TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#DireDawa

" አንዳንዴ አላህን መፍራት ያስፈልጋል። ክርስቲያም ከሆን የምናመልከውን ፈጣሪን መፍራት ያስፈልጋል።

ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል።

በአንድ ለሊት የውጭ ምንዛሬው ሲጨምር ባንክም ውድድር ውስጥ ገብቷል።

ግን እዚሁ ስቶር የነበረውና ከ3 ወር በፊትና ከዛ በፊት የገቡ እቃዎች በአንዴ 300 ፐርሰንት መጨመር ሃጢያት አይደል ? አላህ እራሱ ይወደዋል ወይ ?

የሃላል ነገር ነው አይደል ሰው መብላት ያለበት፤ ይሄ ድሃ ማህበረሰብ ነው ሁሌ እናተን በችግር ጊዜ የሚያግዛችሁ።

ቢያንስ ለ3 ወር ! በአዲሱ ምንዛሬ ሲገባ ያኔ እኮ ባላንስ ይደረጋል ፤ ምን ነበር የሚለውን ማየት ይቻላል።

ወደ እርምጃ ሲገባ ግን የከፋ ይሆናል።

እውነቱን ለመነጋገር ከእናተ የድሃውን ማህበረሰብ እምባውን ማበስ ይሽለናል። በግልጽ ለመነጋገር።

ለሰው ብላችሁ አይደለም፤ ለማንም ብላቹ አይደለም ለህሊናችሁ ብላችሁ ስሩ፤ ዛሬ የዘራችሁትን ነገ ልጆቻችሁ የተሻለ ነገር ያገኛሉ። "

የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር (በቅርቡ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በነበራቸው ውይይት የተናግሩት)

#DireDawaCity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ፣ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ከኢትዮጵያ መንግሥት የተበረከተላቸውን የ2 ሚሊዮን ብር ሽልማት " አልቀበልም " ብለው መልሰው ከመድረክ መውረዳቸው ይታወሳል። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር " ገንዘቡ ወደ መንግስት ካዝና ተመላሽ ይሆናል። ምክንያቱም ስጦታ በግድ ውሰዱ ስለማይባል " ሲል ለኤፍ ኤም 97.1 ተናግሯል። አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ፤ ለሙያውና…
#GemedoDedefo

ከፕሬዜዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እጅ የተሰጣቸውን የ2 ሚሊዮን ብር ሽልማት " የኛ የአሰልጣኞችን ልፋት አመጥንም " ብለው ሳይቀበሉ የቀሩትና በኃላም " እዛ ቦታ ላይ ያን ማድረግ አልነበረብኝ ፤ ተሳስቻለሁ " በማለት ህዝቡን እና ፕሬዜዳንቷን በይፋ ይቅርታ የጠየቁት አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ዛሬ " ታስረዋል " ከሰዓታት በኃላ ደግሞ  " ከእስር ተፈተው ወደ ቤት ገብተዋል " የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩባቸው ነበር።

እሳቸው ግን " እኔ አልታሰርኩም ፤ እስር ቤትም አልነበርኩም  " ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዙሪያ ታማኝ ነው የሚባለው ጋዜጠኛ ኤቢሳ ነገሰ አሰልጣኙን በስልክ እንዳገኛቸውና " ጉዳዩም እንደሚባለው እንዳልሆነ "  ገልጿል።

እሳቸው አሰልጣኝ ገመዶም እስር ቤት እንዳልነበሩ ቃላቸውን እንደሰጡት አመልክቷል።

" እኔ አልታሰርኩም " ማለታቸውን ጋዜጠኛው አሳውቋል።

በሌላ በኩል አሰልጣኙ በራሳቸው የፌስቡክ ገጽ መታሰራቸው " ውሸት ሀሰተኛ ዜና " እንደሆነ እና ቤታቸው እንደሚገኙ ገልጸው ወዲያው ደግሞ አጥፍተውታል።

ጉዳዩን ከሚያውቁ ሌሎች አካላት በተገኘው መረጃ ግን አሰልጣኙ ታስረው እንደነበር ፤ ምሽት ላይ ግን መፈታታቸው ተሰምቷል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አሰልጣኙ " አልወስድም " ያሉት  ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና ተመላሽ እንደሚሆን ማሰወቁ ይታወሳል። " ስጦታ በግድ ውሰዱ አይባልም " ነው ያለው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia አትሌቲክሳችን ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል። ይህ መሆን ያለበት ደግሞ በትክክለኛ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ነው። የኦሎምፒክ ውጤቱ አንገት የሚያስደፋ ነው። በጭቅጭቅ፣ በንትርክ፣ በየሚዲያ ላይ በሚደረግ ምልልስ የተጀመረው የፓሪስ ውድድር ኢትዮጵያን የማይመጥን እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት ተመዝግቦበት አልቋል። ጥፋት ከደረሰ እና ውጤት ከጠፋ በኃላ የሚቀርብ ይቅርታ ተቀባይነት የለውም። …
#Ethiopia

" ኢትዮጵያ ፓሪስ ላይ በአትሌቲክሱ ያስመዘገበችው ዝቅተኛ ውጤት በቀናት ውስጥ ተረስቶ አጀንዳው ተቀይሯል።

ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት ኃላፊነቱን የሚወስደው ማነው ? ቀጣዩ እርምጃስ ምንድነው ? ወይስ ጉዳዩ ተረሳስቶ ይቀራል ነው ?

ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ስሟ ከፍ ብሎ የሚጠራባት አትሌቲክስ ታሟል። ስለሆነም ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።

ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው የአትሌቲክስ ሰዎች ሁሉ ቁጭ ብለው መክረው ለውጥ ያምጡ።  

ዳግም ህዝብ በሚኮራበት #አትሌቲክስ እንዳያዝን እና እንዳይበሳጭ ዘላቂ መፍትሄ በአስቸኳይ መፈለግ አለበት።

ለነገ ዛሬ ካልተሰራ ተመሳሳይ ነገር ይጠብቀናል። " @nousethiopia

@tikvahethiopia
#Oromia

" አገልጋይ ካህንን ጨምሮ 6 ምዕመናን በታጣቂዎች ተገድለዋል " - ነዋሪዎች

በአርሲ ሀገረ ስብከት፣ በአሰኮ ወረዳ በጢዮ ቀበሌ ጠለታ ጨፋ ከተማ " የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን " አገልጋይ ካህንን ጨምሮ 6 ምዕመናን በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎቹን ዋቢ በማድረግ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ካህኑ ሥጋ ወደሙን አቀብለው ምእመናንን እያሳለሙ በነበረበት ሰዓት ነው የተገደሉት።

3 ምዕመናን ከባድ ጥቃት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ነዋሪዎቹ ድርጊቱን የፈጸሙት " ኦነግ ሸኔ " ተብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል።

ግድያው የተፈጸመው ከነሐሴ 7 ቀን 2016 ዓ / ም ጀምሮ እንደሆነ ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።

ከዚህ ባለፈም ፥ በተለያየ መንገድ ቤተ ክርስቲያኗን ሲረዱ የነበሩ ምዕመናን ተለይተው ሀብት እና ንብረታቸው መቃጠሉንና የአካባቢው ምእመናን ቤታቸውን ትተው በዱር በስጋት ውስጥ እንደሆኑ ተጠቁሟል።

ጥቃቱ ከዚህ ቀደምም ተፈጥሮ እንደነበር አንስተው " ለበላይ አካል ብናሳውቅም ጩኸታችንን የሚሰማ አጥተናል " በማለት ጥሪ ማቅረባቸውን ከቴሌቪዥን ጣቢያው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጉምሩክ ° “ ጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን በደብዳቤ ሽሮ ከእጥፍ በላይ ቀረጥ ‘ ክፈሉ ’ እያለን ነው ” - አስመጪዎች ° “ ከአፈጻጸም አኳያ ምን ሊያስቸግረን ይችላል ? የሚለውን ውይይት እየተደረገ ነው ” - ጉምሩክ ኮሚሽን የጉምሩክ ኮሚሽን ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ምክንያት በማድረግ ከተቀመጠው አዋጅ ውጪ የቀረጥ ክፍያ እየጠየቃቸው መሆኑን አስመጪ ነጋዴዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለዋል፡፡…
#ጉምሩክ

➡️ “ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የኮንቴነር ዲመሬጅ በየቀኑ እየጨመረብን ነው ” - አስመጪዎች

➡️ “ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ” - ጉምሩክ ኮሚሽን

አስመጪዎች ፣ ተግባራዊ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን የሚተካ ' አዲስ መመሪያ ' በማውረድ እስከዛሬ ሲከፍሉት ከነበረው ቀረጥ ከእጥፍ በላይ ካልከፈሉ እቃቸውን መውሰድ እንዳይችሉ እያደረጋቸው መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡

ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅነው የጉምሩክ ኮሚሽን፣ “ አስመጪዎቹ የሚያነሳቸውን ጉዳዮችን ኮሚሽኑ ተረድቷል፡፡ ከህግ አንጻርም ምን መሆን ነው ያለበት ? ከአፈጻጸም አኳያስ ምን ሊያስቸግረን ይችላል ? የሚለውን ውይይት እየተደረገ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር፡፡

አስመጪዎቹ ዛሬስ ምን አሉ ?

“ ምንም የተቀየረ ነገር የለም፡፡ አሁንም ከዶላር ጭማሬው በፊት ለተመዘገቡት እቃዎች መፍትሄ አልተሰጠም፡፡ ወቅታዊ ስራ እያለፈን ነው፡፡ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የኮንቴነር ዲመሬጅ በየቀኑ እየጨመረብን ነው፡፡

በሌላ በኩል ፥ ለተማሪዎች መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎች አሉን፡፡ ይህ ጊዜ አለፈን ማለት እቃው ለአንድ ዓመት መጋዘን ነው የሚቀመጠው፡፡ ብዙ ጊዜ የሚያልፍባቸው ዕቃዎችም ይኖራሉ ምግብ እና መድኃኒቶች ” ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ትላንትና (ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ/ም) የተወሰነ ማሻሻያ አድርጎ ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም ወዲህ ለተመዘገቡት እቃዎች መልቀቂያ እንዲሰጥ በቃል ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር ፤ ነገር ግን ‘ ከጉምሩክ ፕሮሰስ ደብዳቤ ነጻ ነህ ’ ተብሎ መልቀቂያ የሚሰጥበት ክፍል ‘ ደብዳቤ አልደረሰኝም ’ እያለ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ውይይት ማድረጉን መግለጹ መልካም ሆኖ እያለ፣ ለውሳኔ በዘገዬ ቁጥር ብዙ አሉታዊ ተፅዕኖዎች እንደሚደርሱባቸው ገልጸው፣ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ በሰጡን ምላሽ፣ “ ኮሚሽኑ እየሰራበት ነው በጉዳዩ ላይ፡፡ ምናልባት ነገ ምላሽ ይሰጣል፡፡ ሌላው ጉዳይ ካልዘገዬ በስተቀር ነገ (ነሐሴ 10) ምላሽ ይሰጣል ብዬ ኤክስፔክት አደርጋለሁ ” ብለዋል፡፡

“ ነገ ጠብቁ ፣ ብቻ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ብዬ ነው ኤክስፔክት የማደርገው ” ነው ያሉት።

(አስመጪዎቹን ቅር ያሰኘው የኮሚሽኑ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ

ስልክዎን በአቢሲንያ POS ማሽኖች ላይ በማስጠጋት በዲጂታል ካርድዎ ቀለል አድርገው ይክፈሉ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#DigitalVisacard #Visa #ApolloVisacard #BoAVisacard #Visacard #Digitalethiopia #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#Infinix_Note40_Pro_Plus

አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ከፍተኛ ጥራት ያለው 108 ሜጋ ፒክስል ካሜራው በተለያዩ አማራጮች ቁልጭ ያለ ፎቶን ይሰጦታል በተጨማሪም የሱፐር ዙም ቴክኖሎጂው ከርቀት ሆነው ጥራት ያለው ምስልን ማንሳት ያስችላል፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
🔈#የመምህራንድምጽ

° " ግንባታው እንዲቆም ተደርጎብናል " - መምህራን

° " ጉዳዩን የጸረሙስና አካላት ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል፤ ምርመራ ተጀምሯል " - የሀዋሳ ፖሊስ

ከሰሞኑን " በማህበር ተደራጅተን የምንገነባውን የመኖሪያ ቤት ግንባታ በማስቆም እንዲገነባልን ውል የገባውን ተቋራጭ አሰሩብን " ያሉ የሀዋሳ ከተማ መምህራን ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

መምህራኑ " አመራሩ ሊደግፈን ሲገባ እየገፋን ነው " ብለዋል።

" በሀገሪቱ ጠ/ ሚኒስትር ሳይቀር ለመምህራን ድጋፍ ተደርጎ የቤት ባለቤት የምንሆንበት መንገድ ይመቻች በተባለበት በዚህ ወቅት መምህራን የሚገነቡትን ቤት አስቁሞ ተቋራጭን ማሰር መንግስትና መምህራንን ለማጋጨት የታሰበ ሴራ እንጅ ሌላ ምንም አይደለም " ብለዋል።

" ድርጊቱ አሳፋሪ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

መምህራኑ፤ ከሳምንት በፊት አመራሩ በመምጣት " በርቱ " እንዳላቸውና ከፌደራል ሳይቀር እንግዳ ጋብዞ ፣ እገዛ ልናደርግ ዝግጁ ነን " እንዳላቸው ተናግረዋል።

በድንገት ግን ተገልብጦ ስራው ህጋዊ አይደለም ማለቱን ጠቁመዋል።

" ችግሮች ቢኖሩ እንኳን በውይይት ማስተካከል ይቻላል " የሚሉት መምህራኑ ለ9 አመታት የቆመ ቤት ድንገት መሰራት ሲጀምር ለማስቆም መሯሯጥ ከጀርባው ሌላ ዓላማ ያነገበ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል።

መምህራኑ ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚያሰሩትን የህንጻ ዲዛይን ከG+3 ወደ G+4 መቀየራቸውን የከተማው ማዘጋጃ ቤት የማህበራት ማደራጃ እና የከንቲባ ጽህፈት ቤት የሚያውቀው እንደሆነ ጠቁመዋል።

ይህ ሆኖ እያለ ግንባታው #እንዲቆም መታዘዙን ገልጸው ፤ " ወቅቱ መምህራን የሚደገፉበት እንጅ ጥሪታቸውን ያፈሰሱበትን የሚቀሙበት አይደለምና እንቅፋት የሆኑብን አካላት ሊተዉን ይገባል " ብለዋል።

" በህግ አምላክ እጃችሁን ከድሀው መምህራን ላይ አንሱልን ፤ ይህ ባይሆን ግን አደባባይ በመውጣት ጩኸታችንን ለማሰማት ዝግጁ ነን " ሲሉም ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የከተማው አስተዳደር ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በአጠቃላይ ለስድስት የመምህራን መ/ቤቶች ህብረት ስራ ማህበራት የጻፈውን ደብዳቤ ደርሶት ተመልክቷል።

በዚህም ደብዳቤው ፦

- የነበረው ዲዛይን ከG+3 ወደ G+4 ማስተካከያ እንዲደረግ ተጠይቆ የG+4 ዲዛይን መሰጠቱ ፤

- ነገር ግን ይህ ዲዛይን የመምህራን መ/ቤቶች ማህበራት ከተደራጁበት አላማ አንጻር ተጻራሪ ዓላማ እንዳለው ስለተደረሰበት የG+4 ዲዛይን መሰረዙን ሌላ ደብዳቤ እስኪላክላቸው ድረስ ቀድሞ በነበረውም G+3 ዲዛይን ግንባታ ማካሄድ እንደማይችሉ ያዛል።

የመምህራኑን ጥያቄ ይዘን ጥያቄ ያቀረብንለት የከተማው ፖሊስ ጉዳዩን የጸረሙስና አካላት ወደ ፍርድ ቤት ወስደዉ ምርመራ እንደጀመሩበት በመግለጽ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጉምሩክ

(አስመጪዎች)

" በኢንቮይስ ያልተከፈሉ አሉ። ብዙ እቃዎች ናቸው ያሉት። እቃዎቹ አንድ ላይ ጉምሩክ የገቡ ናቸው።

የነዛና የነዚህ ልዩነት በጣም ሰፊ ነው። ከ4 እስከ 5 ሚሊዮን በኮንቴነር ጭማሪ የሚያመጡ ናቸው።

እነዚህም አብረው የሚስተናገዱበት መንገድ መኖር አለበት።

እቃዎቹ ሰሞኑን የታሪፍ ፣ የቀረጥ ለውጥ ሁሉ ተደርጎባቸው ነበር። በአንድ አይተም እስከ 10 ዶላር ጭምር ተደርጎ ነበር ከሬት ውጭ እሱ ላይ ብዙ ቅሬታ አልነበረም ሁሉም አንድ ላይ ስለጨመረበት።

አሁን ላይ እቃው አብሮ ገብቷል። እነዚህ ኢንቮይስ ከፍለዋል። እኛ በኢንቮይስ አልከፈልንም። ተመሳሳይ እቃዎች ናቸው።

የእነሱ ይውጣ ፤ እናተ ደግሞ በአዲሱ ሬት ክፈሉ ብንባል በጣም ትልቅ ልዩነት ይኖራል። በአንድ ገበያ ላይ ተወዳድሮ ለመስራት የሚቻል አይደለም።

ጉምሩክ ይኔንም ስጋታችንን ቢይይልን።

ሁለት ቦታ ተከፍለናል ፤ በኢንቮይስ የከፈሉ አሉ በኢንቮይስ ያልከፈልን አለን። ልዩነቱ ብዙ ነው በሚሊዮኖች ነው።

አንድ ገበያ ላይ  ነው የምንሰራውና እኛንም ከገበያ እንዳያስወጣን ይሄም ይታይልን። "

#CustomsCommission

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጉምሩክ ➡️ “ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የኮንቴነር ዲመሬጅ በየቀኑ እየጨመረብን ነው ” - አስመጪዎች ➡️ “ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ” - ጉምሩክ ኮሚሽን አስመጪዎች ፣ ተግባራዊ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን የሚተካ ' አዲስ መመሪያ ' በማውረድ እስከዛሬ ሲከፍሉት ከነበረው ቀረጥ ከእጥፍ በላይ ካልከፈሉ እቃቸውን መውሰድ እንዳይችሉ እያደረጋቸው መሆኑን ለቲክቫህ…
#Update

" ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " - ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ

ጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ናቸው።

በዚህም ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።

ጉምሩክ ፤ " የሠነድ ምዝገባ እና ማጣራት ሂደቱን በአግባቡ እየሠራ ይገኛል " ብለዋል።

" የብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " ሲሉ አረጋግጠው " የቀረቡ ሠነዶች ያልተሟሉ እና ቀሪ ጉዳዮች ኖረው ተቀባይነት ያላገኙ ሠነዶች የሚስተናገዱት በዕለቱ የምንዛሪ ተመን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ባለው የአሠራር መመሪያ መሠረት የገቢ ዕቃዎችን ሠነድ በመፈተሽ ወደ ሀገር እንዲገቡ እያደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

" በምንዛሪ ግብይቱ ላይ ባለው ለውጥ ምክንያት የተለያዩ ጥያቄዎች አሉ " ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ " ከሕግና መመሪያ ውጭ የተሠራም ሆነ የሚሠራ ሥራ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" እኛ #የሥራ_መመሪያዎችን ለደንበኞቻችን ሁሉ የማሣወቅ ሥራ እየሠራን ነው ፤ በአሠራር ሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል " ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#EthiopianCustomsCommission #FBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Alert🚨 ከተ.መ.ድ የጤና ኤጀንሲ እንደተገኘው መረጃ በቅርቡ ኤምፖክስ (Mpox) ለመጀመሪያ ጊዜ በ4 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ፦ - በጎረቤታችን ኬንያ ፣ - በቡሩንዲ ፣ - በሩዋንዳ - በኡጋንዳ ተገኝቷል። ሀገራቱም ሪፖርት አድርገዋል። በነዚህ ሀገራት ውስጥ የታየው በሽታ በኮንጎ ካለው ጋር የተገናኘ ነው። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም Mpox በሽታ የሚከሰተው በቫይረስ አማካኝነት ነው።…
#Mpox🚨

የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የዓለም አቀፍ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት እንደሆነ ካወጀ በኃላ ስውዲን የሚጀመሪያውን ኬዝ አግኝታለች።

በቫይረሱ የተያዘው ሰው ወደ አፍሪካ የጉዞ ታሪክ አለው ተብሏል።

ፓኪስታንም በተመሳሳይ ሶስት በMpox ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ማግኘቷን ይፋ አድርጋለች። 3ቱም ቫይረሱ የተገኘባቸው ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ተጉዘው ፓኪስታን የገቡ እንደሆነ የሀገሪቱ የጤና ባለስልጣናት ገልጸዋል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ቫይረሱ በተለይም አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሳራጨ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜም በ4 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ኬንያ ፣ በቡሩንዲ ፣ በሩዋንዳ ፣ በኡጋንዳ ተገኝቷል።

በቫይረስ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው Mpox በወሲባዊ ግንኙነት ፣ በቆዳ ንክኪ ፣ በቅርብ ርቀት ሆኖ ማውራት / መተንፈስ ፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ባለ የቅርብ ግንኙነት ይተላለፋል።

በአፍሪካ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከ500 በላይ ሰዎችም ሞተዋል።

ፎቶ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#Gamo : ሰሞኑን ለሶስት ተከታታይ ቀናት በጣለ ከባድ ዝናብ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት በጋሞ ዞን በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካምአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

መረጃው  የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጉ/ጽ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia