TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#1 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ችግር ገጥሞት በነበረበት ወቅት ከባንኩ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ወስደው እስካሁን ድረስ ያለመለሱ የ565 ደንበኞቹን ስም ዝርዝር ከአካውንት ቁጥራቸው ጋር ይፋ አደርጓል። @tikvahethiopia
#2

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ችግር ገጥሞት በነበረበት ወቅት ከባንኩ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ወስደው እስካሁን ድረስ ያለመለሱ የ565 ደንበኞቹን ስም ዝርዝር ከአካውንት ቁጥራቸው ጋር ይፋ አደርጓል።

ባንኩ ፥ ግለሰቦቹ የወሰዱትን ገንዘብ ካልመለሱ በቀጣይ በህግ እንደሚጠይቃቸው በጥብቅ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ቴሌብርን ጨምሮ ከተለያዩ ባንኮች ገንዘብ ወደ አፖሎ ማስተላለፍና ማስቀመጥ ይችላሉ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628

#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#ኢትዮ_ቴሌኮም

የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሀገር አቀፍ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የተከበሩ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ፣ የተገኙ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በተደረገ የመድረክ ላይ ወግ ፣ ዘርፉን ከሚመሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ የፖነል ውይይት ተዳሰዋል።

በውይይቱ ወቅት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ረገድ ሀገራችን መልካም ጅማሮዎች እና ወሳኝ ምዕራፎች ላይ የምትገኝ መሆኗን አንስተው በመሰረተ ልማት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሁም በዲጂታል ፋይናንስ የተሰሩት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም፣ መንግስት ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን በመግለጽ የግሉ ዘርፍ በበኩሉ በዲጂታል ሥነምህዳሩ የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በዘርፉ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና መጫወት እንደሚገባው አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምናደርገውን ጉዞ በይበልጥ ለማፋጠን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ሃገራዊ ካውንስል እንዲቋቋም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #MINT
#PMO #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #ITU #SmartAfrica #HOPR #HOF

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#ኢፍጧር

በኢትዮጵያ የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ለአራተኛ ጊዜ ነገ መጋቢት 18/2016 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የከናወናል።

የነገው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መሪ ቃል " ኢፍጧራችን ለአንድነታችን " የሚል ነው።

ዓላማው በታላቁ የረመዳን ወር ሰዎችን በአንድነት በማሰባሰብ በጋራ ጾማቸውን እንዲያፈጥሩ በማስቻል የአብሮነትና የመተባበር መንፈስ ለማዳበር ነው ተብሏል።

በዚህ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጧር የህዝበ ሙስሊሙ፦
- አንድነት የሚንፀባረቅበት ፣
- ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣
- ወረሐ ረመዷን ከመሆኑ አንፃር የቁርአን ክብር በአደባባይ የሚልቅበት እንደሚሆን ተነግሯል።

ዝግጅቱ ሀላል ፕሮሞሽንና ከነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢፍጧር በኢትዮጵያ የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ለአራተኛ ጊዜ ነገ መጋቢት 18/2016 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የከናወናል። የነገው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መሪ ቃል " ኢፍጧራችን ለአንድነታችን " የሚል ነው። ዓላማው በታላቁ የረመዳን ወር ሰዎችን በአንድነት በማሰባሰብ በጋራ ጾማቸውን እንዲያፈጥሩ በማስቻል የአብሮነትና የመተባበር መንፈስ ለማዳበር ነው ተብሏል። በዚህ ታላቅ…
#ኢፍጧር

የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር  ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን

- ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ   ኦሎምፒያ

- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ  አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች  አጎና ሲኒማ፤ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

- ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች  በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ

- ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ

- ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጧር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ ይደረጋሉ።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል።

ኅብረተሰቡ ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia