TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Mekelle

° " መንግስት ቃሉና መመሪያው ማክበር አለበት " - የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች

° " ወደ ላይ እንጂ ወደ ጎን የሚሰጥ የቤት መስሪያ ቦታ የለም " - የትግራይ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ


በመላ ትግራይ በተለይ በመቐለ የሚገኙ የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች ከቤት መስሪያ ቦታ ጋር በተያያዘ ከአንድ ሳምንት በላይ ወደ ክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት ምላሽ ለማግኘት ቢመላለሱም ሰሚ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

ትላንት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፅ/ቤት የተሰባሰቡት የ 3043 የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች ለጥያቄያቸው ምላሽ ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀርተዋል።

በቦታው የተገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮችና ጥያቄና የክልሉ መንግስት ምላሽ ተመልክቷል።

60,860 አባላት ያቀፉት 3,043 የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበራት ከጦርነቱ በፊት ተደራጅተው ህጋዊ እውቅና በማግኘት ለቤት መስሪያ የሚሆን ገንዘብ በባንክ ሲቆጥቡ መቆየታቸው ይናገራሉ።

ማህበራቱ ቢያንስ በአንድ ቤተሰብ 5 አባላት ቢኖሩ መንግሰት ቃሉ እንዲጠብቅ እየቀረበለት ያለው ጥያቄ የ300 ሺህ ሰዎች መሆኑን ጠቁመዋል።

ተወካዮቹ ፤ " እኛ በሦስተኛ ዙር የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር ስንደራጅ በክልሉ መመሪያ 4/2011 መሰረት ከኛ በፊት በሁለት ዙር እንደተስተናገዱት 70 ካሬ ለቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጠን ተሰማምተን ነው " ብለዋል።

የክልሉ አስተዳደር ግን ከጦርነቱ በኋላ ጥያቄያቸውን ላለመለስ ጀሮ ዳባ ልበስ ማለቱ እንዳሰዘናቸው በአደባባይ ወጥተው ገልፀዋል።

" የክልሉ አስተዳደር በመመሪያ 4/2011 የገባው ቃል ይተግብር " ተወካዮቹ ፥ በሚሰጣቸው 70 ካሬ ቦታ ቤት ለመስራት እንጂ ኮንደሚንየም ማለትም የጋራ መኖሪያ ቤት ለመስራት ቃል እንዳልፈፀሙ አስረድተዋል።

የማህበራቱ አመራሮች ከቀናት በፊት ለጥያቄያቸው ተገቢ ምላሽ ለማግኘት ለክልሉ ምክትል ጊዚያዊ አስተዳደር ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ጥያቄ አቅርበው ከክልሉ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በመነጋገር መልስ እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ቢሆንም አስከ አሁን የተሰጣቸው ምላሽ እንደሌለ ተናግረዋል።

ከአንድ ሳምንት በፊት የክልሉ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ አልማዝ ገ/ፃድቕ ለድምፂ ወያነ ትግራይ ጉዳዩ በማስመልከት በሰጡት ማብራርያ ፤ ማህበራቱ ከጦርነቱ በፊት ለእንያንዳንዱ አባል 70 ካሬ መሬት ለቤት መገንብያ እንዲሰጥ በሚፈቅደው መመሪያ መደራጀታቸው አምነዋል።

"ይሁን እንጂ ከአሁን በኋላ ወደ ላይ እንጂ ወደ ጎን የሚሰጥ የቤት መስሪያ ቦታ የለም ፤ ስለሆነም ማህበራቱ የሚሰጣቸው ቦታ G+4 ወደ ላይ የሚገነባ የጋራ መኖሪያ አፓርታማ ነው " ብለዋል።

የማህበራቱ ተወካዮች በቢሮ ሃላፊዋ መልስ እንደማይስማሙ ገልጸዋል።

ለፍትሃዊ ጥያቄያቸው ፍትሃዊ ምላሽ ለማግኘት በማለምም ትላንት ቅዳሜ ቀኑን ሙሉ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፅ/ቤት ጠብቀው የሚያናግራቸው የመንግስት የስራ ሃላፊ ባለመገኘቱ ነገ ሰኞ ጥያቄቸውን በሰላማዊ ሁኔታ ማቅረብ እንደሚቀጥሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" የፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሥልጣን ዘመን የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ የተያዘ ፕሮግራም የለም ፤ ምናልባት ወደፊት ሊኖር ይችላል " - የሕ/ተ/ም/ቤትና የአፈ ጉባዔው አማካሪ ኮሚቴ አባል (ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ)

የ6 ዓመት የሥልጣን ዘመናቸውን ያጠናቀቁት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶችን የ2017 የሥራ ዘመን ነገ ያስጀምራሉ። 

የሁለቱ ምክር ቤቶች የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በተገኙበት ነገ ሰኞ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ የሕ/ተ/ም/ቤት መረጃ ያሳያል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የመጀመርያ የሥልጣን ዘመናቸውን ያገባደዱ ቢሆንም፣ ሰኞ የሚጠበቀው የሁለቱ ምክር ቤቶች የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ከተካሄደ በኋላ ቀጣዩ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ምርጫ የሚካሄድ ስለመሆኑ ግን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መረጃ ያለው ነገር የለም። 

የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር የሥልጣን ዘመን 6 ዓመት እንደሆነ፣ ነገር ግን ርዕሰ ብሔሩ ለሁለተኛ ጊዜ ሊመረጥ እንደሚችል ሕገ መንግሥቱ ይደነግጋል። 

የሥልጣን ዘመናቸውን ባጠናቀቁት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ምትክ ሌላ ርዕሰ ብሔር ይመረጥ ይሆን ? ወይም እሳቸው ለሁለተኛ ጊዜ በርዕሰ ብሔርነት የመመረጥ ዕድል ያገኙ ይሆን ? የሚለውን ለማወቅ ሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ የም/ቤቱ አባላትን ያነጋገረ ቢሆንም ሁሉም ስለዚህ ጉዳይ የሰሙት ነገር እንደሌለና ከምክር ቤቱም ይህንን ጉዳይ የተመለከተ መረጃ እንዳልደረሳቸው ገልጸዋል።

ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የአፈ ጉባዔው አማካሪ ኮሚቴ አባል ፤ ሰኞ በሚጀመረው የሁለቱ ምክር ቤቶች መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ አዲስ ርዕሰ ብሔር ምርጫ የሚካሄድ ቢሆን ኖሮ እሳቸው ሊያውቁት እንደሚችሉ በመጠቆም፣ የርዕሰ ብሔር ምርጫ ይካሄዳል የሚል ዕምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል። 

" የፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሥልጣን ዘመን የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ የተያዘ ፕሮግራም የለም፣ ምናልባት ወደፊት ሊኖር ይችላል " ብለዋል።

አንድ የሕግ ባለሙያ ስለ ጉዳዩ በሰጡት ቃል ደግሞ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በርዕሰ ብሔርነት የተሰየሙት ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ/ም መሆኑን አስታውሰው 6ኛ ዓመታቸውን የሚያገባድዱት በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. በመሆኑ አዲስ ርዕሰ ብሔር የመምረጥ ሒደት እስከዚያ ድረስ ሊገፋ እንደሚችል አስረድተዋል።

ከ20 የአገሪቱ የካቢኔ አባላት ግማሹ ሴት ሆነው በተመረጡ በሳምንቱ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፣ በወቅቱ አድርገውት በነበረው ንግግር በዋናነት ሰላምና ሴቶች ላይ ያጠነጠኑ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፣" በኃላፊነት ቆይታዬ ዋነኛ ትኩረቴ ሰላም በማስፈን ላይ እንድንረባረብ ማድረግ ይሆናል… ኢትዮጵያዊነትን ከሰላም ጋር አንድና ህያው ለማድረግ በጋራ እንሥራ "  ብለው ነበር።

አክለውም፣ " የሴቶችን ማንኛውንም ዓይነት ጥቃት የማይቀበል ትውልድ መገንባት አለብን… ሴቶች የቤተሰብም የአገርም ምሰሶ ናቸው፡፡ ሴት አገር ነች፣ አገርን ደግሞ ሴቱም ወንዱም ሊንከባከበው ይገባል " ብለው ነበር።

