TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ደመወዝ

" የደመወዝ ጭማሪ ዝርዝሩ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል " - የገንዘብ ሚኒስቴር

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ፤ ከመስከረም ወር 2017 ጀምሮ የሚጨመር ደመወዝ በካቢኔ መፅደቁን አሳውቀዋል።

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ትኩረት ያደረገ የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ መደረጉን አመልክተዋል።

አቶ አህመድ " የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ ለኑሮ ድጎማ ጭምር እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ በካቢኔ ፀድቋል ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ ይደረጋል። የደመወዝ ጭማሪው ከ91 እስከ 92 ቢሊዮን ብር መካከል ተጨማሪ በጀት የሚጠይቅ ይሆናል " ብለዋል።

በነባሩ በጀት የተወሰነ መግባቱን ፤ በተጨማሪ በጀትነትም የሚታወጅ መኖሩን ጠቁመዋል።

" ሲቪል ሰርቫንቱ አጠቃላይ የመንግሥት ሰራተኛው በሁሉም መስክ በፀጥታም በሌሎችም ዘርፍ ያሉትን የኑሮ ጫና ለመቋቋም የሚያስችለውን ድጋፍ ለማድረግ መንግሥት በከፍተኛ ቁርጠኝነት ተገባበት ነው " ሲሉ አቶ አህመድ ተናግረዋል።

" የባለፉት ሁለት ወራት የኢንፍሌሽን አፈጻጸም በሚታይበት ጊዜ እንደተሰጋው አይደለም። የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ ነው ያለው። የተወስነ ጭማሪ በአንዳንድ እቃዎች ላይ እንጂ በአብዛኛው የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው። " ብለዋል።

" እንደዛም ሆኖ የደመወዝ ጭማሪው እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ የሰራተኛውን ቋሚ ደመወዝተኛ ገቢ ያለውን ዝቅተኛውን ትኩረት አድርገን የዝቅተኛውን በጣም ከፍተኛ ጭማሪ አድርገናል የላይኛውን ዝቅተኛ ጭማሪ አድርገን ነው የተሰራው ዝርዝሩ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
" የ5 ተማሪዎቻችን ህይወት አልፏል " - መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ

በቀን 22/01/2017 በግምት ከጥዋቱ 4:00 ገደማ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ በተለምዶ " አባዱላ " የሚባለው መኪና ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል።

እንደ አማራ ፖሊስ መረጃ ፤ አደጋው የደረሰው በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ 015 ቀበሌ ደቦት ልዩ ቦታው እቧዮች ኪዳነምህረት አካባቢ ነው። መኪናው ከባህር ዳር ወደ ወልድያ መስመር ወደ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ ነበር።

መኪናው በወቅቱ 21 ሰው ጭኖ ሲጓዝ እንደነበር ተነግሯል።

ከተሳፋሪዎቹ 7 ሰዎች ሲሞቱ 14 ሰዎች ላይ ጉዳት አጋጥሟል።

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ 5 ተማሪዎቹ በአደጋው እንደሞቱበትና በ13 ተማሪዎቹ ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰ አሳውቋል።

ህይወታቸው ያለፈው ተማሪዎች ፥ አሜሪካ ሙሉ፣ ይርጋ ወርቁ፣ ሰናይታ ካሳ፣ አቤል ግደይ ፣ በላይነሽ ሽፈራው እንደሆነ ገልጿል።

ነፍስ ይማር !

@tikvahethiopia
🎉🎉ኢትዮ 130 lucky slot አሸናፊዎች ሽልማታቸው እየወሰዱ ነው!!

🔥3ቱ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ገና አልተነኩም

በቴሌብር ሲገበያዩ፣ የአየር ሰዓት ወይም ጥቅል ሲሞሉ፣ ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ፣ ሲያወጡ ወይም ሲላላኩ፣ የአገልግሎት ክፍያ ሲፈጽሙ በሚሰበስቧቸው ሲልቨር/ጎልድ ሳንቲሞች በመጠቀም የዕድል ጨዋታ እና የማስታወስ ጨዋታ በመመለስ ሽልማቶችን ያግኙ!

🚘 3 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች
🛺 3 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች
💰 በየቀኑ የ20 ሺህ እና በየሳምንቱ የ50 ሺህ ኢ-የገንዘብ ሽልማቶች በቴሌብር
📱 70 ዘመናዊ ስማርት ስልኮች
🎁 130 ሺህ የሞባይል ጥቅሎች

💁‍♂️ ከእርስዎ የሚጠበቀው አገልግሎቶቻችን እየተጠቀሙ በ131 ጨዋታዎች እየተዝናኑ ዕድልዎን መሞከር ብቻ ነው!
በቴሌብር ሱፐርአፕ ኢትዮ 130 ላኪ ስሎትን (Ethio 130 lucky slot) በመምረጥ ወይም ወደ 131 ok ብለው በመላክ ይመዝገቡ፡፡

ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት አላቸው

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/4dckxdb
🎉የአሸናፊዎችን ዝርዝር ለመመልከት 👇🏼

#130_ዓመታትን_በጽናት_ታላቅ_አገርና_ሕዝብ_በማገልገል_ላይ

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ህጋዊ እና ትክክለኛ 14ኛ ጉባኤ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን " - በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት   " ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ " በሚል መሪ ቃል ሰብሰባ የተቀመጠው በምክትል ሊቀመንበር  አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት  ሰብሰባውን ቀጥሏል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ከፍተኛ ካድሬዎች " ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ…
#Tigray

" የህወሓትን ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል ሲል " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ገለጸ።

በህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የሚመራው ህወሓት ከመስከረም 20 አስከ 22 /2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ያካሄደውን የማእከላዊ ኮሚቴ እና የከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባ ማጠቃለሉ በማስመልከት የአቋም መግለጫ አውጥቷል። 

በዚህም ፥ " የህወሓት ህጋዊነት ለመመለስ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል " ገልጿል።

" ውይይቱን የሚያስቀጥል የትግራይ የሰላም ልኡክ አንደ አዲስ እንዲደራጅና በሰው ሃይል እንዲጠናከር ይደረጋል " ብሏል።

" ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየው የሪፎርም እቅድ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል " ሲልም ገልጿል።

አቶ ጌታቸው የሚመሩት ህወሓት " ድርጅቱን በማጠናከር የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ እንሰራለን " ብሏል። 

በትግራይ የሚታየው ቀላል የማይባል የህግ ጥሰት ስርዓት ለማስያዝና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ በመግለፅም የፀጥታ መዋቅርና የህዝብ ድጋፍ ጠይቋል።

በአቶ ጌታቸው የሚማራው ህወሓት " ከጎረቤቶች ጋር የሚደረግ ግንኙነት ለማሻሻል ሰላማዊ ዝምድና ለማጠናከር ከሁሉም ጎረቤቶች በጋራ እንሰራለን " ብሏል።

ቡድኑ ባካሄዘው የ3 ቀን ውይይት በሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ያልሆኑ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከሰባቱ  የትግራይ ዞኖች የተወጣጡ ከፍተኛ ካድሬዎች መገኘታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

@tikvahethiopia 
" እስከ ሰኞ ንጋት 12:00 ድረስ ሞተር ማሽከርከር አይቻልም " - የትራንስፖርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከሚከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ ለደህንነት ሲባል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 እስከ ንጋቱ 12:00 ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ የሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ኢሬቻ2017

የኢሬቻ ' ሆራ ፊንፊኔ ' እና ' ሆራ አርሰዲ ' በዓልን ለሚያከብሩ ታዳሚዎች ትራንስፖርት መዘጋጀቱን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል።

በአዲስ አበባ በ5ቱም መግቢያ በሮች ወደ በዓሉ ማክበሪያ ቦታ የሚያደርሱ ከአዲስ አበባ ሲቲ ባስ 907 የከተማ አውቶብሶች፣ 400 የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶብሶች መዘጋጀታቸውን ተገልጿል።

ቢሾፍቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል 150 የሚሆኑ ሀገር አቋራጭና መለስተኛ አውቶቢሶች ዝግጁ እንዲሆኑ መደረጉን ተመላክቷል።

በአጠቃላይ ታክሲዎችን ሳይጨምር 1 ሺህ 457 ተሸከርካሪዎች ተዘጋጅተዋል ተብሏል።

#AddisAbaba #Bishoftu

@tikvahethiopia
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከተቀጠሩ ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው እና የ2ኛ ዲግሪ የሌላቸው ከ300 በላይ መምህራኑን በ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ኮርስ እንዳይሰጡ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።

ዩኒቨርስቲው በመምህራኑ ላይ ወርሃዊ ደመወዝ እንዳይከፈላቸው እግድ አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም ይህንን ውሳኔውን ለጊዜው መቀልበሱን ገልጿል።

" ይህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው የመጀመሪያ ዲግሪ ኖሯቸው የተቀጠሩ መምህራን ፤ የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ዩኒቨርሲቲው ያስተላለፋቸውን ተደጋጋሚ ጥሪዎች ተቀብለው ወደ 2ኛ ዲግሪ ትምህርት ባለመግባታቸው ነው " ሲል ዩኒቨርሲቲው አመልክቷል።

የጅግጅጋ ዩኒቨርሰቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዲ አህመድ ምን አሉ ?

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከ1,400 መምህራን በላይ እንዳሉት ፤ ከእነዚህ ውስጥ 800 ገደማው የሁለተኛ ዲግሪ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ከአጠቃላይ መምህራን ውስጥ 350 ያህሉ የመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ያላቸው ናቸው ብለዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ካላቸው መምህራን ውስጥ በትምህርት ላይ ያሉት " የተወሰኑት " እንደሆኑም ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከ4 ዓመት በፊት ባደረገው እንቅስቃሴ ከተቀጠሩ 5 እና ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው አብዛኞቹ መምህራን በ2 ዓመት ውስጥ 2ኛ ዲግሪ እንዲይዙ አድርጎ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከዚያን ጊዜ ጀምረው 2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ እና እየተከታተሉ ያሉ መምህራን እንዳሉ የገለጹት ም/ ፕሬዝዳንቱ፤ " አንዳንዶች ለመማር ፈቃደኛ ያልሆኑ ግን እዚያው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የቀጠሉ ናቸው " ብለዋል።

መምህራኑ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ላለመቀጠላቸው የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ አንስተው " አንዳንድ መምህራን ሌላ ተደራቢ ሥራ አግኝተው መምህርነቱን እንደ ሁለተኛ ሥራ መመልከታቸው አንዱ ምክንያት " ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው እነዚህ መምህራን የድኅረ ምረቃ ትምህርት ያልጀመሩበትን ምክንያት በተመለከተ በተደጋጋሚ ስብሰባዎችን ቢጠራም " ሳይሳተፉ ቀርተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

" 2017 ዓ.ም. ሊጀመር ሲል አንደኛ ዲግሪ ያላቸውን መምህራን ብቻ ስብሰባ ጠርተን ነበር። መጀመሪያ ላይ የመጡልን 11 መምህራን ብቻ ናቸው። ሁለተኛ ዕድል እንስጥ ብለን የዛሬ ሳምንት ስብሰባ ጠርተን ነበር። ከ300 በላይ መምህራን ውስጥ 48 መምህራን ነው የመጡት "  ሲሉ ወቅሰዋል።

በዚህም መምህራኑ 2ኛ ዲግሪ ባለመያዛቸውና እና የዩኒቨርሰቲው አመራር በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ አለመካፈላቸውን ተከትሎ እየተጀመረ ባለው የ2017 ትምህርት ዘመን " ምንም ዓይነት ኮርስ እንዳይሰጡ " ውሳኔ መተላለፉን አስታውቀዋል።

" እነዚህ መምህራን መማርም ስለማይፈልጉ፤ በአንደኛ ዲግሪ ያለ መምህር አንድም ኮርስ እንዳይሰጥ ወስነናል። " ሲሉ ተናግረዋል።

መምህራኑ ከተላለፈባቸው የማስተማር እገዳ በተጨማሪ ደመወዝም እንዳይከፈላቸው ውሳኔ ተላልፎ እንደነበር ዶ/ር አብዲ ተናግረዋል።

ይሁንና ውሳኔው በተላለፈበት በአሁኑ ወቅት የመስከረም የደመወዝ መክፈያ ጊዜ በመድረሱ እና " በዚህ ጊዜ ደመወዝ ማቋረጥ ስለማይቻል " ዩኒቨርሲቲው ይህንን ውሳኔውን ለጊዜው መሻሩን ዶ/ር አብዲ አስታውቀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-AMHARIC-10-04

መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
" ወደ ቤይሩት እና ቴልአቪቭ የሚያደርገው በረራ ተቋርጧል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ላይ በሀገራቱ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ ቤይሩት እና ቴልአቪቭ የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት ማቋረጡን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ወደ ቴላቪቭ የሚያደርገውን በረራ እስከ ጥቅምት 7 ቀን አቋርጧል።

ወደ ቤይሩት የሚያደርገውን በረራ ለጊዜው ላልተወሰነ ጊዜ ማቆሙን ነው ያስታወቀው፡፡

የመካከለኛው ምስራቅ በጦርነት እየታመሰ እንደሆነ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ የ2017 ኢሬቻ ' ሆራ ፊንፊኔ ' በዓል ዋዜማ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ #ኢሬቻ2017 #Irreecha2017

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia