TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " - ማርክ ጉዬ
➡️ የእስልምና እምነት ተከታዩ ሳም ሞርሲም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ሳያደርግ ወደ ሜዳ ገብቶ ጨዋታውን አድርጓል !
ማርክ ጉዬ የተባለው እግር ኳስ ተጫዋች በድጋሚ ክንድ ላይ በሚጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " የሚል ፅሁፍ በመፃፍ ወደ ሜዳ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።
ክሪስታል ፓላስ ለተባለው ክለብ የሚጫወተውና የቡድኑ አምበል የሆነው ጉዬ ከቀናት በፊት ኒውካስል ዩናይትድ ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስን እወደዋለሁ " ብሎ ፅፎ በመግባቱ የሊጉን አስተዳዳሪዎች አስቆጥቶ ነበር።
ይኸው ተጫዋች ትላንት ምሽት ቡድኑ ኢፒስዊች ታውን ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባለው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ብሎ በመፃፍ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።
ባለፈው ቅዳሜ ከፃፈው " ኢየሱስን እወደዋለሁ ! " ከሚለው ፅሁፍ በኃላ ፉትቦል አሶሲዬሽን የተባለው የሊጉ አስተዳዳሪ " ኃይማኖታዊ ምልክቶች የእግር ኳስ ማሊያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ላይ መፃፍ ክልክል ነው " ሲል ለክለቡ እና ለአምበሉ ማስጠንቀቂያ ቢልክም ማስጠንቀቂያው ወዲያ በሉት ብሎ ትላንት ምሽት በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ሲል በመፃፍ ገብቶ ተጫውቷል።
የሊጉ አስተዳዳሪ ቅጣት ሊጥልበት ይችላል እየተባለ ነው።
በሌላ በኩል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነው ሳም ሞርሲ የተባለው የኢፒስዊች ታውን ተጫዋች ትላንትም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ያለበትን የአምበልነት መለያ ሳያደርግ ነው የገባው።
ተጫዋቹ " ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት ባለፈው ቅዳሜም ይህንን የግብረሰዶሞች ምልክት ሳያደርግ መግባቱ የሚዘነጋ አይደለም።
' እኩልነት እና ብዝሃነት ' በሚል ሰብሰብ በዓለም ላይ የግብረሰዶማውያንን እንቅስቃሴ ለማስተዋወቅ እና ሰዎች ጋር ለማድረስ የግብረሰዶማውያን ደጋፊዎች ብዙ አይነት መንገድ ይከተላሉ።
አንዱ ግብረሰዶማውያንን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ በተለይም ወጣት ተመልካቾች ያሉትን የእግር ኳስ ፍልሚያ ነው።
ከነዚህ የእግር ኳስ ፍልሚያዎች አንዱ ደግሞ በኢትዮጵያ / አፍሪካ ሆነ በዓለም ላይ ብዙ ተመልካች ያለውን እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነው።
በዚሁ ሊግ የሊጉ አስተዳዳሪ አካላት በ ' እኩልነት እና ብዝሃነት ' ሰበብ የክለብ አምበሎች ክንዳቸው ላይ የግብረሰዶማውያንን ምልክት እንዲያጠልቁ አድርገው ለግብረሰዶማውያን ማስታወቂያ እንዲሰሩ ያደርጋሉ።
ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ የሊጉ ፍልሚያ በሚጋጋልበት ወቅት ነው።
ግብረሰዶማውያን እና የነሱ ደጋፊዎች እጅግ በጣም ተወዳጁን የእግር ኳስ ፍልሚያን ተጠቅመው ግብረሰዶምን የሚያስተዋውቁት በልጆች ፣ ታዳጊዎች ፣ ወጣቶች ዘንድ ድርጊቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግና እነሱን ለማነሳሳት ነው።
#TikvahEthiopia
#Guehi #Christian #PremierLeague
#SamMorsy #Muslim
@tikvahethiopia

#MPESASafaricom
🎁 ስድስት ወር ሙሉ ዳታ እንደልብ! በየትኘውም ሰአት ያልተገደበ ፍጥነት እና ደስታ! ለረጅም ጊዜ የሚቆዩትን ሜጋ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 1,000 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ፏ እንበል! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም አስተማማኝ ኔትወርክ ጋር ወደፊት!⚡
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether

#Namibia
በናሚቢያ ምርጫ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት አሸንፈዋል፡፡
የገዢው ስዋፖ ፓርቲ (SWAPO) እጩ የሆኑት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋህ ከ57 በመቶ በላይ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አሳውቋል፡፡
ተቀናቃኛቸው ፓንዱሌኒ ኢቱላ ደግሞ 26 በመቶ ድምጽ አጊኝተዋል፡፡
የሎጂስቲክ ችግር እና በተወሰኑ አካባቢዎች የነበረን እስከ ሦስት ቀናት የዘለቀ የድምጽ አሰጣጥ መዘግየትን ተከትሎ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት ተቃዋሚው ኢቱላ አሳውቀዋል፡፡
በዚህም በመዲናዋ ዊንድሆክ ትናንት ማምሻውን ውጤቱ ይፋ ሲደረግ በርካታ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አልተገኙም ነበር፡፡
የውጤቱን ይፋ መሆን ተከትሎ " የናሚቢያ ህዝብ ሰላም እና መረጋጋትን መርጧል " ሲሉ ተመረጯ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡
SWAPO ፓርቲ አገሪቱ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣችበት እንደ አውሮፓውያኑ 1990 ጀምሮ በስልጣን ላይ ይገኛል፡፡
ተመረጯ ፕሬዝዳንት በቅርቡ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑ ሲሆን በተለያዩ የመንግስት ኃላፊነተች ላለፉት 25 ዓመታት አገልግለዋል፡፡
ተመረጯ ፕሬዝዳንት ከታንዛኒያዋ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሀሰን በመቀጠል በአፍሪካ ሁለተኛዋ ሴት ፕሬዝዳንት ይሆናሉ፡፡

“ ችግራችን ብዙ ነው። ዘርፈ ብዙ የሆነ ምላሽ ያስፈልገናል ” - ማኀበሩ
የአካል ጉዳተኞችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች መንግስትን ጭምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ ትኩረት እንዲሰጡ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል በአጽንኦት አሳሰበ።
የማኀበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ጥላሁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ብዙ ጉዳዮች ላይ ሕጎች የሉም። እንደሚባለው አይደለም። በቂና ተፈጻሚ ሕጎች አሉ ማለት አይቻልም” ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በዝርዝር ምን አሉ?
“ለምሳሌ ዓይነ ስውራንን በተመለከተ በተለይ ገጠር አካባቢ ያሉት ህፃናት ብሬል/የሚፅፉበት ማተሪያል ያስፈልጋቸዋል።
የኮሚፒዩተር አቅርቦት እንኳ ቢኖር ለመጠቀም የሚያስችል ስክሪን/ማንበቢያ ሶፍትዌር ያስፈፍጋል። ያ የለም።
በዘርፉ የሰለጠኑ ብሬል ማስተማር የሚችሉ መምህራን የሉም ለዓይነ ስውራን። መስማት የተሳናቸው ወገኖች ውስጥ የምልክት ቋንቋ የሚችል የለም ማለት ይቻላል።
በከፊል መስማት የተሳናቸው የመስሚያ መርጃ መሳሪያ ቢያገኙ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀልና መማር ይችላሉ። በተለይ በገጠር አካባቢ ያሉ ያሉ አካል ጉዳተኞች በባትሪ የሚሰሩ ጠንካራ ዌልቸሮችን ተደራሽ ማድረግ ያስፈልጋል።
ችግራችን ብዙ ነው። ዘርፈ ብዙ የሆነ ምላሽ ይፈልጋል። አመለካከትን፣ ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ ብዙ የሚቀሩ ሥራዎች አሉ።
➡️ የትምህርት መብት፣
➡️ የመስራት መብት፣
➡️ የተደራሽነት መብት፣
➡️ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት፣
➡️ የመኖሪያ ቤት መብት፣
➡️ ከቀረጥ ነጻ የአካል ጉዳተኞች መገልገያ እቃዎች አገር ወደ ውስጥ እንዲገቡ ከማድረግ የሚያስችል ሁኔታ፣
➡️ የአካል ጉዳተኞችን ሁኔታ በበላይነት የሚመራ ራሱን የቻለ ተቋም ከማቋቋም አኳያ፣
➡️ ሕጉን የሚጥሱ አካላት ላይ ተጠያቂ ማድረግን የሚያስችሉ ሁሉን አቀፍ አሰራሮች ያስፈፍጋሉ።
አንድ ጊዜ ሕግ ማውጣት ብቻም በቂ ላይሆን ይቻላል። ለምሳሌ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት ዐዋጅ የሚባል አለ። ከወጣ 17 ዓመታት ሆነው።
ነገር ግን በቂ በቂ መመሪያ እንኳ በየጊዜው እየተሻሻለለት አይደለም። ለማሻሻልም ምንም አይነት እንቅስቃሴ ተደርጎ አያውቅም” ሲሉ ተናግረዋል።
ከ20 ሚሊዮን በላይ የአካል ጉዳተኞች ከ90 በመቶ በላይ ህፃናት የትምህርት እድል እንደሌላቸው፣ 95 በመቶ ከድኀነት ወለል በታች እንደሚኖሩ፣ 98 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላቸው ወይም ተቀጥረው የማይሰሩ መሆናቸው ተነግሯል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#EthiopianInvestmentHoldings
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን ጨምሮ 8 ተቋማት ከአሁን በኃላ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንደሚተዳደሩ ተነገር።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 8 ተጨማሪ የመንግስት ድርጅቶችን በስሩ በማካተት ፖርትፎሊዮውን ማስፋቱን በላከልን መግለጫ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) በስሩ ከሚገኘትና ከሚያስተዳድራቸው የመንግስት የልማት ድርጅቶች በተጨማሪ 8 አዳዲስ ቁልፍ ተቋማትን በስሩ በማካተት የድርጅቶቹን ቁጥር ጨምሯል።
8ቱ ተቋማት እነማን ናቸው ?
- ኢትዮ ፖስት፣
- ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፐ
- የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት፣
- የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣
- የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣
- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣
- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን እና ለኢትዮ ፋርማ ግሩT ተጠሪ የሆኑት ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥቢታ ተቋምና ሺልድ ቫክስ ናቸው።
እነዚህ ቀደም ሲል ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ተጠሪ የነበሩት የልማት ድርጅቶች ከአሁን ጀምሮ በባለቤትነት የሚተዳደሩትና የሚመሩት በኢኢሆ ስር ሆኗል።
(ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

" እናንተም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የወጣችሁት፣ አታንገላቱን ወዴት እንደሚሄድ ንገሩን ብንል ምላሽ አላገኘንም ! ” - ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ
የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር እና የኦሮሚያ ክልል ም/ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደአ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ከፈቀደላቸው እና ዛሬ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከወጡ በኃላ በር ላይ ተይዘው እስካሁን ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል።
አቶ ታዬ ደንደአ በዋስ እንዲለቀቁ የወሰነው የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ባለፈው ሰኞ በዋለው ችሎት ነው።
ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ምን አሉ ?
" ከሰዓት በኋላ ወደ 11 ሰዓት ገደማ ላይ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤቱ በር ላይ ነው የተወሰደው ፤ እስካሁን ድረስ ወደየት እንደተወሰዱ ማወቅ አልቻልንም።
ሰኞ በዋለው ችሎት ይግባኝ ብሎ ስለነበር በ20 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቅ እና ጉዳዩን ከውጭ ሆኖ እንዲከታተል ተወስኖለት ነበር።
ለአንድ ዓመት ተለያይተን ስለነበር ጓጉተን ስንጠብቀው ነበር።
ከማረሚያ ቤቱ ከመውጣቱ በፊት በአካባቢው ሲቪል የለበሱ እና ማስክ ያደረጉ ሁለት የደኅንነት አባላት እንዲሁም ሌሎች የታጠቁ ሰዎችም ነበሩ። የፌደራል ፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱም ነበሩ።
ተለቆ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ሊወጣ ሲል ውጭ ላይ የነበሩት ያዙት።
ከጠዋት 5 ሰዓት አንስቶ በዋስ ይወጣል ብለን ስንጠብቅ ነበር።
እኔን ጨምሮ የተቀረው ቤተሰብ ማረሚያ ቤቱ ደጃፍ ላይ ነበርን።
ሲቪል የለበሱና ማስክ ያደረጉት ሁለት የደኅንነት አባላት ሲገቡ እና ሲወጡ፣ በስልክ በተደጋጋሚ ሲነጋገሩም እያየን ነበር።
ከእኛ ቀድመው ነው በፍጥነት ሄደው ደርሰው ነው የያዙት። ሲይዙት ግብግብ ነበር።
ለዚህ እንደተዘጋጁ የሚያሳዩ ብዙ እንቅስቃሴዎች ስለታዘብኩ፣ በሕግ አምላክ ይሄ ሰው ሊያመልጥ አይደለም፤ በዋስ ወጥቶ ጉዳዩን ከውጭ ሆኖ ሊከታተል ነው። እናንተም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የወጣችሁት፣ አታንገላቱን ወዴት እንደሚሄድ ንገሩን ብንል ምላሽ አላገኘንም።
በፓትሮል መኪና ነው የወሰዱት።
አሁን የት እንዳለ አላውቅም።
እዚ ነው ያለው መጥታችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ ያለንም አካል የለም።
በወቅቱ አንዱን ስጠይቅ ‘ ወዴት እንደምንወስደው አናውቅም፤ ይዛችሁት ኑ ነው የተባልነው ’ አሉኝ።
‘ለሌላ የሕግ ጉዳይ ይፈለጋሉ’ የሚል አንድ ቃል ብቻ ከፖሊስ ሰምቻለሁ። ጠመንጃ የያዙት ሁለቱ ግን ግብግብ ነው የጀመሩት።
እሱ (ታዬም) በወቅቱ ' ምንድን ነው የሆነው ነገር? ወዴት ነው የምሄደው? ' ብሎ ሲጠይቅ ሰምቻለሁ። ምላሽ ግን አልተሰጠውም።
የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አክብሮ ለመልቀቅ ቢወስንም የያዙት አካላት ከውስጥ መረጃ እየተከታተሉ ነበር።
የተሰጠው ወረቅት እንኳን ምን እንደሚል በውል ሳያነብ እና ሳይረዳ በቅርብ የነበረው ፓትሮል ውስጥ እየተገፈተረ ሄዷል።
የሕግ አካል እጅ ከሆነ ያለው ሊደወለልን ይችላል ብለን እናስባለን። ካልሆነ ደግሞ አድረን እንፈልጋለን " ብለዋል።
የአቶ ታዬ ደንደአ የፍርድ ሂደት ምን ይመስላል ?
° አቶ ታዬ ባለፈው ዓመት ታኅሣሥ ወር መጀመሪያ ላይ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
° ዐቃቤ ሕግ 3 ተደራራቢ ክሶችን ባለፈው ዓመት ሚያዚያ 2016 ዓ. ም. መስርቷል።
° ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት፣ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እንዲሁም የጦር መሣሪያ ሕጉን በመተላለፍ ወንጀሎች ተከሰዋል።
° የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ከዚህ ቀደም ከሦስቱ ክሶች መካከል በሁለቱ፣ ሁከት እና ብጥብት በማነሳሳት እና የፀረ- ሰላም ኃይሎችን ድጋፍ ማድረግ ክሶች በነጻ አሰናብቷቸዋል።
° የጦር መሣሪያ ወንጀሎችን በተመለከተ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል።
° የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቶ ታዬ ደንደአ 20 ሺህ ብር የዋስትና ገንዘብ በማስያዝ ወይም በዋስ እንዲፈቱ / ጉዳያቸውን ከውጭ እንዲከታተሉ ብያኔ አሳልፏል።
መረጃው ከቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት የተገኘ ነው።

#ኡሙሩ
🔴 " ሹፌሩን ጨምሮ 6 ሰዎች ተገድለዋል " - ነዋሪዎች
🔵 " መኪናውን መተው ከጣሉት በኃላ 5 ሰዎች ሞተዋል " - የአጋምሳ ከንቲባ
በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ከአጋምሳ ከተማ ወደ ጫቦ ሲሄድ በነበረ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ በተከፈተ ጥቃት 6 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።
ጥቃቱ ከትላንት በስቲያ ጥዋት የተፈጸመ ሲሆን ነዋሪዎቹ " ሰዎችን እና በጎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪ ላይ አባይ ሸለቆ አካባቢ ነው ጥቃት የተከፈከተው " ብለዋል።
አንድ ነዋሪ ፤ የሞቱት ሰዎች ከአጋምሳ እና ጫቦ እንደሆኑ በዚሁ ቦታ ላይ ሁለት ጊዜ ተመሳሳይ ጥቃት እንደተፈጸመ ፤ ከዚህ በፊት አንድ ሲኖ ላይ ጥቃት ተፈጽሞ ሰዎች መጎዳታቸውን ተናግረዋል።
ቃላቸውም የሰጡ ነዋሪዎች ሹፌርን ጨምሮ የሞቱት 6 ናቸው ብለዋል።
የአጋምሳ ከንቲባ ጌታሁን ደሳለኝ የጥቃቱን መፈጸም አረጋግጠው የተገደሉት ሰዎች 5 ናቸው ብለዋል።
" መኪናውን መተው ከጣሉ በኃላ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ቆስለዋል " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

የሪል_ስቴት_ልማት_እና_የማይንቀሳቀስ_ንብረት_ግብይትና_ግመታ_አዋጅ_1.pdf
1.7 MB
የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?
👉 የሪል ስቴት አልሚ የቦታና የተናጠል ይዞታ ማረጋገጫ አሰጣጥን በተመለከተ ፦
1) በከተሞች ለሪል ስቴት ልማት የሚውል ቦታ በሚከተለው አግባብ የሚቀርብ ይሆናል፤
ሀ. በአዲስ አበባ ከ5 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፤
ለ. እንደከተሞች ተጨባጭ የቤት ፍላጎትና ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባለ ከተሞች ከ1 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፣
ሐ. ከነዚህ ባነሰ ስፋት ቤት ለሚፈልጉ ከተሞች ደግሞ 500 ቤት በላይ የሚገነባና የሚያስተላልፍ የሪል ስቴት አልሚ መሬት ቅድሚያ ተሰጥቶት በስፋት እንዲቀርብለት ይደረጋል።
2) የሪል ስቴት አልሚው የገነባውን ቤት በተናጠል ለቤት ፈላጊ በሽያጭ ለማስተላለፍ ግንባታው የተፈቀደለትን መስፈርት አሟልቶ 80 በመቶ ሲጠናቀቅ ለየቤቱ የተናጠል የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይችላል፤
👉 የሪል ስቴት አልሚ ግዴታዎች ምንድናቸው ?
የሪልስቴት አልሚ በውል ሰነዱ በህንጻ እዋጁ እና በሌሎች የህግ ማዕቀፎች የተመላከቱ ግዴታዎችን ማክበር እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪነት የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል ፡-
1) ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ #አይችልም፡፡
2) በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል #የውሸት_ማስታወቂያ ማስነገር አይችልም፡፡
3) ቤቶቹን ለመገንባት የሚያስችለውን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከመረከቡ በፊት ደንበኞችን መመዝገብና ቅድመ ክፍያዎችን መሰብሰብ አይችልም፡፡
4) በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም።
5) የመኖሪያ ቤት ገዢ ደንበኞች ማኀበር እንዲያቋቋም ያበረታታል ፤ የህንጻ መግለጫ ያስረክባል።
6) ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የተሰጠውን የይዞታ ማረጋገጫ፣ የቤቱ የግንባታ ዕቃዎች ዓይነት፣ አርክቴክቸራል፤ ሳኒተሪ ፣ ስትራክቸራል እና ኤሌክትሪካል ዲዛይን፤ የግንባታ ፍቃድና የሪል ስቴት ልማት ፍቃዱን ቅጂዎች ከውል ሰነዱ ጋር አያይዞ ለደንበኛው መስጠት አለበት።
7) ደንበኛው ለከፈለው ገንዘብ ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት አለበት።
👉 ዋስትና ስለመስጠት ፦
የአገር ውስጥ አልሚ ቤቱን ሳይገነባ ለቤት ፈላጊዎች በቅድሚያ በሚሽጥበት ወቅት የሚከተሉትን የዋስትና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለበት፡፡
1) የሪል ስቴት አልሚው በቤት ቅድሚያ ሽያጭ ስልት ለመስራት መፈለጉን አግባብ ላለው አካለ አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት፡፡
2) ከቤት ገዥዎች የሚሰበስበውን ገንዘብ አግባብ ካለው አካለ ፈቃድ መሰረት በሚከፈተው የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ፣
3) የሪል ስቴት አልሚው በቅድሚያ መሽጥ የሚፈልገውን ቤት የመስሪያ ቦታ የይዞታ ማስረጃ ቤቱ ለተጠቃሚዎች ተገንብቶ እስከሚተላለፍ ድረስ በሚመለከተው አካል እንዳይሽጥ እንዳይለወጥ እንዲታገድ ማድረግ፤
⚫ በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል፡፡
(ሙሉ ረቂቁን ከላይ አያይዘናል ያንብቡ)

#Oromia
🕊 " ሰው በየሄደበት ይገደል ነበር በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለፍነው አሁን ከሰላም በላይ ምን ጥቅም አለ ? ሰላምን የሚበልጥ ነገር የለም ! " - ነዋሪዎች
🟢 " ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ " - አቶ ሽመልስ አብዲሳ
⚪ " የሰላም ስምምነቱን የተቀበልነው የህዝባችንን ስቃይ ከተመለከትን በኃላ ነው፤... ስምምነቱ ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታ ይሰጣል " - ጃል ሰኚ
⚫ " ስምምነቱን ቀድሞውኑ ከተባረሩ ግለሰቦች ጋር ነው የተፈጸመው " - ከዚህ ቀደም ከመንግሥት ጋር ለድርድር ቁጭ ብሎ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት
ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የቀድሞው የማዕከላዊ ዞን አዛዥ ጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል የሰላም ስምምነት ተፈርሟል።
የስምምነት ሰነዱ ምን እንደያዘ ፣ ምን ምን ጉዳዮች ላይ መግባባት ተደርሶ ስምምነት እንደተፈረመ ፣ በጃል ሰኚ ስር ምን ያህል ታጣቂ ወደ ሰላም እንደሚመለስ (በቁጥር) ፣ የነዚህ ታጣቂዎች ቀጣይ እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ በይፋና በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።
ነገር ግን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ይህ የሰላም ስምምነት ለዜጎች እረፍትን የሚሰጥ ሰላም የሚያሰርጽ መሆኑን ገልጿል።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፤ " ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ " ብለዋል።
" የኦሮሞ ህዝብ በባህልና በወጉ መሰረት በሮቹን ጠምዶና ፈረሶችን ጭኖ በመውጣት ሰላም ይውረድ ባለው መሰረት ጥሪውን ተቀብላችሁ በመምጣታችሁ በራሴና በክልሉ መንግስት ስም አመሠግናለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህ ሂደት ትልቁን ስራ ለሰራው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ምስጋና አቅርበዋል።
ጃል ሰኚ " የሰላም ስምምነቱን የተቀበልነው የኦሮሞ ህዝባችንን ስቃይ ከተመለከትን በኃላ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" በዓለም ላይ የሰው ልጅ የፖለቲካ ልዩነት አለው ፤ እኛም ያለንን የፖለቲካ ልዩነት በጠመንጃ ከመፍታት ይልቅ በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ወስነን ነው ስምምነቱን የመረጥነው " ብለዋል።
ስምምነቱ ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም ከመንግሥት ጋር ውጭ ሀገር ለሰላም ድርድር ቁጭ ብሎ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ባወጣው መግለጫ " ስምምነቱ ህዝቡን ለማምታታ የተፈጸመ ነው " ሲል ተችቷል።
ስምምነቱን ቀድሞውኑ ከተባረሩ ግለሰቦች ጋር ነው የተፈጸመው ብሏል።
ያም ሆነ ይህ ስምምነቱን ተከትሎ በርካታ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ መርጠው ወደ ማዕከል እየገቡ እንደሆነ ተነግሯል።
ለመሆኑ ነዋሪዎች ምን ይላሉ ?
ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች በርካታ ታጣቂዎች ወደተዘጋጀላቸው ማዕከላት እየገቡ እንደሆነ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በርካታ የታጣቂ አባላት የሰላም መንገድ መርጠው በተለይ በምዕራብ ሸዋ ዞን እና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች እየተመለሱ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ምዕራብ ሸዋ ጮቢ፣ ኢልፈታ፣ ዳኖ እና ጅባት ፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ እና ዳው በሚባሉ ወረዳዎች የቡድኑ አባላት ቅብላ እየተደተገላቸው ነው።
ጃለታ አበበ ፤ " ትላንት እና ዛሬ ብቻ 7 መኪና ነው የተሃድሶ ትምህርት ለመውሰድ ወደ ዞን ከተማ የገቡት። የሰላም ጥሪውን ከተቀበሉት ምንም የቀሩ አይመስለኝም ፤ ክላሽ መትረየስ እና ስናይፐር ይዘው ነው ያሉት " ብለዋል።
" ኢልፈታ፣ ግንደበረት ፣ ወዴሳና አምቦ አጠቃላይ ምእራብ ሸዋ ላይ ብዙ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባል የሰላም ጥሪ ተቀብሎ እየገባ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በዚህ ልክ የሰላም ጥሪ ተቀብሎ የተመለሰ የታጣቂ ቡድን አባላትን አይተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ጀልዱ ወረዳ በተመሳሳይ ቅበላ እየተደረገላቸው እንደነበር ተሰምቷል።
አቶ ግርማ ሌሎ የጀልዱ ወረዳ ኪልቤ ቀበሌ አስታዳዳሪ ፥ " በትክክልም በሁሉም አቅጣጫ እየተመለሱ ናቸው። ዛሬ እና ትላንት ጀልዱ ወረዳ ጉጁ ከተማ ሲደረሱ ሰው ሁሉ ወጥቶ ሲመለከታቸው ነበር " ብለዋል።
" መጀመሪያ ሲመጡ በየቀበሌያቸው በየቦታው ይሰበሰባሉ ከዛ ወደ መንግሥት ኃይሎች ስልክ ደውለው ነው የቅበላ ሰርዓት የሚደረገው። በጀልዱ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ነው እየተበልን ያለነው " ሲሉ አክለዋል።
ዊቱሺኩቴ፣ ኢልኬ ፣ጎሮ ቀበሌዎች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የመጡባቸው እንደሆኑ ጠቁመዋል።
አሁን ላይ በጃል ሰኚ የሚመሩት የሰላም አማራጭ ተከትለው እየተመለሱ ቢሆንም የሌሎች የቀሩትን እንደማያውቁ አቶ ግርማ ገልጸዋል።
" የህዝቡን ፍላጎት ተመልክተው ይመለሳሉ ብለን እናምናለን " ብለዋል።
ባለፈው ጥቅምት ወር በኪልቤ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በመንግሥት የፀጥታ አካላት መካከል በነበረ የተኩስ ልውውጥ የብዙ ሰው ህይወት አልፏል።
" አሁን ሰላም መውረዱ መሰል የሰው ህይወት ቀጥፈትን ይታደጋል " ሲሉ አቶ ግርማ ተናግረዋል።
እርስ በእርስ መተኳኮሱ ከቆመ በአካባቢው የተደናቀፈው ልማት ይቀጥላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ፤ የህዝቡ ፍላጎትን ስለሚያስጠብቅ ሰላም መውረዱ አስደሳች እንደሚሆን አክለዋል።
የጮቢ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ጃለታ በቀለ ፤ " ሰው በየሄደበት ይገደል ነበር በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለፍነው አሁን ከሰላም በላይ ምን ጥቅም አለ ? ሰላምን የሚበልጥ ነገር የለም። አሁን ህዝቡ ለ5 ዓመታት በቀጠለው ጦርነት ተጎድቷል መንግሥት እና ግብረሰናይ ድርጅቶች የህዝቡ ህይወት የሚንሰራራበትን መላ ይዘው ቢመጡ መልካም ነው " ብለዋል።
[ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዋሪዎች ቃል ምንጭ ቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ሬድዮ እንደሆነ ይገልጻል ]
ኦሮሚያ ባለፉት አመታት ?
ከ6 ዓመታት በፊት " ለውጥ መጥቷል " ከተባለና መንግሥት ኤርትራ አስመራ ላይ ከኦነግ ጋር ስምምነት ደርሷል ከተባለ በኃላ (ምንም እንኳን የስምምነት ሰነዱ ለህዝብ ይፋ ባይደረግም) ወደ ክልሉ በርካታ ታጣቂዎች ገብተዋል።
ከነዚህም ውስጥ ትጥቅ ሳይፈቱ የገቡ በርካቶች ነበሩ።
ወደ ሃገር ከገቡት ውስጥ " ከኦነግ ፓርቲ ጋር ተለያይተናል " ያሉ አባላት " መንግሥትን በትጥቅ ነው የምንታገለው " ብለው ወደ ጫካ ገብተዋል።
ይህን ተከትሎ በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች መካከል በሚደረግ የተኩስ ልውውጥ በርካቶች አልቀዋል።
እገታ፣ ዘረፋ ተስፋፍቷል።
ተማሪዎች ትምህርት መማር አልቻሉም ፡ ገበሬዎች ማረስ አልቻሉም። ንፁሃን ዛሬም ድረስ ፍዳቸውን እያዩ ነው።
ሰላም ወጥቶ መግባትም የማይታሰብ የሆነባቸው በርካታ ቦታዎች ተፈጥረዋል።
በተለያዩ ቦታዎች ትጥቅ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ትንንሽ ቡድኖችንም እንዲበዙ ሆኗል።
በክልሉ ያለውን የትጥቅ እንቅስቃሴ ሆነ ሰላም የራቃቸውን ቦታዎች ወደ ሰላም ለመመለስ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና መንግሥት መካከል የጠረጴዛ ድርድር ሁለት ጊዜ ከሀገር ውጭ ቢደረግም ጠብ ያለ ተስፋ ያለው ውጤት ሳይመጣ ቀርቶ የትጥቅ እንቅስቃሴ በክልሉ ቀጥሏል።
አሁን ተደርጓል የተባለው የሰላም ስምምነት በጃል ሰኚ ከሚመራው ቡድን ጋር ቢሆንም ሌሎችም የሚመሯቸው ታጣቂዎች በክልሉ ይንቀሳቀሳሉ።
#ቲክቫህኢትዮጵያ
#ኦሮሚያ