TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሐይማኖት ሐገር የሆነችውና በርካታ የችግር መፍቻ ባህልና ልምድ  ያላት ሀገር ላይ ዜጎች በሰላም እጦት ምክንያት መቸገር  የለባቸውም ! " - የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችና  የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ትውውቅ ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል። ሚኒስትሩ በሰላም…
" የሃይማኖት ተቋማት ትብብርና አብሮነት ለሰላም ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና አለው " - አቶ መሀመድ እድሪስ

የሰላም ሚኒስትር ከሃይማኖት ተቋማትና መሪዎች ጋር እያደረጉ ያሉትን ትውውቅና ውይይት ቀጥለው ዛሬ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር ተገናኝተዋል።

በዚህም ወቅት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ፥  " የሃይማኖት ተቋማት ትብብርና አብሮነት ለሰላም ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና አለው " ብለዋል።

" በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳይ ሰላማዊና የተረጋጋ ማህበረሰብ እንዲኖር የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ አስተዋፆ ሊኖራቸው ይገባል "  ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በቀጣይ በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ እያከናወነ ያለውን  ተግባር አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተው የሰላም ሚኒስቴርም በትብብርና በቅንጅት ከካውንስሉ ጋር ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ፤ ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) ፥ ከመገፋፋት ይልቅ በመተባበር እና በመደጋገፍ ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ ሃይማኖቶች ትልቅ አቅም ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ሲሰራ የቆያቸውን የሰላም ግንባታ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል በሀገራችን ሰላም ጉዳይ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ እንደሆነ አሳውቀዋል።

#MinistryofPeace

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አክሱም 🧕" እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው። ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን " - ተማሪዎች ➡️ " የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ከትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል " - የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት 👉 " ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም "…
#Update

የፌዴራል መጅሊስ ከቀናት በኃላ ዝምታውን ሰብሮ መግለጫ አወጣ።

ምን አለ ?

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ፤ " አገራችን ኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ከፍተኛ ርብርብና በሃይማኖት አባቶች ዱአ በምናደርግበት በአሁኑ ወቅት በተፃራሪው አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚከሰቱ ሃይማኖታዊ ተንኮሳዎች የመንግስት አካላትን ጨምሮ የስጋት ምንጭ እየሆኑ ይገኛሉ " ብሏል።

ምክር ቤቱ ፥ " በትግራይ ክልላዊ መስተዳደር የአክሱም ከተማ ትምህርት ቢሮ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን የእምነት አለባበስ (ሂጃብ) አስመልክቶ ትምህርታቸውን በሚጐዳ መልኩ ከአንድ ወር ባላነሰ ጊዜ ከትምህርት ገበታቸው እንዲስተጓጐሉ አድርጓል " ብሏል።

ከዚህ ባሻገር አንዳንድ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው በእስር ያቆዩ በመሆኑ ጉዳዩን ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ጋር ሲነጋገርበት መቆየቱን ከአሁን አሁን ሁነኛ መፍትሄ እስኪገኝ በትዕግስት እየጠበቀ እንደሆነ ገልጿል።

ነገር ግን ምንም አይነት እልባት አለመኖሩን በተግባር መረዳት እንደቻለ አመልክቷል።

" የአክሱም ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ለዘመናት የነበረባቸውን የእምነት ነፃነት፣ የመስገጃ ቦታ ችግርና የቀብር ቦታ ችግር እልባት ያልተሰጠበትና ወደ ባሰ ሁኔታ እየሄደ ነው " ያለው ምክር ቤቱ " የክልሉና የፌዴራል መንግስት የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤቶች በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግጋትና በህገ መንግስቱ አንቀጽ 27 መሠረት በዚህ ዘመን በጋራ እምነቶች ተከባብረው በሚኖሩበት አገር እሴቱን የሚሸረሽር ተግባር መፈፀሙን በጥብቅ እናወግዛለን " ብሏል።

በመሆኑም የሙስሊም ማህበረሰብ መብቶች ሳይሸራርፉ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረጉና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም ይህንኑ እንዲያስፈጽሙ ምክር ቤቱ ጠይቋል።

ይህንን ድርጊት በፈፀሙ ግለሰቦች ላይም ህጋዊ እርምጃ እዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል።

የጠቅላይ ም/ቤቱ የህግ ክፍል አስፈላጊውን ክትትል የሚያደርግ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን መላው የሙስሊም ማህበረሰብና ሌሎች የእምነት ተቋማትና ተከታዮች ጉዳዩን እንዲያወግዙና ከአክሱም ሙስሊም ማህበረሰብ ጐን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል።

ከሰሞኑን የአክሱም ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " ሂጃብ አድርጋችሁ አትገቡም " በመባላቸው ከትምህርት ገበታቸውን እንዲወጡ መደረጉን መግለጻቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Axum

" በአሁኑ ሰዓት የተለየ አዲስ መመሪያና ክልከላ ባልወጣበት ፤ የነበረውን የአለባበስ ስርዓት የሚቀይር አዲስ ጥያቄ ባልቀረበበት ሁኔታ የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም " ሲል የትግራይ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮ ለአክሱም የትምህርት ፅህፈት ቤት በፃፈው ደብዳቤ ፤ " ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ምን ዓይነት አለባበስ መከተል እንዳለባቸው የሚያዝ የቆየ መመሪያ እና አሰራር አለን " ብሏል።

" ነባሩ የአለባበስ መመሪያ እና አሰራር እያለ የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም በከተማው በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ተለይቶ ያልነበረ የአለባበስ ህግ እንዲተገበር ያቀረበው ጥያቄ ልክ አይደለም "  ሲል ገልጿል።

" ከመ/ቤታችን የተላኩ ባለሙያዎች ለተነሳው ጥያቄ መፍትሄ ለማምጣት መግባባት ላይ ቢደርሱም ምክር ቤቱ ጥያቄውን እልባት እንዳላገኘ አድርጎ ቅሬታ ማቅረቡ ትክክል አይደለም " ሲል አመልክቷል።

በአሁኑ ሰዓት የተለየ አዲስ መመሪያና ክልከላ ስለሌለ የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው የአለባበስ ስርዓቱ በነበረው እንዲቀጥል ቢሮው አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ " ሙስሊም ተማሪዎች ከተፈቀወድ አለባበስ ውጭ ለብሰው (ሂጃብ አድርገው) መግባት ተከልክለዋል ፤ ከትምህርታቸውም ተሰተጓጉለዋል " ከተባለባቸው ትምህርት ቤቶች የአንዱን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ለማነጋገር ስልክ ቢደውልም በጉዳዩ ላይ ለሚድያ መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ገልፀዋል።

ትናንት የትግራይ አስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለሚዲያ መግለጫ ሊሰጥ ዝግጅት አድርጎ የነበረ ሲሆን ከላይ ያለውን የትምህርት ቢሮን መገለጫ ተስፋ በማድረግ ሊሰጠው ያሰበውን መግለጫ ለሌላ ጊዜ አስተላልፏል።

ይሁን እንጂ ዛሬም ተማሪዎች " ከተፈቀደው አለባበስ ውጪ ለብሳችኋል " በሚል ምክንያት ወደ ትምህርት መአድ እንዳይገቡ ተደርገዋል።

ጉዳዩ ብዙዎችን እንዳስቆጣ የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 4:18 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.8 ተመዝግቧል። የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ልክ 4:18 ላይ ከአዋሽ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አመላክቷል። ይህ 4.8 ሆኖ የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ከተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተመሳሳይ ነው። ትላንትና ሰኞ ከጥዋት አንስቶ የተለያየ…
#Earthquake : እየተከሰተ ያለው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬም ቀጥሏል።

ዛሬ ረቡዕ ከጥዋት አንስቶ እስከ ምሽት በተለያየ ጊዜ በሬክተር ስኬል ከ4.5 እስከ 4.9 ድረስ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌና አካባቢው ተከስቷል።

ሰሞኑን ጠንከር ያለውና ተደጋግሞም እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር ላይ የንብረት ጉዳት አድርሷል።

ወገኖቻችን የመሬት መንቀጥቀጡ ካየለባቸው ቦታዎች ቤታቸውን ጥለው ለመውጣት እየተገደዱ ይገኛሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyAfar

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በተአምር የተፈረች ነፍስ !

" ከዚህ ትልቅ አደጋ መትረፌን ማመን አቅቶኛል" - ከቦናዉ የመኪና አደጋ የተረፈችው የኔነሽ ለገሠ


በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ተከስቶ የ71 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈዉ የመኪና አደጋ የተረፉት 4 ሰዎች ብቻ ናቸው።

ከእነዚህ ዉስጥ ሁለቱ ገና መኪናዉ ወደ ገደል ሳይገባ ዘለዉ በመውረዳቸው መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ሁለት ሴቶች ደግሞ ተሽከርካሪዉ ወንዝ ዉስጥ ከገባ በኋላ በከፍተኛ ጉዳት በሕይወት ተርፈዉ ከቦና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተሻለ ህክምና ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላዝድ ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸዉን የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን መረጃ ያሳያል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ቤተሰብ አባል ከዚህ አስከፊ አደጋ የተረፉትን ሁለት ሴቶች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለመጠየቅ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላዝድ ሪፈራል ሆስፒታል አቅንቷል።

ከአደጋው የተረፉት ሁለቱ ሴቶች ስማቸው የነኔሽ ለገሠ እና ከበቡሽ ሃይሌ ይባላሉ።

ከበቡሽ ኃይሌ በአደጋዉ ምክንያት ቀዶ ህክምና ተደርጎላት በመተንፈሻ ማሽን እርዳታ ዉስጥ ትገኛለች።

የኔነሽ ገለሠ ደግሞ በድንጋጤና ከፍተኛ ሕመም ዉስጥ ብትሆንም ማዉራት እና የተፈጠረውን አደጋ በመጠኑም ቢሆን ማስታወስና ከአስታማሚዎቿ ጋርም መግባባት ትችላለች።

ከአደጋው ስለተረፉት ሁለት ሴቶች በምን አይነት የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማብራሪያ ከሆስፒታሉ የጠየቅን ቢሆንም ሆስፒታሉ ከአደጋው ጋር በተያያዘ " ከፖሊስ በስተቀር መረጃ ለመስጠት እንቸገራለን " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

በወቅቱ የኔነሽ ለገሰን ሲያስታምሙ ያገኘናቸው አቶ ደበበን አሁን ስላለችበት የጤና ሁኔታ ጠይቀናቸዋል።

አቶ ደበበ እንደነገሩን የኔነሽ ስለ አደጋዉ ዝርዝር ጉዳዩ እንዳልተነገራትና በዚህ ዘግናኝ አደጋ ምክንያት አንድ እህቷን እና ሁለት ወንድሞቿን ማጣቷን ነግረውናል።

በሆስፒታሉ በተገኘን ጊዜም የኔነሽ ነቃ ብላ እያወራች ነበር።

አማርኛ ቋንቋን በሚገባ መናገር ባትችልም በሲዳምኛ ቋንቋ ስለ አደጋው ስታስረዳ ማዳመጥ ችለናል።

" አደጋዉ የተከሰተዉ የአጎቴ ልጅ ሚስት ሊያገባ ስለነበር ቤተ-ዘመድ ተሰባስቦ ሙሽራዋን ለመዉሰድ ወደ ወራንቻ ቀበሌ እየሄድን በነበርንበት ወቅት ነዉ" ብላለች።

" እኔ መሃል ነበርኩ፤ ሁላችን በደስታ በዝማሬ ላይ ነበርን ወደ ዋናዉ መስመር ወጥተን ጋላና ወንዝ ስንደርስ በድንገት መኪናዉ ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ መግባት ሲጀምር በጩኸት ብዛት.... " ንግግሯን መጨረሽ አልቻለችም።

ይኽን በምታወራበት ወቅት እምባ በሁለቱም ዐይኖቿ ይወርድ ነበር።

ከተወሰነ መረጋጋት በኋላ የኔነሽ ስለ አሰቃቂው አደጋ የምታስታውሰውን ማስረዳት ቀጠለች ፤ " አላዉቅም እኔ ዛሬ ነዉ ሀዋሳ መሆኔን እንኳን የተነገረኝ! ሌላዉን አላዉቅም ፤ አጎቴ አብረዉኝ ስለነበሩ አጠቃላይ ስለ ሰርገኛዉ ደጋግሜ ስጠይቀዉ 'እነሱ ቦና ናቸዉ! አንቺ ስለተጎዳሽ ነዉ እዚህ የመጣሽዉ' ይለኛል " በማለት አስታማሚዋ የነበሩት አቶ ከበደ እንደነገሩን ይኽንን መሪር ሀዘን አለመስማቷን አረጋግጣልናለች።

ይህንን በተናገረችበት ቅጽበት አጠገቧ የነበሩት ሁሉ ዝምታን መረጡ ሁሉም እንደተፈራራ ዝም ተባባለ በዚህ ጊዜ አንድ ጥያቄ ቀረበላት "ከቦታዉ አደገኝነት አንፃር በመትረፍሽ ምን ተሰማሽ ? " የሚል።

የኔነሽ ከነበረችበት ትካዜ በመጠኑም ነቃ ብላ " ከቦታዉ አደገኛነትና ከነበረዉ ሁኔታ አንፃር ከዚህ ትልቅ አደጋ መትረፌን ማመን አቅቶኛል " ስትል በመደነቅ ስሜት ገልጻልናለች።

እኛም ፈጣሪ ፈጽሞ እንዲምራትና ብርታቱን እንዲሰጣት ገልጸንላት ተለያየን።

የየኔነሽ አጎትና አደጋዉን ያደረሰው መኪና ባለቤት የሆኑትን አቶ ሀይሌ ሀሮንም አግኝተን ስለ አደጋዉ፣ ስለ መኪናዉ ሁኔታና ስለ ሹፌሩ ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር።

አቶ ሀይሌ ፥ " መኪናዉ አዲስ ነበር። ሹፌሩ ደግሞ የገዛ ወንድሜ ሲሆን ሙሽራዉም የወንድሜ ልጅ ነዉ። መኪናዉ በአባቢዉ ልምድ ከቡና ሳይት ሰራተኞችን የማመላለስ ስራ ይሰራ ስለነበርና አብዛኞቹ የቤተሰቦቻችን አባላት የቡና ስራ ስለሚሰሩ በዕለቱ ሰርገኞችን ጭኖ ወደ ወራንቻ እየሄደ ነበር አደጋዉ የተከሰተዉ " ሲሉ ነግረውናል።

አክለውም ፤ " ከቤተሰቦቻችን ብቻ ከ30 በላይ ሰዎች በአደጋዉ የሞቱ ሲሆን ከዛ ዉስጥ ግማሽ ያህሉ የወንድማማች ልጆች ናቸዉ. . . የቀን ክፉ አንገት አስደፋን ከፍተኛ የልብ ስብራት ነዉ ያጋጠመን ጌታ ብርታቱን ይስጠን " ሲሉ በሀዘን ውስጥ ሆነው አውርተውናል።

በአደጋው ምክንያት ሕይወታቸው ያጡ 71 ሥርዓተ ተቀብራቸዉ የተፈፀመ ሲሆን የሟቾችን ቤተሰብ ለማገዝ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱንና የገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ እየተሰባሰበ እንደሚገኝም ተረድተናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
በአዋሽብር ፕሮ ክፍያ ቀሏል!
===========
የአዋሽብር ፕሮ መተግበሪያን ሲጠቀሙ በግብይት እና በአገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሳይጠበቅብዎ ‘QR’ ኮድ ስካን በማድረግ ብቻ ክፍያዎን በቀላሉ ይፈፅሙ!
ስለባንካችን ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን https://yangx.top/awash_bank_official ይቀላቀሉ!
አዋሽ ባንክ

#AwashBank #NurturingLikeTheRiver #AwashBirrPro #AwashBank30thAnniversary
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፖሽ የእንጨት ስራዎች / Posh wood works

ከመጀመሪያዎቹ መሀል ይሁኑ ! ውጭ ሀገር ያዩት እርሶ ቤትም አይቀርም በሀገራችን የመጀመሪያው የሆኑ የአልሙኒየም ፍሬም መስታዎት በሮችን የተላበሱ የእንጨት ስራ ውጤቶችን ለእናንተ ለደንበኞቻችን ፤ይዘን መተናል
" ልዩ ውበት ይገባዎታል! "
ፖሽ የእንጨት ስራዎች / Posh wood works
Closet / Cupboard
Kitchen cabinet
TV Unit
Dressing

📍አድራሻ፦ ጀሞ 1 የተባበሩት ማደያ ውሰጥ
- 22 ከጎላጎል አጠገብ ኖህ ሪልስቴት 3ኛ ፎቅ
📲 0929414154
📲 0983915600
📲 0954777788 /99
ቴሌ ግራማችንን ይቀላቀሉ
https://yangx.top/webnewood
#HaileResortJimma

“ ወደ 1.7 ቢሊዮን ብር ፈሰስ ተደርጎበታል" - ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ

የሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ ሆቴልና ሪዞርት 10ኛ መዳረሻ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ዛሬ (ሐሙስ ታኀሳስ 24 ቀን 2017 ዓ/ም) ተመርቋል።

ሆቴሉ 3 የመመገቢያ አደራሾች፣ የልጆች መጫወቻ፣ ሞሮኮ ባዝ እንዳሉት፣ ለ210 ሰዎች ቋሚ የሥራ እድል እንደፈጠረ፣ ለወደፊት ደግሞ ወደ 400 ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ተነግሮለታል።

ሆቴሉ አሁን የተጠናቀቁ ወደ 106 ክፍሎች እንዳሉት፣ ሁሉም ሰጠናቀቁ ደግሞ ወደ 114 ክፍሎች እንደሚኖሩት ተመልክቷል።

በመርሀ ግብሩ የተገኙት ሻለቃ ኃይሌ ባደረጉት ንግግር፣ በአንድ ዓመት ከስምንት ወራት የሆቴሉን ግንባታ በአጭር ጊዜ ላጠናቀቁት ሠራተኞች በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ጅማ ላይ የኮንስትራክሽን እቃ ውድ መሆኑን የገለጹት ሻለቃ ኃይሌ፣ “ብሎኬት ከአዲስ አበባ እየተጓጓዘ ነው የተሰራው” ሲሉ ተናግረዋል።

“ኮንስትራክሽኑን ውድ ያደረገው የመንገዱ መበላሸት ነው” ያሉት ኃይሌ፣ “ብሎኬቶች እየተሰባበሩ ነበር። ሁሉ ሰው በአውሮፕላን መጓጓዝ አይችልም” ነው ያሉት።

የሆቴሉን ወጪ በተመለከተ በገለጹበት አውድ ደግሞ፣ “ወደ 1.7 ቢሊዮን ብር ፈሰስ ተደርጎበታል” ብለዋል።

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር በመርሀ ግብሩ ተገኝተው ባደረጉት ገለጻ ደግሞ፣ “ጅማ አባጅፋር ሁሉንም የምታቅፍ ከተማ ናት። ባለሃብቶች ጅማን ለመቀየር ከኅይሌ እንዲማሩ ማሳያ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትጃኒ ናስር ፥ “ኃይሌ ሲጠራ እንስቃለን፣ ኃይሌ ሲጠራ እንባችን ይመጣል፣ ኃይሌ እንኳን አገኘንህ” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።

“ሱልልታ ላይ የኃይሌን ሆቴል ሳይ እንዲህ አይነት ሆቴል ጅማ ላይ ቢገነባ ብዬ ተመኝቼ ነበር። አሁን እንደዚህ ተሰርቶ አየሁትና እንባዬ ነው የመጣው። የተመረቀው ለኃይሌ ሳይሆን ለጅማ ህዝብ ነው” ሲሉ አመስግነዋል።

በ10ሩም የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች 900  ሩሞች እንዳሉ፣ ለ2500 ሠራተኞች የሥራ እድል እንደተፈጠረ ተመልክቷል።

ፎቶ ፦ በግዛቱ አማረ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia