TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
" የሟሟቱ ሁኔታ በሚመለከታቸው አካላት እየተጣራ ይገኛል " - አክሱም ዩኒቨርሲቲ

በአክሱም ዩኒቨርስቲ የሽረ ካምፓስ ተማሪ ህይወቱ እንዳለፈ ዩኒቨርስቲው አስታወቀ።

" ተማሪያችን ካሕሱ ሃይሉ በእፅዋት ሳይንስ የትምህርት ክፍል የአንደኛ ዲግሪ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ነበር ብሏል " ዩኒቨርስቲው።

ዩኒቨርሲቲው የተማሪው ሕይወት ያለፈው ከካምፓስ ውጪ ሌሊት ባጋጠመ ድንገተኛ ግጭት እንደሆነ ጠቁሟል።

ግጭቱ በምን ምክንያት እንደነበረ ፣ ከምን ጋር እንደሆነ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

የተማሪ ካሕሱ ሃይሉ ሃደራ የሟሟት ሁኔታ በሚመለከታቸው አካላት እየተጣራ ይገኛል ያለው ተቋሙ ውጤቱ በሚመለከታቸው አካላት ይፋ እንደሚደረግ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሲጠበቁ የነበሩ ሁለት መመሪያዎች ፍትህ ሚኒስቴር ማጽደቁ ተሰምቷል። መመሪያዎቹ " የሰነደ ሙዓለ ነዋይን ለህዝብ የማቅረብ ግብይት መመሪያ " እና "ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ ድርጅቶች ቁጥጥር መመሪያ  "  ናቸው። ሁለቱን መመሪያዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  በትላንትናው ዕለት መዝግቦ አጽድቋቸዋል። የሰነደ ሙዓለ ነዋይን ለህዝብ የማቅረብ ግብይት መመሪያን በሚመለከት የኢትዮጵያ…
በኢትዮጵያ በይፋ የአክሲዮን ግብይት ተጀመረ።

የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዛሬ ዓርብ የአክሲዮን ሽያጭና ግዢ ግብይቱን በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።

የአክሲዮን ገበያ ሥራውን በይፋ ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ " በጉጉት ሲጠበቅ የቆየው የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ግብይት በዛሬው ዕለት ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም የመጀመሪያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደወል ደውለናል " ብለዋል።

የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያው ዋና ዳይሬክተር ጥላሁን ካሳሁን በቀጣዮቹ ዓመታት ውስጥ 50 ያህል ኩባንያዎች በዚህ ገበያ ላይ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለግብይት እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።

በተለምዶ ክፍት ገበያ በመባል የሚታወቀው የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ የተማከለ የፋይናንሺያል ገበያን የሚያመለክት ሲሆን የተዘረዘሩ ኩባንያዎችን የዋስትና ሰነዶች፣ኮሞዲቲዎች ጨምሮ በአክሲዮን ሻጮች እና ገዥዎች መካከል የሚገዙበት እና የሚሸጡበት ማዕከል መሆኑ ይታወቃል።

የመረጃው ባለቤት ካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
" ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን " - ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ።

ቅዱስነታቸው ፤ በሀገራችን በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

" ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ አባታዊ ጥሪ በድጋሚ እናስተላልፋለን " ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ፤ በትግራይ ክልል ያለው የአስተዳዳሪዎች አለመግባባት በሕዝቡ ላይ ተጨማሪ ችግርና ጭንቀት እያመጣ መሆኑን ጠቁመዋል።

" በትሕትና መንፈስ እርስ በርስ መገናዘብ ተፈጥሮ ዕረፍት ያጣው ሕዝብ መረጋጋት እንዲችል ታደርጉ ዘንድ አደራችን የጠበቀ ነው " ብለዋል።

በተጨማሪም ቅዱስነታቸው በትግራይ ክልል ስለሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ጉዳይ በአባታዊ የሰላም ጥሪ መልዕክታቸው አንስተዋል።

" መበደላችሁን እናውቃለን ፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው " ያሉት ቅዱስነታቸው " ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን እኛ የገፋነውን እርቅ ዓለም ሊቀበለው ስለማይችል፤ በእጃችንም የያዝነው መስቀለ ክርስቶስ የሰላም ዓርማ ነውና ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ቅዱስነታቸው በመሬት መንቀጥቀጥ እየተጨነቁ ላሉ እና ስለተጎዱ ልጆቻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

" የመሬት መንቀጥቀጥ ባለበት አካባቢ እየተጨነቃችሁ ያላችሁ ልጆቻችን ረድኤተ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን በጸሎት የምታስባችሁ መሆኑን እየገለጽን መላው ኢትዮጵያውያን ለጉዳቱ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ለሚኖሩት ወገኖቻቸው አቅማቸው በፈቀደው መጠን ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን " ብለዋል።

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
" በአዲስ አበባ ከተማ ' ቃሊቲ አካባቢ ' ባለ ሰፊ መጋዝን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች ይገኛሉ " - ኢሰመኮ

በጎዳና ላይ ያሉ ሰዎችን ያለፈቃዳቸው መያዝ እና ወደ ማቆያ ማእከላት ማስገባት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ስለሚያስከትል ሊቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።

ኮሚሽኑ " ከጎዳና ላይ ለሚነሱና ወደማቆያ ለሚገቡ ሰዎች ሰብአዊ መብቶችን ያማከለ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል "ም  ብሏል።

ኢሰመኮ ዛሬ በላከልን መግለጫ ፥ በሚያዝያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በጎዳና ላይ ያሉ ሕፃናት በጅምላ ተይዘው የሚቆዩበትን ሁኔታ በተመለከተ እንዲሁም መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ሲዳ አዋሽ ወረዳ በሚገኘው ማቆያ ማእከል ተይዘው የነበሩ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ያደረጉ ሰዎችን (በተለምዶ አጠራር ‘‘ ጎዳና ተዳዳሪዎች ’’ ተብለው የሚታወቁ) ሁኔታ አስመልክቶ ክትትል በማድረግ የተለዩ ክፍተቶችንና ምክረ ሐሳቦችን የያዘ መግለጫ ማውጣቱ አስታውሷል።

በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. ባደረጋቸው ክትትሎች ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ “ ቃሊቲ አካባቢ ” ተብሎ በሚጠራው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ባለ ሰፊ መጋዝን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ሰዎችን የመያዝና ወደ ማቆያ ማእከል/ቦታ የማስገባት ድርጊት አሁንም መቀጠሉን አመልክቷል።

ወደ ማቆያው ከገቡት ሰዎች መካከል በማእከሉ ከመቆየት እና የእርሻ ሥራ ከመሥራት እንዲመርጡ በማድረግ፤ የእርሻ ሥራ ለመሥራት የመረጡ ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች ወደሚገኙ እርሻ ጣቢያዎች ተወስደው  እንዲሠሩ እንደሚደረግ ለመገንዘብ መቻሉን ጠቁሟል።

ይህም " የነጻነት መብታቸውን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶቻቸውን የሚጥስ ነው " ብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት ፣ የሚደረጉ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ጉባኤዎች እንዲሁም ከሌሎች ተመሳሳይ ኹነቶች ጋር በተያያዘ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎችን በኃይል በማንሳት በአንድ ስፍራ እንዲቆዩ የማድረግ አሠራር እንዲቆም ፤ ወደመጡባቸው አካባቢዎች የመመለስ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ሰብአዊ መብቶቻቸውን ባከበረ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ እና ችግሩ ሁሉ አቀፍ የፖሊሲ ምላሽ የሚያስፈልገው መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ የኢሰመኮ ክትትሎች መጠቆሙን አስታውሷል።

ኢሰመኮ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር  ውትወታ እያደረገ መሆኑን ጠቁሟል።

ጎን ለጎን የነጻነት መብትን ከማክበር እና ከማስከበር አኳያ እንዲሁም በጊዜያዊ ማቆያ ማእከሉ ከንጽሕና እና ከጤና አጠባበቅ ጋር በተያያዘ በሰዎች ሕይወትና ጤና ላይ አደጋ የሚጥሉ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ውይይቶችን በማድረግ ጉዳዩን በመከታተል ላይ እንደሆነ በላከል መግለጫ ገልጿል።


#EHRC #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የቁስ አካላቱ ሞያሌ ላይ አልወደቁም " - ነዋሪዎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ  ነገር ሞያሌ ላይ አለመዉደቁን ነዋሪዎች ገለጹ። ትላንት ምሽት በደቡባዊ የሀገራችን ክፍሎች ሰማይ ላይ ከተለመዱት ተወርዋሪ ኮከቦች በተለየ መልኩ በመጠን የገዘፈና በዘገምተኛ አኳሃን ሲጓዝ እንደነበር የተገለጸው ብርሃናማ የተቀጣጠሉ ቁስ አካላት " ሞያሌ አከባቢ…
የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ምን አለ ?

" በትናንቱ እንግዳ የሕዋ ክስተት ዙሪያ ከተለያዩ የሕዋ አካላት መከታተያ እና የመረጃ ቋቶች ያገኘናቸውን መረጃዎች በማጠናቀር ባደረግነው ጥልቅ የሆነ ትንተና መሰረት የሚከተለው ሳይንሳዊ መላምት ላይ ደርሰናል።

በመረጃው መሰረት የሕዋ አካሉ ባለቤትነቱ የቻይና የሆነ ሺ ጂያን-19 (ShiJian-19) የተባለ ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆን እንደሚችል ያመላክታል።

ከዚህም በተጨማሪ የሳተላይቱን ቀሪ አካል የምህዋር እና የይዘት መረጃ ጠቅላላ ትንታኔውን ከላይ አጋርተናል።

ሳተላይቱ በመስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ምህዋር የተወነጨፈ ሲሆን ተልዕኮውን ጨርሶ በጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ መሬት ተመልሷል።

ነገር ግን ሳተላይቱ በተልዕኮው ላይ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ክፍሎቹ ከዋናው ሳተላይት ተነጥለው በምህዋር ላይ ሲዞሩ ቆይተዋል።

ለትንተናው የተጠቀምናቸው መረጃዎች ከሶስተኛ ወገን የመረጃ ቋቶች የተገኙ በመሆኑ የተረጋገጠ መረጃውን የሳተላይቱ ባለቤት ሃገር ቻይና እስክታረጋግጥ መጠበቅ ይኖርብናል።

ዋቢ ምንጮች ፦
https://www.satcat.com/sats/61506  / http://www.satflare.com/track.asp?q=61506&sid=2#TOP ናቸው "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በትግራይ ክልል የምትገኙ የሃይማኖት አባቶች መበደላችሁን እናውቃለን ፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው። ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን እኛ የገፋነውን እርቅ ዓለም ሊቀበለው ስለማይችል፤ በእጃችንም የያዝነው መስቀለ ክርስቶስ የሰላም ዓርማ ነውና ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን " -  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ንጉስ ማልት ከምግብ ጋር አቤት ደስስስስስስስስስስስስስስ ማለቱ!
ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ https://yangx.top/Negus_Malt

#nonalcoholic #ንጉስ #DesDesWithNegus #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት#ንጉስማልት
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Somalia #Egypt የሶማሊያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ኤንድ ሴኪዩሪቲ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አብዱላሂ ሞሐመድ ዓሊ ኢትዮጵያ ይገኛሉ። አብዱላሂ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር መክረዋል። ውይይቱ የአንካራውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ከሁለቱ ሀገራት አቻ ተቋማት የሚጠበቁ የትብብርና የአጋርነት መስኮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።…
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ መጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድን ተቀብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት " የሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ " ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አንካራ ስምምነት ከተፈራረሙ በኃላ በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረው መቃቃር እየለዘበ መምጣቱ ይታወቃል።

ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ መጥተው እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያ መጥተዋል።

@tikvahethiopia