TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
🎁 ጥምቀት የሞባይል ጥቅል!!

እስከ 20% በሚደርስ ቅናሽ ያቀረብናቸውን ልዩ የበዓል ጥቅሎች በ*999#፣ በማይ ኢትዮቴል እና አርዲ ቻትቦት ይግዙ!

👉 ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ሲገዙ 20% ቅናሽ ከተጨማሪ 20% ስጦታ ጋር ያገኛሉ!

🗓 ከነገ ጥር 10 – 13/2017 ዓ.ም   

መልካም የጥምቀት በዓል!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
ሕብር ሙዳይ የቁጠባ ሒሳብ

ሙዳይ ተቀማጭ ሒሳብ በአነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች የሚከፍቱት የቁጠባ ሒሳብ ሲሆን፤ አገልግሎቱ የቁጠባ ባህልን ለማዳበር አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቆጣቢዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ በመሆኑ ደንበኞችን ለማበረታታት በነፃ የገንዘብ ቁጠባ ሣጥኖች የሚሰጥበት የቁጠባ ሒሳብ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች  እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://yangx.top/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡
የፋሲል ግንብ እድሳት እንዴት ተካሄደ ? የመንጣቱስ ምክንያት ምንድን ነው ?

በአስደናቂነቱ ፣ በታሪካዊነቱና በኪነ ህንጻ ጥበቡ ብዙ የተባለለት እና እና በአራት አስርት ዓመታት በፊት በዩኔስኮ የዓለማችን ቅርስ አንዱ ሆኖ የተመዘገበው የፋሲል ግንብ ተሰነጣጥቆ እና አርጅቶ መቆየቱ በርካቶች ሲያነሱት የነበረ ጉዳይ ነው።

በእርጅናም የህልውና ስጋት እንደገጠመውም ሲነገር ነበር።

የጥገና እድሳት እየተከናወለት ያለው ታሪካዊው የፋሲል ግንብ በቅርቡ ይፋ ተደርጓል።

ታሪካዊው ሽሯሟ ቀለም ያለው የፋሲል ግንብ ቀለሙ ነጥቶ መታየቱ ለበርካታ መላምት ክፍት እንዲሆን አድርጎታል።

የታሪካዊው ግንብ ቀለም ለዘመናት ከሚታወቅበት ተለውጦ ለምን ነጣ ? የሚል ጥያቄ እንዲነሳም ምክንያት ሆኗል።

አንዳንዶች " ቅርሱ በአግባቡ አልታደሰም፤ የታወቅበትን ታሪካዊነቱንና ቀለሙንም እንዲያጣ  ተደርጓል " ብለዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ በጥገና እድሳቱ በአማካሪነት እንዲሁም በጥናት የተሳተፉት አንጋፋው አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ ምን አሉ ?

" የፋሲል ግንብ ህንጻ ሲገነባ በአነስተኛ ድንጋዮች እና በኖራ ሲሆን፣ ለረጅም ዓመታት ዝናብ፣ በፀሐይ እና በተፈጥሯዊ ሂደቶች ውስጥ ሲያልፍ በርካቶች የሚያውቁትን ይሄንን ' ሽሯማ ' መልክ አምጥቷል።

አሁን እድሳቱ የተደረገበት ኖራ አዲስ በመሆኑ ቀለሙ ነጣ ብሏል።

የእድሳት ሥራው የተከናወነው የፋሲል ግንብ በመጀመሪያ በተገነባበት ማቴሪያል (ቁስ) በዋናነት በኖራ እና በድንጋይ ነው።

የቅርስ አጠባበቅ ሕግን በተከተለ መልክ ነው የተሠራው።

የኖራው አዲስ መሆን ብቻ ይሄንን ነጣ ያለ ቀለም አምጥቷል። የኖራ እና የድንጋይ መልኩ ከተወሰነ ዓመታት በኋላ ወደ ድሮው መልኩ ይመለሳል።

ልዩነቱ አዲስ የመሆን እና የማርጀት ጉዳይ ነው።

የፋሲል ግንብ መጀመሪያ ሲሠራ ኖራው ለብዙ ወራት ወይም ለዓመታት ተቀብሮ የነበረ ነው አሁንም ሲታደስ መነሻውን ተከትሎ ኖራው ለበርካታ ጊዜያት እንዲቀበር ተደርጎ ጥገናው ተካሂዷል።

ቅርሶች በተፈጥሮ፣ በፀሐይ፣ በዝናብ፣ በአቧራ ምክንያት በዓመታት ቀለማቸው እየተቀየረ የሚሄድ ነው ፤ ይሄኛውም ከዓመታት በኋላ የሚታወቀውን ቀለም ይይዛል።

በዓለም አቀፉ የቅርስ ጥገና ሕግ መሠረት ዋነኛው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በተሠራበት ቁስ (ማቴሪያል) ታድሷል ወይ ? የሚለው ነው በተሠራበት ድንጋይ እና ኖራ መልሶ መጠገኑ ዋናው ነገር ነው።

ይህንንም በትክክል መሥራቱን አረጋግጠናል።

በአንዳንድ ሁኔታዎች የድሮ ቀለሙን ለማምጣት ለመልክ ሲባል ኬሚካል ይቀላቀላ እነዚህ ግን ኬሚካል ነክ ነገሮች ስለሆኑ ያልታሰበ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ቀለሙ እንደ ድሮው ቢመስል እንወድ ነበር፤ ሆኖም ለቀለም ተብለው የሚጨመሩ ነገሮች ያልታሰበ አደጋን በቅርስ ላይ ያመጣሉ።

በዓለም የቅርስ አጠባበቅ ደረጃ ዋነኛው ነገር ቅድሚያ የሚሰጠው የመነሻ ሃሳቡ ነው። ኖራው ትክክለኛ እና አስተማማኝ በመሆኑ የጥንቱ እንደያዘ የጥገና እድሳቱ እየተከናወነ ነው።

መነሻውን ሳይለቅ ጥርሳችንን ነክሰን የሠራንበት ነው።

የቀደመ መልኩ በጊዜ ብዛት ይመጣል የነበረው ገጽታ በጊዜ ሂደት ይመለሳል።

በሽሯሟ መልኩ የሚታወቀው የፋሲል ግንብ መቼ ተመልሶ ይመጣ ይሆን ? የሚለው ዝናብ ሲመታው እና የአየር ሁኔታዎች ሲፈራረቁበት እየተቀየረ ይሄዳል።

ህንጻው ወደ ቀደመ ቀለሙ ለመመለስም ከሦስት እስከ አራት ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ሊወስድ ይችላል።

አንዳንድ ቦታ ላይ በጣም የጠቋቆሩ የግንቡ አናት ላይ አካላት ነበሩ። ድንጋዮቹ ወደ ነበሩበት ለመመለስ እስከ አምስት ዓመት ድረስ የሚደርስ ወይም የግንቡ አናት ላይ ያሉትን ጠቆር ያሉትን የቀደመ ገጽታ ለማምጣት ከዚያ ረዘም ያለ ጊዜ ይወስዳል " ብለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
🔈 #የጤናባለሞያዎችድምጽ

🔴 " እስከሚከፈለን ድረስ ወደ ሥራ ላለመመለስ ተስማምተናል ለሁሉም ባለሞያ እስከሚከፈል ድረስ አንሰራም " - የጤና ባለሞያዎች

🔵 " ዝም ያለ አካል የለም ዘግቶ መሄዳቸው ትክክል አይደለም " - የጤና ቢሮ ሃላፊ

በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ በዘጠኝ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች የትርፍ ሰዓት ስራ(ዲዩቲ) ክፍያ ስላልተከፈላቸው 05/05/17 ዓ/ም ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የጤና ባለሞያዎች ተናግረዋል።

ባለሞያዎቹ ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በተለያዩ ጊዜያት ያልተከፈላቸው የ1 አመት ከ 5 ወር በላይ የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ መኖሩን ተናግረዋል።

እስከ ክልሉ የበላይ አካላት ድረስ ሄደን ጠይቀናል በተደጋጋሚ የሚሰጠን ምላሽ ግን " ታገሱ " የሚል ነው በዚህ ምክንያት ተነጋግረን ስራ ለማቆም ተገደናል ነው ያሉት።

" አብዛኛው ባለሞያ ከወረዳው ሸሽቶ ወደተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ ተደብቆ ነው ያለው አመራሮችም በአንቡላንስ ቤት ለቤት በመሄድ የህክምና ባለሞያዎችን እያፈለጉ እያስፈራሩ ነው " ብለዋል።

ባለሞያዎቹ " በተለያዩ ጊዜያት ከወረዳ እና ከዞን አመራሮች ጋር በርካታ ውይይቶችን አድርገናል ነገር ግን ' ግብር እስከሚሰበሰብ ጠብቁ፣ ገንዘብ የለም ታገሱ ' ከማለት የዘለለ እስካሁን ምንም ምልሻ ባለመግኘታችን እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ተገደናል ነው " ያሉት።

" እስከሚከፈል ድረስ ወደ ሥራ ላለመመለስ ተስማምተናል ለሁሉም ባለሞያ እስከሚከፈል ድረስ አንሰራም የተጠራቀመ ክፍያው እስከ 100 ሺ የደረሰለት ባለሞያም አለ " ብለዋል።

" በዚህ ደመወዝ ፣በዚህ ኑሮ ውድነት መኖር አልቻልንም የመጨረሻ ደረጃ ላይ ነው የደረስነው ልጆች ያላቸው ልጆቻቸውን ማሳደግ አልቻሉም መስራትም መኖርም አልቻልንም ይሄንን እርምጃ ስንወስድም ወደ ፖለቲካ ተቀይሮ ' ትታሰራላቹ ' ወደ ሚል ማስፈራሪያ ተሸጋግረዋል " ሲሉ አክለዋል።

ባለሞያዎቹ በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ጤና ጣቢያዎች አድማው ቢቀጥልም ለወሊድ ለሚመጡ እናቶች ብቻ አንዳንድ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ነገር ግን በሁሉም ጤና ጣቢያዎች መደበኛ ስራዎች ማቆማቸውን ተናግረዋል።

የአዳባ ወረዳ የጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሽመልስ ፈይሳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የባለሞያዎቹ የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ አለመከፈሉን አረጋግጠዋል።

ሃላፊው በዝርዝር ምን አሉ ?

" በየደረጃ ያሉ ቢሮዎችን እየጠየቁ መምጣት ይችሉ ነበር እኔ የቢሮ ሃላፊ ነኝ ወደ እኔ የመጣ የለም ስራቸውን ነው ዝም ብለው ያቆሙት።

የኑሮ ውድነት በሃገሪቱ እና በአለም ያለ ሁኔታ ነው የትርፍ ሰዓት ስራ ባይሰሩም በመደበኛ ስራቸው መገኘት ነበረባቸው የሙያ ስነምግባሩ ይህንን አይፈቅድም።

የገቢ ማነስ ይኖራል፣ የጸጥታ ችግርም ሊኖር ይችላል በእነዚህ ምክንያቶች ነው እንጂ ዝም ያለ አካል የለም ዘግቶ መሄዳቸው ትክክል አይደለም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለሞያዎቹ የጠየቁት ከአመት በላይ ሳይከፈላቸው ስለቀረ ክፍያ ነው ችግሩ በምን ያህል ጊዜ ይፈታል ብለን እንጠብቅ ሲል ጠይቀናቸዋል ? በምላሻቸው ፦

" ከእዚህ በፊት ጥያቄውን ለበላይ አካል አቅርበው ጉዳዩ ወደ ወረዳ እንዲመለስ ተደርጎ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፈታል ተብሎ ነበር ለዚህ እንቅስቃሴ እያደረግን ባለበት ሰዓት ነው ይሄ የተፈጠረው ገቢ ላይ የተመሰረት አከፋፈል ነው የሚኖረው ከስር ከስር እየተከፈለ በጊዜ ሂደት ችግራቸው ይፈታል " ብለዋል።

የቦርድ አባላት በየጤና ጣቢያው በመሄድ ሰራተኛው መጥቶ የራሱን ቅሬታ እንዲያቀርብ ጠይቀው እስካሁን መጥቶ ያቀረበ አካል የለም እኛም መፍትሄ ለመስጠት ተቸግረናል ብለዋል።

ሃላፊው ባለው ሰራተኛ ስራው እንዲቀጥል ለማድረግ እየጣርን ነው ያሉ ሲሆን " የሰራተኛው ችግር ምን እንደሆነ በቢሮ ደረጃ አናውቅም መጥቶ ያቀረበልን አካልም የለም " ነው ያሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወረዳው የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ከክፍያ ጋር ተያይዞ የሚያነሱትን ጥያቄ ለመቅረፍ ወረዳው ምን ያህል ብር ይፈልጋል ሲል ጠይቋል።

ሃላፊው " የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን በየጊዜው ስለሚጨምር ይሄን ያህል ነው ማለት ያስቸግራል ነገር ግን በ 2016 ዓም ብቻ ያልተከፈላቸውን ክፍያ ለመፈጸም እስከ 5 ሚሊየን ብር ያስፈልጋል " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ከትላንት ጀምሮ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ምዝገባው እስከ ጥር 14/2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ታውቋል።

ከተጠቀሰው ቀን ውጭ ምዝገባ ማድረግ አይቻልም።

ምዝገባው በ
https://exam.ethernet.edu.et ላይ የሚካሄድ ሲሆን ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ በቀጣይ ይፋ ይደረጋል።

የመፈተኛ User Name እንዲሁም Password በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም እንዳለበት ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ማንኛውም አይነት ጥያቄ ዘውትር በሥራ ሰዓት በኢሜል
[email protected] በስልክ ቁጥር 0911824528 / 0913678404 / 0913949676 / 0910076453 / 0923106826 / 0913866717 / 0911335683 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ተብሏል።

Via
@tikvahuniversity
#AddisAbaba #እንድታውቁት

የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።

ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት መንገዶች ይዘጋሉ።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

➡️ ከ6 ኪሎ አደባባይ - ምኒልክ ሆስፒታል
➡️ ከምኒልክ ሆስፒታል - መከላከያ 3ኛ ሻለቃ አደባባይ
➡️ ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ - 6 ኪሎ አደባባይ እንዲሁም አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ
➡️ ከዋልያ ቢራ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
➡️ ከአቃቂ ዋናው መንገድ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
➡️ ከ08 - አቃቂ ድልድይ ድረስ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናሉ።

በተጨማሪ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በ11ዱም ክ/ከተሞች ጥምቀተ ባህር ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ በ500 ሜትር  ክልል ውስጥ ታቦታት ሲወጡና ሲገቡ እንዲሁም በሚሄዱባቸው መንገዶች ለአጭር ጊዜም ይሁን ለረዥም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
⚠️ የፀጥታ ኃይል ዩኒፎርም በአግባቡ የለበሰና መሳሪያ በአግባቡ የታጠቀ ሰው እጁ ወደኃላ የፊጥኝ የታሰረ ወጣትን አንገላቶ ሲተኩስበት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ቪድዮ በማህበራዊ ሚዲያው ተሰራጭቷል።

ለጊዜው ቪድዮ የት ፣ መቼ እንደሆነ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ለማየት የሚከብድ ጭካኔ መፈጸሙን ያመላክታል።

ቪድዮው ላይ 5 የፀጥታ ኃይል ልብስ በአግባቡና በስርዓት የለበሱ ሰዎች ይታያሉ።

ከነዛም አንዱ መሳሪያውን እንደታጠቀ አንድን የፊጢኝ ወደ ኃላ የታሰረ ወጣት አንገላቶት ሲያበቃ ከጀርባው ጭንቅላቱ ላይ ሲተኩስበት ይታያል።

በቪድዮው ላይ እንደማታየውም ይህ ድርጊት ሰዎች በተሰበሰቡበት ፊታቸው ላይ የተፈጸመ ነው።

ስለ ቪድዮውም ሆነ ስለ ድርጊቱ በይፋ ወጥቶ የተናገረና ያብራራ አካል እስካሁን ብቅ አላለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ድርጊቱን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ለማነጋገር ይጥራል።

ባለፉት ጊዜያት መሰል የጭካኔ ተግባራት በሀገራችን አንድም በፀጥታ አካላት፣ በታጣቂ ኃይሎች እንዲሁም ደግሞ ሲቪል በለበሱ አካላት ሲፈጸም ታይቷል።

ሰው በቁሙ ሲቃጠል፣ ተዘቅዝቆ ሲሰቀል፣ ገደል አፋፍ ላይ ተረሽኖ ወደ ገደል ሲከተት፣ በድንጋይ ተወግሮ ሲገደል ... ብዙ ብዙ ለማየት የሚከብዱ ድርጊቶች ተፈጽመው በቪድዮ ማስረጃ ጭምር ታይተዋል።

" በቪድዮ ያልተቀረፀ ስንት ጭካኔና ግፍ ይኖር ይሆን ? " የሚሉ ጥያቄዎችን ያስነሱ በርካታ ተግባራት ባለፉት ዓመታት ተመዝግበው ተቀምጠዋል ፤ የአሁኑ ቪድዮ ጉዳይ ምንድነው ? የተገደለው ወጣትስ ማነው ? የት ነው ? መቼ ነው ? የሚለውን የተደረሰበትን እና ያገኘነውን መረጃ እንለዋወጣለን።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#TikTok ' ቲክቶክ ' የተሰኘው መተግበሪያ አልባኒያ ውስጥ ለአንድ አመት እንደሚታገድ መገለጹ ይታወሳል። " እገዳው በኦንላይ የንግድ ስራ የሚሰሩ / ማርኬቲንግ ላይ ያሉ እንዲሁም የንግግርና ሃሳብ ነጻነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያመጣል " በሚል የመብት ተሟጋች ነን በሚሉ አካላት እገዳው ቢተችም የሀገሪቱ መንግሥት እገዳውን ተግባራዊ ያደርጋል ተብሏል። ቲክቶክ በቀጣይ ሳምንታት ይወርዳል ተብሏል። …
#TikTok📱

' ቲክቶክ ' አሜሪካ ውስጥ ከእሁድ ጀምሮ እስከ ወዲያኛው እንዲዘጋ ወይም እንዲሸጥ የሚለውን ውሳኔ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደገፈ።

ዛሬ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ' ቲክቶክ ' በአሜሪካ እንዲዘጋ ካልሆነም እዲሸጥ ለሚጠይቀው የፌደራል ህግ ድጋፍ ሰጥቷል።

' ቲክቶክ ' ይግባኝ ቢጠይቅም ውድቅ ሆናል።

ከዚህ ቀደም መተግበሪያው " የአሜሪካውያንን የግል መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፎ ይሰጣል በዚህ የብሔራዊ ጸጥታ አደጋ ደቅኗል "  በሚል እንዲታገድ ካልሆነም ለአሜሪካ ሰዎች እንዲሸጥ የሚል ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል።

ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም የተላለፈውን ውሳኔ ደግፏል።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ ' ቲክቶክ ' ከእሁድ ጀምሮ ይታገዳል።

የእግዱ ተግባራዊነት ' ቲክቶክ 'ን ከአፕስቶር እና ፕሌይስቶር ላይ እንዲወገድ ያደርጋል።

አዲስ ተጠቃሚዎች ' ቲክቶክ ' ማውረድ አይችሉም ፤ ነባር ተጠቃሚዎች አፕዴት ማድረግ አይችሉም።

ተመራጩ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ' ቲክቶክ ' ን ለመታደግ እና የመታገዱ ውሳኔ እንዲዘገይ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን የመጨረሻ ያለውን ውሳኔ አሳልፏል።

እንሆ ስልጣኑ ያበቃው የባይደን አስተዳደር " ህጉን ማስተግበር የቀጣዩ አስተዳደር ኃላፊነት ነው " ብሏል።

የ' ቲክቶክ ' ን እገዳ ለማዘግየት የሞከሩት ትራምፕ ሰኞ ስልጣናቸውን ይረከባሉ። ህጉን ማስተግበርም በሳቸው ላይ ተጥሏል።

ትራምፕ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኃላ በሰጡት ቃል " ውሳኔውን እኔው ወስናለሁ ፤ ውሳኔው እኔ ጋር ነው ምን እንደማደርግ ታያላችሁ " ብለዋል።

170 ሚሊዮን ተጠቃሚ አሜሪካ ውስጥ ያለው ' ቲክቶክ ' እስከወዲያኛው ይታገድ ይሆን ? ወይስ ከዚህ በኃላ ትራምፕ ማድረግ የሚችሉት ነገር ይኖር ይሆን ? በቀጣይ ይታያል።

መረጃው ከኤፒ፣ ፎርብስ፣ ሲኤንኤን የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል። ምርጫ ቦርድ ፤ ህወሓት በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር መሠረት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን አስታውሷል። ፖርቲው ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ…
#TPLF

" የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔን ዛሬ ይሁን ነገ አልቀበልም " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ

በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ከጥር 5 እስከ ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ አተኩሮ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።

ይህንን ተከትሎ ዛሬ ምሽት መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም ቡድኑ ፦
- እስከ አሁን ያልተረጋገጠው የትግራይ ግዛታዊ አንድነት፤
- ተፈናቃዮች እና ስደተኞች ወደ ቄያቸው አለመመለስ፤
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያወጣውን መግለጫ፤
- የፕሪቶሪያ የሰላም ውል አፈፃፀም በሚሉ አጀንዳዎች ላይ መወያየቱን ገልጾ " ቀጣይ የመፍትሄ እና የትግል አቅጣጫ አስቀምጫለሁ " ብሏል።

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ፤ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት እውቅና የሰጠው የትግራይ ግዛታዊ አንድነት አለመረጋገጡ ጠቅሶ " ተፈናቃይ እና ስደተኞች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው ሃዘን እና ቁጣ ተስምተኞናል ይህንን አስመልክቶ ' ይበቃል ' በሚል የተካሄደው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እደግፋለሁ " ብሏል።

ቡድኑ በመግለጫው " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በአግባቡ እንዳይፈፀም የኢትዮጵያ መንግስት እንቅፋት እየሆነ ነው ፡ በትግራይ ውስጥ የበቀለ
#ከሃዲ_ሃይልም በተጨማሪ ስምምነቱ እያደናቀፈ ነው " የሚል ክስ አሰምቷል።

እንዴት እንደሆነ ባያብራራም " ችግሩ ከስር መሰረቱ ለመለወጥ ቆርጬ ተነስቻለሁ " ብሏል።

በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ DDR ተቀባይነት ያለው እንደሆነ የገለፀም ሲሆን " ይሁን እንጂ DDR እንደምክንያት በመጠቀም የትግራይ ሰራዊት ለማፍረስ እየተደረገ ያለው ሴራ ተቀባይነተ የለውም " ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ህወሓት ህጋዊ ጉባኤ እንዲያካሂድ በማስመልከት በቅርቡ ያወጣው ቀን ገደብ ያካተተ መግለጫ አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ ፥ " ቦርዱ ' ጉባኤ አካሂዱ ' የሚል ጨምሮ በተንኮል የተተበተቡ የተለያዩ  ትእዛዞች ከመስጠት ተቆጥቦ የተፈጠሩ ልዩነቶች  በፓለቲካዊ ውይይት ለመፍታት የተጀመረው ጥረት በማስቀጠሉ ላይ ያተኩር "  ብሏል።

" ህወሓት ሁሌም ለሁለትዮሽ ውይይት ዝግጁ ነው ፤ የትግራይ ህዝብ ትግል እና መስዋእትነት የሚያራክስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔ ግን ዛሬ ይሁን ነገ አልቀበልም " ሲል አቋሙን አንጸባርቋል።

ህወሓት ጊዚያዊ አስተዳደሩ በማቋቋም የአንበሳ ድርሻ እንደነበረው እና እንዳለው የጠቀሰው መግለጫው " አሁንም እንዲጠናከር ይሰራል ይሁን እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማጠናከር እና ለመቆጣጠር በሚል ይቋቋማል የሚባለው ካውንስል አካል መሆን አልፈግም " ሲል ግልፅ አድርጓል።

በሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በመግለጫው ማጠቃለያ ፤ " የኢትዮጵያ መንግስት ከጣልቃ ገብነት ተቆጥቦ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በቅን ልቦና በመፈፀም ለዘላቂ ሰላም እንዲሰራ " የሚል ጥሪ አቅርበዋል። 

የህወሓት ቡድን ለሁለት ተከፍሎ የለየለት አለመግባባት ውስጥ ከገባ ወራት የተቆጠሩ ሲሆን ከወራት በፊት ለሁለት የተከፈሉት አመራሮች እና የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች አዲስ አበባ ሄደው ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት አድርገው ነበር።

ወደ መቐለ ከተመለሱ በኃላ ግን እስከ ዛሬ መግባባት ሳይፈጥሩ በመግላጫ ምልልስ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደግሞ ህወሓት በልዩ ሁኔታ የተመዘገበው ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን በመግለጽ ጠቅላላ ጉባኤውን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ አሳስቧል።

ይህ በሕግ ፓርቲው ላይ የተጣለ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጾ ነበር።

ከዚህ ቀደም የህወሓት አመራሮችን ለሁለት የከፈለ ጉባኤ መደረጉ አይዘነጋም። በወቅቱም ምርጫ ቦርድ ያልተገኘበትን እና ስርዓቱን ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እውቅና እንደማይሰጥ ማስገንዘቡ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia