TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ፎቶ ፦ የአልነጃሺ መስጂድ መልሶ የመጠገን ስራ በመከናወን ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

ከትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተገኘው መረጃ ፥ በትግራይ ጦርነት ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው ቅርሶች አንዱ የሆነው ቅዱሱ መስጂድ አልነጃሺን መልሶ የመጠገን እና የማልማት ስራ ከያዝነው ወር መጀመሪያ ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

ጥገናው የመስጂዱን ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ይዘት በጠበቀ መልኩ በመከናወን ላይ ነው ተብሏል።

በሚቀጥሉት 8 ወራት ጥገናው ተጠናቅቆ ክፍት እንደሚደረግ ተመላክቷል።

የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የአልነጃሺ ቅዱስ መስጂድን መልሶ ለመጠገን ከቱርክ ልማት ኤጀንሲ (ቲካ) ጋር መፈራረሙ ቢሮው አስታውሷል።

@tikvahethiopia            
#ኢትዮጵያ

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ከደቂቃዎች በኃላ መካሄድ ይጀምራል።

የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ከ8 ሰዓት ጀምሮ ነው የሚካሄደው።

በዚህ መክፈቻ ላይ #የሪፐብሊኩ_ፕሬዚዳንት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ለሁለቱ የፌደራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊውን ስራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌደራል መንግስትን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ህዝብ በማደናገር ላይ ይገኛሉ " - በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማዕከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ክፍፍል ተቀራርቦ ከመፈታት ይልቅ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየተካረረ መጥቷል። " ከህወሓት አባልነት የተባረሩ በማንኛውም ቦታና ጊዜ በህወሓት ስም ፓለቲካዊ ስራና እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም " ሲል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት…
#TPLF

ከዛሬ ጀምሮ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ጨምሮ ሁሉም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ በጉባኤ ያልተሳተፉ የስራ ሃላፊዎች በጉባኤ በተሳተፉ ሹማምንት መቀየሩን በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት " ወስኛለሁ " ብሏል።

" ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ህወሓት ከሰጣቸው የስራ ሃላፊነት ተነስተዋል እንዴትና በማን እንደሚተኩ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገርኩ ነው " ብሏል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት።   

ከየትኛው የፌዴራል መንግሥት አካል ጋር እየተወያየ እንደሆነ በግልጽ ያለው ነገር የለም።

ስለ ጉዳዩ እስካሁን በምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚመራው ህወሓት በኩል የተሰጠ መልስ የለም። 

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት ባወጣው የውሳኔ መግለጫ ፥ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔዎች ፣ ቢሮዎች ፣ ኤጀንሲዎች ፣  ኮሚሽኖች የዞን አስተዳደሮች የሚገኙ በጉባኤ ያልተሳተፉ የስራ ሃላፊዎች በማንሳት በጉባኤ በተሳተፉ አባላቱን ሙሉ በሙሉ መተካቱ አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት  ፦

- አቶ በየነ መክሩ 
- ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት 
- ዶ/ር ሓጎስ ጎዲፋይ
- ወ/ሮ አልማዝ ገ/ፃዲቕ 

ከጊዚያው አስተዳደሩ ካቢኔ በማንሳት በ
- ዶ/ር አብራሃም ተኸስተ
- አቶ አማኒኤል አሰፋ
- ዶ/ር ፍስሃ ሃብተፅዮን
- አቶ ተወልደ ገ/ፃድቃን
- ወ/ሮ ብርኽቲ ገ/መድህን
- አቶ ይትባረክ አምሃ 
- ዶ/ር ፀጋይ ብርሃነ መተካቱ ገልጿል።

- አቶ ርስቁ አለማው
- አቶ ሰለሙን መዓሾ
- አቶ ሺሻይ መረሳ 
- አቶ ሃፍቱ ኪሮስ  ከዞን ዋና አስተዳዳሪነት በማንሳት

- በአቶ ተኽላይ ገ/መድህን
- በአቶ ወልደኣብራሃ ገ/ፃዲቕ 
- በአቶ ሺሻይ ግርማይ
- በአቶ ፍስሃ ሃይላይ
- በአቶ ሃይላይ ኣረጋዊ 
- በዶ/ር አብራሃም ሓጎስ ተተክተዋል ብሏል።

በተጨማሪ 
- አቶ ረዳኢ ሓለፎም
- ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ
- አቶ ነጋ አሰፋ 
- ዶ/ር ገ/ሂወት ገ/ሄር ከኤጀንሲ እና የኮሚሽን የስራ ሃላፊነት ወርደዋል ያለው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት በእነ ማን እንደተተተኩ ያለው የለም።

ይህ ዘገባ አስከተጠናቀረበት ቀንና ሰዓት
ድረስ በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ ከሚመራ ህወሓት በኩል የተሰጠ መልስ የለም።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሾሙ በእጩነት ቀረቡ። @tikvahethiopia
#Update

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህም የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።

አምባሳደር ታዬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
የብርሃን ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች 15ኛ መደበኛ እና 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የጉባኤ ጥሪ

ለተጨማሪ መረጃ ወደ 8292 ይደውሉ
እንዲሁም ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://yangx.top/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzM
ዋሪት !

የቤትም ሆነ የቢሮ እቃዎች መግዛት ሲፈልጉ ትክክለኛ ምርጫዎ ወደሆነው ዋሪት ብቅ ይበሉ። ወደየትኛውም ቅርንጫፋችን ጎራ ሲሉ የዓይን አዋጅ የሚሆኑብዎትን ምርቶቻችንን ከሙሉ ግርማ ሞገስ እና ውበት ጋር ያገኛሉ። ስለ ጥራታቸውም ሆነ ውበታቸው ሃሳብ እንዳይገባዎ።
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!!
* 22- ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ- ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ- ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
* ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት
* አዳማ- ሶረቲ ሞል
* ወሎ ሰፈር- ጋራድ ህንፃ
📞0911210706 | 0911210707
www.warytze.com
ፌስቡክ፡ www.fb.com/WARYTZE
ቴሌግራም፡ https://yangx.top/warytfurniture
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/warytfurniture/
ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/@warytzefurniture
#ኮሬ

“ ባለፉት ዓመታት ከ300 በላይ ንጹሐን በታጣቂዎች ተገድለዋል ” - ኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን 

“መንግስት ቸልተኛ ሆኗል የሚል ግምገማ አለን። ዛሬ ጠዋትም ሰው ተገድሏል” - የክልሉ ተወካዮች ምክር ቤት

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ  ንጹሐን ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች፣ ዞኑና የክልሉ ተወካዮች ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በዞኑ ጎርካ ወረዳ ዳኖና ኬረዳ ቀበሌዎች የምዕራብ ጉጂ ታጣቂዎች መስከረም 27 እና 25 ቀን 2017 ዓ/ም በዳኖና ኬረዳ ቀበሌዎች ታጣቂዎቹ በፈጸሙት ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሁለት ቆስለዋል ብለው፣ አሁንም ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ስለጉዳዩ ማረጋጠጫ የጠየቅናቸው የኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ተወካይ አቶ አማረ አክሊሉ በበኩላቸው ፣ “ከምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላና ወረዳ የሚመጡ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በኬረዳ ቀበሌ አንድ አርሶ አደር ወዲያው ሲሞት፣ አንዱ ክፉኛ ቆስሏል” ብለዋል።

“በዳኖ ቀበሌ ደግሞ ማሳ ላይ በነበሩ አርሶ አደሮች ላይ ከፍተኛ የተኩስ ሩምታ ከፍተው አንድ አርሶ አደር ወዲያው ሲሞት፣ አንዱ ደግሞ ቆስሏል” ሲሉም አክለዋል።

“መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ/ም የ 'ሸኔ’ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አራት አርሶ አደሮች ሲገደሉ፣ አንድ አርሶ አደር ነበር የቆሰለው። የአሁኑን ጥቃት ያደረሰው ግን በምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላና ወረዳ የተሰማራ ሌላ ታጣቂ ኃይል ነው” ብለዋል።

“በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ባለፉት ዓመታት ከ300 በላይ ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል” ነው ያሉት።

ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ  የጠቅናቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የኮሬ ህዝብ የቀድሞው አማሮ ምርጫ ክልል ተወካይ አቶ ዘናነህ አዱላ ምላሽ ሰጥተዋል።

“አካባቢው ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በጸጥታ ችግር የወደቀ አካባቢ ነው። በአካባቢው ከመንግስትን ተቃርኖ የሚንቀሳቀሰው የ‘ሸኔ’ ታጣቂ መኖሩ ሁኔታውን አባብሶታል።

ህዝቡ በጸጥታ ችግር ላይ ነው ያለው። ቀዳሚው ትኩረትም ሊሆን የሚገባው ሰላም ነው። በምዕራብ ጉጂ በኩል የመንግስት ክንፉ ሙሉ ለሙሉ የሚተገበርበት ነው ብዬ አላምንም። ምክንያቱም በሌሎች ታጣቂዎች እጅ የወደቀ ስለሆነ። 

አሁንም ህዝቡ ቅሬታው 'ችግር ፈጣሪው ተለይቶ መንግስት ሙሉ ለሙሉ እርምጃ አልወሰደም' የሚል ነው። ህዝቡ መንግስት ላይ ቅሬታ አለው። የቀጠለ ችግር አለ እውነት ነው ህዝቡ የሚያነሳው
” ነው ያሉት።

የአካባቢው ህዝብ ተወካይ እንደመሆናችሁ መጠን ችግሩ እንዲቀረፍ ወደ መንግስት ምን ግፊት አድርጋችኋል? ለሚለው ጥያቄ ምላሻቸው “በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ከመንግስት ጋር እያወራን ነው። አሁንም ህዝቡን ድምጽ እያሰማን ነው” የሚል ነው። 

“መንግስት ሰፊ የኦፕሬሽን ሥራዎችን የሰራበት ሁኔታ አለ። ግን በመሀል አርሶ አደርን በማፈናቀል፤ የኮሬንና ጉጂን ህዝብ በማጋጨት የፓለቲካ ትርፍና ሀብት ለማግኘት የሚፈልግ ክንፍ ነው አስቸጋሪ የሆነው” ብለዋል።

ችግሩ የቆዬ ነውና መፍትሄው ለምን ዘገዬ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ፣ “በዚህ ጉዳይ እኛም መንግስት ቸልተኛ ሆኗል የሚል ግምገማ አለን። ዛሬ ጠዋትም ሰው ተገድሏል። ስለዚህ መንግስት የህዝብን ችግር ይቅረፍ” ሲሉ አስተያየት ተሰጥተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia