንከፍለው።
ምግብ ለማብሰል እንጨት እና ከሰል ነው እየተጠቀምን ያለነው ተማሪዎች አሉ የሚመገቡትን ትተን ፈተና የሚፈተኑበት ጊዜ እንደመሆኑ ያጥኑ እንኳን ቢባል በምን ? ለተጨማሪ እና አላስፈላጊ ለሆነ ወጪ ነው የተዳረግነው።
ፊዩዝ በተደጋጋሚ እያመጡ እየነቀሉ እያዋጣን መክፈል ሥራ ሆነብን ሲበዛብን ከወር በፊት ሊነቅል የመጣውን ሰራተኛ ለማስቆም ሞከርን ለምን ታስቆሙታላቹ በሚል አጠፉብን በዚህ ምክንያት እየተበቀሉን ነው እስካሁን መብራት የለንም።
እያዋጣን ጉቦ መክፈል ሰልችቶናል ' ብር ክፈሉና እንቀጥልላቹ ' ያለን የቴክኒክ ክፍል ሰራተኛ አለ ይሄንን እና ሌሎች ነገሮች ስላሳወቅንባቸው ሌሎች ተመሳሳይ የሆኑ ቆጣሪ ያለባቸው ሳይቶች ላይ እንደዚህ አይነት እርምጃ ሳይወሰድ እኛ ላይ የተደረገው ለብቀላ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፣የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጡት ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል።