TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#እድታውቁት #አዲስአበባ

አጠቃላይ በ571 የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች " የተለያዩ ሥራዎች (ጥገናና የመልሶ ግንባታ ስራ) ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

በተለዩት አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚቋረጠው እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሲሆን የሚቋረጥበትን ሰዓት እንዲሁም ቀናት በዝርዝር ይፋ አድርጓል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አፋር በአፋር ክልል ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል። በቦታው የባለሙያ ቲም አዋቅሮ የላከው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው እንደተከሰተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጦ ለአካባቢው ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት እንዲደረግ በአጽንኦት አሳስቧል። ህዝቡ ላይ የከፋ ከደጋ እንዳይደርስ የሚመለከታቸው አካላት ሊያደርጉት…
#EarthQuake

" በኢትዮጵያ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ለ22 ቀናት ወደ መሬት ለመውጣት ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ቅልጥ አለት የመወጠር ሁኔታ አሁን ረገብ ብሏል " ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ኤልያስ ሊዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን/ኢቲቪ ተናግረዋል።

" አሁን ባለን መረጃ ቅልጥ አለቱ ወደታች እየወረደ ነው ፤ በዚህም ምክንያት ባለፉት 2 ቀናት የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ዝቅተኛ ነው " ብለዋል።

" ቀደም ሲል የነበረው ስጋት ባለፉት ቀናት ቀንሷል " ያሉት ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ፥ " ነገር ግን በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የምንገኝ እንደመሆናችን ስጋቱ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ስምጥ ሸለቆ እና አካባቢው በተፈጥሮ ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ መሆኑ የማይቀየር ተፈጥሯዊ እውነታ ስለሆነ እንደ ሀገር፣ እንደ ህዝብ የራሳችንን ጥንቃቄና ዝግጀት ማድረግ ያስፈልጋል " ሲሉ ለቴሌቪዥን ጣቢያው በሰጡት ቃል አስገብዝበዋል።

ባለፉት ቀናት እና ሳምንታት በአፋር ፣ ፈንታሌ አካባቢ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ እንደነበር ይታወቃል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ እና ሌሎችም ከተሞች ዘልቆ የተሰማ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመንግሥት_ሰራተኞች_የደመወዝ_ጭማሪ_1.pdf
" የጥቅምት ወር ደመወዝ ክፍያ በአዲሱ የተሻሻለው ስኬል መሆን ይጀምራል " - አቶ አህመድ ሽዴ

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ፤ የጥቅምት ወር ደመወዝ ክፍያ በአዲሱ የተሻሻለው ስኬል መሆን እንደሚጀምር አሳውቀዋል።

" ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ደመወዝ በካቢኔ ተወስኗል። ባለፉት ሳምንታት በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ቅድመ ዝግጅቱ አልቋል ፤ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንም በኩል ቅድመ ዝግጅት አልቋል ፤ የአፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጅቷል " ብለዋል።

የጥቅምት ወር ደመወዝ ክፍያም በአዲሱ ስኬል ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።

" ዝቅተኛ ተከፋይ ለሆነው የመንግሥት ሰራተኞች ፣ ለጸጥታ ተቋም አባላት ፤ በየደረጃው ባሉ የመንግሥት ተቋማት በክልልም በፌዴራልም ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራል " ብለዋል።

" ይሄ በመላው ሀገሪቱ የሚፈጸም ነው። ክልሎችም ለሰራተኞቻቸው / የደመወዝ ተከፋዮቻቸው የሚመጣውን ደመወዝ ከጥቅምት ወር ጀምሮ የክልል ድርሻ በፌዴራል መንግሥት የሚሸፈን ሆኖ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ለክልሎች ይላካል " ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
" በግቢ ውስጥ ብዙ የአእምሮ ህሙማን ፤ አረጋውያን አሉ በእነሱ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም " - አቶ ንጋቱ ማሞ

ዛሬ ቀን ላይ አዲስ አበባ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 " መቄዶኒያ የአእምሮ ህሙማንና የአረጋዊያን መርጃ ማህበር " እያስገነባ ባለዉ አዲስ ህንጻ ስር ባለ መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " በደረሰን ጥሪ መሰረት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቻችን ከሁለት ቅርንጫፍ ወደ ቦታዉ ፈጥነዉ በመድረስ እሳቱ ሳይስፋፋ በፍጥነት ተቆጣጥረውታል " ብለዋል።

በእሳት አደጋዉ በመጋዘን ዉስጥ የነበሩ ልዩ ቁሳቁሶች ላይ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ ተናግረዋል።

አቶ ንጋቱ ማሞ ፤ " ግቢ ውስጥ ብዙ የአእምሮ ህሙማን፣ አረጋውያን አሉበት በእነሱ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም። አካባቢው ላይ ካሉ ፀጥታ ኃይሎች፣ ከግቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን እሳቱን በቀላሉ መቆጣጠር ተችሏል " ሲሉ አስረድተዋል።

መጋዘን ውስጥ የነበሩ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ላይ ግን መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰ ጠቁመዋል።

የአደጋውን ምክንያት ፖሊስ እያጣራው ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የሐኪሞችድምጽ " በህክምና ሞያ ብቻ 10 ዓመት በላይ ተምረናል እድሜያችን ወደ ጎልማሳነት ተጠግቷል ቤተሰብ ማስተዳደር ፣ ለልጆቻችን ወተት እና ዳይፕር መግዣ እስከማጣት ድረስ ነው ያቃተን "  - ሐኪም በማዕከላዊ የኢትዮጵያ ክልል፣ ሃዲያ ዞን የሚገኘው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ የሚያስተምሩ ሐኪሞች ፦ ➡️ የ4 ወር ዲዩቲ (የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ)፣ ➡️ የ14 ወር የኦቨር ሎድ…
" እኛ እኮ ትርፍ ነገር አልጠየቅንም ፤ የኑሮ ውድነቱ የሚታወቅ ነው በደሞዝ ብቻ መኖር አልቻልንም ፤ ለልጆቻችን የምንቋጥረው ምግብ ከአቅም በላይ ሆኖብናል።

መሰረታዊ ፍላጎታችንን እናሟላ የሰራንበተን ክፈሉን ነው እያልን ያለነው።

በህክምና ሞያ ብቻ ከ10 ዓመት በላይ ተምረናል ፤ እድሜያችን ወደ ጎልማሳነት ተጠግቷል ቤተሰብ ማስተዳደር ፣ ለልጆቻችን ወተት እና ዳይፕር መግዣ እስከ ማጣት ድረስ ነው ያቃተን። "

➡️ የ4 ወር ዲዩቲ (የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ)፣
➡️ የ14 ወር የኦቨር ሎድ ክፍያ (Over load)፣
➡️ የ2016 የአንዋላይዜሽን (Annualization) ክፍያ እስካሁን አልተከፈለንም ያሉ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ የሚያስተምሩ ሐኪሞች ድምጽ !

@tikvahethiopia
#Infinix_TV

አዲሱ የኢንፊኒክስ X5 ስማርት ቴሌቭዥን ምቾት እና ዲዛይንን አንድ ላይ አጣምሮ እንዲሁም ከፍ ያለ የምስል ጥራትን እንዲሰጥ ተደርጎ ከመሰራቱም ባሻገር Ultra HD ስክሪኑ ከጓደኛ፣ከወዳጅ እና ከቤተሰብ ጋር ተሰብስበው ያሻዎትን ነገር አጅግ ከፍተኛ በሆነ ጥራት የሚመለከቱበት ጊዜዉን የሚመጥን ስማርት ቴሌቭዥን ነው፡፡

@Infinix_Et | @Infinixet

#InfinixTVX5 #Infinix #ElevateYourSpace #Perfectview #tvx5
#DStvEthiopia

🏆 👉 ይህንን ድንቅ ፍልሚያ ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

የዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው
#AddisAbaba

" የህዝቡን ኑሮ አይታችሁታል ? ይሄ ማህበረሰብ ከኮሪደር ልማቱ ይልቅ የዕለት ጉርሱን ሸፍኖ የሚበላበት ነገር አያስፈልገውም ? " - ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ

የኮሪደር ስራው ላይ የሚነሱት ጥያቄዎች ምንድናቸው ?

የአዲስ አበባ ከተማን ገጽታ ይቀይራል የተባለው የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

አሁን ላይ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ስራ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ ነው።

የአሁኑን ጨምሮ ከቀደመው (የተጠናቀቀው) ስራ ጋር በተያያዘ ግን ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ።

ሰሞኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት አንድ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር። በዚህም ወቅት የተለያዩ ጥያቄዎች ተጠይቀዋል። ከንቲባዋን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን ተጠየቀ ? ምንስ ተመለሰ ?

በውይይቱ ተሳታፊ ከነበሩት አንዱ ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ ናቸው።

አቶ አበበ " የትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ ይሄ የኮሪደር ልማትን አይቃወምም። እኛ የአሮጌ ከተማ ፍቅር የለብንም። ቡቱቶ የሆነ ከተማ ፍቅር የለብንም። urbanization እየሰፋ ነው የሚሄደው ፤ ከተሜነት እየሰፋ ሲሄድ የህዝብ ቁጥር ሲጨምር ከዓለም ጋር መዘመን አለብን። ምንም ጥርጥር የለውም። እኛም እኮ የምንዝናናበት ነው የተሰራው ኮሪደር። ነገር ግን የሚሰሩት ልማቶች የሚሰሩት ለሰው ነው ፤ ስለዚህ ምን ያክል ነው የተጠናው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በተጨማሪ ለከንቲባዋ ፦

ለመሆኑ ከኮሪደር ስራ ጋር ተያይዞ ለአዲስ አበባ ህዝብ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የለም ? የአዲስ አበባ ህዝብ ኑሮ አያሳስበውም ? አሁን ያለበት የኑሮ ደረጃ አያሳስበውም ?

የህዝቡን ኑሮ አይታችሁታል ?

' እዬዬም እኮ ሲደላ ነው ' ለምን ኑሮው አይታይም የህዝቡ ?

ይሄ ማህበረሰብ ከኮሪደር ልማቱ ይልቅ የዕለት ጉርሱን ሸፍኖ የሚበላበት ነገር አያስፈልገውም ?

ፒያሳ ተነሳ ጥሩ ስራ ተሰርቷል በጣም ውብ ነው ደስ ይላል ፤ የተሰራው ውስጥም ነው ተቀምጠን የምንወያየው ግን በዚህ ፍጥነት አልተቻኮለም ?

በየመንገዱ የሚሰሩ ፣ ጀብሎ የሆነው የሚቸረችሩ ወጣቶች የት ሄዱ ? ሁሉም ነገር ዝግ ተደርጎባቸዋል። ... ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?

" የኮሪደር ስራ ቅድሚያ ልንሰጠው ይገባል ወይ ? እንዲህ መቸኮልስ ለምን አስፈለገ ፤ በርካታ የከተማው ህዝብ ጥያቄዎች የሉም ወይ ? የሚለው መነሳቱ ጥሩ ነው።

የኮሪደር ልማት ስራ ሲሰራ ሌሎች ስራዎችና አገልግሎቶች ወደኃላ ተብለዋል ማለት አይደለም። አስማምተን ነው እየሰራን ያለነው።

በተናበበ መንገድ አቅደን ፤ ሌሊትም ቀንም ለመስራት ራሳችንን አሳምንነን ነው እየሰራን ያለነው። ስራም ተከፋፍለን ነው። ቢሮ ማገልገል ያለበት ቢሮ ነው። እኛም ሙሉ ጊዜያችን ኮሪደር ብቻ አይደለም። ኮሪደር እያስተባበርን ሌሎች ስራዎችም እንሰራለን።

የኑሮ ውድነት ተነስቷል ፤ ችግሩ ስለገባን ነው  የአዲስ አበባ ህጻናት ባዶ ሰሃን ያለ ሃጢያታቸው ምግብ ሳይኖራቸው ምግብ ያላቸው እንዲመስሉ ተደርጎ ያለ እድሜያቸው እንዲዋሹ ያለ ጥፋታቸው ፤ ከመራባቸው በላይ ምግብ ያላቸው እንዲመስሉ ባዶ ሰሃን ይዘው ትምህርት ቤት የሚወደቁበትን ታሪክ አይደል እንዴ የቀየርነው ?

ለ800 ሺህ ተማሪዎች ዩኒፎርም እናቀርባለን፣ ደብተርና የትምህርት ቁሳቁስ እናቀርባለን ፤ ምግብ በቀን ሁለት ጊዜ ጥዋት ቁርስ ይበላሉ ምሳቸውን በልተው ወደቤት ይሄዳሉ ፤ ቤት ውስጥ ያለውን ገመና ስለምናውቅ ነው።

ትውልድ መገንባት አለበት ሀገራቸውን እየጠሉ እያማረሩ ማደግ ስለሌለባቸው። የአዲስ አበባ እናቶችን የኑሮ ጫና በሚገባ አይተነው ነው። ጓዳቸውን አይተን ነው።

ሁለተኛ በየቦታው ቦታ አመቻችተን ከ190 በላይ የእሁድ ገበያ የፈጠርነው ከስግብግብ ነጋዴዎች ነዋሪዎችን ለማስጣል የሰራነው የኑሮ ውድነቱ ስለሚገባን አይደለም ?

እነኛህ የአዲስ አበባ ከተማ የመግቢያ በሮች ላይ 5 ትልልቅ የገበያ ማዕከላት በቢሊዮን ልክ እንደ ኮሪደር ልማት በፍጥነት የገነባነው የኑሮ ውድነት ጫናው ስለሚገባን አይደለም ? ለምን አልተደረገም ከዚህ በፊት።

ገበሬው ቀጥታ አምጥቶ ምርት እንዲሸጥ ደላላው ከመሃል እንዲወጣ አላደረግንም እንዴ ?

አረጋውያን በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ማግኘት አቅቷቸው አልተመለከትንም ፤ ' ተረጂነትን ታስፋፋላችሁ ' እየተባለን ስንተች ትችቱን ወደጎን ብለን በቀን አንድ ጊዜ ምግብ የሚያገኙበትን 21 የምገባ ማዕከላት ገንብተን እየመገብን ነው።

ከመንግሥት በጀት ውጭ 30,000 ቤቶች ገንብተን በነጻ ድሆችን አንስተን ዝቅ ብለን ያስገባንበት የህግ ግዴት አለብን እንዴ ? 30,000 ከመንግሥት በጀት ውጭ ነው። ውሃ የሚያፈስባቸው ከመጸዳጃ ቤት ጋር የሚኖሩ አንስተን አስገብተናቸዋል።

የኮሪደር ስራ በሰራንበት 2016 ዓ/ም ላይ ብቻ 18,000 ከትንሽ ፕሮጀክቶች እስከ አድዋ ድረስ ሰርተን ለህዝባችን ክፍት አድርገናል። የት የት እንደሆኑ ዳታ እንሰጣለን ሂዱና እዩ።

አጠቃላይ የከተማው ችግር እና ያለንበት ጥልቅ ድህነት በ1 ፣ በ3 ፣ በ5 ዓመት ተስርቶ አያልቅም የዘመናትን ውዝፍ በአንድ ጊዜ አልጨረሳችሁም ከሆነ ትክክል አይደለም። ሊያልቅ አይችልም።

በአንድ በኩል እኚህን ቶሎ ቅረፉ በሌላ በኩል አትቸኩሉ አብሮ አይሄድም።

ኮሪደር ስራ በባለሞያዎች በደንብ ተጠንቶ ነው የተጀመረው። መነሻው መዋቅራዊ ፕላን ነው። ያጠናንባቸውን አካባቢዎች ዶክመንቱ ይፋዊ ስለሆነ ማየት ይቻላል። የፕላን ጥሰቱ ልክ የለውም።

በየሰፈሩ ያሉ የፍሳሽ መስመሮች የተዘጉ ናቸው፣ እሳት አደጋ ሲፈጠር እንኳን ገብተን ማጥፋት አቅቶናል። ይቃጠሉ ይለቁ ? ከቆሻሻ ጋር መኖር የኢትዮጵያውያን ክብር ይመጥናል ? ጠረኑን አይታችሁታል ? እንዲህ ባልናገር ጥሩ ነበር ግን እውነታው ይሄ ነው።

ሰው ፍሳሽ ከላይ እየወረደበት እንዲተኛ፣ እናቶች ቆጥ ላይ እንጀራ እንዲጋግሩ ፣ እናቶች ከስር ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን ይዘው ያድራሉ ከላይ ቆጥ ሰርተው ያከራያሉ። እነዚህ አካባቢዎች ታሪካቸው ይኸው ነው።

ቤቶቹ አርጅተዋል። በጭቃና በእንጨት ነው የተሰሩት አረጁ ግዜያቸው አለፈ ወደቁ በቆርቆሮ ቢለበዱ፣ ላስቲክ ቢታሰርባቸው ችግር መከላከል አይችሉም።

ወቀሳ የምታነሱ ሰዎች ፒያሳ ዶሮ ማነቂያ በሴት እህቶቻችን እና እናቶች ላይ የሚፈጸመው ወንጀል ለምን አያማችሁም ? ወይስ አታውቁም ? የዜግነት ክብራችንን አይመጥንም ነበር። ስለዚህ ክብራችንን በሚመጥን መንገድ ማልማት ይገባል።

ወደው አልነበረም ከቆሻሻ ጋር ሲኖሩ የነበሩት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አልፈው መጥተው ያ እንዲቀጥል የሚቀርበው ጥያቄ ፍጹም ተቀባይነት የለውም።

- ገቢያችን እንዲያድግ
- የስራ እድል በስፋት እንዲፈጠር
- ዜጎች ንጹህ ፅዱ ቦታ እንዲገበያዩ፣ እንዲሰሩ ፣ እንዲኖሩ ለማስቻለው ስራዎችን እየሰራን ያለነው።

የምንቸኩለው ጊዜ ስለሌለን ነው። ጉስቁልና ድህነት ውስጥ ነው ያለነው። ውርደት አለ ከዚህ ውስጥ መውጣት አለብን። አንዳንዶች የኛ ኑሮ ሻል ስላለ የድሃው አይታየን ይሆናል ! ከዚህ በላይ እንቸኩላለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
" ትናንትና 2 ዛሬ ደግሞ 10 አስክሬን ተገኝቷል " - የጋሞ ዞን ፖሊስ

ከአቡሎ አርፋጮ ወደ አርባምንጭ ከተማ 16 ሰዎችን እና ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ባሳለፍነው ሐሙስ 10 ሠዓት ከ20 ገደማ ጫሞ ሐይቅ ላይ ሰጥማ ነበር።

ይህ ተከትሎ እየተከናወነ ባለ የነፍስ አድን ሥራ ትናንት 2 ዛሬ ደግሞ 10 አስከሬን መገኘቱን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አሳውቋል።

እስከ ዓርብ ድረስ ባለው 3 ሰዎች በሕይወት መገኘታቸውን ገልጿል።

በአጠቃላይ በጀልባዋ ከተሳፈሩት መካከል እስከ አሁን የአንዱ ሰው ሁኔታ ስላልታወቀ ፍለጋው መቀጠሉ ተመላክቷል።

የጋሞ ዞን ፖሊስ የአደጋው መንስኤን በተመለከተ ፥ " የጀልባዋ የመጫን አቅም 35 ኩንታል ሆኖ ሳለ በዕለቱ 70 ኩንታል ሙዝ እና 16 ሰዎችን ጭና ነበር፤ ይህም ከልክ በላይ መጫን በመሆኑ ለአደጋው መከሰት መንስዔ ሆኗል " ብሏል።

መረጃው የኤፍ ቢ ሲ ነው።

@tikvahethiopia
" ደምፅ ሁኗቸው በጣም ተጨንቀናል !! " - ቤተሰቦች

ሲሪላንካ ውስጥ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን መንግስት ጣልቃ ገብቶ ወደ ሀገራቸው እንዲመልሳቸው ቤተሰቦቻቸው ተማጸኑ።

" ያሉበት ሁኔታ ስለማይታወቅ እና ድምፃቸውን ከሰማን ስለቆይን ቤተሰቦቻቸው በጣም ጭንቀት ውስጥ ነን " ብለዋል።

" ታስረው የሚገኙት ልጆች በአጭበርባሪዎች ተታለው ነው ወደዛ የሄዱት " ያሉት ቤተሰቦቻቸው "  የሚመለከተው አካል እና መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ደምፅ ሁኗቸው በጣም ተጨንቀናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ምን ያህል ናቸው የታሰሩት ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " 4 ናቸው " ብለዋል።

" መጀመሪያ ላይ UAE ዱባይ ውስጥ ይሰሩ ነበር ፤ እዛም ህጋዊ ነበሩ ከዛ ግን ' ሲሪላንካ ውስጥ ጥሩ ደሞዝ እና ህጋዊ የሆነ ስራ አለ በኦንላይን ላይ እቃ መሸጥ ነው ' ተብለው ነበር ወደዛ የሄዱት እዛ ከደረሱ በኃላ ግን ስራው የተባሉት አልነበረምና ስልክ መጠቀም ከልክሏቸው እና ከሚሰሩበት ቦታ ወደ ውጪ መውጣትም ሆነ ከሌላ ሰው ጋር መግናኝት አትችሉም ተብለው ከልክሏቸው ነበር " ሲሉ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም በማይናማር ፣ ካምፖዲያ እና ሌሎች አቅራቢያ ያሉ ሀገራት ውስጥ ባሉ አጭበርባሪዎች እና እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ደላሎች ተታለው ወደ ሌላ ሀገር የተወስደው በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ስላሉ ወገኖች ተደጋጋሚ መረጃዎችን ማድረሳችን ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#MoE

የ2ኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ተከታዩን ሊንክ ተጠቅማችሁ የምዝገባ ቁጥር ወይም Username በማስገባት ውጤቶቻችሁን ማየት ትችላላችሁ :https://result.ethernet.edu.et

ከሐምሌ 22 - ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም የተሰጠውን ስልጠና፣ ከ49 ሺህ በላይ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " የህዝቡን ኑሮ አይታችሁታል ? ይሄ ማህበረሰብ ከኮሪደር ልማቱ ይልቅ የዕለት ጉርሱን ሸፍኖ የሚበላበት ነገር አያስፈልገውም ? " - ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ የኮሪደር ስራው ላይ የሚነሱት ጥያቄዎች ምንድናቸው ? የአዲስ አበባ ከተማን ገጽታ ይቀይራል የተባለው የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ ይገኛል። አሁን ላይ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ስራ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ ነው።…
#AddisAbaba

ለምን የልማት ተነሺዎችን እዛው ቦታቸው ላይ ቤት ሰርቶ ማስገባት አልተቻለም ?

በአዲስ አበባ ከሚሰራው የኮሪደር ልማት ስራ ጋር በተያያዘ በርካታ ነዋሪዎች ረጅም ዓመታት ከኖሩባቸው ሰፈሮች እንዲነሱ እየተደረገ ነው።

አስተያየት ሰጪዎች ፤  " ይሄ ነገር ነባር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመሃል ለማስወጣት ፤ የማህበራዊ ትስስሩንም ለመበጣጠስና ፤ ነባሩን ነዋሪ ለመበታተን ፤ የልማት ተነሺ ቦታዎችንም ለሚፈልጉት ባለሃብት ለመስጠት ነው ፤ እውነት ልማት ከሆነ ለምን ባሉበት በኖሩበት ቦታ የጋራ መኖሪያ ቤት አይሰራላቸው ? " ሲሉ ይጠይቃሉ።

ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች በተገኙበት ከዚሁ ከኮሪደር ልማት ጋር የተያያዘ የውይይት መድረክ ላይ ፤ " ለምን የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ከተገነባ በኃላ ከለማ በኃላ በነበሩበት ቦታ መኖር አይችሉም ? ልክ እንደ አዋሬ ለምን አልተደረገም ? እዛው እንዲኖሩ ለምን ማድረግ አልተቻለም ? " የሚል ጥያቄ ተስቷል።

እንዲሁም ረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ ነዋሪዎች ፦
- ከእድራቸው
- ከእቁባቸው
- ከሰንበቴያቸው ፤ በእስልምናም በኩል ያሉት የማህበረሰቡ መገናኛዎች እንዲበተኑ እየተደረጉ ነው የሚል ሃሳብ ተነስቶ ነበር።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?

" እዛው አካባቢ ላይ ብታለሙ አይሻልም ወይ ? እውነት ነው ይሻላል እንላለን። በነበሩበት አካባቢ ቢሆን የበለጠ ቅድሚያ የሰጠዋል።

አዋሬ እንደዛ ነው የለማው። አዋሬ ብቻ ሳይሆን 70 ደረጃ የገነባናቸው ቤቶች እዛው ሰፈራቸው ነው። በተመሳሳይ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ የበጎነት መንደር ብለን የሰራነው እዛው ነው። ለሚኩራም ሎውኮስት ሀውስ የተሰሩት እዛው ነው፣ ጉለሌ፣  አየር ጤና ሁሉንም መዘርዘር ይቻላል።

ሰፋፊ አካባቢዎችን ስናነሳ አንደኛ የሚገነባበት ቦታ የለም ፤ ካልተነሱ በስተቀር። ሁለተኛ በጥናታችን ሲገነባ የመስረተ ልማቱ የፍሳሽ፣ የጎርፍ መውረጃው የከተማ ልማት የመሬት አጠቃቀሙ የመኖሪያ ቤት መሆን የሌለበት አካባቢ አለ። ተዘግቶ የተገነባበት አለ ጥናቱ በዝርዝር ያስረዳል።

ስለዚህ ሰፋ ወዳለ ቦታ ይሄንን ማህበረሰብ መውሰድ ያስፈልጋል። ቤት ብቻ አይደለም ያየነው። በአካባቢያቸው የሚያስገልጉ ሌሎች መሰረተ ልማቶች አብረው መኖር አለባቸው።

ሌሎች ሀገሮችን እኮ እናውቃለን መኖሪያ ቤቶች መሃል ዋናው ከተማ ላይ ናቸው እንዴ ? ንጹህ አየር ወዳለበት ከተማ ውስጥ ነው ከከተማ አልወጣም። እዚህ ነው የተሻለ ቦታ የተሻለ ሰፋ ያለ ለልጆችም የሚሆን ፤ ብዙ ሰው ሊይዝልን የሚችል ቦታ ላይ ገንብተን አዲስ ቤት መሰረተ ልማት የተሟላለት ቤት አስገብተናል።

ጥያቄ የምታነሱ ወገኖቻችን ኑ አብረን እንሂድና ገላን ጉራን፣ አቃቂን እንመልከት ፣ አቃቂ የቁጠባ ቤቶች ግቢ እንሂድ አብረን ፣ አራብሳ ግቢም የልማት ተነሺዎች የገቡበት አካባቢን እንይ።

አንዳንድ ቦታዎች የተጠቆሙ (የመሰረተ ልማት ችግር ያለባቸው) ካሉ እንደግብዓት እንወስዳለን ህዝባችን እንዲንገላታ አንፈልግም ፤ ህዝባችን እንዲንገላታ ምንም አይነት ፍላጎት የለንም።

ግን እሱም ቢሆን ይኖሩበት ከነበረው ጋር አይወዳደርም።

ከማህበራዊ ትስስራቸው ተበታተኑ የሚለው ፍጹም ውሸት ነው። አልተበታተኑም። የአንድ አካባቢ ሰዎችን አንድ አካባቢ ነው ዕጣ ያስወጣነው። ዕጣውን ለሁሉም ከየአካባቢው ለሚነሱት በጋራ አይደለም ያደረግነው ቀጠናቸውን እንኳን ጠብቀንላቸዋል።

እቁብ፣ እድር፣ ማህበር አላቸው፣ ትስስር አላቸው። ' አይ የቁጠባ ቤት ላይ አንገባም ኮንዶሚኒየም ነው ' ሲሉ የተወሰኑ ሰዎች ኮንዶሚኒየም ሲመርጡ ወደ ሌላ ሄደው ሊሆን ይችላል። ይሄ ለተባለው ግን በቂ ማሳያ አይሆንም።

ባለቤቱ መርጦ ' ይሄ ይሻለኛል በዛው ንብረት ይዛለሁ የጋራ መኖሪያ ቤት ማግኘት ማለት ባለቤት መሆን ነው በቁጠባ እየከፈልኩ ከምኖር ባለቤትነትን እመርጣለሁ ' ካለ ለምንድነው ? ከማህበራዊ ትስስርህ ተነጥለህ ፤ እዚህ እቁብ፣ እድር አለ እዚህ ሰፈር ካልሆነ አትገባም አንለውም። እንደዛ የተባለ ካለ ይዛችሁ ኑ " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaAddisAbabaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሶማሌክልል

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ካለፈው ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በሱማሌ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰቢያ የምክክር መድረክ እያደረገ ይገኛል፡፡

ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)  ፥ ከጥቅምት 4-6/2017 ዓ.ም በክልሉ ሶስት ማዕከላት ፦
- በጅግጅጋ ፣
- በጎዴ
- በዶሎ አዶ ማዕከላት ከ 1 ሺ በላይ የማህበረሰብ ወኪሎችን በማመካከር አጀንዳዎቻቸውን እንዲለዩ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ጠቁመዋል።

" በሶስቱም ማዕከላት በነበረው የምክክር መድረክ የማህበረሰብ ተወካዮች የነበራቸው ተሳትፎ እጅግ የሚደነቅ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችለናል " ሲሉ አክለዋል።

ዛሬ ደግሞ የተመረጡ 100 የህብረተሰብ ወኪሎችን ጨምሮ የክልሉ አራት  የምክክር ባለድርሻ አካላት ማለትም ፦
° የፖለቲካ ፓርቲዎች፣
° የክልሉ መንግስት፣ 
° የልዩ ልዩ ማህበራትና ተቋማት
° የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች የሚሳተፉበት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ መጀመሩን ገልጸዋል።

" ለተከታታይ 3 ቀናት በሚካሄደው የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከላይ ከተጠቀሱ አምስቱ ባለድርሻ አካላት የተመረጡ ከ1 ሺ 200 በላይ ተወካዮች የሚሳተፉ ይሆናል " ብለዋል።

" ተወካዮች በዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ወኪሎችን ይመርጣሉ፤ ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ አጀንዳዎችንም ለይተው ለኮሚሽኑ የሚያስረክቡ ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ የምክክር መድረክ እጅግ መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮች የሚለዩበት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሆነ ጠቁመው ወኪሎች በንቃት በመሳተፍ ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች በመለየት በተጀመረው ዘላቂ የሀገራዊ መግባባት የማረጋገጥ ጉዞ አሻራቸውን እንዲያስቀምጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሙሉ ቃላቸው ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-20

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba #ኮንዶሚኒየም

🔵 " ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ? ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " - አቶ አበበ አካሉ

" የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ


ከአዲስ አበባ የኮሪደር ስራ ጋር በተያየዘ በርካቶች በልማት ተነሺነት ከኖሩበት አካባቢ ተነስተው ወደ ተለያዩ ጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲገቡ እየተደረገ ነው።

ምንም እንኳን ተነሺዎቹ መግባታቸው ላይ ቅሬታ ባይፈጥርም ከ97 አንስቶ ሲቆጥቡ የኖሩ ነዋሪዎች መፍትሄ ሳያገኙ መቅረታቸው እና አሁን ላይ አስተዳደሩ ቤት የተሰጠ መሆኑ ቅሬታ አሳድሯል።

ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በተካሄደ የኮሪደር ስራውን በሚመለከት የውይይት መድረክ ላይ ይኸው ቅሬታና ጥያቄ ተነስቷል።

ጥያቄውን ካነሱት አንዱ ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ ናቸው።

" ሲቆጥቡ የኖሩ ሰዎች ጉዳይ ምን ደረሰ ? አሁን ማህበረሰቡ ምን ያማል ከተማ አስተዳደሩን ' እኛ በቆጠብነው ገንዘብ ነው የልማት ተናሺዎችን እያሰፈረ ያለው ' የሚል ሮሮ አለ።

ለዚህ ምንድነው ምላሻችሁ ?

ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " ሲሉ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?

" የኮንዶሚኒየም ቤት እስኪ ከየት አምጥታችሁ ነው በዚህ ደረጃ ያላችሁ ኃላፊዎች ' በቆጡት ገንዘብ ነው የሚሰራው ' የምትሉት።

እነ ንግድ ባንክ ናቸው ብሩን የሚያቀርቡት እስቲ እንነጋገር ትንሽ ወደ መረጃው ጠጋ ብላችሁ ብናወራ ምናለበት።

ኮንዶሚኒየም በብድር ነው የሚሰራው። የከተማ አስተዳደሩ በጀቱን አስይዞ ነው የሚበደረው።

ለምንድነው የሚቆጥቡት ? ከተባለ ዕጣ የደረሳቸው ዕለት የሚከፍሉትን እንዳያጡ ነው። እንጂ ቤቱን መገንቢያ አይደለም። ልክ ቤቱ ሲገነባ ብሩን ይከፍሉታል።

ሁለተኛ እንዴት ነው እኛ ብቻችንን የምንጠየቅበት ? ቤት ባልተዘጋጀበት በሚሊዮኖች መዝግቦ ቆጥቡ ብሎ ኃላፊነት ወስዶ የሰራ አካል እያለ ለምንድነው እኛ የምንወቀሰው ?

ቤት ሳያዘጋጅ ዜጎችን ልክ እንደ ማታለያ በሚሊየን መዝግቦ የበተነ እያለ ለምንድነው እኛ የምንወቀሰው ?

የኮንዶሚኒየም ቤት አጠቃላይ አንድ ቦታ እጅብ ብሎ ስለተሰራ ብዙ ይመስላችኋል እንጂ እስካሁን እስካጠናቀቅነው ያለው 300,000 ነው። የተመዘገበው በሚሊዮን ነው። በየጊዜው ተስፋ ቆርጦ፣ ተጣርቶ ተጣርቶ እኛ የደረስንበት 600,000 ነው። አክተቭ ይቆጥብ የነበረው። ግን ቤት ማግኘት እንዳለባቸው እናምናለን። ቤት ማግኘት አለባቸው።

ካለቁት ኮንዶሚኒየሞች ብራቸው ተዘርፎ፣ ቀድሞ ተከፍሎ ያልተሰራ 80 ህንጻ ብር ተከፍሎበት ጥለው ሄደዋል። በብዙ ውጣውረድ ነው 139,000 ቤቶችን የጨረስነው። የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ብቻ።

አሁንም ቢሆን ግን የከተማችን ነዋሪዎች ቤት ማግኘት አለባቸው። ለዚህም በኮንዶሚኒየም ብቻ አይደለም እንደ ቀድሞ በሚፈለገው ደረጃ ብድር ማግኘት አልቻልንም ከባንክ። ኮንዶሚኒየም መጥፎ ስለሆነ አላቆምነውም።

ከተማ አስተዳደሩ ዕዳ እየከፈለ ነው። ንግድ ባንክ የሚያበድረው የባለሃብትን ገንዘብ ነው አይደል ? 56 ቢሊዮን የኮንዶሚኒየም ዕዳ ነው የተረከብነው ዋስትና የሚሰጠው ከተማ አስተዳደሩ ስለሆነ ክፈሉ ተባልን ተገደድን በለውጥ ዘመኑ 30 ቢሊዮን ከፍለናል የኮንዶሚኒየም ዕዳ።

ይህ ሁሉ ዕዳ አንደኛ በከፍተኛ ሰብሲዲ ስለሚሰራ ነው ፤ ሌላው ያልተሰሩ ቤቶች የተከፈለባቸው አሉ። ሳይከፍሉ ሲሸጡ በተለያየ መንገድ ሲተላለፉ የነበሩ ቤት ውስጥ ያገኘናቸው ሰዎች ከግለሰብ የገዙ ናቸው፤ ሊገደዱ አይችሉም የኮንዶሚኒየም ክፈሉ ተብለው። አጣርተን እኮ በሚዲያ ነግረናችኋል ፤ ያጋጠመንን።

አሁን በግልና በመንግሥት አጋርነት ወደ 100,000 ቤቶች አስጀምረናል። የቁጠባ ቤቶችንም እየሰራን እያከራየን ነው። በሪስልቴትም በግል የሚሰሩትን እንደ ከተማው ፕሮጀክት ጠጋ ብለን እያገዝን ቶሎ እንዲጨርሱ እያደረግን ነው።

እስካሁን የቆጠቡትን አሁን በግልና መንግሥት ትብብር ከምንሰራው  ውስጥ ቅድሚያ ሊያገኙ የሚችሉበትን አግባብ እየተከተልን ነው። ሁለተኛ ደግሞ ተደራጅተው በማህበር እንዲሰሩ ...እስካሁን ለተደራጁት መሬት አስረክበናል።

መነገጃ አታድርጉት፤ ከእውነታው ውጭ መነጋጃ ማድረጉ አይጠቅምም።

የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል። ባለፈው ያስጨረስናቸውን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቅድሚያ 97 አክቲቭ ቆጣቢዎች ሁሉ ዕጣ እንዲወጣላቸው ተደርጓል።

እነሱ ከወጣላቸው በኃላ ዲአክቲቬት ያደረገውን አካውን አክቲቬት ያደረገ ካለ እሱ ስለቆጠበ ቤት ስለሚፈልግ ለሚቀጥለው ጊዜ ሊታይ ይገባል ፤ እንጂ በዚህ መንገድ መቅረብ የለበትም " ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia