TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ምንድነው ያስተላለፈው ውሳኔ ?

💡" ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር  ውሳኔ ተላልፏል ! "

🌃 " ዋና እና መጋቢ መንገድ ላይ የሚገኙ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል ! "

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

የተለያዩ አጀንዳዎች ላይም ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

ከነዚህም አንዱ ፥ በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚል ነው።

ሌላኛው የምሽት ትራንስፖርትን ይመለከታል።

በዚህም ከተማ አስተዳደሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ መርምሮ በመወያየት በመንግስት እና  የግል አጋርነት (PPP) እንዲተዳደሩ ብሎም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ ተብሏል።

በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ተወስኗል።

ከዚህ በተጨማሪ ካቢኔው ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር  ውሳኔ ተላልፏል።

በተጨማሪ ካቢኔው ፦

- የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጤና፣ ፅዳት እና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ ስለሆነ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

- በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፣ አፈፃፀም ቁጥጥር እና ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የፈረሙት ሁለቱ አገራት ናቸው፣ እኛ ሶማሊላንድ ነን ! " - ሞሐመድ ፋራህ አብዲ

ሶማሌላንድ ስለ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ምን አለች ?

በአንካራው ስምምነት ዙሪያ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ (ኢሮ) ዋዳኒ ፓርቲ ቃል አቀባይ ሞሐመድ ፋራህ አብዲ የሶማሌላንድ መንግሥትን አቋም ለቢቢሲ ሶማሊኛ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ፤ " የፈረሙት ሁለቱ አገራት ናቸው፣ እኛ ሶማሊላንድ ነን። ሁለቱ ወንድማማች አገራት የራሳቸውን ስምምነት ነው የተፈራረሙት። እነሱ ተነጋግረው ከስምምነት ላይ መድረሳቸው የተለመደ ነገር ነው። እኛን የሚመለከት አይደለም " ብለዋል።

በተጨማሪ ቀደም ሲል በሶማሊላንድ ሥልጣን ላይ የነበረው መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ያለበትን ሁኔታን በተመለከተ ተናግራዋል።

ሞሐመድ ፋራህ ፥ " ገና ሥልጣን መረከባችን ነው፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን ስምምነት አልተመለከትነውም። ነገር ግን የምናየው ይሆናል፤ አይተነው የሶማሊላንድን ጥቅም የሚያስጠብቅ ከሆነ እንሠራበታለን፤ ካልሆነ ግን የሚቀር ይሆናል። ስለዚህ ምን እንሚሆን ለማወቅ መጠበቅ አለብን፣ ከዚያ በኋላ ውሳኔ ይሰጥበታል " ብለዋል። #BBCSOMALI

@tikvahethiopia
#ደመወዝ

🚨 " የሚከፈለው ክፍያና እንከፍላለን ብለው የሚያሳውቁት በጣም የሚያስቅ ልዩነት ያለው ነው " - ገቢዎች ቢሮ

🔴 " ቢሮው የፈጸመው ህገወጥ ድርጊት ነው " - የህግ ምሁር


የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሆቴሎች እና መጠጥ ቤቶችን ጨምሮ በተመረጡ የንግድ መስኮች የሚሰሩ ሰራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እና የሰራተኞቻቸውን ብዛት የሚተምን ተመን አውጥቶ ስራ ላይ አውሏል።

ሆቴሎች፣ ስጋ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች ፣ ምግብ ቤቶች፣ ካፍቴሪያዎችን ጨምሮ ሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ የሰራተኞች ደመወዝን በተመለከተ አሰሪዎች ትክክለኛ መረጃ ስለማይሰጡ ግብር እያጭበረበሩ ነው ብሏል።

ይህንን ተከትሎም ነው ይህን አሰራር መዘርጋቱን ገልጻል።

ስራ ላይ በዋለው ተመን መሰረት ፦
👉 የሆቴሎች ከ32 እስከ 50 ሰራተኞች
👉 ባርና ሬስቶራን ከ20 እስከ 24 ሰራተኞች
👉 ካፍቴሪካ ከ17 እስከ 25 ሰራተኞች
👉 ምግብ ቤት ከ17 እስከ 22 ሰራተኞች
👉 ምግብ፣ መጠጥ እና ስጋ ቤት ከ28 እስከ 48
👉 ስጋ ቤት እና መጠጥ ንግድ ከ20 እስከ 28 ሰራተኞች ይኖራቸዋል ተብሎ ተተምኗል።

በዚህ መሰረት የደመወዝ ግብር በተጠቀሰው የሰራተኛ ቁጥር ልክ ይጠየቃሉ።

ከአስተናጋጅ፣ ጥበቃና የፅዳት ሙያ ውጭ ላሉ ሰራተኞች ትንሹ የሚከፍሉት ደመወዝ 5,000 ብር ሆኖ ተተምኗል።

የወር ደመወዝ ተመኑ ምን ይመስላል ?

ስጋ ቤት እና መጠጥ ንግድ
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ5,000 እስከ 9,500
° ካሸር 5,000 እስከ 6,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,000 እስከ 18,000
° አስተናጋጅ ከ3,000 እስከ 3,500
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ2,500 እስከ 3,000
° ዋና ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 7,000
° ረዳት ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 5,500
° ስጋ ጠባሽ ከ6,000 እስከ 9,000

ምግብ፣ መጠጥ እና ስጋ ቤት
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ8,000 እስከ 13,500
° ካሸር 5,000 እስከ 7,000
° ዋናው ሼፍ ከ6,000 እስከ 18,000
° አስተናጋጅ ከ2,500 እስከ 4,000
° ፅዳት ከ3,000 እስከ 3,500
° ጥበቃ ከ3,500 እስከ 4,000
° ዋና ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 6,000
° ረዳት ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 5,500
° ስጋ ጠባሽ ከ6,000 እስከ 9,000

ምግብ ቤት
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ / ከ6,000 እስከ 10,000
° ካሸር 5,000 እስከ 6,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,000 እስከ 7,000
° አስተናጋጅ ከ2,000 እስከ 3,000
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ2,500 እስከ 3,000

ካፍቴሪያ
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ6,000 እስከ 7,000
° ካሸር 5,000 እስከ 7,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,500 እስከ 7,000
° አስተናጋጅ ከ2,500 እስከ 3,000
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ2,500 እስከ 3,000
° ሻይ ቡና / ጁስ አስተናጋጅ ከ5,000 እስከ 8,000

ባርና ሬስቶራንት
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ7,000 እስከ 10,000
° ካሸር 5,000 እስከ 6,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,000 እስከ 7,000
° አስተናጋጅ ከ2,000 እስከ 2,500
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ3,000 እስከ 3,500

ሆቴል
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ8,000 እስከ 13,500
° ካሸር 5,000 እስከ 7,000
° ዋናው ሼፍ ከ6,000 እስከ 18,000
° አስተናጋጅ ከ2,500 እስከ 4,000
° ፅዳት ከ3,000 እስከ 3,500
° ጥበቃ ከ3,500 እስከ 4,000
° ዋና ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 6,000
° ረዳት ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 5,500

ወርሃዊ ደመወዝ ተተምኗል።


ይህ ለአንድ ሰራተኛ ይከፈላል ተብሎ የተተመነ ነው።

በዚህ ተመን ባለቤቶቹ የደመወዝ ግብር ሲከፍሉ ለተጠቀሱት የስራ መደቦች " ከዚህ ያነሰ ነው የምከፍለው " ማለት አይችሉም።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ምን አሉ ?

ቢሮው ተመን ማውጣቱን አረጋግጠዋል።

ዳይሬክተሩ " በጥናት ላይ ተመስርቶ ነው ውሳኔው የተቀመጠው።

ከደመወዝ ግብር ጋር በተያያዘ የሚከፈለው ክፍያና እንከፍላለን ብለው የሚያሳውቁት በጣም የሚያስቅ ልዩነት ያለው ነው። በጣም ትልቅ ክፍተት ነው ያለው እኛ በከተማችን ያሉ የስራ መደቦችን በዝርዝር ጥናት አድርገን አብዛኛው በትንሹ የሚከፈላቸው ከ5000 ብር በላይ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።

ለፅዳት እና የቤት ሰራተኛ እንኳን ስንት እንደሚከፈል ይታወቃል።

እነሱ እንከፍላለን ብለው የሚያቀርቡት ዋጋ በጣም በጣም ዝቅተኛ ነው። ያንን ምንቀበልበት ሁኔታ የለም አሰራሩም አይፈቅድም። ጥናት ላይ ተመስርተን ዝቅተኛውን ተመን አስቀምጠናል " ብለዋል።

ገቢዎች ቢሮ ከተማውን የምታመነጨውን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ ኃላፊነት እንደተጣለበትና በዚህም ምክንያት ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን ስራ ላይ እንዳዋለ አሳውቋል።

ጉዳዩ በሚመለከተው አካል ህግ ሆኖ ሳይወጣ ገቢዎች ቢሮ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን አስቀምጦ ግብር መሰብሰብ ይቻላል ወይ ? የሚለው የህግ ጥያቄ ተነስቶበታል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ንግድና የኢኮኖሚ ህጎች መምህር አቶ ጌዲዮን ወ/ዮሐንስ ምን ይላሉ ?

" ድርጊቱ ህገወጥ ነው።

እስካሁን ባለው ነባራዊ  ሁኔታ በገቢዎች በኩል አነስተኛ ደመወዝን መወሰን ያንን ተከትሎ ግብር መሰስበብ እስካሁን ባለው የህግ ማዕቀፍ ይህንን የሚፈቅድ ነገር ስለሌለ ህጋዊ አይደለም።

በተለይ ከግብር ጋር ተያይዞ ህገመንግስቱ ግብር የሚጣለው በህግ ነው ይላል። በአንድ አስፈጻሚ / በአንድ የስራ ክፍል ኃላፊ ወይም እንደ ገቢዎች ቢሮ አይነት ደብዳቤን መሰረት አድርጎ ደመወዝን መወሰን አይቻልም።

ደመወዝ ግብር የሚከፈልበት አንድ ገቢ ነው። ይሄም ታክስ ቤዝ / ግብር የሚጣልበት አንድ ገቢ እንለዋለን። እሱ በህግ ተወስኗል። ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ከዚህ እስከዚህ ሲሆን ይሄን ያህል ... ከዚህ እስከዚህ ይሄን ያህል ... ብር እየተባለ በግብር አዋጃችን ላይ ተቀምጧል።

በዚህ በገቢ ግብር አዋጅ ላይ በተለያዩ የስራ ክፍሎችና አይነቶች የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዝቅተኛውን የደመወዝ መጠን ለመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል የሚል ህግ የለም ኢትዮጵያ ላይ።

በህግ ባልተከለከለበት / አይቻልም ባልተባለበት ሁኔታ አንድ ሰው 10,000 ብር ነው ዝቅተኛ መቅጠር የምትችለው ፣ በ8,000 ነው በ18,000 እያሉ ሰንጠረዥ ማውጣት የሰዎችን የመዋዋል ነጻነት ይጎዳል።

ድርጊቱ፦
- የመዋዋል ነጻነትን የሚገድብ
- ህገመንግስታዊ ድንጋጌን የሚጥስ ተግባር ነው።

ቢሮው ' ግብር እየተጭበረበርኩ ነው ' ብሎ ካሰበ የተለያዩ የምርመራ ስራዎችን በመስራት ፣ የስራ ውሉን ከአሰሪዎቹ በመቀበል ይሄም ደግሞ በህግ አነስተኛ ደወመዝን በማውጣትና በመደንገግ ነው። እንጂ የግብር ማጭበርበር ለመከላከል ተብሎ የገቢ ግብርን በዚህ መንገድ ለማስተዳደር መሞከር የታክስ ህግን፣ መርሆችን የሚጥስ ነው። "

NB. በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ መንግሥት ለግሉ ዘርፍ ለተቀጣሪዎች ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል አላስቀመጠም። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲያስቀምጥ ጥረቶች እየተደረጉ እነደሆነ ይታወቃል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው። #ሸገርኤፍኤም

@tikvahethiopia
ስኬት ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል አካሂዷል፡፡

በጉባኤው ላይ የስኬት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን ወርቁ የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ለባለ አክሲዮኖች ያቀረቡ ሲሆን ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ያገኘው የተጣራ ትርፍ 1.54 ቢሊዮን ብር መሆኑን ገልፀዋል፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ50 በመቶ ብልጫ አለው፡፡

ባንኩ ያገኘው አጠቃላይ ገቢ 2.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን ይህም ከባለፈው ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ42 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ በ2023/24 በጀት ዓመት አጠቃላይ ካፒታሉ 7.9 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ31 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 15.9 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ30 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ ስኬት ባንክ አጠቃላይ የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 537,428 ማድረስ የቻለ ሲሆን ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ17 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

በበጀት አመቱ የባንኩ ዋና መ/ቤትን ጨምሮ ሁሉንም ቅርንጫፎች በTemenos T24 core banking ሲስተም ማስተሳሰር ተችሏል፡፡ በሌላ በኩል ለደንበኞቹ አስተማማኝና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት Tier Three የተባለ ዘመናዊ የሆነ የመረጃ ማዕከል በመገንባት ወደ አገልግሎት አስገብቷል፡፡ በተጨማሪም የማህበራዊ ኃላፊቱንት ለመወጣት ከባንኩ እና ከሰራተኞች በማስተባበር በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 10 ሚሊዮን ብር በማውጣት ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ማህበራዊ ግልጋሎቶች እንዲውል ተደርጓል፡፡

ስኬት ባንክ
የስኬትዎ መሰረት!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ንጉስማልት

የንጉስ ማልት ጠርሙስን በስክሪን ሾት ይይዙት ይሆን? በመጀመሪያ ሙከራ ያገኛችሁትን በፌስቡክ ወይም በቴሌግራም ቻናሎቻችን ያጋሩን!

https://fb.watch/wiDa1wrfDa/ https://yangx.top/Negus_Malt


#nonalcoholic #ንጉስማልት #DesDesWithNegus #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት
#MPESASafaricom

ከM-PESA ወደ የትኛውም የነጋዴ የባንክ አካውንት መክፈል ተችሏል ፤ በM-PESA ሁሌም ሽልማት ሁሌም ቅናሽ አለ!

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details... የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://yangx.top/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://yangx.top/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የመምህራንድምጽ #Update " ሰባቱን ፍርድ ቤት ዋስትና እያስሞሉ ነው። ሌሎቹን ደግሞ ፈተዋቸዋል " - የኮሬ ዞን መምህራን ማኀበር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ያለፈቃዳቸው ከደመወዛቸው የተቆረጠ ገንዘብ እንዲመለስ በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑና የክልሉ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው የሚታወስ ነው። በአጠቃላይ ታስረው የነበሩት ከ66 በላይ…
“ ገንዘቡ ይመለስ አይመለስ የሚለው ገና ውሳኔ ላይ አልደረስንም ” - የኮሬ ዞን ትምህርት መምሪያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ከደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው የተቆረባቸው ገንዘብ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑና የክልሉ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

ከታሰሩት መምህራን መካከል የተደበደቡ እንደነበሩና የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተው ታሳሪዎቹ መፈታታቸውን የዞኑ መምህራን ማኅበር ገልጾልን ነበር።

እስራቱ ለምን እንደተፈጸመ በወቅቱ የጠየቅነው የዞኑ ትምህርት መምሪያ፣ የመምህራኑ ደመወዝ የተቆረጠው የተማሪዎች መፅሐፍ ለማሳተም በተገባው በስምምነት እንደሆነ ነበር ምላሽ የሰጠው።

“ መምህራኑ የታሰሩት ድንጋይ በመወርወር ሌሎችን ረብሸዋል ” በሚል መሆኑን፣ መታሰራቸው ልክ ስላልሆነ በኋላም ውይይት ተደርጎ እንደተፈቱ ነበር የነገረን።

ጉዳዩ ከምን ደረሰ ?

የመምህራኑ ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ስንል የጠየቅነው የዞኑ መምህራን ማኅበር፣ ገንዘቡን የመመለስና አለመመለስ በተመለከተ ጉዳይ ገና በሂደት ላይ መሆኑን ገልጿል።

የመምህራኑ ጥያቄ  ያለፈቃዳቸው የተቆረጠው ገንዘብ እንዲመስላቸው መሻት ነበር፤ ገንዘቡ ተመለሰላቸው ? ሙሉ ለሙሉ ስምምነት ተፈጠረ ? ስንል ለዞኑ ትምህርት መምሪያ ጥያቄ አቅርበናል።

ትምህርት መምሪያው ምን ምላሽ ሰጠ ?

ገንዘቡ ተቆርጦ መፅሐፍ ታቶሞበታል። ግን ይሄንን ወደ ታች ወርደን ከመምህራኑ ጋር መወያዬት አለብን። ገንዘቡን ሰጡ መፅሐፉ ታትሞ መጥቷል። 

ስለገንዘቡ ገና አልተስማማንም። ወደ ታች ወርዳችሁ በጋራ እንወያይ የሚል አቅጣጫ ነው ያለው። ግርግሩ፣ እስሩ ተገቢነት እንደሌለው የማረጋጋት ሥራ ቢሰራ ይህን ያህል የተጋነነ አይሆንም ነበር ብለን ነው የተነጋገርነው።

ገንዘቡ ይመለስ አይመለስ በሚለው ገና ውሳኔ ላይ አልደረስንም።

የክልሉ መምህራን ማኀበር፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ የዞኑ ትምህርት መምሪያ፣ የዞኑ መምህራን ማኀበር፣ ችግሩ ተከስቶበት የነበረው የወረዳ መምህራንና አመራር ባለፈው ሳምንት ችግሩ ተከስቶበት የነበረ ቦታ ላይ ቁጭ ብለን ተነጋግረናል።

በመምህራን ማኀበርም፣ በወረዳ ጽ/ቤት በኩልም ችግር ነበር፤ በመምህራን በኩል ቀርቦ አመራር ጋር ተነጋግሮ ችግሩን ከመፍታት ጋር ችግሮች እንደነበሩ ገምግመናል።

መምህራኑ ‘ሳንንስማማ ነው ገንዘቡ የተቆረጠው’ የሚል ነበር የገለጹት። በኛ በኩል ደግሞ ሌሎች ሁለት መዋቅሮች በተመሳሳይ ተስማምተው ስላልቆረጡ ነው የሚለውን ነበር ስንገልጽ የነበረው።

በኋላ መተማመን ላይ ደርሰናል። ጉራማይሌ ነው የሆነው። የተስማማ አካባቢ አለ ያልተስማማ አካባቢ አለ። ችግሩ ይሄው ነበር። የተስማሙም፣ ተስማምተው ሲያበቁ አልተስማማንም ብለው ግርግር ውስጥ የተሳተፉም ነበሩ።

መምህራኑ ወደ መማር ማስተማር ገብተዋል። ችግሩ ምንድን ነው? የሚለውን ከማኀበሩ ጋራ ወደ ታች ወርደን የቀጣይ አቅጣጫ ልናስቀምጥ ተስማምተን፣ ክልሉም አቅጣጫ አስቀምጦ ነው የተለያየነው። ”


#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray : በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት የራሱን ምክር ቤት አቋቁሟል።

" የሃላቀርነት እና ወንጀል ቡድን " ሲል የገለፀውን በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን የህወሓት ቡድን በፅኑ ለመታገል ቆርጦ እንደተነሳ ገልጿል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት እስከ ቀጣዩ 14ኛው የደርጅቱ መደበኛ ጉባኤ የሚቆዩ ሊቀመንበር እና ምክትል ያቀፈ 7 አባላት ባሉት አስተባባሪ ኮሚቴ የሚመራ ም/ቤት አቋቁሟል።

የደርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር ማን አድርጎ እንደሰየመ ያልገለፀው መግለጫው  ፤ አስተባባሪ ኮሚቴው የቀጣይ 3 ወራት እቅድ ማዘጋጀቱ አስታውቋል።

ደርጅቱ 14 ኛ ጉባኤውን መቼ እንደሚያካሂድ ያልገለፀ ሲሆን የተመሰረተው ምክር ቤት አባላት ሁሉም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከሚመራው ህወሓት " አንሰለፍም " ብለው የተቆራረጡ ናቸው።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት በከተማና ገጠር ከክልል ፣ ዞን ፣ ወረዳ እና እስከ ቀበሌ ድረስ አደራጃጀቶች በመዘርጋት " የኃላቀርነት እና ወንጀል ቡድን " ሲል የገለፀውን በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት በፅኑ ለመታገል ቆርጦ መነሳቱ ገልጿል።

መላው የትግራይ ህዝብ ፣ የህወሓት አባላት ፣ የፀጥታ ሃይሎች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ በተለይ ወጣቶች ፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች እና የዳያስፓራ ማህበረሰብ ከጎኑ እንዲሰለፉ ጥሪ ያቀረበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " በሰላማዊ ትግል የትግራይን ህዝብ ጥቅም ለማስክበር እታገላለሁ " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " - ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ከድምጺ ወያነ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ፤ የትግራይ አመራሮች በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐበይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በወቅታዊ ጉዳይ በነበራቸው ቆይታ በክልሉ ጉዳይ የሃሳብ ልዩነት አልነበራቸውም ብለዋል፡፡

ነገር ግን " የትግራይ ፓለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ እያመራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" የፀጥታ ሃይሎች ከማንኛውም ጫና ነፃ ሆነው የህዝቡ ብሄራዊ ጥቅም ማረጋገጥ ይገባቸዋል " ሲሉ አክለዋል፡፡

በአዲስ አበባው ውይይት በደብረፅዮን (ዶ/ር) ይሁን በአቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት ልኡካን እንዲሁም የጊዚያዊ አስተዳደሩ ተወካዮች መካከል በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታና ችግሮች ዙሪካ ያለልዩነት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

በወቅቱ " የፌደራል መንግሰት የትግራይ ችግሮች እንዲፈቱ አላገዝክም " በማለት ወቀሳ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።

" የፌደራል መንግስት ' ጉባኤ እንድናካሂድ ፤ የትግራይ ፓለቲካ እንድናስተካክል ጊዜ ስጠን በማለት ዕድል እና ጊዚያችሁን አባክናቹሃል ' በማለት መልሶልናል " ሲሉ አብራርተዋል።

ሌተናል ጄነራሉ ፥ " በመሃከላችን እየታየ ያለው ክፉኛ መሳሳብ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዳይረጋገጥ ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቁያቸው እንዳይመለሱ አደገኛ መሰናክል ሆኗል " ብለዋል።

የፕሪቶሪያ ውል በይፋ የተቃወመ የለም ፤ በተግባር ግን ውሉን የሚያደናቅፍ አሉታዊ ተግባር የሚፈፀሙ አካላት አሉ ብለዋል።

" የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ በመተግበር ብቻ ነው አቃፊ መንግስት ማቋቋም የሚቻለው " በማለትም አስረግጠዋል።

" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እኛም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የፌደራል መንግስት ዓለምአቀፋዊ ወሰኖች የመጠበቅ እና የማስከበር ስልጣን አለው፤ ይህንኑ ስልጣኑ ተጠቅሞ በቦታው የሚገኙ የውጭ ሃይሎች አውጥቶ የግዛት አንድነት እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት ጠይቀናል " ብለዋል።

በዚህ ምክንያት " ' ከሃዲዎች ' በሚል ስማችንን ማጠልሸት ተገቢ አይደለም " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በፌደራል መ/ቤቶች የትግራይ ውክልና ባለመኖሩ ምክንያት የህዝቡ ድምፅ በተገቢው መንገድ ሊሰማ ባለመቻሉ ምክንያት ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልሉ ውክልና እንዲመለስ ለፌደራል መንግስት ጥያቄ መቅረቡን  ሌተናል ጀነራሉ አሳውቀዋል።

በተጨማሪ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል አንቀፅ 8 ዓለምቀፍ ወሰኖች በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ ስለሚያዝ ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ከኤርትራ እና ከሱዳን የሚያገናኙ ወሰኖች ጠባቂ ስለሌላቸው የውጭ ሃይሎች እየገቡ ግፎች እየፈፀሙ ፣ ወርቅ ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች ህገ-ወጥ ወንጀሎች እየተፈፀመባቸው በመሆኑ ወሰኖቹ በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ " ሲሉ መጠየቃቸውን አሳውቀዋል።

#Tigray #TPLF

@tikvahethiopia
" ለጥንቃቄ ሲባል መንገደኞች እና የበረራ ሠራተኞች በአስቸኳይ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደርጓል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የበረራ ቁጥሩ ET 612 የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ታህሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ በሚያደርገው በረራ ከተነሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞታል።

በዚህም አውሮፕላኑ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም አርፏል።

ለጥንቃቄ ሲባል መንገደኞች እና የበረራ ሠራተኞች በአስቸኳይ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ መደረጉን አየር መንገዱ አሳውዋል።

" ሁልጊዜም ለመንገደኞቼ ደህንነት ቅድሚያ እሰጣለሁ " ያለው አየር መንገዱ መንገደኞች ለደረሰባቸው መጉላላት አየር ይቅርታ ጠይቋል።

የቴክኒክ ችግሩ በመጣራት ላይ መሆኑንም ገልጿል።

@tikvahethiopia