TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#DigitalEthiopia

ዛሬ " የዲጂታል ኢትዮጵያ " የግምገማ መድረክ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተካሂዷል።

ጠ/ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌደራል እንዲሁም የክልል ከፍተኛ አመራሮች እና የዘርፉ ተዋናዮች በመድረኩ ተሳታፊ ነበሩ።

የ " ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 " ስትራቴጂ በዋናነት የዲጂታል መሰረተ ልማት በመገንባት እና በማስፋት የአገሪቱን ምጣኔ ኃብታዊ እድገት ማፋጠንን ዓላማ ያደረገ ሲሆን በአምስት ዓመታት ውስጥ ለመተግበር የታቀደ ነው።

ዛሬ ላይ የስትራቴጂውን የ4 አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።

- ዲጂታል ሊትረሲን ለማስፋት፤
- የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቱን የማሳደግ
- የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፤
- የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትና የሳይበር ጥበቃ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጎባቸዋል።

በዚህ መድረክ በቅርቡ በንግድ ባንክ ላይ ያጋጠመው ጉዳይ በስፋት እንደማሳያ ሲቀርብ ነበር።

ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የብሔራዊ ባንክ ገዢው አቶ ማሞ ምህረቱም አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ?

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ " በሳይበር ጥቃት በ2022 በዓለም ላይ 9 ትሪሊዮን ዶላር በጠላፊዎች ተመዝብሯል" ብለዋል።

" ይህ ያጋጠመው ችግር ሰዎች አቅደው አምሯቸውን ተጠቅመው ለማለት ያስቸግራል፤ ከውስጥ ያሉ ሰዎች የፈጠሩት ችግር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይሄ ማለት [የሳይበር ጥቃት] አይከሰትም ግን ማለት አይደለም። በሺዎች የሚቆጠሩ አታኮች በየቀኑ ተቋሞቻችን ላይ ይፈጸማሉ፤ ኢንሳ ብትመጡ ይሄንን ትመለከታላችሁ " ብለዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢው ምን አሉ?

አቶ ማሞ ምህረቱ " የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ችግር በውስጥ ሰዎች የተፈጠረ ነው [ Human Error] ነው " ብለዋል።

" በዚሁ አጋጣሚ የፋይናንስ ሥርዓቱ ግልጽ ነው። ምን አይነት ገንዘብ የት እንደተላከ ከየት እንደወጣ የት እንደገባ ይታወቃል። በእንደዚህ አይነት ስህተቶች የሚጠፋ ገንዘብ አይኖርም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" አሁን ላይ 80 በመቶ የወጣው ገንዘብ ተመላሽ ተደርጋል " ብለዋል።

ብሔራዊ ባንክ የዚህን ክስተት ሙሉ የምርመራ ውጤት በሳምንት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

#AddisAbabaTikvahFamily

@tikvahethiopia
" 2 አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል " - የአካባቢው ምዕመናን

የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገ/ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች #ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው መገደላቸውን የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለጸ።

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ የደብረ  ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 2 አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለጊዜው " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት መገደላቸው ተነግሯል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ፤ ግድያው የተፈፀመው ትናንት መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ገደማ መሆኑን የአካባቢው ምዕመናን እንደነገሩት ገልጿል።

በተፈጸመው በዚህ ግድያ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን  አገልጋይ የሆኑት አንድ መሪጌታና ዲያቆንን ጨምሮ 5 የቤተሰብ አባሎቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገልጿል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ፥ በዶዶላ ከተማ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን አስታውሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምን አለ ? " ... አንድ ሰው ያወጣው ትልቁ ገንዘብ 304 ሺህ ብር ነው ፤ 567 ደንበኞች ጠፍተዋል፤ የጠፉት ደንበኞች 9.8 ሚሊዮን ብር ነው ያወጡት " - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም መግለጫቸው ባንኩ አጋጥሞት ከነበረው ችግር ጋር በተያያዘ እስካሁን ስለደረሰበት ደረጃ አብራርተዋል።…
" ... ብዙዎቹ ወላጆቻቸው እንዲከፍሉ ተደርጓል " - ንግድ ባንክ

ዓርብ መጋቢት 6/2016 ዓ/ም ለሊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የሲስተም ችግር አጋጥሞት በነበረበት ወቅት ገንዘብ ከኤቲኤሞች ሲያወጡ እንዲሁም ሲያዘዋውሩ (ግብይት ሲፈፅሙ) ከነበሩት መካከል 57 በመቶዎቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሆኑ ተነግሯል።

ባንኩ ፥ በ25,761 ደንበኞች ተወስዷል ካለው ከ801 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ 622 ሚሊዮን ያህሉን እስካሁን ተመላሽ መደረጉን ገልጿል።

በቀጣይም የሚመለስም እንዳለ ጠቁሟል።

ብር ከወሰዱት እና ካዘዋወሩ / ግብይት ከፈፀሙ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው።

አሁንም በህገወጥ መንገድ ገንዘብ ከወሰዱት መካከል 567ቱ ብሩን እንዳልመለሱ እነዚህም የወሰዱት የገንዘብ መጠንም 9.8 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተመላክቷል።

በዕለቱ መጀመሪያ ገንዘብ #በኤቲኤም (ATM) አውጥተው የሄዱ ቡድኖች በመጠጥ ቤቶች እና ለሌሎች ጥፋቶች ላይ ማዋላቸው ተመላክቷል።

በእንዲህ ያለ መልኩ የወጣ ገንዘብ ለመመለስ አስቸጋሪ ቢሆንም ብዙዎቹ ግን ወላጆቻቸው እንዲከፍሉ ተደርጓል።

መረጃ ስላለ ለወላጆቻቸው እየተደወለ " ልጃችሁ እንዲህ አድርገዋል " እየተባሉ መክፈላቸው ተመላክቷል።

እስከ ባለፈው ቅዳሜ ድረስ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ገንዘብ ያልመለሱ ደንበኞች የስም ዝርዝራቸው በየዲስትሪክቱ ከትላንት ምሽት ጀምሮ መለጠፍ ተጀምሯል ፣ ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያ ስማቸው ይሰራጫል ተብሏል።

እስካሁን በአንድ ሰው ተወስዶ ያልተመለሰው ከፍተኛ ገንዘብ 304 ሺህ ብር መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#1 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ችግር ገጥሞት በነበረበት ወቅት ከባንኩ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ወስደው እስካሁን ድረስ ያለመለሱ የ565 ደንበኞቹን ስም ዝርዝር ከአካውንት ቁጥራቸው ጋር ይፋ አደርጓል። @tikvahethiopia
#2

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ችግር ገጥሞት በነበረበት ወቅት ከባንኩ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ወስደው እስካሁን ድረስ ያለመለሱ የ565 ደንበኞቹን ስም ዝርዝር ከአካውንት ቁጥራቸው ጋር ይፋ አደርጓል።

ባንኩ ፥ ግለሰቦቹ የወሰዱትን ገንዘብ ካልመለሱ በቀጣይ በህግ እንደሚጠይቃቸው በጥብቅ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia