TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Earthquake
ትላንት ለሊት 9:52 ላይ በርካቶችን ከተኙበት የቀሰቀሰው በሬክተር ስኬል 5.8 ከተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።
ዛሬ ደግሞ በሬክተር ስኬል ፦
➡️ 4.7
➡️ 4.6
➡️ በድጋሚ 4.7
➡️ በድጋሚ 4.6
➡️ 4.9 የተለኩ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።
ሁሉም አዋሽ እና አካባቢው ናቸው።
ባለፉት ሰዓታት ከተመዘገበው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ 4.9 ከፍተኛው ነው።
በሌላ በኩል አፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው የኢፌዴሪ ከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል።
በስኳር ፋብሪካው አስተዳደር ህንፃ፣ በኃይል ማስተላለፊያ ክፍል፣ የላብራቶሪ እና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
አሁን ላይ መሬት መንቀጥቀጡ በከፍተኛ ሁኔታ በአከባቢው እየጨመረ በመምጣቱ ጉዳት በደረሰባቸው ህንፃዎች ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች ንብረቶችን ለማዳን የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።
የፋብሪካው ሰራተኞች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስቀድሞ እንዲለቁ መደረጉ ተነግሯል።
ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያለው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆሙን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በተያያዘ መረጃ ፥ መንግሥት የርዕደ መሬቱ ማዕከል ከሆኑ አካባቢዎች ነዋሪዎችን የማራቅ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አሳውቋል።
በተለይም ደግሞ የርዕደ መሬቱ ማዕከል የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሰሳ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማስፈር ርብርብ እየተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
#Ethiopia #Afar #Earthquake
@tikvahethiopia

#Earthquake ትላንት ለሊት 9:52 ላይ በርካቶችን ከተኙበት የቀሰቀሰው በሬክተር ስኬል 5.8 ከተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ በሬክተር ስኬል ፦ ➡️ 4.7 ➡️ 4.6 ➡️ በድጋሚ 4.7 ➡️ በድጋሚ 4.6 ➡️ 4.9 የተለኩ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል። ሁሉም…
#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።
ቤት ውስጥ ፣ አልጋ ላይ፣ ከቤት ውጭ የነበሩ ሰዎች ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል።
ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም በመቀጠሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትዘናጉ።
@tikvahethiopia
ቤት ውስጥ ፣ አልጋ ላይ፣ ከቤት ውጭ የነበሩ ሰዎች ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል።
ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም በመቀጠሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትዘናጉ።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር። ቤት ውስጥ ፣ አልጋ ላይ፣ ከቤት ውጭ የነበሩ ሰዎች ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል። ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም በመቀጠሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትዘናጉ። @tikvahethiopia
#Update
ከጥቂት ከደቂቃዎች በፊት ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አሳውቋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ 31 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ ነው።
ዛሬ በተለያየ ሰዓት አምስት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን የአሁኑ ለስድስተኛ ጊዜ የተከሰተው (በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካው ) በመጠን ከፍተኛው ነው።
ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ላይ በደንብ ተሰምቷል።

#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር
በዓሉን አስመልክቶ የተደርገው ልዩ ቅናሽ ሳያመልጥዎ እነዚህን ውብ እቃዎች የግልዎ ያድርጉ።
🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይቀላለቀሉ
Telegram 👉 Telegram/yonatanbtfurniture
Facebook 👉 Facebook/yonatanbtfurniture
Instagram 👉 Instagram/yonatanbtfurniture
TikTok 👉 TikTok/yonatanbtfurniture
📍አድራሻችን
1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)
☎️ +251957868686/ +251995272727/ +251993828282

#Update 🚨 “ ግብረሰዶም ወደ ሚፈጸምበትና ኩላሊት እያወጡ የሚሸጡበት ሰዎች ወዳሉበት ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል” - በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ ➡️ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ኑሮን ለማሻል በሚል ወደ ታይላንድ የሄዱና በኃላም ወደ ማይናማር የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን በጋንግስተሮች እጅ ወድቀው ከውላቸው ውጪ ህገወጥ የዶላር ማጭበርበር…
#Update
“ ከ29 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሌላ ቦታ ሸጠዋቸዋል። ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት አለባቸው ” - በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያውያን ወላጆች ኮሚቴ
በማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲያስወጣቸው በተደጋጋሚ እየተማጸኑ እንደሚገኙ ይታወቃል።
የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ፣ “ ግብረሰዶም ወደማፈጸምበትና ኩካሊት እያወጡ የሚሸጡ ሰዎች ወዳሉበት ካምቦዲያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል ” ሲል ስጋቱን ገልጾልን ነበር።
ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቅነው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ልጆቹ ያሉበት ቦታ አዳጋች እንደሆነ፣ ከአገራቱ ጋር የሥራ ስምሪት አለመኖሩ ሁኔታውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲገልጽ መቆየቱ አይዘነጋም።
ከቶኪዮ ኤምባሲ ጋር እየተነጋገረ መሆኑንም ገልጾ የነበረው ሚኒስቴሩ ከዚያ በኋላ ላቀረብለት ጥያቄ፣ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” ቢልም እስካሁን ያለው ነገር የለም።
አሁንስ የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?
የወላጆች ከሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ከ29 በላይ የማሆኑ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሌላ አገር ሸጠዋቸዋል። ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት አለባቸው ” ብሏል።
በመሆኑም ልጆቹ ካሉበት ስቃይ እንዲወጡ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ ቢሯዎቻቸውን እያንኳኳ በደብዳቤ ጭምር እየተማጸነ መሆኑን ገልጾ፣ መንግስት አሁንም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል።
ኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?
“ ምንም መፍትሄ የለም። እንዲያውም የተወሰኑ ልጆችን ወደሌላ ቦታ ሸጠዋቸዋልና ያን የሰሙ ልጆች በጣም ተረብሸዋል።
ወደ ካምቦዲያ እየሸጧቸው ነው ስለተባለ ተጨናንቀዋል። በየቀኑ ‘ምን አዲስ ነገር አለ?’ ነው የሚሉን። እኛም ውጪ ጉዳይን አሳስበን መፍትሄ በመጥፋቱ አሁን የሃይማኖት ተቋማትን እየተማጸንን እንገኛለን።
ልጆቹን በማይናማር ከነበሩበት ቦታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ እየሸጧቸው ነው። ይሄ ነው ችግር የሆነው። በየጊዜው አዲስ ነገር ነው የሚሰማው በጣም ይጨንቃል።
ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ምንም አዲስ ነገር የለም። አሁንም ተሰባስበን ልንሄድ ነው። የሃይማኖት ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ እየተማጸንን ነው።
ዱኣ አድርጉ፤ ጾም ጸሎት ይታወጅ ብለን እየጠየቅን ነው።
ሀገራቱንም፣ ህዝብንም፣ ቤተሰብንም መጥቀም የሚችሉ የተማሩ ልጆቻችን ስቃዬ ላይ እያሉ ውጪ ጉዳይ ሰምቶ ዝም ከማለት ያስቸገረው ነገር ካለም ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እንዲያቀርቡልን እንጠይቃለን።
ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትም ሄደን ነበር ለቅሬታ ሰሚ ክፍል ጥያቄያችንን በኢሜይል እንድናስገባ ነው የነገሩን። ግን በኢሜይል ብቻ አስገብተን አንቀመጥም ደብዳቤም እንወስዳለን ” ብሏል።
(ጉዳዩን እስከ መጨረሻው የምንከታተለው ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል። ምርጫ ቦርድ ፤ ህወሓት በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር መሠረት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን አስታውሷል። ፖርቲው ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ…
#TPLF #Tigray
ለሁለት ቡድን የተከፈሉት የህወሓት አመራሮች አሸናፊ እና ተሸናፊ በሌለበት የፓለቲካ ችግሮቻቸውን ለመፍታት የተደረገው ተደጋጋሚ ድርድር አልተሳካም አለ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር።
ሁለቱ ቡድኖች ፓለቲካዊ ልዩነታቸው እንዲፈታ ከመጣር ይልቅ ፤ አንዱ ሌላውን ጠርጎ ለማጥፋት በሚል እሳቤ መጠመዳቸው ለድርድሩ አለማሳካት አንዱ እና ዋነኛ ምክንያት ነው ተብሏል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?
- የፓለቲካ ልዩነቱ ዋና መነሻ ከፍተኛ አመራሩ በመሆኑ ችግሩ በድርድር እንዲፈታ ጥረት የተደረገው በከፍተኛ አመራሩ ነው ብለዋል።
- የክልሉ የፀጥታ ሃይል ጨምሮ ሌሎች አካላት " ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ችግሮቻቸው ፓለቲካዊ ነው መፈታት ያለበትም በፓለቲካዊ መግባባት ነው " በሚል ለማደራደር በርካታ ጥረት ተደርጓል።
- በሁለቱ ቡድኖች መካከል የተፈጠረ የፓለቲካ ልዩነት አሁን የተፈጠረ ሳይሆን በወቅቱ ሳይፈታ ለዓመታት እየተከማቸ የመጣ መሆኑ ቡድኖቹ ለማቀራረብ አዳጋች አድርጎታል።
- በሁለቱን ቡድኖች ያለው ፓለቲካዊ መሳሳብ አሁንም ፓለቲካዊ መፍትሄ ያሻዋል። የፀጥታ ሃይሉ " የኛ ደጋፊ ነው " የሚል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚናገረው ተቀባይነት የለውም።
- የፀጥታ ሃይሉ የክልሉ እና የህዝቡ ፀጥታ እና ሰላም ከማስከበር ባለፈ አንዱን ቡድን በመደገፍ ሊቆም አይችልም። ህዝቡ ሁለቱ ቡድኖቹ ችግራቸው በጠረጴዛ ውይይት እንዲፈቱ ጫናውን ማሳደር ይጠበቅበታል።
- የፀጥታ ሃይሉ የአንዱ ደጋፊ ለማሰመሰል የሚደረግ ጥላሸት የመቀባት ተግባር ልክ አይደለም። ይህን መሰል በሬ ወለደ ውሸት የሚያራግቡ አካላትም ሆነ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባቸዋለን።
መረጃውን የትግራይ የመገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#Update ከጥቂት ከደቂቃዎች በፊት ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አሳውቋል። የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ 31 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ ነው። ዛሬ በተለያየ ሰዓት አምስት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን የአሁኑ ለስድስተኛ ጊዜ የተከሰተው (በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካው ) በመጠን ከፍተኛው ነው። ንዝረቱ አዲስ…
#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።
በተለይ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ረዘም ላለ ሰከንድ ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል።
የአሁኑ ንዝረት ከትላንት ምሽቱ አንፃር ጠንክሮ የተሰማ ነው።
@tikvahethiopia
በተለይ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ረዘም ላለ ሰከንድ ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል።
የአሁኑ ንዝረት ከትላንት ምሽቱ አንፃር ጠንክሮ የተሰማ ነው።
@tikvahethiopia
በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ፤ በሳቡሬ ቀበሌ የሚገኙ ሁለት ት/ቤቶች በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ትምህርት ቤቶቹ ዑንጋይቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና ሳቡሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ናቸው።
የወረዳው ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት እንዳለው ፥ ዑንጋይቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ካሉት 12 የመማሪያ ክፍሎች ስድስቱ ፤ ሳቡሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ካሉት 16 ክፍሎች ስምንቱ መስኮታቸው ረግፏል ፤ ግድግዳቸው የመሰንጠቅና የመፍረስ አደጋ ደርሶበታል፣ ወለላቸውም ሰርጓል።
የዑንጋይቱ ት/ቤት ፤ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በመማሪያ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ተማሪዎችን በዛፍ ስር እና ድንኳን ውስጥ ሲያስተምር ነበር።
ማክሰኞ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ/ም ጠዋት 2፡30 የመሬት መንቀጥቀጡ በባሰ ሁኔታ በመከሰቱ ተማሪዎች እና መምህራን በድንጋጤ ት/ቤቱን ለቀው ወጥተዋል ተማሪዎች ከዚያ በኋላ አልተመለሱም።
ትምህርት ቤቱ ወላጆቻቸውን ጠርቶ ካነጋገረ በኋላ ወልጆች " ልጆቻችን አብረውን ቢቆዩ ይሻለናል " ስላሉ የመማር ማስተማር ሂደቱ ተቋርጧል።
በወረዳው ከሚገኙት 6 ቀበሌዎች በአራቱ ላይ የመሬት መንቀጥቀጡ በተደጋጋሚ መከሰቱን ተከትሎ ነዋሪዎችን ወደተሻሉ አካባቢዎች የማስፈር ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።
በሌላ በኩል ፥ በሃንሩካ ወረዳም በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በትምህርት ቤት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ነው።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ ነዳጅ ጭነው ያለአግባባ በየቦታው ቆመው የሚገኙ የነዳጅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ከተደበቁበት እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አሳወቀ።
የአፋር ክልል ንግድ ቢሮን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጠየቀው ትብብር መሠረት ከክልሉ የፀጥታ አካል ጋር በመሆን በሰጠው ምላሽ ነው ከተደበቁበት እንዲወጡ እየተደረገ ያለው።
አዲስ አበባን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚጓጓዝን ነዳጅ ይዘው በአፋር ክልል ልዩ ቦታው " ሰርዶ አድማስ " በሚባል ቦታ በየጥሻው የቆሙት ቦቴዎች የፀጥታ አካል ባደረገው አሰሳ ተደብቀው በቆሙበት መያዛቸውን ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።
" በአሁን ሠዓት የክልሉ ንግድ ቢሮ ለተሸከርካሪዎቹ እጀባ በመስጠት ወደ የመዳረሻቸው እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል " ብሏክ።
" ' በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ይሠራል ' በሚል ያልተጨበጠ ተስፋ ነዳጁን ይዘው የተሸሸጉት እነዚህ ተሸከርካሪዎች ያለአግባባ የሚያገኙትን ትርፍ ከማሰብ ውጪ የጫኑት ነዳጅ በባህሪው በትነት የሚባክን፣ አደጋን የማስከተል አቅም ያለው መሆኑን ለማሰብ አልፈቀዱም " ሲል ኮንኗል።
" ከዚህ ባለፈ በየክልል ከተሞች የነዳጅ ማደያዎችን በማድረቅ እጥረት በመፍጠር ህብረተሰቡን የማጉላላት ስራን መስራታቸውን ማመን አይፈልጉም " ሲል አክሏል።
በዚህም " የፈፀሙት ሕገወጥ ተግባር በተጨባጭ የተረጋገጠ በመሆኑ ይህን ተግባር የፈጸሙት ላይ መንግስት ለህብረተሰብ ተጠቃሚነት ሲል በድጎማ የከፈለበትን የነዳጅ ወጪ እንዲሸፍኑ የሚደረግ እንደሆነ እና ከምርት መሰውር ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሚደረጉ ይሆናል " ብሏል።
" በነዳጅ ግብይት ሂደት ውስጥ የሚፈፀሙ ሕገ-ወጥ ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መጥተዋል " ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ " በግብይት የሚሳተፉ አካላት ጤናማ የንግድ ስርዓትን ተከትሎ ትርፍ ከማግኘት ይልቅ ለህብረተሰቡ ጥቅም ሲባል ድጎማ ተደርጎበት የሚቀርበውን ነዳጅ በኮንትሮባንድ እና በጥቁር ገበያ አሳልፈው ይሰጣሉ " ብሏል።
በዚህም " በየክልሉ ከሚፈጠሩት እጥረት ባሻገር በዚህ መልኩ ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች በየቦታው እንዲዘገዩ በማድረግ ተጨማሪ ትርፍ ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ተጠቃሚውን ህብረተሰብ የማጉላላት ተግባር ይፈጽማሉ " ሲል ወቅሷል።
" ነዳጅ አቅርቦት ላይ ሰው ሰራሽ እጥረት በየጊዜው እንዲፈጠር የሚያደርጉ መሰል ተግባራት በግልጽ እየታዩ ባለበት አንዳንድ መረጃ ሰጪዎች ለመገናኛ ብዙኃን በሚሰጡት መረጃ ' የነዳጅ እጥረቱን የፈጠረው ለኛ የሚሰጠው የገበያ ድርሻ ማነስ ነው ' የሚል የማይገናኝ ምክንያት ሲያቀርቡ ይሰማሉ " ሲል ኮንኗል።
" የነዚህ ተሸከርካሪዎች እና የነዳጁ ባለቤቶች በዚህ ወቅት የፈፀሙት ተግባር ግን የችግሩን ዋነኛ ባለቤት አሳይቷል " ብሏል።
#PetroleumandEnergyAuthority

#NationalExam : የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
ምዝገባቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድመው እንዲያጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።
የፈተና ይዘትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ተገልጿል።
ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው እንዲዘጋጁ ተብሏል።
በሌላ በኩል ፥ ዘንድሮ በመደበኛው እና በግል 750,000 ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
እስካለፈው ሳምንት ባለው ዳታ ወደ 500 ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበል።
በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ለመመዝገብ እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ባለው 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ አከናውነዋል ፤ በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።
ኢንተርኔት ማይሰራበት ቦታ ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን እየተጫነ ነው።
የመረጃ ባለቤቶች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ኤፍኤምሲ መሆናቸውን እንገልጸለን።

#DireDawa
" በወንጀል ተግባሩ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አመራር እና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ወደ መጠናቀቁ ነው " - ድሬ ፖሊስ
ከሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ አንድ ወጣት በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ አባላት ድብደባ መገደሉ በርካቶችን አስቆጥቷል ፤ አሳዝኗል።
በተለይ ገንደቦዬ ዛሬም ድረስ ሀዘን ላይ ናት።
የ1 ልጅ አባት የሆነው ወጣት ሙራድ መሀመድ (አሳዶ) ከሰሞኑን በፖሊስ ድብደባ ለሞት መዳረጉ ተነግሯል።
የቅርብ ወዳጆቹ ፥ " ሙራዴ ከሰው ጋር ተግባቢ ፤ በሚኖርበት አካባቢ ገንደቦዬ ላይም የሚታወቅ ፤ የሚወደድ ወንድማችን የሰፈራችን ድምቀት ነበር። ህግ አለባት በምንልበት ከተማችን ያውም ደግሞ ህግ አስከባሪ ተብሎ ዩኒፎርም በለበሱ ፖሊስ አባላት በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድቦ ተገደለ መባሉ እጅግ በጣም አስደንግጦናል፣ አሳዝኖናል ፣ አስቆጥቶናል " ብለዋል።
" የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ሰዎች በፖሊስ እና የህግ የበላይነት ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ የሚያደርግ ነው። ሙራድ ሰላማዊ ህይወቱን እየመራ ባለበት ነው ይህ ግፍ የተፈጸመው " ሲሉ አክለዋል።
" ፍትህ ሊሰጥ ፤ እውነት ሊወጣ ፣ ወንድማችንን ለሞት የዳረጉት የሚገባቸውን ቅጣት ሊያገኙ ይገባል " ሲሉ አክለዋል።
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፥ " ወጣት ሙራድ መሀመድን በግል ቂም በቀል ተነሳስተው ኢሰብዓዊ በሆነ መልኩ በመደብደብ ፣ ለሞት በመዳረግ አስነዋሪ ተግባር የፈጸሙ አባላቶችን በቁጥጥር ስር አውለን ምርመራ በማጣራት ላይ ነን " ሲል መግለጫ አውጥቷል።
ድርጊቱ " ጥቂት " ሲል በጠራቸው የፖሊስ አባላት መፈጸሙን አመልክቷል።
ወጣት ሙራድ በፖሊስ አባላት ተደብድቦ ለሞት በመዳረጉ እጅግ ማዘኑን ገልጾ " ጠቅላይ መምሪያውን በፍጹም የማይወክል ነው " ብሏል። " አስነዋሪ " ሲል የጠራውን የወንጀል ተግባርም አውግዟል።
አሁን ላይ በወንጀል ተግባሩ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አመራር እና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ወደ መጠናቀቁ እንደሆነ ገልጿል።
ወጣቱ ተደብድቦ ለሞት ከተዳረገ በኃላ ስርዓተ ቀብሩ በተፈጸመበት ወቅት የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀር ፤ " ግለሰባዊ የቂም በቀል ጥላቻ ነው የመንግሥትን ልብስ ሽፋን አድርጎ የተፈጸመው " ያሉ ሲሆን ድብደባውን ፈጽመው ሙራድን ለሞት የዳረጉት 3 የፖሊስ አባላት እንደሆኑ ገልጸዋል።
" ጣቢያ አላመጡትም ፤ ከዚራ አላመጡትም እኛም ምንም መረጃ አልነበረንም ፤ ወስደው በድብደባ ነው የሞተው። ማታ ጤና ጣቢያ መልካ ላይ ነው የተወሰደው ከዛ በኃላ ነው መረጃው የደረሰን " ብለዋል።
በሙራድ መሀመድ ህልፈት ሀዘናቸውን ገልጸው " ልጅ አለው፣ ሚስት አለው እናትም አለው ቤተሰቦቹን የማገዝ እና መርዳት ኃላፊነት አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።
#Murad #DireDawa #Police