" ስለሴቶች አብዝቼ የተናገርኩ ከመሰላችሁ ገና ምኑ ተነክቶ ? " ሲሉ የምክር ቤቱን አባላት በፈገግታ ሞልተውት ነበር። 

በተጨማሪ " ታላቅ አገር የመገንባት ህልማችንን ዕውን ለማድረግ ከሰላም ውጪ አቋራጭም አማራጭም የለንም፡፡ ስለዚህም ሁላችንም ሰላማችንን አጥብቀን እንድንጠብቅ ከሁሉም በላይ ሰላም ሲታወክ በምትሰቃየዋ የእናት ስም አጥብቄ እጠይቃችኋለሁ " በማለት ጥሪ አቅርበው ነበር።

የሥልጣን ዘመን ጉዟቸው እጅግ ውስብስብና በርካታ ፈተናዎች ያሉበት እንደሚሆን እንደሚጠብቁ ያስታወቁት ፕሬዚዳንቷ " የተጀመረው ለውጥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖርባትን አገር ዕውን እንደሚያደርግ እተማመናለሁ " በማለት ተስፋቸውን ገልጸው ነበር።

ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሥልጣን ዘመን፣ " ዋነኛ ትኩረቴ ሰላም በማስፈን ላይ እንድንረባረብ ማድረግ ይሆናል " እንዳሉት ሳይሆን እንደ ሥጋታቸው ማለትም፣ " እጅግ ውስብስብና በርካታ ፈተናዎች ያሉበት ኃላፊነት ይሆናል " ብለው እንደ ሠጉት ሆኖ አልፏል። 

በርካታ ሰብዓዊ ጉዳትና የኢኮኖሚ ውድመት ካስከተለው የሰሜኑ ጦርነት አንስቶ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እስካሁን ደም እያፋሰሰ የዘለቀው ግጭትና መከራ በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሥልጣን ዘመን ተከስቷል።

በዚህም ዋነኛ ገፈት ቀማሾቹ ሴቶችና ሕፃናት ዋነኛ ገፈት ቀማሾች መሆናቸው፣ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የምርመራ ሪፖርት ጭምር የተረጋገጠ መሆኑ ይታወሳል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በአዲስ አበባ ከተማ ተወልደው ያደጉ ሲሆን፣ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ተከታትለው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ፈረንሣይ ከሚገኘው ሞንትፔለ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ አግኝተዋል።

የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሣይኛና የአማርኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኢትዮጵያን በመወከል ፦
- በሴኔጋል፣
- በኬፕቨርዴ፣
- በጊኒ ቢሳኦ፣
- በጋምቢያ
- በጊኒ በአምባሳደርነት አገልግለዋል።

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርና የኢጋድ ቋሚ መልዕክተኛ በመሆንም አገልግለዋል፡፡

በተጨማሪ በፈረንሣይ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ፣ በቱኒዚያና በሞሮኮም የኢትዮጵያ ተጠሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተቀናጀ የሰላም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሠርተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በርዕሰ ብሔርነት ከመሾማቸው በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ልዩ ረዳትና በአፍሪካ ኅብረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ በመሆንም አገልግለዋል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተጠናቋል " - ፖሊስ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፤ ዛሬ በቢሾፍቱ የተከበረው የኢሬቻ ' ሆራ አርሰዴ ' በዓል በሰላም መጠናቀቁን አሳውቋል።

" በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል " ሲል ገልጿል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ፦
- አባገዳዎች፣
- ሀደሲንቄዎች፣
- ለበዓሉ ታዳሚዎች፣
- ለቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪ፣
- ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ
- ለወጣቶች እንዲሁም ደግሞ ኃላፊነታቸውን በትጋት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት አካላት ምስጋና አቅርቧል።

#Irreechaa2017 #HoraaHarsadee

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle

የኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
 
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) ስርዓተ ቀብር ዛሬ በመቐለ ተፈጽሟል።

የቀብር ስነስርዓቱ በመቐለ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን የአርበኞች የመቃብር ቦታ ነው የተፈጸመው።

በቀብር ስነስርዓቱ የሟች ቤተሰቦች፣ የመቐለ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች ፣ የህወሓትን ጨምሮ የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም የትግል ጓዶቻቸው ተገኝተው ነበር።

የ3 ሴት ልጆች አባት የሆኑት ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) ባደረባቸዉ ህመም ምክንያት ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው መስከረም 24 / 2017 ዓ.ም በተወለዱ በ60 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

Photo Credit - Tigrai Communication & Demtsi Woyane

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ይህ የሆነው አሁን ከመሸ ከ2:00 በኃላ ነው።

በአንዳንድ ቦታዎችም ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች በስጋት ወደ መሬት ወርደው ተሰብስበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎች ከባለሙያዎች ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል። ይህ የሆነው አሁን ከመሸ ከ2:00 በኃላ ነው። በአንዳንድ ቦታዎችም ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል። የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች በስጋት ወደ መሬት ወርደው ተሰብስበዋል። ተጨማሪ መረጃዎች ከባለሙያዎች ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው። @tikvahethiopia
#Update : በአዲስ አበባ ከተማ በበርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቷል።

ከምሽት 2 ሰዓት በኃላ በርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነበር።

ህፃዎች ላይ የነበሩ ሰዎችም በደንብ ንዝረቱ የተሰማቸው ሲሆን በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ከስጋት አንጻር ወደ መሬት ወርደው ተሰባስበው ነው የሚገኙት።

ከአዲስ አበባ ውጭም በሌሎች አንዳንድ ከተማዎች / ቦታዎች መሰል ሁኔታ እንደነበር ከቤተሰቦቻችን በሚላኩ መልዕክቶች ተረድተናል።

በጉዳዩ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚሰጡትን አስተያየት እናቀርባለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update : በአዲስ አበባ ከተማ በበርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቷል። ከምሽት 2 ሰዓት በኃላ በርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነበር። ህፃዎች ላይ የነበሩ ሰዎችም በደንብ ንዝረቱ የተሰማቸው ሲሆን በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ከስጋት አንጻር ወደ መሬት ወርደው ተሰባስበው ነው የሚገኙት። ከአዲስ አበባ ውጭም በሌሎች አንዳንድ ከተማዎች / ቦታዎች…
#Update

" እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ ሳይሆን አዋሽ አካባቢ የተከሰተ ነው።

ግን በመሬት ውስጥ አልፎ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተሰምቷል።

ይሄን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም። ግን በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ እዚህ ያሉ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።

በሪክተር ስኬል 4.9 ነው ያገኘነው። ይሄም ከፈንታሌ የሚባል ተራራ አለ ወደ መተሃራ አካባቢ ነው የተከሰተው። እስካሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው።

ሰውም ይረጋጋ እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ከሩቅ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በተለይ እዚህ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጣም ተረብሸዋል። ልክ ነው ከዛም ሊሰማ ይችላል።

በሬክተር ስኬል 4.9 ነው ይሄ ነው ያለው መረጃ።

ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን በግልጽ እንነግራለን። " ብለዋል።

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ምክንያት በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ህንጻቸው ሲንቀጠቀጥ እንደነበር ገልጸውልናል። በዚህ ምክንያት ከቤታቸው ወጥተው መሬት ላይ ወርደው ተሰባስበዋል።

#Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ? " እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ…
#Attention🚨

በአዋሽ ፣ መተሀራ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

" በሬክተር ስኬል 4.9 ነው። 150 ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የተፈፀመ ነው። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል " ብሏል።

" በስምጥ ሸለቆች ውስጥ ንዝራቱ ከማሰማት  በሻገር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፈንታሌ ተራሮች ውጭ የደረሰ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም " ሲል አክሏል።

" በደሴ መስመር እስከ ኮምቦልቻ የተየውም ንዝራቱ ነው። ክስተቱ ከሰሞኑ ጀምሮ በፈንታሌ ተራራ እና አዋሽ አካባቢዎች የነበረ ስሜት ነው " ብሏል።

@tikvahethiopia