TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Ethiopia

በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ትላንት በተጠናቀቀው የካቲት ወር በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል። ጉዳትም ደርሷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወሩ ስለነበሩት ሁኔታዎች ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት እጅግ በርካታ ቀናትን የወሰደ ሙከራ ቢያደርግም ምንም ምላሽ የሚሰጠ አካል አላገኘም።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ግን ስለነበሩት ሁኔታዎች እንደማያውቅ እና ክትትል ላይ እንደነበር በመግለፅ ያለውን ትንሽም ቢሆን አስተያየት ሰጥቶናል።

የተዘጋጀውን ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-10

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ፤ " ውሉ የተቋረጠው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው " ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። " የመክፈል አቅም እንዳላቸው በተደጋጋሚ ማስረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቅም ' እንከፍላለን ' ከሚል ደብዳቤ በስተቀር የሚጠበቅባቸውን ብር ለመክፈል አቅም እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም " ሲልም ገልጿል። ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ግብር ለመክፈል ወደኋላ የሚል…
#ቢጂአይ #ፐርፐዝብላክ

" ገንዘቡንም አልመልስም ሲል በደብዳቤ አሳውቋል " ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ

" የመመለስ አለመመለሱ ጉዳይ በቀብድ ውሉ መሰረት የሚታይ ነው " - ቢጂአይ ኢትዮጵያ

ስምንት ወራትን የፈጀውና ያለስኬት የተጠናቀቀው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደት አሁን ላይ ወደ ክስ ሂደት አምርቷል።

ገዢ ሆኖ የቀረበው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ ጊዜያዊ የእግድ ትዕዛዝ እንዲተላለፍለት ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቧል።

የእግድ ጥያቄው ምን ይላል?

- ተጠሪ (ቢጂአይ ኢትዮጵያ) ውሉን እንዳያቋርጥና እንዳይጥስ ታግዶ እንዲቆይ

- በብሔራዊ ባንክ ስር በሚተዳደሩ ማንኛውም ባንክ በተጠርጣሪ ስም ያለ እስከ 1ቢሊዮን 519 ሚሊዮን ብር ሳይንቀሳቀስ ታግዶ እንዲቆይ፤

- ለሽያጭ የቀረበው በአጠቃላይ ስፋቱ 29 ሺህ 896.51 ካ.ሜ የሆነው ይዞታ እንዲታገድ ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

ከዚህ በተጨማሪ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ " በውላችን አንቀጽ 6 መሰረት በሰነዶች ማረጋገጫና  ምዝገባ አገልግሎት ቀርቦ ውሉን መፈረም ሲጠበቅበት ውሉን አቋርጫለው ክፍያውንም አልመልስም ሲል የህዝብና የደሃ ማኅበረሰብን ገንዘብ ከህግና ከሥርዓት ውጪ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ውሉን አቋርጧል፤ ገንዘቡንም አልመልስም ሲል በደብዳቤ አሳውቋል " ሲል ገልጿል

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሐሙስ የካቲት 28 ዕለት በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ የህግ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ነጋ ምህረቴ " ገንዘቡን የመመለስ ያመመለስ ጉዳይ በቀብድ ውሉ መሰረት የሚታይ ነው " ሲሉ ገልጸው ነበር።

ተጨማሪ መረጃ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የቢጂአይ የኮርፓሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በኃይሉ አየለ " ቢጂአይ-ኢትዮጵያ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ አስተያየት አይሰጥም " የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

የፍርድ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ ምን ይላል ?

በብሔራዊ ባንክ ስር በሚተዳደሩ ማንኛውም ባንክ በተጠርጣሪ ስም ያለ እስከ 1ቢሊዮን 519 ሚሊዮን ብር ሳይንቀሳቀስ ታግዶ እንዲቆይ እና የክርክሩ ምክንያት የሆነው ይዞታ እንዲታገድ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ተጠሪ ውሉን እንዳይቋረጥ እና እንዳይጥስ የቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገው ሲሆን ለዚህም "የውሉ ህጋዊነት ክርክር የሚያስነሳ ስለሆነ አመልካች (ፐርፐዝ ብላክ) ተጠሪ ውሉን እንዳይጥስ የጠየቀውን እግድ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም" ሲል በትዕዛዙ ላይ ጠቅሷል።

ይህ የእግድ ውል የሚቆየው ለ20 ቀናት (እስከ መጋቢት 17) ወይም ከግራ ቀኙ አንዱ አቤቱታ ሲያቀርቡ መሆኑን የካቲት 28 ስምት ቀን ባሳለፈው ትዕዛዝ ጠቅሷል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
ረመዷን ነገ ይጀምራል።

በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የታላቁና ቅዱሱ የረመዳን ወር ጾም ነገ ሰኞ ይጀምራል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ረመዷን ነገ ይጀምራል። በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የታላቁና ቅዱሱ የረመዳን ወር ጾም ነገ ሰኞ ይጀምራል። @tikvahethiopia
#ረመዷን

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፦

" ታላቁ የረመዳን ወር የእዝነት፣ የመተሳሰብ፣ የምህረት ወር በመኾኑ ደካሞችን፣ ችግረኞችን፣ ተፈናቃዮችን እንዲሁም ወላጅ አልባ ሕጻናትን በመርዳትና ማዕዳችንን በማካፈል በመተሳሰብና አላህን በመለመን ልናሳልፈው ይገባል።

የረመዳን ወር የእዝነት፣ የምህረትና ከእሳት ነጃ የምንወጣበት፣ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው የዒባዳ ወር ይሁንልን።

መንፈሳዊ ልዕልና የሚኖረው #ሰላም ሲኖር በመኾኑ፣ ለሀገራችን ሰላም እና ለሕዝባችን ደኅንነት ዱዐ ልናደርግ ይገባል።

ለመላው ሙስሊም ማኀበረሰብ እንኳን ለ1445 ዓ.ሂ /2016 የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ረመዷን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፦ " ታላቁ የረመዳን ወር የእዝነት፣ የመተሳሰብ፣ የምህረት ወር በመኾኑ ደካሞችን፣ ችግረኞችን፣ ተፈናቃዮችን እንዲሁም ወላጅ አልባ ሕጻናትን በመርዳትና ማዕዳችንን በማካፈል በመተሳሰብና አላህን በመለመን ልናሳልፈው ይገባል። የረመዳን ወር የእዝነት፣ የምህረትና ከእሳት ነጃ የምንወጣበት፣ አላህ ዘንድ ተቀባይነት…
#ረመዷን

ሙፍቲ ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) ፦

" ረመዷን ምንድን ነው ? ሰዎች እየፆምን ነው ይላሉ ይህ ግን የረመዷን አንዱ ክፍል ብቻ ነው።

ረመዷን ፦
🤲 #የሰላም ወር ነው፤
🤲 #የመረጋጋት ወር ነው፤
🤲 #የመፈወሻ ወር ነው፤
🤲 #የቸርነት ወር ነው፤
🤲 #የምህረት ወር ነው፤
🤲 #የይቅርታ ወር ነው፤
🤲 #ጀነትን የምናገኝበት ወር ነው፤
🤲 ይህ ወር #ሙስሊም መሆናችንን የምናከብረበት ነው ፤ ሙስሊም በመሆናችን #ራስን_መግዛትን የምንለማመድበት የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ የወሰነውን የምናደርግበት ወር ነው ፤  ሱብሃንአላህ ! ስለዚህ ለአላህ ቃል ጥረት ማድረግ ግዴታችን ነው። "

መልካም #የረመዷን_ጾም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይመኛል።

@tikvahethiopia
በነገው ዕለት የዐቢይ ጾም እንዲሁም የረመዷን ወር ጾም ይጀምራል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልካም የዐቢይ ጾም እንዲሁም መልካም የረመዷን ጾም እንዲሆን ከልብ ይመኛል።

በነገው ዕለት የሚጀምሩት አጽዋማት የፈጣሪን በረከት ፣ ዕርቅ ፣ ምህረት ፤ ለመላው ሀገራችን ፍጹም ሰላም እና መረጋጋትን የሚያመጡ እንዲሆኑ እንመኛለን።

#ኢትዮጵያ #Ethiopia #ክርስትና #እስልምና

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Empowering Africa, One Venture at a Time. Jasiri Talent Investor strives to remove barriers that hinder the success of new businesses. The program guides the Fellows from ideation to venture creation, by providing funding, coaching, strategic advisory, and guidance in the complex innovation space.

Application for Cohort 6 is ongoing, submit your application via http://jasiri.org/application

#Jasiri4Africa
#MertEka

እነዚህ የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የሁሉንም ዕቃዎች ዋጋ  ይሄንን👉  t.me/MerttEka 👈 ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
አድራሻችን፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ሱቅ 376
PHOTO ፦ የመጀመሪያው ምሽት ተራዊህ ሶላት በሳዑዲ አረቢያ - #RAMADAN #ረመዷን ☪️

Photo Credit : Haramain

@tikvahethiopia