TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaRegion #Gojjam ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላና ኧሌ ዞኖች ተነስተው ለደን ምንጣሮ ስራ ወደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እያመሩ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ጎዛምን አካባቢ በ " ፋኖ ታጣቂዎች " የተያዙ የቀን ሰራተኞችን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ መሆኑን የምልመላና የቅጥር ሂደቱን የፈፀመው " ኒኮቲካ ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር አሳውቋል። የታገቱት ሰራተኞች ብዛታ 272…
#EHRC

ወደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለሥራ ሲያመሩ በአማራ ክልል ጎጃም ውስጥ ስለታገቱ ዜጎች ሰምቶ እንደሆነና መረጃው ይኖረው እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን ጠይቋል።

የተጀመረ ምርመራ ካለም ማብራሪያ ጠይቀናል።

አንድ የኮሚሽኑ አካል በሰጡት ምላሽ፣ “ መረጃው አለን። በሥራ ላይ ነን። ምናልባት እንግዲህ ፋይንዲንጎች ሲኖሩ እናሳውቃለን ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

እኚሁ የኮሚሽኑ ባልደረባ ፤ “ መረጃው ደርሶናል ” ያሉ ሲሆን፣ ምርመራ ጀምራችኋል ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ አዎ መረጃ የመሰብሰብና የማጣራት እንቅስቃሴ አለ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን የተሰኘው ቀጣሪ ድርጅት ሰራተኞቹን በህጋዊ መንገድ እንደወሰዳቸው የገለጸ ሲሆን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ጋርም የተለዋወጠው ደብዳቤ ስለመኖሩ ተነግሯል።

ታዲያ የነዚህን ሰራተኞች ጉዳይ በተመለከተ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዋኖ ምን አስተያየት እንዳላቸው ለማወቅ ስልክ ደውለን ነበር።

ኃላፊው ፤ ጥያቄውን በጽሞና ከሰሙ በኋላ ማብራሪያ ለመስጠት ቀጠሮ ቢሰጡም ፣ በሰጡት የቀጠሮ ሰዓት በተደጋጋሚ ስልክ ሲደወል ለማንሳትም ሆነ ስለጉዳዩ የፅሑፍ ምላሽ እንዲሰጡ ለተላከላቸው የፅሑፍ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ወደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ እየተጓዙ ነው የተባሉና ጎጃም ውስጥ በፋኖ ታጣቂዎች ታግተዋል የተባሉ ሠራተኞች በቁጥር 272 እንደሆኑ ቀጣሪ ድርጅቱ ገልጿል።

ሠራተኞቹን ለማስለቀቅም ሽምግልናን ጨምሮ ሌሎች ጥረቶችን በስፍራው ተገኝቶ እያደረገ እንደሚገኝ አመላክቷል።

ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የሰጡት ' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ነኝ ' ያሉት ፋኖ ማርሸት ፀሀዩ ፤ " ልጆቹ አውቀውም ይሁን ተጭበርብረው ጎጃም ውስጥ ወደሚገኘው የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲወሰዱ እንዳገኟቸው " ገልጸዋል።

ሲመሯቸው የነበሩትም ወታደሮች እንደነበሩ ከተገኘው መታወቂያቸው ማረጋገጣቸውን ነገር ግን በቀጣይ ከ72 እስከ 100 ሰዓታት ውስጥ ለቀይ መስቀል ለማስረከብ እየተዘጋጁ እንደሆነ አሳውቀዋል።

መረጃው በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ የዲጂታል ባንክ አግልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ገለጸ። ባንኩ ፤ በሲስተም ችግር ምክንያት ፦ - በቅርንጫፎች፥ - በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ - በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር አስውሷል። በቅርንጫፍ እና በኤቲኤም የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ብለው መጀመራቸውን ገልጾ አሁን ደግሞ በዲጂታል የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶች…
#Update #CBE #NBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትላንት ባጋጠመው ችግር የደንበኞች መጉላላትን ጨምሮ የደረሱ #ጉዳቶች ስለመኖራቸው ተነግሯል።

ጉዳቶቹ ምርመራ ተደርጎ ወደፊት ለህብረተሰቡ ይገለጻሉ ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጋቢት 7 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ  ስርዓት ላይ ያጋጠመውን ችግርና የአገልግሎት መቋረጥ በተመለከተ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

" ባንኮች በሥርዓቶቻቸዉ ላይ በየጊዜዉ የደህንነት ፍተሻ እንዲሁም የማሻሻያ ሥራዎችን ያከናዉናሉ " ያለው ብሔራዊ ባንክ ፤ " በሥርዓቶቹ ላይ በሚከናወን ለዉጦችና ፍተሻዎች የባንኮች አገልግሎት አልፎ አልፎ ሊቋረጥ ይችላል " ብሏል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትናንትና ዕለት የተከሰተዉ የአገልግሎት መቋረጥ ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን #አረጋግጫለሁ ሲል ገልጿል።

ችግሩ ከተከሰተበት ሰዓት አንስቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የባንኩን እና የደንበኞቹን ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ክትትል ሲያደርግ እንደቆየና በተደረገው ርብርብ አገልግሎቶች እንዲመለሱ መደረጉን ጠቁሟል።

ብሔራዊ ባንክ በዚሁ መግለጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባጋጠመው ችግር #ጉዳቶች እንደደረሱ ጠቁሟል።

ስለ ጉዳቶቹ በዝርዝር ያለው ነገር ባይኖርም አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ወደፊት ለህዝብ ይገለጻል ብሏል።

በተፈጠረው ችግር የደንበኞች መጉላላትም መከሰቱን አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፋይናንስ ተቋማት ላይ በየጊዜዉ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግ አመልክቶ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ያሉ በሁሉም የፋይናንስ ተቋማት የሚገኙ የፋይናንስ ሥርዓቶች ደህንነቸዉ የተጠበቀ ነው ብሏል።

" ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት የፋይናንስ አገልግሎቶችን መጠቀም መቀጠል ይችላል " ሲል አሳውቋል።

የፋይናንስ ተቋማትም የሥርዓቶቻቸዉን ደህንነትና ቀልጣፋነት ይበልጥ ለማሳደግ የቴክኖሎጂ ተለዋዋጭ ባህርይ በማየት በቀጣይነት መሥራት እንደሚኖርባቸዉ #ጥብቅ_ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሶማሊያ እና ኤርትራ ምን መከሩ ? የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ወደ ኤርትራ አቅንተው የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት አድርገው ወደ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል። ፕሬዜዳንቱ ጉብኝታቸውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በማብራሪያቸውም ፤ " ኤርትራን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። ኤርትራ ለኛ እንደ ቤታችን ናት " ብለዋል። ወደ ኤርትራ የሄዱት ፦ - ኤርትራ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች ባለችበት በሶማሊያ…
#Somalia #Eritrea

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ ማሕሙድ ዳግም ወደ አስመራ ማቅናታቸው ተነግሯል።

ፕሬዝደንቱ ዛሬ አስመራ ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተቀብለዋቸዋል።

ሐሰን ሼይክ ማሕሙድ በፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ #ግብዣ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ወደ አስመራ እንደተጓዙ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ገልጸዋል።

የሶማሊያ ብሔራዊ የዜና ወኪል (SONNA) ሀሰን ሼይክ መሕሙድ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር በሁለቱ ሀገሮች ትብብር ላይ እንደሚወያዩ አስታውቋል።

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ባለፈው ጥር ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ “የአጋርነት እና የትብብር የመግባቢያ ሥምምነት” በተፈራረሙ በቀናት ልዩነት ወደ አስመራ አቅንተው ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተገናኝተው ነበር።

መረጃውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር / SONNAን ዋቢ በማድረግ ያጋራው ዶቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

Photo Credit - Yemane G. Meskel

@tikvahethiopia
#ፑቲን

ቭላድሚር ፑቲን ለቀጣይ 6 ዓመታት ሩስያን መምራት የሚያስችላቸውን የምርጫ ውጤት ማስመዝገባቸው ተነገረ።

ሩስያን በፕሬዜዳንትነት እየመሩ የሚገኙት የቀድሞው የKGB ሰላይ ቭላድሚር ፑቲን በሀገራቸው የተካሄደውን የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ በከፍተኛ ብልጫ ማሸነፋቸውን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ባለፉት 3 ቀናት በመላ ሩስያ ህዝቡ ድምፅ ሲሰጥ ቆይቷል።

የ71 ዓመቱ ፑቲን " ጠንካራ ተቀናቃኝ አልገጠማቸውም " በተባለው በዚህ ምርጫ ከ87% በላይ ድምፅ በማግኘት ሀገሪቱን በፕሬዜዳንትነት መምራት እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸውን ውጤት እንዳገኙ ተገልጿል።

ፑቲን ለቀጣይ 6 ዓመታት ሩስያን ይመራሉ።

በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲሁም በፕሬዜዳንትነት ረጅም ዓመታትን የሀገሪቱን ዋነኛ ስልጣን በመያዝ እየመሩ የሚገኙት ቭላድሚር ፑቲን ይኸኛው የ2024ቱ ምርጫ ለ5ኛ የስልጣን ዘመን ያሸነፉት ምርጫ ነው።

@tikvahethiopia
#ዎላይታ

“ ሆስፒታል ባለመኖሩ ሕዝቡ እስከ ሞት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ነው ” - አንድ የጤና ባለሙያ

“ ዞኑም፣ ከተማ አስተዳደሩም ሆስፒታል ቢኖር የሚል ሀሳብ አለው ” - የወላይታ ሶዶ ዞን ጤና መምሪያ።

በወላይታ ዞን የሚገኙ አንድ የጤና ባለሙያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦ " የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ሕዝብ የመንግሥት ሆስፒታል ባለመኖሩ ሕዝቡ እስከ ሞት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ነው " ብለዋል።

" እንደ አገር የሚተገበረው የሕዝብ ጤና ተቋማ ጥምርታ ሌሎች አካባቢዎች ላይ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ ያለ ቢሆንም ለቦሎሶ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ግን ተግባራዊ አልሆነም " ሲሉ ወቅሰዋል።

" የሕዝብ ብዛት ከ1 ሚሊዮን እስከ 1.5 ሚሊዮን ከሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ተሰርቶ አገልግሎት መሰጠት እንዳለበት ይገለጻል። የቦሎሳ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ሕዝብ ከ1 ሚልዮን እንደሚበልጥ ይገመታል። ህዝቡ ግን ይህንን ሰብአዊ መብት ለማግኘት አልታደለም " ብለዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ አነጋግሯል።

ምን መለሱ ?

አረካ እና ቦሎሶ ሶሬን አማክሎ አገልግሎት የሚሰጥ ዱቦ የመጀመሪያ ደረጃ የግል ሆስፒታል አለ። የሕዝቡ ቅሬታ ‘የመንግሥት ሆስፒታል ለምን አይኖርም’ የሚል ነው ቅሬታው አግባብነት ያለው ነው።

ሌሎችም ምንም አይነት ሆስፒታል የሌለባቸው አካባቢዎች ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶ የመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እየገነባ ነው የቆየው ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ይኼኛውም አካባቢ (ቦሎሳ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ) በመንግሥት ሆስፒታል ተደራሽ ቢሆን ጥሩ ነው የሚለውን እንደ ዞን መግባባት ላይ እየደረስን ነው።

እንደ ዞን፣ የከተማ አስተዳደርም ይሄ ጥያቄ የሕዝብ ጥያቄ እንደሆነ ተቀብሏል። ጥያቄው እንደ ጥያቄ እንዳለ እናውቃለን፤ ለግንባታው የሚያስፈልገው በጀት እንዲታቀድበት፣ በመደበኛ የመንግሥት በጀት እንዴት መስራት እንደሚቻል እየታሰበበት ነው።

በሌላ በኩል ቅሬታ አቅራቢ ጤና ባለሙያው በበኩላቸው፣ “ ለህዝብ ተሰርቶ አገልግሎት እንዲሰጡ የተሠሩ ጤና ጣቢያዎች ቢኖሩም ብዙዎቹ #ዝግ_ናቸው” ብለዋል።

አንድ የግል ሆስፒታል ቢኖርም ለመታከም የዋጋ መናር እንደሚስተዋልበት፣ የብቁ ቀዶ ጥገና ችግር እንዳለ፣ በዚህም አንዲት እናት ችግር እንደደረሰባቸው፣ የጤና ባለሙያዎች ከሰለጠኑበት ሙያ ውጪ ስለሚሰሩ ከዚህ በፊት ሁለት እናቶች እንደሞቱ አስረድተው፣ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

ይህንኑ ቅሬታ በተመለከተ የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ  ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ምን ምላሽ ሰጡ ?

ትክክል ነው። ያለው ሂደት አጠቃላይ ዝርዝሩን እኛም ይዘናል። ሕዝቡም ያነሳል፣ ትክክል ነው። የሕክምና ባለሙያዎች (የዱቦ ሆስፒታል) አሁን በቂ እውቀት ያላቸው ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ነው። አጋጣሚ የተፈጠሩ ክፍተቶች ለምን ተፈጠሩ የሚለውን እናያለን።

በእኛ ደረጃ ዝግ የሆነ ጤና ጣቢያ የለም። ጤና ባለሙያ ተመድቦ ሁሉም ጤና ባለሙያዎች አገልግሎት እየሰጡ ነው በሥራ ሰዓት። ግን አልፎ አልፎ ከትርፍ ሰዓት ክፍያ በጊዜ ባለመከፈሉ ምክንያት ‘አልተከፈለም’ በሚል ሥራ ቦታ ላይ የባለሙያ አለመገኘት ሁኔታዎች አሉ።

የጤና ባለሙያው በበኩላቸው ፦
- የትርፍ አበል አለመከፈል፣
- በደመወዝ መቆራረጥ ምክንያት ቅሬታ ስላለ፣ ሌጋማ፣ ዎይቦ፣ ጋራ ጎዶ፣ ባንጫ እና ሌሎች ጤና ጣቢያዎች በቀን አንድ ባለሙያ ገብቶ የሚመጡ ሕሙማንን ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ መረጃ ከመስጠት ውጭ የሚሰጠዉ አገልግሎት የለም " ብለዋል።

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ🇪🇹

" የትጥቅ ትግል ላይ ያለውም ጫካ የገባውም በሰላም የሚታገለውም ለእኛ ሁሉም እኩል ልጆቻችን ናቸው " - ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ፤ በሀገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች ያሉ ጦርነት / ግጭቶች ሀገራዊው የምክክር ሂደት እንዲጓተት ምክንያት እንደሆነ አሳውቀዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ምን አሉ ?

- በተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎች ያሉት የሰላም እጦቶች የሀገራዊ የምክክሩ ስራ እንዲጓተት ሆኗል።

- በሄድንበት ህዝቡ " ሰላም ናፍቆናል ቶሎ ቶሎ በሉ ይላል " የሰላም እጦት ደግሞ ያንን ለማድረግ አይፈቅድም።

- " ተጓቷል " የሚባለው እውነት ነው። ሁሉም ጋር በየወረዳው ስንሄድ ያለው የሰላም ጥማት ነው።

- ህብረተሰቡ መጓጓዝ ይፈልጋል፣ ሰርቶ ማደር ይፈልጋል፣ ሰላም ይፈልጋል የሰላም እጦት ደግሞ ሁሉንም ህብረተሰቡን ነው የሚጎዳው ሴቶችን ፣ ወጣቶችን ህፃናትን።

- የሚሞቱት የኛው ልጆች ናቸው የሚገድሉትም ልጆቻችን ናቸው የነዚህ ልጆቻችን ጥያቄ በአጀንዳ መልክ ተቀርጾ ወደ ምክክር መመንዘር አለበት። ያ ነው የሚሻለው።

- አንዳንዶች " እናተ ከመጣችሁ ከተቋቋማችሁ (ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን) በኃላ ግጭቱ የበዛው " ይላሉ ከእኛ ጋር እነዚህ ግጭቶች / ጦርነቶች ምንም ግኙነት የላቸውም። እኛ ስርዓት ተከትለን አከታችነትና አሳታፊነትን ስለሚል አዋጁ ያንን ተከትለን ነው እየሰራን ያለነው።

- ሰላም ያልጠማው ወገን የለም። ሁሉም ማለት ይቻላል። በትጥቅ ትግል ላይ ያሉትም ቢሆን ሰላም ይጠላሉ ብዬ በጭራሽ አላስብም።

- እኛ በሶስት ዓመት ውስጥ ስራችንን ሰርተን ጨርሰን መውጣት አለብን ብለን እናስባለን ግን ከአቅማችን ውጭ የሆኑ ጉዳዮች ከተፈጠሩ እኛ ከምንፈታው አይደለም።

- የትጥቅ ትግል ላይ ያለውም ጫካ የገባውም በሰላም የሚታገለውም ለእኛ ሁሉም እኩል ልጆቻችን ናቸው። በችግሮቻቸው ዙሪያ እንድንመክር ጥሪ እያቀረብን ነው።

- ታጣቂዎችን ወደ ምክክር ለማምጣት በተዘዋዋሪ እንሞክራለን ፣ ጥሪ እናደርጋለን፤ ታጣቂዎች እዚህ አዲስ አበባ አካባቢ ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም ግን ጥሪ እናደርጋለን። ልጆቻችን ናቸው።

- ኦሮሚያ ይሁኑ ፣ ቤኒሻንጉል ይሁኑ ፣ አማራ ይሁኑ በየቦታው ያሉት ሁሉም ልጆቻችን ናቸው (ታጥቀውም የሚንቀሳቁትን)። ልጆቻችን ወደ ትምህርት ቤት ፣ ወደ ስራ ፣ ወደ ልማት እንጂ መሳሪያ ታጥቀው አካል ጉዳት፣ ህይወት መጥፋት ውስጥ እንዲገቡብን አንፈልግም።

- ከሁሉ በላይ የጦርነት ክፋቱ አእምሮን #ይሰብራል የተሰበረ አእምሮ ደግሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሸጋገራል፤ ስለዚህ መቆም አለበት። ወደ ትጥቅ ያስገቧችሁን ምክንያቶች ወደፊት አምጧቸውና ተወያዩባቸው። ትጥቁን አስቀምጡትና ወደ ምክክሩ ኑ ! በእርግጠኝነት ወደ ምክክር የመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች መግባባታቸው አይቀርም።

- የአንድ ወገን ወገተኞች በጭራሽ አይደለንም። የምንደክመው ሀገራችን ሰላም እንድትሆን ብቻ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፕሮፌሰር መስፍን አርአያን ቃል ያዳመጠው ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ከሰጡት ቃለምልልስ ነው።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

" ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ናቸው ፤ ሰራተኞቹም በቁጥጥር ስር ውለዋል " - አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰሞነኛና በአየር መንገዱ እንቅስቃሴ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች አየር መንገዱን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ተቀባይነት የለውም " ብለዋል።

በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከአየር መንገዱ በተጨማሪ፦
- ኢሚግሬሽን ፣
- የጉምሩክ ፣
- የብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ የራሳቸው ድርሻ አላቸው ሲሉ ገልጸዋል።

በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስናና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እንጅ የአየር መንገዱ ሰራተኞች አይደሉም ብለዋል።

" ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም " ሲሉ የነበሩት አካላት የጉምሩክ ክፍል ሰራተኞች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

አቶ መስፍን ፤ ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም የተባሉት ደንበኛ ጉዳይ ዋነኛው ቅሬታ እንደነበር አስታውሰው " ድርጊቱን የፈፀሙ የከስተም ወይም የጉምሩክ ክፍል ሰራተኞች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ግለሰቦቹን በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ተናግረዋል።

በቀጣይም አየር መንገዱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን የማይታገስ መሆኑንና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ የደህንነት ካሜራዎች እንዳሉም ተሰምቷል።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም እና WMCC ነው።

@tikvahethiopia
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን " በሲስተም መበላሸት " ምክንያት አጋጥሞት ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ያሉ ጉዳዮች ላይ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በዋና መ/ቤቱ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NationalExam

" የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት እየተገባደደ ነው ፤ ... በቀጣይ የፈተናው ሕትመት ይጀመራል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የፀጥታ ችግር በሌላባቸው አካባቢዎች ብቻ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው ሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተማሪዎች ምዝገባ ተካሂዶ መጠናቀቁን የገለጸው መ/ቤቱ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተናው ምዝገባ ማከናወናቸውን ጠቁሟል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በዚህ ሣምንት ይከናወናል ብሏል።

የፈተና ዝግጅት ሥራው የሀገሪቱን ሥርዓተ ትምህርት የተከተለ እና ተማሪዎቹን በአግባቡ መመዘን በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን አገልግሎቱ ገልጿል።

የፈተናው ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን አመልክቶ በቀጣይ #የፈተናው_ሕትመት እንደሚጀመር አሳውቋል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የመስጫው የጊዜ ሰሌዳ ወደፊት ይፋ እንደሚሆንም የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#CBE የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን " በሲስተም መበላሸት " ምክንያት አጋጥሞት ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ያሉ ጉዳዮች ላይ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በዋና መ/ቤቱ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል። @tikvahethiopia
" ገንዘቡን ተመላሽ ባደረጉ ተማሪዎች ላይ ባንኩ ምንም አይነት ክስ አይመሰርትም " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀናት በፊት ባንኩ ላይ አጋጥሞ ስለነበረው ችግር መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የባንኩ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ናቸው።

ምን አሉ ?

የባንኩ ፕሬዜዳንት አርብ ለሊት ባንኩ አጋጥሞት በነበረው ችግር የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት እንደሌለ ገልጸዋል።

ባንኩ የውስጥ አሰራሩን ለማዘመን (የሲስተም ማሻሻያ) ሲያደርግ በነበረው እንቅስቃሴ ምክንያት በተፈጠረ ስህተት የአርብ መጋቢት 6 ለሊቱ ክስተት መፈጠሩን እና ጉዳዩ ከሳይበር ጥቃት ጋር የሚያያዝ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

" በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ጤናማ ያልሆነ የገንዘብ እንቅስቃሴ ነበር " ብለዋል።

አርብ ለሊት ብቻ ከ490 ሺህ በላይ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር ገልጸዋል። ይህ የገንዘብ ልውውጥ ጤናማ የሆነውንም እንደሚጨምር ጠቁመዋል፡፡

" ገንዘብ በተለያየ መንገድ ጤናማ ባልሆነ መልኩ ከባንኩ በማውጣት ላይ በዋናነት የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው " ሲሉ ገልጸዋል።

የድርጊቱ ተሳታፊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በባንኩ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ እነደሆነና ገንዘቡን ተመላሽ ባደረጉ ተማሪዎች ላይ ባንኩ ምንም አይነት ክስ እንደማይመሰርት አሳውቀዋል።

አሁንም ያልመለሱ ስም ዝርዝራቸው የወጣ ተማሪዎች የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ አሳስበዋል።

ከዚህ ባለፈ ወደ ሌሎች ባንኮች የተደረጉ እና ጤናማ የማይመስሉ የገንዘብ ዝውውሮች ታግደው እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ በባንኩ ላይ ጉዳት መድረሱን ያልደበቁ ሲሆን ባንኩ አጠቃላይ ሀብት አንፃር ሲታይ በጣም አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት ባለመኖሩ የባንኩ ደንበኞች ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባቸው ማለታቸውን የብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia