TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Somaliland
አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ሶማሊለንድ ፤ ሀርጌሳ ገብተዋል።
አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ለተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱረህማን መሀመድ አብዱላሂ በአቶ ሙስጠፋ የተመራውን ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለዋቸዋል።
ልዑኩ በሀርጌሳ ቆይታው ተመራጩ አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱረህማን መሀመድ አብዱላሂ በዓለ ሲመት ላይ ይሳተፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሊ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል።
#Ethiopia #Somaliland
@tikvahethiopia

#Ethiopia #Somalia #Turkey ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው አንካራ ቱርክ ይገኛሉ። የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጽሕፈት ቤታቸው አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ከልዑካን ቡድናቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። በሌላ በኩል ፤ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሼክ መሐመድ አንካራ ይገኛሉ። እሳቸውም ከኤርዶጋን ጋር ተነጋግረዋል።…
#Ethiopia #Somalia
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ላይ ደረሱ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት በቱርክ አንካራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
(ዝርዝር መረጃዎችን ይጠብቁ)
@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ላይ ደረሱ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት በቱርክ አንካራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
(ዝርዝር መረጃዎችን ይጠብቁ)
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Somalia ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ላይ ደረሱ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት በቱርክ አንካራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። (ዝርዝር መረጃዎችን ይጠብቁ) @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ምን ተስማሙ ?
በቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አደራዳሪነት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ስምምነቱ " የአንካራ ስምምነት " ተብሏል።
ይህ ተከትሎ በወጣው የስምምነት ሰነድ የተስማሙባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ተቀምጠዋል።
ምንድናቸው ?
➡️ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መሪዎች አንዳቸው ለሌላኛቸውን ሉዓላዊነት ፣ አንድነት ፣ነፃነት እና የግዛት አንድነት ለማክበር ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።
➡️ በወዳጅነት እና በመከባበር መንፈስ ልዩነቶችን እና አከራካሪ ጉዳዮችን በመተው ፤ በመተጋገዝ ለጋራ ብልጽግና ለመስራት ተስማምተዋል።
➡️ ሶማሊያ በአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና ሰጥታለች።
➡️ ኢትዮጵያ የሶማሊያን የግዛት አንድነት ባከበረ ሁኔታ የባህር በር ተጠቃሚ መሆኗ / ወደ ባህር እና ' ከ ' ባህር / ሊያስገኝ የሚችለው ልዩ ልዩ ጥቅም ላይ ተማምነውበታል።
➡️ ሁለቱንም ተጠቃሚ ባደረገ ሁኔታ የንግድ ውል ይታሰራል።
➡️ ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና እና ቀጣይነት ያለው / ዘላቂ የባህር በር መዳረሻ / አክሰስ እንዲኖራት ስምምነት ላይ ተደርሷል ፤ ይህም በሉዓላዊ የሶማሊያ መንግሥት ስልጣን ስር የሚተገበር ነው።
ለዚህም የሚሆን ፦
- የኮንትራንት
- የሊዝ ውልን ጨምሮ ሌሎች ሞዳሊቲዎች ላይ በቀጣይ በቅርበት አብሮ ለመስራትና ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል።
ለነዚህ ዓላማዎች መሳካት በጥሩ እምነት ከየካቲት 2025 መጨረሻ በፊት የቴክኒካል ድርድር ለመጀመር ወስነዋል። ይህም በቱርክ አመቻችነት የሚሳለጥ ሲሆን በ4 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ስምምነት ይፈረማል።
ለዚህም ቁርጠኝነትና ለቃል ኪዳኑ ተግባራዊ መደረግ የቱርክን እገዛ በደስታ ተቀብለዋል።
➡️ በአተገባበር ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያሉ ልዩነቶችን በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ' እንደአስፈላጊነቱ ' በቱርክ ድጋፍ ለመፍታት ቃል ገብተዋል።
#TikvahEthiopia

#TecnoAI
ዘምኖ የሚያዘምኖ፣ ህይወቶን የሚያቀል፣ ከበርካታ አርቴፊሻል ቴክኖሎጂ ካመጣቸው ከፍ ያሉ ቴክኖሎጂዎች ጋር የሚያስተዋውቆት በኪስዎት ውስጥ ይዘውት የሚዞሩት ፕሮፌሽናል አጋዥ ቴክኖ ኤ አይ ወደ እርሶ እየመጣ ነው፡፡
ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡
https://www.tiktok.com/@tecnoet
@tecno_et @tecno_et

#Ethiopia🇪🇹
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በቱርክ አንካራ ፤ ከሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ጋር ያደረጉትን የፊት ለፊት ውይይትና ድርድር አጠናቀው ጥዋት አዲስ አበባ መግባታቸውን ከጠ/ሚ ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ምን ተስማሙ ? በቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አደራዳሪነት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ስምምነቱ " የአንካራ ስምምነት " ተብሏል። ይህ ተከትሎ በወጣው የስምምነት ሰነድ የተስማሙባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ተቀምጠዋል። ምንድናቸው ? ➡️ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መሪዎች አንዳቸው ለሌላኛቸውን…
ሶማሊያውያኑ ምን እያሉ ነው ?
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሶማሊያውያን በተለይም አክቲቪስቶች " ሀሰን ሼክ ሀገራችንን ሸጠብን ፤ በዲፕሎማሲ ተበልጦ አስበላን " ማለት ጀምረዋል።
ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉላዓዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነት ባከበረ ሁኔታ ዘላቂነት ያለው አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር ታገኛለች መባሉ የሶማሊያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አበሳጭቷቸዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ በX ቪላ ሶማሊያ ገጽ ስር ፤ ከወራት በፊት ሲያሞጋግሷቸው የነበሩትን ፕሬዜዳንታቸውን ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ላይ ውግዘት ማዝነብ ጀምረዋል።
እኚህ አስተያየት ሰጪዎች ምን እያሉ ነው ?
➡️ " ሀሰን ሼክ ባህራችንን ሸጠብን። ካደን ፤ ከሀዲ ነው "
➡️ " እንዴት በድርድሩ ላይ ሆነ በስምምነቱ ላይ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የባህር በር ለማግኘት የፈረመችው የመግባቢያ ስምምነት / MoU አልተነሳም ፤ በግልጽ ቀርቷል ለምን አልተባለም "
➡️ " አዋረደን ! ለሶማሊያ ጨለማ ቀን ነው "
➡️ " ስለ ኢትዮጵያ የቀጣይ የሰላም ማስከበር ተሳትፎ (ሶማሊያ ውስጥ) ለምን አለተነሳም "
➡️ " ዘላቂነት እና አስተማማኝ የባህር በር ኢትዮጵያ ስታገኝ ሶማሊያ በምላሹ ምን ታገኛለች ? "
➡️ " ሁሉንም ኢትዮጵያ የፈለገችውን ነው የተቀበልነው፤ ኢትዮጵያ በመረጠችው መንገድ ሄዳ ፤ በዚህም በዚያ ብላ ባህር በር ስታገኝ እኛ ምን አገኘን ? "
➡️ " ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲው እና ድርድሩ በልጣ ባህር በር አሳካች " ... የሚሉ አስተያየቶችን በመስጠት ፕሬዜዳንታቸው ላይ ውግዘት እና የስድብ ናዳ እያወረዱ ነው።
አንዳንዶቹ ከቦታው ይነሳልን ወደማለትም ገብተዋል።
120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ " በፍጹም የማልተወው የህልውዬ ጉዳይ ነው " ብላ በይፋና በድፍረት አደባባይ ከወጣች በኃላ ጉዳዩ ከፍተኛ አጀንዳ ሆኖ ዓለም አቀፍ መወያያ መሆን ችሏል።
ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ከተፈራረመች በኃላ ሶማሊያ አኩርፋ ብዙ ስትል ከርማለች ፤ ከኢትዮጵያ ጋርም ተጎረባብጣለች።
ፕሬዜዳንቷ እና አስተዳደራቸው በየጊዜው ወደ ሚዲያ እየወጡ ፦
- ከኢትዮጵያ ጋር በፍጹም አንነጋገርም፤
- የኢትዮጵያ ወታደሮች በሰላም ማስከበር ላይ አይሳተፉም፤
- እንድንነጋገር ከፈለገች MoU ቀዳ ጥላ በይፋ ይቅርታ ትጠይቅ ይህ ካልሆነ ኢትዮጵያን አንሰማትም፤
- በኢትዮጵያ ያሉ ታጣቂዎችን እንደግፋቸዋለን / እናስታጥቃለን፤
- ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ደሟን እንዳልገበረችላት የኢትዮጵያ እድገት እንቅልፍ ከሚነሳቸው አካላት ጋር እየሄደ ጥምረት ሲፈጥር
- ከኢትዮጵያ ለመነጋገር ቅድመ ሁኔታዎችን ሲደረድር ... ሲዝት ፣ ሲፎክር ከርሟል።
በመጨረሻ በቱርክ አሸማጋይነት አንካር ሄደው ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በስምምነቱ ይፋዊ ሰነድ ላይ ሆነ በመሪዎች መግለጫ ምንም ቦታ ላይ ስለ ሶማሊለንዱ MoU አለመነሳቱ ፤ ማብራሪያ አለመሰጠቱ እንዲሁም በግልጽ ተሰርዟል አለመባሉን በማንሳት " ኢትዮጵያ የምትፈልገውን አገኘች " በማለት ሶማሊያውያን በፕሬዜዳንታቸው ላይ ተነስተዋል።
#TikvahEthiopia
#Ethiopia🇪🇹
#Seaaccess

#JawarMohammed
" አልፀፀትም " / " HIN GAABBU "
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የገዘፈ ስም ካላቸው ፖለቲከኞች አንዱ የሆኑት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ መፅሀፍ ይዘው እየመጡ እንደሆነ ገለጹ።
የኢህአዴግን ስርዓት በሰላማዊ መንገድ በመታገል ስርዓቱ ሳይወድ በግዱ እንዲቀየር በማድረጉ ረገድ ግንባር ቀደሙን ድርሻ እንደሚይዙ የሚነገርላቸው አቶ ጃዋር መሀመድ ከዚህ ቀደም ሰፋ ያለ መፅሀፍ እየጻፉ እንደነበር መግለፃቸው ይታወሳል።
በመጨረሻም መፅሀፋቸው መጠናቀቁን እና ለአንባቢያ ሊደርስ መሆኑን አሳውቀዋል።
በቀጣይ ሳምንት ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ በሚዘጋጅ ዝግጅት መፅሀፉ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።
" አልፀፀትም " / " HIN GAABBU " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መፅሀፋቸው በርካታ እና ከዚህ ቀደም ይፋ ያላደረጓቸው ጉዳዮች የተዳሰሰበት እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።
አቶ ጃዋር መሀመድ ፦
° በኢትዮጵያ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የገዘፈ ስም ያላቸው ፤
° አሜሪካ ሆነው የኢህአዴግን ስርዓት በሰላማዊ ትግል በመጣሉ በኩል ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፤
° ' ለውጥ መጣ ' ተብሎ ወደ ሀገር ከገቡ በኃላ የሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከቀብር ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ሁኔታ ታስረው ለበርካታ ወራት በእስር ቆየተው መፈታታቸው ይታወሳል።
ፖለቲከኛው ከእስር ቤት ቆይታ በኃላ ቀድሞ የሚታወቁባቸውን ኃይለኛ ንግግሮችን እና ፅሁፎችን በመተው ዝምታን መርጠው ብዙ ጊዜያቸውን በመፅሀፍ ዝግጅት ላይ እንዲሁም በሀገሪቱ ያሉ ግጭቶች እንዲቆሙ የድርሻቸውን የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይነገራል።
ከእስር በኃላ ኢትዮጵያ እንዲሁም ኬንያ ናይሮቢ እየተመላለሱ የሚኖሩ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜያቸውን ግን ናይሮቢ ናቸው።
በኬንያ ፣ ናይሮቢ ገቢ የሚያገኙባቸውን ስራዎች ከመስራት ባለፈ እንደ ኢትዮጵያ ብዙ ሰዎች ሊያገኟቸው / ሊጠይቋቸው ስለማይመጡ በጥሞና ለማሰብ፣ ለማንበብ እና መፅሀፋቸውን ለማዘጋጀት ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ለመረዳት ተችሏል።
" አልፀፀትም / HIN GAABBU " የተሰኘው መፅሀፋቸው ቀጣይ ሳምንት ሀሙስ ናይሮቢ ውስጥ ላውንች ይደረጋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Somaliland
የአዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዱረህማን መሀመድ አብዱላሂ (ኢሮ) በዓለ ሲመት በሀርጌሳ እየተከናወነ ይገኛል።
በበዓለ ሲመቱ ላይ የቀድሞ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ፣ የቀድሞ ፕሬዜዳንት ዳሂር ሪያሌ ካሂን፣ የአሜሪካው አምባሳደር ሪቻርድ ሪሌይን ጨምሮ የሀገራት ዲፕሎማቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ሙስጠፋ ሙሁመድ በዚሁ የበዓለ ሲመት ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ትላንት ልዑካቸውን ይዘው ሀርጌሳ መግባታቸው ይታወሳል።
ከሶማሊያ ተነጥላ ላለፉት በርካታ አመታት ራሷን የምታስተዳድረው ሶማሊላንድ በሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲሁም ደግሞ በዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ምርጫ በግንባር ቀደምነት ትታወቃለች።
ቪድዮ፦ አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሮዜዳንት እና የቀድሞው ፕሬዜዳንት በፈገግታ ተሞልተው ወደ አዳራሽ ሲገቡ።

#DStvEthiopia
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የማንቼስተር ደርቢ በጎጆ ፓኬጅ💥
63ተኛውን ጨዋታዎቸውን የሚያደርጉት ሁለቱ ቡድኖች ማን ሲቲ 25 ጊዜ ሲያሸንፍ ማን ዩናይትድ 28 ጊዜ ድል አድርጓል! ሁለቱ ብድኖች 9 ጊዜ በአቻ ተለያይተዋል
🏆 ማን ሲቲ ከማን ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ጨምሮ 10 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በጎጆ ፓኬጅ በ400 ብር ብቻ በቀጥታ ይከታተሉ!
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው

" የጦር ሰፈሩን መልሰን ተቆጣጥረናል " - የጁባላንድ ባለስልጣናት
የሶማሊያ የፌዴራሉ ሰራዊት የጁባላንድ ከፊል ራስ ገዝ ክልልን ለቆ መውጣቱት ተነግሯል።
በሶማሊያ መከላከያ ሰራዊት እና በጁባላንድ ከፊል ራስ ገዝ ኃይሎች መካከል ትናንት ረቡዕ ከተቀሰቀሰ ዉጊያ በኋላ የሶማሊያ መከላከያ ግዛቲቱን ለቆ መውጣቱን የፌዴራሉ መንግስት ዛሬ አስታውቋል።
የመንግስት እና ወታደራዊ ባለስልጣናት በራስ ካምቦኒ ከተማ እና አካባቢው ለበርካታ ሰዓታት ለቆየው ዉጊያ የጁባላንድ ፕሬዜዳንት አህመድ ማዶቤን በግጭት ቀስቃሽነት ከሰዋል።
የጁባላንድ ባለስልጣናት ትናንት ግጭቱ ሲቀሰቀስ ባወጡት መግለጫ የፌዴራል ኃይሎች በድሮን የታገዘ ጥቃት ፈጽመውብናል ሲሉ ለግጭቱ መቀስቀስ የፌዴራል መንግስቱን ተጠያቂ አድርገዋል።
ከጁባላንድ ዛሬ የተሰማው ዜና ግን ከዉግያው በኋላ የፌዴራል ኃይሎች ጁባ ላንድን ለቀው መውጣታቸውን ነው የሚያመለክተው።
የጁባላንድ ባለስልጣናት ይህንኑ በሚያረጋግጠው መግለጫቸው " የጦር ሰፈሩን መልሰን ተቆጣጥረናል " ብለዋል።
የአካባቢው የፀጥታ ጥበቃ ምክትል ሚኒስትር አዳነ አህመድ " በመጨረሻም የጁባላንድ ወታደሮች ከቀትር በኋላ የራስ ካምቦኒ ከተማ ተቆጣጥረውታል " ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
በአንድ ቀን ዉግያው ከሁለቱም ወገኖች የተገደሉ ወታደሮች መኖራቸውን ያመለከተው የሮይተርስ ዘገባ ነገር ግን አኃዙን በተመለከተ መረጃ አለማግኘቱን ጠቅሷል።
በራስ ገዟ አስተዳደር የግንኙነት ችግር መፈጠሩንም ዘገባው አመልክቷል።
በጁባ ላንድ የተቀሰቀሰው ግጭት ከሶማሊያ ባሻገር ሶማሊያ ውስጥ አልሸባብን የሚዋጉት ኢትዮጵያ እና ኬንያን ያሳስባቸዋል።
መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ / ሮይተርስ ነው።