#SafaricomEthiopia
በምንፈልገው ሰዓት እና ቦታ ያለመቆራረጥ የሚሰራልን ኢንተርኔት ያስፈልገናል ፤ አሁኑኑ የM-PESA ሳፋሪኮምን የ4G ዋይ ፋይ ጥቅል ከM-PESA mini app በመግዛት የማይቆራረጠውን ኢንተርኔት እናጣጥም !
🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#MPESASafaricom
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether

#TecnoAI
ታህሳስ 10 በስካይ ላይት ሆቴል የሚካሄደው በሀገራችን ትልቁ የቴክኖ ኤ አይ ኢቬንት ጥቂት ቀናት ቀርተውቷል፡፡ ታዋቂው የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሰለሞን ካሳ የዝግጅቱ አካል ሲሆን ስለ ቴክኖ ኤ አይ እና ስለ አዲሶቹ የቴክኖ የቴክኖሎጂ ምርት ውጤቶች ሙያዊ ማብራሪያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡
https://www.tiktok.com/@tecnoet
@tecno_et @tecno_et

“ የልብ ክፍተት ህመም ያለበት ልጄን አድኑልኝ ” - አባት
በሞጆ ከተማ የሚገኙ አቶ አማረ አለማየሁ የተባሉ አባት የአንድ አመት ጨቅላ ህፃን ልጃቸው በልብ ክፍተት ህመም እየተሰቃዬ በመሆኑ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተማጸኑ።
የህፃኑ አባት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
“ ህፃኑን ይዤ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተመላለስኩ። ‘የሚሆን ነገር አይደለም’ ብለው ወደ ህፃናት ልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል መርተውኝ ነበር።
በማዕከሉ ያለው ወረፋም የሚቻል አይደለም። ‘በአስቸኳይ መሰራት አለበት ክፍተቱ ከ7 ሚሊ ሜትር የበለጠ ነው’ አሉኝና ወደ ግል ሆስፒል መሩኝ።
ቦሌ አካባቢ በሚገኘው ኢሉዜር ሆስፒታል ሄጄ ስጠይቅ ለማሳከሚያ 685 ሺሕ ብር ጠየቁኝ። በአካባቢዬ እርዳታ ብጠይቅም እስካሁን ምንም ገንዘብ አላገኘሁም።
የልጄ ህመም የተፈጥሮ የልብ ክፍተት ነው። ክፍተቱ በተፈጥሮ መዝጋት ነበረበት ሳይዘጋ ቀረ። ‘መደፈን ያለበት ደግሞ ግዴታ በህክምና ነው’ ተባለ።
ህመሙን ያወቅነው በ6 ወሩ ነው። አዳማ ኃይለማርያም ሆስፒታል ወሰድነወሰና የልብ ኬዝ እንዳለብ ነገሩን። ከዛም ወደ ጥቁር አንበሳ ሪፈር ፃፉልኝ። በሽታው እንዳይባባስበት በመድኃኒት እየተከታተለ ነው ያለው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ልበ ቀና ነው። በመረዳዳት የታወቅን ነን። ወገኖቼ አነሰ በዛ ሳትሉ በመተባበር ልጄን አድኑልኝ ” ሲሉ ተማጽነዋል።
ለመርዳት 1000045518586 የአቶ አማረ አለማዬሁ ደስታ የኮፕራትቭ COOP ባንክ ሒሳብ ቁጥር ሲሆን 1000263542979 የንግድ ባንክ ነው።
ለመደወል እና ዝርዝር ማስረጃዎችንም ለመጠየቅ 0915846447 የእጅ ስልካቸው ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
" በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ ኦፌኮ እንዲሳተፍ ጥሪ አቀርባለሁ " - ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈቱ ዘንድ አጀንዳዎች እያሰባሰበ መሆኑ ይታወቃል። ኮሚሽኑ እስካሁን በ10 ክልሎች አጀንዳ እንዳሰባሰበ፣ አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲዎች ግን አጀንዳቸውን በማስረብ ፋንታ ከኮሚሽኑ እንዳገለሉ መግለጻቸው ይታወሳል።…
" ኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ የሆኑት የቋንቋ፣ የወሰን ጥያቄዎች ይፈታሉ ብለን እናምናለ ፤ የአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ነው " - አባገዳዎቹ
የኦሮሚያ ክልል የምክክር ተሳታፊዎች የኦሮሞ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቅ የነበረው ጥያቄ መልስ እንዲያገኝለት አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ አባገዳዎች ጠየቁ፡፡
አባ ገዳዎች ይህን የጠየቁት ዛሬ በአዳማ ከተማ የ ሀገራዊ ምክክር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት የመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ ነው፡፡፡
አባ ገዳዎቹ " የኦሮሞ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች አንድም እንዳይዘነጉ " ሲሉ ለምክክሩ ተሳታፊዎች አሳስበዋል፡፡
" በምክክሩ የኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ ናቸው የተባሉት ፦
➡️ የቋንቋ፣
➡️ የወሰን ጥያቄዎች ይፈታሉ ብለን እናምናለን " ብለዋል፡፡
‘" የአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ነው " ያሉት አባገዳዎቹ ይህም በምክክሩ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡
የምክክሩ ተሳታፊዎች የወከሉት የኦሮሞ ህዝብ ተቆራርጠው የቀሩት ፦
- የመሬት ጥያቄዎች፣
; የወሰን ጥያቄዎች እንዲፈቱ አጀንዳ ሆነው እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡
አፋን ኦሮሞ ቋንቋም የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆን አባ ገዳዎቹ ለተሳታፊዎቹ " አጀንዳ " አድርጋችሁ አቅርቡ ብለዋቸዋል፡፡
አባ ገዳዎቹ የኦሮሞ ህዝብ መልስ እንዲያገኝ ጠይቁ ባሉበት ወቅት፤ በምክክር ሂደት ላይ ለመሳተፍ በስታዲየም የተገኙት ሰዎች በጭብጨባና በፉጨት ድጋፋቸውን አሳይተዋቸዋል፡፡
በዛሬ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በተጀመረው የምክክር ምዕራፍ ከ356 ከክልሉ ወረዳዎች የተወከሉ ከ7,000 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወክለዋል፡፡
መረጃው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ የተወሰደ ነው።

" የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ ቀጣይነት ይኖረዋል " - የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናቶች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ዋቢ በማድረግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳውቋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣…
" የዘንድሮው ቅዝቃዜ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጠንከር ያለ ነው " - ባለሙያዎች
አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ አብዛኛው ስፍራዎች ሰሞኑን የተከሰተው ጠንከር ያለ ብርድ ከዚህ ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ እየተዳከመ እንደሚሄድ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
በዚህ ወቅት ከሳይቤሪያ በመነሳት ወደ ኢትዮጵያ በሚገባው ደረቅና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ጠንከር ያለው ቅዝቃዜ መከሰቱን የሚያስረዱት ባለሙያዎች የዘንድሮው ቅዝቃዜ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጠንከር ያለ መሆኑን አረገጋግጠዋል።
" ዘንድሮ ህዳር መጨረሻ አከባቢ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ነው ያለው፡፡ አሁን ደግሞ ያለንበት ታህሳስ ወር በጣም የባሰበት ቅዝቃዜ እያስተዋልን ነው " ብለዋል አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ።
አዲስ አበባ ውስጥ በተለይ ካለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ጀምሮ አሁን እስካለንበት ታህሳስ ወር ከተለመደውም ጠንከር ያለ ከፍተኛ ብርድ ተስተውሏል፡፡
የሜትዮሮጂ ባለሞያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ዓመታዊ የአየር ጠባይ ወቅቶችን ፦
- ክረምት፣
- በጋ
- በልግ በማለት በሶስት ይከፍሉታል፡፡
የወቅቶቹን ባህሪያት የሚወስኑትም በካባቢ አየር ውስጥ፣ በየብስ እና በውሃ አካላት ላይ የሚፈጠሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች እንደሆኑ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
በኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ከጥቅምት እስከ ጥር ወራት ያሉትን የሚሸፍነው አሁን የምንገኝበት በጋ ተብሎ የሚጠቀሰው ወቅት ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች ደረቅና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋልበት ነው ብለዋል።
" ይህ ወቅት ለአብዛኛው የአገራችን አከባቢዎች፤ ለአብነትም ለትግራይ፣ አፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አብኛው የኦሮሚያ እና ማዕከላዊና ምስራቃዊ የኢትዮጵያ አከባቢዎች በዚህ በበጋ ወቅት የበጋ ደረቃማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታዎች የሚያመዝንበት ወቅት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
በተለይ ከሳይበሪያ የሚነሳው ደረቅና ነፋሻማ የአየር ጠባይ በነዚህ አከባቢዎች ለሚስተዋለው የአየር ጠባይ ወሳኙን ሚና እንደሚጫወቱ የሚያነሱት ባለሙያው በተጠቀሱት አንዳንድ አከባቢዎች በሚከሰት ከፍተኛ ቅዝቃዜ የሙቀት መጠኑ ከአንድ ድግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚወርድ ጠቁመዋል።
ዘንድሮ አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ አከባቢዎች ከባለፈው ዓመት እንኳ ሲነጻጸር ጠንከር ያለ የማለዳ ቅዝቃዜ አሁን መስተዋሉን አንስተዋል፡፡
" በተለይም አዲስ አበባን ከባለፈው በጋ 2016 ዓ/ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር አነጻጽረን ስንመለከተው የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ10 ወደ 6.6 ድግሪ ሴንትግሬድ ዝቅ ብሎ ተመልክተናል " ብለዋል።
" በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች አከባቢዎች ላይ የማለዳው ቅዝቃዜ ማለዳ ላይ መጠናከሩን ተመልክተናል " ሲሉ አስረድተዋል።
ይህ ከሳይበሪያ ላይ በመነሳት ወደ አገሪቱ ስገባ የነበረው ደረቅና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በመጠናከሩ ነው ብለዋል፡፡
ይህ ቅዝቃዜ እስከ ታህሳስ ወር አጋማሽ ድረስ እንደሚቀጥልና ከታህሳስ 13 በኋላ ግን የቅዝቃዜ መጠኑ እየተዳከመ እንደሚሄድ አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ብርዱ በጥቅምት ላይ እንደሚጠነክር፤ ዘንድሮ ግን ከህዳር መጨረሻ ጀምሮ አሁን እስከ ምንገኝበበት ታህሳስ ወር የተጠናከረበትን ምክንያት የተጠየቁት ባለሙያው፤ ባለፈው ግንቦት ወር የተሰጠውን የአየር ሁኔታ ትንቢያ ማስታወስ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡
" የክረምቱ ዝናብ አወጣጥ ሊዘገይ እንደሚችል ባለፈው ግንቦት 2016 ኣ.ም. አንስተን ነበር " ያሉት ዶ/ር አሳምነው፤ እስከ ህዳር አጋማሽ ከበርካታ አገሪቱ አከባቢዎች ያልጠፋው ዝናብና ደመና ወበቅ በመፍጠሩ የቅዝቃዜውን ወቅት ወዲህ መግፋቱን አስረድተዋል፡፡
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#ጥንቃቄ
ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ በተለይም ኮድ 3 እና ኮድ 2 መኪና ይዘው እየተነቀሳቀሱ ሰዎችን የሚዘርፉ የዘነጡ ሌባዎች በከተማይቱ እንዳሉ በተለያዩ ቦታዎችም ዜጎች እየተዘረፉ መሆኑን ጥቆማ ሰጥተናችሁ ነበር።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ አንድ መረጃ አጋርቷል።
መረጃው ምን ይላል ?
በተሽከርካሪዎች ላይ ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር በመለጠፍ ቅሚያ ሲፈጽሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች እንደተያዙ ይገልጻል።
ተጠርጣሪዎቹ ተሽከርካሪ #በመከራየት በቂርቆስ፣ በቦሌ እና በጉለሌ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ ሞባይል ስልክ እየቀሙ እንደሚሰወሩ ፖሊስ ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል፡፡
ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ/ም በቂርቆስ ክ/ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው በተለምዶ " ወሎ ሰፈር " እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ተጠርጣሪዎቹ በኮድ 2 A-28629 አአ በሆነ ተሽከርካሪ ላይ ኮድ 3 B-35824 አአ የሚል ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር ለጥፈው ግምቱ 12 ሺህ ብር የሚያወጣ አይነቱ ሳምሰግ ሞባይል ቀምተው ይሰወራሉ።
ወንጀሉን በፈፀሙ በአንድ ሰዓት ልዩነት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ጉለሌ ሸገር አካባቢ ከአንድ ግለሰብ ላይ 8 ሺህ ብር የሚገመት ቴክኖ ሞባይል ይቀማሉ፡፡
የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል ፈፃሚዎችን ለመያዝ በክትትል ላይ እያለ ወንጀሉን በፈጸሙበት እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።
በተመሳሳይ ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎች በኮድ 2C -28629 አዲስ አበባ በሆነ ተሽከርካሪ ላይ ኮድ 3A-21634 አዲስ አበባ የሚል ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር በመለጠፍ በተመሳሳይ የቅሚያ ወንጀል ለመፈፀም በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 " ሸዋ ዳቦ " አካባቢ ተይዘዋል።
በተሽከርካሪ ውስጥ ከተለያዩ ግለሰቦች የተቀሙ ሶስት ሞባይሎች የተገኙ ሲሆን ከሶስቱ ተጠርጣሪዎች መካከል አንደኛው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ሲሆን ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ በቀን ገቢ ተሽከርካሪዎችን በመከራየት እና ሀሰተኛ የሰሌዳ ቁጥር አዘጋጅተው በመለጠፍ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ ወንጀል ሲፈፅሙ መቆየታቸውን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል።
የሞባይል ቅሚያ የተፈፀመባቸው ግለሰቦች ቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ንብረታቸውን መረከብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
ተሽከርካሪን ማከራየት የሚቻለው የህግ አግባብን ተከትሎ መሆን ስላለበት መኪና የሚያከራዩ ባለንብረቶች ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገበ ፖሊስ አሳስቧል።
ህብረተሰቡ ተመሣሣይ የወንጀል ድርጊት እንዳይፈፀም ተገቢውን ጥንቃቄ ከማድረግ ባሻገር አጠራጣሪ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ቁጥር ካጋጠመው ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

መኪኖቻችሁን ለማን እንደምታከራዩ ለማንስ እንደምታውሱ እወቁ ፤ ተጠንቀቁ !
@tikvahethiopia
#ዶክተርበየነአበራ👏
" ባለቤቴን ጨምሮ ጓደኞቼና ጓደኞቿ ለሙያው ያለኝን ፍቅርና ቁርጠኝነት ስለሚያዉቁ ሊጫኑኝ አልፈለጉም " - ዶ/ር በየነ አበራ
በሰርጉ ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች ከጠሩት የመልስ ፕሮግራም ላይ ላይ ተነስቶ በመሄድና የተሳካ ቀዶ ሕክምና በማድረግ እናትና ልጅን የታደገዉ የማህፀንና ፅንስ ስፖሻሊስቱ ዶክተር በብዙዎች ምስጋና ተችሮታል።
ይህ የሚያስመሰግን ተግባር የተፈጸመው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው።
በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር በየነ አበራ በትላንትናው ዕለት በሰርጋቸው ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች በጠሩት የመልስ ዝግጅት ላይ ነበሩ።
በዚህ ዝግጅት ላይ እንዳሉ ነው ከሚሰሩበት ሆስፒታል የስልክ ጥሪ የደረሳቸው።
የስልክ ጥሪውም እናትና ልጅን እንዲታደጉ የቀረበ ነበር።
ዶክተር በየነ ስለሁኔታው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲናገሩ " መልስ በሀገራችን ባህልና ወግ ትልቅ ቦታ እደሚሰጠዉ አዉቃለሁ በዕለቱ አማቾቼ አክብረው ጠርተዉን ፕሮግራሙ እየተካሄደ ነበር ስልክ የተደወለልኝ " ብለዋል።
" የመጀመሪያውን ዙር አላነሳሁም ፤ በድጋሚ ሲደወልልኝ አነሳሁት አንዲትን እናት ምጥ እንዳስቸገራትና ቀዶ ሕክምና የግድ እንደሚያስፈልጋት ተነገረኝ፤ ለመሄድ አላመነታሁም " ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።
በኃላም ዶክተር የመልስ ዝግጅቱን አቋርጠው የእናት እና ልጅን ሕይወት ለመታደግ እየከነፉ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ይወስናሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ጉዳዩን እንዴት ለሙሽሪት እንዳስረዱና ሙሽሪትን እንዳሳመኗት ጠይቋቸዋል።
እሳቸውም ፤ " በፍቅር ሕይወታችን ወቅት የትዳር አጋሬን በተደጋጋሚ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በተደጋጋሚ እነግራት ነበር፤ በሰርግ መልሳችን ቀን ግን ይሆናል ብዬ አሰቤ አላዉቅም ነበር " ብለዋክ።
" ለሙሽራዋ ባለቤቴና ለሚዜዎቼ ነገርኳቸዉና ወደ ሆስፒታሉ አመራሁ። ባለቤቴን ጨምሮ ጓደኞቼና ጓደኞቿ ለሙያው ያለኝ ፍቅርና ቁርጠኝነት ስለሚያዉቁ ሊጫኑኝ አልፈለጉም " ሲሉ ተናግረዋል።
ዶክተር በየነ " ቤተሰቦቿን ግን ተመልሼ ይቅርታ ለመጠየቅ ወስኜ ነበር ወደ ሆስፒታል የሄድኩት " ብለዋል።
" ወደ ሆስፒታሉ ስደርስ የቀዶ ሕክምና ቲሙ ዝግጁ ስለነበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌ ቀዶ ሕክምናውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ዶክተር በየነ አበራ የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉን በሕክምና ትምህርት ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ያገኙ ሲሆን የስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ደግሞ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል።
#TikvahEthiopia
Via @TikvahethMagazine

#AAiT
Call for Applications in MSc and PhD Programs 2024/25 Second Semester
1. Computer Engineering - MSc and PhD
2. Communication Engineering - MSc and PhD
3. Control Engineering - MSc and PhD
4. Electrical Power Engineering - MSc and PhD
School of Electrical & Computer Engineering, Addis Ababa University,
Application Deadline for GAT: Friday December 20, 2024
More information, see our channel https://yangx.top/TrainingAAiT or check application procedure here.
Email: [email protected]

#BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ
ጊዜያዊ መቸገር ወደ ኋላ አይጎትትም! ምክንያቱም ከአፖሎ እስከ መቶ ሺህ ብር ድረስ በመበደር ስራን ማቀላጠፍ ይቻላል።
አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ ይጠቀሙ።
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

ወደ ኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች መግባት እንዲችሉ የሚፈቅደው አዋጅ ፀድቋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲሳተፉ የሚፈቅደውን የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ ዛሬ አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።