TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
ብር ለኢትዮጵያ የ800ሜትር ሴቶች ውድድር ፍፃሜውን ሲያገኝ አትሌት ፅጌ ድጉማ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገራችን ሁለተኛውን የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች። @tikvahethiopia
#TsigeDuguma

ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ በ800 ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ለሀገሯ ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘችው ፅጌ ዱጉማ ከውድድሩ በኃላ " JESUS IS LORD ! " የሚል ጽሁፍ አሳይታለች።

ፅጌ ስሟ ተጽፎ ደረቷ ላይ ከተለጠፈበት ወረቀት የጀርባ ክፍል ላይ ነው ይህን መልዕክት ፅፋ ገብታ ያስተላለፈችው።

የዘንድሮ የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ስነስርዓት በክርስቲያኖች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሶ እንደነበር ይታወሳል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
ፌዝ ኪፕዬጎን ውጤቷ ተሰረዘ ፤ ሲፋን ሃሰን ሁለተኛ ሆነች። ከደቂቃዎች በፊት በ5000ሜትር ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው ፌዝ ኪፕዬጎን ውጤቷ መሰረዙ ተገልፆል። ኪፕዬጎን በውድድሩ ከጉዳፍ ፀጋይ ጋር በነበራቸው አካላዊ ንክኪ (መደነቃቀፍ) ምክንያት ውጤቷ ሊሰረዝ ችሏል። ይህንንም ተከትሎ ሲፋን ሀሰን ሁለተኛ ፤ ጣልያናዊቷ ባቶሶሌቲ ሶስተኛ ሆነዋል። Via @tikvahethsport
ኬንያ የብር ሜዳሊያዋን አስመለሰች።

ከጉዳፍ ፀጋይ ጋር በነበረው መገፋፋት (መደነቃቀፍ) የፌዝ ኪፒዬጎን ውጤት መሰረዙን ተከትሎ የኬንያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ይግባኝ በማቅረብ ይግባኙ ተቀባይነት አግኝቷል።

ይህን ተከትሎ የኪፕዬጎን 2ኛ ደረጃ መፅደቁን የሀገሪቱ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አሳውቋል።

በዚህም ኬንያ በ5000ሜትር ውድድር የወርቅ እና ብር ሜዳልያ አሸናፊ መሆን ችላለች።

ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ወደ ሶስተኛ ደረጃዋ ተመልሳለች።

ድራማዊ ነው !

@tikvahethiopia
We are Hiring !

Ethio telecom is seeking to hire young, energetic, and customer-focused professionals with zero years of experience for the position of Contact Center Advisor proficient in:

👉🏼 Amharic
👉🏼 Afaan Oromoo
👉🏼 Af-Somali and
👉🏼 Tigrigna

Qualified individuals who meet the requirements are encouraged to apply through the Ethio telecom website before August 11, 2024. 

Click here to apply: https://bit.ly/3AchAM4
Watch how to apply for the vacancy: youtu.be/6h-78lnmft8
" እባካችሁ የመኖሪያ ፍቃዴን አፋልጉኝ !

እኔ ወንድማችሁ ከጀርመን ሀገር ነው የመጣሁት።

ከላይ የምትመለከቱት የጀርመን ሀገር የመኖሪያ ፍቃድ ጠፍቶብኛል።

ፍቃዱ የጠፋብኝን ትክክለኛ ቦታ ማወቅ ባልችልም በዕለቱ ከለቡ ወደ አዳማ መስመር በመኪና ተጎዤ ነበር።

የኤምባሲው ፕሮሰስ ረጅም ጊዜ የሚወስድ ነው። ረጅም ዓመታት በጀርመን ሀገር የሰራሁበት ፍቃድ ነው።

ለትብብራችሁ በፈጣሪ ስም እያመሰገንኩ ፤ ወረታውንም እከፍላለሁ

0911251959 የስልክ ቁጥሬ ነው "

@tikvahethmagazine
“ የልጅነት ልጄን አድኑልኝ። ሁለት የልብ ክፍተት ህመም አለበት ፤ ለህክምና 665 ሺህ ብር ተጠይቄአለሁ ” - የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህር

የ2 ዓመት ከ5 ወር ልጃቸው የታመመባቸው አቶ ገ/መድህን መብርሃቱ የተባሉ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ለህክምና የተጠየቁት ገንዘብ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ እርዳታ እንዲደረግላቸው ተማጸኑ።

ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡት የህፃኑ አባት፣ “ ህፃኑ ሁለት የልብ ክፍተት አለበት። ጥቁር አንበሳ የህፃናት ልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ሂጄ ነበር ‘ወረፋው ብዙ ነው’ አሉኝ ” ብለዋል።

“ የግል ህክምና ሂጄ ደግሞ ‘ልጄህ በአስቸኳይ ካልታከመ አደጋ ላይ ነው’ አሉኝ። ለህክምናው 665 ሺህ ብር ተጠይቄአለሁ። ይህ ገንዘብ በጣም ከአቅሜ በላይ ነው ” ሲሉ አክለዋል።

“ መምህር ነኝ። የማስተምረው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ነው። ይሄ የልጅነት ልጄ ነው። ገና 29 ዓመቴ ነው " ያሉት መምህሩ፣ " የኢትዮጵያ ህዝብ ያቅሙን በማዋጣት የልጅነት ልጄን በማትረፍ ይተባበረኝ ” ሲሉ ተማጽነዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ሀኪም ቤት ደብዳቤ ለህክምና የተጠየቀው ገንዘብ 665 ሺህ ብር መሆኑን፣ ሌላኛው የህክምና ውጤት ደግሞ፣ ህፃኑ ሁለት የልብ ክፍተት እንዳለበት ያስረዳል።

መርዳት ለምትሹ፣ የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000543793508 (ገብረመድህን መብራህቱ ኣብርሃ)፣ ለመደወል 0914178980 (አባት)፣ 0946482480 ተ/ወይኒ ፍሰሃ (እናት) መጠቀም ይቻላል።
 
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ : ንግድ ባንክ ምዛሬውን በትላንትናው ተመን ሲያስቀጥል በግል ባንኮችም ዛሬ ያን ያህል ለውጥ የለም።

በንግድ ባንክ ዛሬ ዶላር እንደትላንቱ መግዣው 95.6931 ሲሆን መሸጫው 101.4347 ነው።

የሌሎችም ሀገራት ምንዛሬ በትላንቱ ቀጥሏል።

ባንኩ ከቅዳሜ አንስቶ ተመሳሳይ የምንዛሬ ተመን እየተጠቀመ ነው።

እስካሁን ድረስ ዕለታዊ ምዛሬያቸውን ይፋ ያደረጉ የግል ባንኮችም ቢሆኑ የአብዛኞቹ ምንዛሬያቸው ከትላንት ብዙ የሚለይ አይደለም።

(የዛሬ ሐምሌ 30/2016 ዓ/ም የባንኮች ዕለታዊ ምንዛሬ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ  ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ። ቤንዚን በሊትር 82 ብር ከ60 ሳንቲም ሲገባ ነጭ ናፍጣ 83 ብር ከ74 ሳንቲም ሆኗል። ከዛሬ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአይሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣ እና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል። በዚህ መሰረት ፦ ቤንዚን - ብር 82.60 በሊትር ነጭ ናፍጣ - ብር 83.74…
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።

የነሀሴ ወር 2016 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ሃምሌ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።

የነዳጅ ማደያዎችም ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ እንደታዘዙ አመልክተዋል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ቢዝነስ በዚህ ዘመን ቅልጥፍና ይፈልጋል፤ አፖሎ መርቻንት አፕ በቀላሉ ያገበያያል።

አፖሎ መርቻንት አፕ ለካፌ፣ ለሬስቶራንቶች ፣ ለሱፐርማርኬቶች እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎት ሰጪ አካላት የተዘጋጀ ሲሆን ለሸጡት እቃ ወይም አገልግሎት ክፍያ የሚቀበሉበት የሞባይል መተግበሪያ ነው፡፡ 

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=apollo.boa.com&hl=en&pli=1


አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
የፅህፈት ቤት ኃላፊው ከግድያ ለጥቂት አመለጡ።

በትግራይ ማእከላዊ ዞን የአክሱም ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ለጥቂት ማማለጣቸው ተሰምቷል።

በኃላፊው ላይ የግድያ ሙከራ የተፈፀመው ሀምሌ 28/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ነው ተብሏል።

ኃላፊው ስራ ላይ አምሽተው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ከተኮሱባቸው ሁለት ጥይቶች ያለ ጉዳት ተርፈዋል።

የአክሱም ከተማ ፓሊስ የግድያ ሙከራ ተግባሩን የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋል በጥረት ላይ እንደሚገኝ ገልፆ ህዝቡ የተለመደ ትብብሩ እንዲያደርግለት ጠይቋል።

የቱሪዝም መናገሻዋ የአክሱም ከተማ ከአስከፊውና ደም አፈሳሹ የትግራይ ጦርነት በኃላ በተጀመረው የአውሮፕላን በረራ አገልግሎት የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች መቀበል ጀምራለች።

ስለሆነም ይህንን መሰል የፀጥታ ስጋቶች የቱሪስት ፍሰቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳለው በመገንዘብ የፀጥታ መዋቅሩ የተቀናጀና የተናበበ ስራ መስራት እንዳለበት በርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች አስተያየት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ከተማና ወምበራ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ ችግር ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። በተለይም በወምበራ ወረዳ አገልግሎቱ ከተቋረጠ አራት ወራት እንዳስቆጠረ ገልጸው፣ እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ) መፍትሄ እንዳልተገኙ ተናግረዋል። ሞባይል በጀነሬተር ቻርጅ ለማድረግ እንኳ በየቀኑ 20 ብር እንደሚያወጡ…
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ የተለያዩ ቦታዎች ኤሌክትሪክ እንደተቋረጠ፤ በተለይም በአንዳንዶቹ አካባቢዎች ከተቋረጠ ከ3 ወራት በላይ እንዳስቆጠረ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤት ማለታቸው ይታወሳል፡፡

አሁንም ድረስ ችግሩ መቀጠሉን መብራት እንደሌለ ክረምቱን እጅግ እንዳከበደባቸው፣ ህይወታቸውንም ማመሰቃቀሉን እንደቀጠለ ተናግረዋል።

እኛም የወገኖቻችንን ጥያቄ ይዘን ' ይመለከታቸዋል ' የሚባሉትን አነጋግረናል።

ለምን ኃይል ተቋረጠ ? ችግሩን ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው ?

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሚኒኬሽን " እኛ እኮ ኃይል ማቅረብ ነው ከዚያ የዘለለ የስርጭት ሥራ አንሰራም፡፡ ስለዚህም የሥርጭት ሥራን የሚሰሩትን ብትጠይቁ ነው የተሻለ የሚሆነው " አለን።

እሺ ብለን፣  የኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሚኒኬሽን ጠየቅን ፥ " እኛ አይደለንም የምንሰራው፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነው፤ ከተማ ውስጥ አይደለም የተቋረጠው የከፍተኛ መስመር ላይ ነው " ሲል መለሰልን።

" ከፍተኛ መስመር ላይ ጉዳት ደርሶ ኃይል እየደረሰን አይደለም ለኛም፡፡ ኃይል ከእነርሱ ነው የምንገዛው። ስለዚህ እነርሱ ኃይል እያደረሱን አይደለም፡፡ ችግሩ ምን እንደሆነ እነርሱ ናቸው ባለቤቶቹ የሚያውቁት " ሲል አክለልን።

እሺ የኤሌክትሪክ ኃይልን እንጠይቅ ብለን ደወልን " ከኛ ጋር የሚገናኝ ነገር ስለሌለው ነው " ተባልን።

ቆይ ታዲያ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥን ማንን ነው የሚመለከተው ? የት ብለን እንጠይቅ አልን ፥  " ኃይል በተለያዬ ምክንያት ሊቆራረጥ ይችላል፡፡ መቋረጥ ሁሉ ወደ እኛ አይመጣም ። አጠቃላይ ክልሉ ላይ አይደለም ችግሩ አለ ያላችሁት የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ነው፡፡ የተወሰኑ አካባቢዎች ደግሞ ችግር ካለ ከስርጭት ሊሆን እንደሚችል ነው እኛ የምንገምተው። " ብሎናል።

እስከዛሬ ድረስ ችግሩን አልዳሰሳችሁትም ? ወንበራ ላይ ለምሳሌ አራት ወራት ሊሆነው ነው፤ የመተከል ደግሞ አመታት አስቆጥሯል፤ ብለን ጠየቅን ፥ " መተከል ወደ 2 ዓመት ይስለኛል፡፡ እርሱ ላይ እርግጠኛ አይደለሁም " ብሏል።

አጣርታችሁ ምላሽ እስከምትሰጡን እንጠብቅ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " ይሄ እኛን የሚመለከት ስላልሆነ ምንም የተለዬ የማጣራው ነገር የለም " የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM