TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ከተራ2017

የ2017 ዓ/ም የጥምቀት ከተራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በቤተክርስቲያኗ ሥርዓት እና ትውፊት ተከብሮ ውሏል።

ዛሬ ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ-ጥምቀት ገብተዋል።

በነገው ዕለት በመላው ሀገሪቱ የጥምቀት በዓል ይከበራል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ  ፦ #ሀማስ እና #እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው መነገሩን ተከትሎ ፍልስጤማውያን ደስታቸውን ለመግለፅ በጋዛ አደባባይ ወጥተዋል። " አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! " ይህ በስምምነቱ መረጃ የተደሰቱ ፍልስጤማውያን ድምፅ ነው። በርካቶች የሰላም ወሬ በመንፈሱ በደስታ አልቅሰዋል ፤ አንብተዋል ፤ ፈጣሪ ቀጣዩን ጊዜ ደግሞ የሰላም ያደርግላቸው ዘንድ ተማፅነዋል። ፍልስጤማውያን ስምምነቱን…
#Peace🏳

ጋዛ ተኩስ አቁም ነገ ተግባራዊ ይሆናል።

የተኩስ አቁሙ ነገ ተግባራዊ እንደሚሆን የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ነገ በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል ላይ የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋግጧል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ዛሬ ቅዳሜ የተኩስ አቁሙን አፅድቋል።

ተኩስ አቁሙ ስራ ላይ ሲውል 1,904 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤቶች እንደሚለቀቁ የእስራኤል መንግሥት አሳውቋል።

ሀማስ ደግሞ ከ98 እስራኤላውያን ታጋቾች መካከል 33ቱን ለ6 ሳምንታት በሚዘልቀው የተኩስ አቁም ወቅት ይለቃል።

ግብፅ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ለመላክ እየተዘጋጀች ነው።

በሌላ በኩል ግን ሀማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ከተገለጸ በኃላ 122 ፍልስጤማውያን በእስራኤል መገደላቸውን የጋዛ የሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ኤጀንሲ ገልጿል።

እስካሁን በ15 ወራት ጦርነት የተገደሉት ፍልስጤማውያን ቁጥር 46,899 ደርሷል። 110,725 ሰዎች ታጎድተዋል።

መረጃው ከዶቼ ቨለ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
" በተራሮቹ ላይ የተከሰተው እሳት ከመስፋፋቱና ከፍተኛ ችግር ከማስከተሉ በፊት ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ እና አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን " - ወረዳው

በኦሮሚያ ክልል፣ በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ " ጎቱ ኦኖማ " በተባለው አከባቢ ከሰዓት 10 ሰዓት አከባቢ በተራሮች ላይ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

የእሳቱ መከሰት መንስዔው በድርቅ ምክንያት የተከሰተ ነው ያለው ቢሮው የተከሰተውን ቃጠሎ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ለማጥፋት እየተሞከረ ነው ሲል አስታውቋል።

ሆኖሞ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያው በ 'እሳተ ገሞራ' የተከሰተ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል ገልጿል።

በተራሮቹ ላይ የተከሰተው እሳት ከመስፋፋቱ እና ከፍተኛ ችግር ከማስከተሉ በፊት ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግም ቢሮው ባወጣው መረጃ ጠይቋል።

Via @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update : ቲክቶክ በመጪው እሁድ በአሜሪካ አገልግሎቱን እንደሚያቆም አስታውቋል። ቲክቶክ የተጣለበት እገዳ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት መንግሥት ጣልቃ ካልገባ በስተቀር ከመጪው እሁድ ጀምሮ መተግበሪያውን በአሜሪካ ለማቆም እንደሚገደድ ገልጿል። ኩባንያው በሰጠው መግለጫ ዋይት ሃውስ እና የፍትህ ዲፓርትመንት " ቲክቶክ በቀጣይነት እንዲቀጥል ለማህበራዊ ሚዲያው መሰረታዊ የሚባሉ ግልጽነት እና ማረጋገጫ መስጠት…
አሜሪካ ቲክቶክን ዘጋች።

' ቲክቶክ ' የተባለው የአጫጭር ቪድዮ ማጋሪያ እስከ ዛሬ እሁድ ድረስ እንዲሸጥ ካልሆነ ግን እንዲታገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል።

በዚህም ቲክቶክ በመላ አሜሪካ ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ እንዳይሰራ ተደርጓል።

መተግበሪያው ገና እግዱ ተግባራዊ የሚሆንበት ሰዓት ሳይደርስ ቀደም ብሎ (ከሰዓታት በፊት) ነው የዘጋው።

በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ስክሪን ላይ ፥ " ቲክቶክን ለማገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል በዚህም አሁን ቲክቶክን መጠቀም አይችሉም " የሚል ፅሁፍ ነው የሚታየው።

ቲክቶክ ትራምፕ ስልጣናቸውን ተረክበው ወደ ቢሮ ሲገቡ መፍትሄ ለማበጀት አብረዋቸው እንደሚሰሩ እንደጠቆሟቸው በማመልከትም እስከዚያው ድረስ ተገልጋዮቹ እንዲጠባበቁት ጠይቋል።

ትራምፕ ቲክቶክ መተግበሪያ ካልተሸጠ እንዲታገድ የሚለው ህግ እንዲዘገይ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ከመታገድ ሊያድነቱ አልቻሉም።

ፕሬዜዳንታዊ ስልጣናቸውን ሲረከቡ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ? የሚለው በቀጣይ ይታያል።

ቲክቶክ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ነበሩት።

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ! በዓሉ በደስትና በረከት የተሞላ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

መልካም የጥምቀት በዓል !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

የ2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና መንፈሳዊ ስነ-ስርአቶች እየተከበረ ይገኛል።

ዛሬ ጥዋት የእምነቱ ተከታዮች በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ በዓለ ጥምቀቱን በማህሌት ፣ በቅዳሴ፣ በመንፈሳዊ መዝሙሮች እና በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብረዋል።

በተለይም በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ በተገኙበት ልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተከብሯል።

ፎቶ፦ Pax Catholic TV

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ ፤ በሀገሪቱ በሚገኙ የጥምቀተ ባህር ስፍራዎች ቀሳውስት እና ሊቃውንት ለምዕመናን ትምሕርት ሰጥተው፣ ጸሎት ተደርጎና ጥምቀተ ባሕሩ ተባርኮ ሥርዓተ ጥምቀቱ ተካሂዷል።

አሁን ላይ ዛሬ የሚገቡ ታቦታትን የማስገባት ስነስርዓት ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ፎቶዎቹ ከተለያዩ የማህበራዊ ገጾች የተሰበሰቡ ናቸው።

@tikvahethiopia