TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ " ዛሬ ይመረቃል። አጫጭር መረጃዎች ስለ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ " ፦ - በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ከምድር በታች ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ 5 ወለል እና 8 በሮች አሉት። - 8ቱ በሮች ፦ * የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ * የምዕራብ ጀግኖች በር፣ * የሰሜን ጀግኖች በር፣ * የደቡብ ጀግኖች በር፣ * የፈረሰኞች በር፣ * የአርበኞች በር፣ * የፓንአፍሪካኒዝም…
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ተመረቆ ተከፈተ።
ዛሬ በአዲስ አበባ መሀል ፒያሳ ላይ የተሰራው ግዙፉ የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ " በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተመርቆ ተከፍቷል።
በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ፣ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ፣ የጦር መኮንኖች፣ ሚኒስትሮች ፣ የክልል ፕሬዜዳንቶች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች ... ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እግዶችም ተገኝተው ነበር።
በስነስርዓቱ ላይ መልዕክት አስተላልፈው የነበረው ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፤ " የዓድዋ ድል ከሀገርና አኅጉር ተሻግሮ በዓለም የተስተጋባ አኩሪ ድላችን ቢሆንም ይህን በአንድ ቦታ በአግባቡ የሚገልጽ የዓድዋ ድል መታሰቢያ አለመገንባቱ የሚያስቆጭ ነው " ብለዋል።
" ዛሬ ላይ የዓድዋን ድል ታሪክ በሚመጥን አግባብ መታሰቢያ ተገንብቷል " ያሉት ፕሬዜዳንቷ ፤ ለዚህም ሐሳብ ከማመንጨት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደረጉትን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደርን አመስግነዋል፡፡
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በበኩላቸው፤ " የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሌሎች የጥቁር ሕዝቦች ሀገራት ሊሠሩት ቢችሉም፤ የምኒልክ ልጅ፣ የባልቻ ልጅ፣ የገበየሁ ልጅ፣ የአሉላ አባ ነጋ ልጅ መሆን ግን አይችሉም " ብለዋል፡፡
" የድል መታሰቢያውን ሰርተንና ጥረን ያሳካነው ነው " ያሉ ሲሆን " ከ128 ዓመታት በኋላ ተገንብቶ ለትውልድ ማለፍ በሚችልበት መልኩ ኢትዮጵያን መስሎ ተሠርቷል " ሲሉ ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የዓድዋ ድል መታሰቢያን ማርከስ ማለት የአባቶቻችንን አጥንት እና ደም ማርከስ ነው " ሲሉም ተደምጠዋል።
Photot Credit - PMOfficeEthiopia & S.H
@tikvahethiopia

#እቴጌጣይቱ " ብርሃን ዘኢትዮጵያ " እየተባሉ ለሚጠሩት ስመ ጥር የሀገር ባለውለታ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በትውልድ ቦታቸውና ለቁምነገር በበቁበት በደብረታቦር ከተማ የመታሰቢያ ሀውልት ቆመላቸው። ሀውልቱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተገንብቶ በዛሬው እለት መመረቁ ተነግሯል። እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ነሀሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ ነበር የተወለዱት። ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ…
" ብርሃን ዘኢትዮጵያ "
የዓድዋ ድል ሲነሳ ስማቸው በግንባር ቀደምነት ከሚነሳው አንዱ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ናቸው።
" ብርሃን ዘኢትዮጵያ " እየተባሉም ይጠራሉ።
ነሀሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ የተወለዱት እቴጌ ጣይቱ በጊዜያቸው በሀገር አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ፣ ለዓድዋ ጦርነት ድል መሳካት ሚናቸው ከፍተኛ ነበር ፣ የውጫሌ ውል ችግር እንዳለበት በመረዳት እንዲሰረዝ ከፍተኛ ሙግት አድርገዋል፣ የዓድዋ ጦርነት እንደማይቀር ሲያቅዉም የአዲስ አበባ ሴቶችን በማስተባበር ሎጅስቲክስ አዘጋጅተዋል፤ ወደ ጦርነት ስፍራም የተመደበላቸውን ጦር እየመሩ ተመዋል።
ከዚህ ባለፈም ለዛሬዋ የኢትዮጵያ መቀመጫ አዲስ አበባ ከተማ ምስረታ መሰረት የጣሉ ናቸው።
በርካታ ሴቶችም እቴጌ ጣይቱን በነበራቸው ብርታት፣ ብልህነት፣ ጥንካሬ፣ ሀገር ወዳድነት እንደ ዓርአያ ይመለከቷቸዋል።
እቴጌ ጣይቱ ልክ በዛሬው ቀን የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ/ም ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።
ለክብራቸው እና ለሀገር ባለውለታነታቸው በደብረ ታቦር እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ (የዓድዋ ድል መታሰቢያ ማዕከል) ሃውልት ቆሞላቸዋል።

#ETHIOPIA ኢትዮጵያ ላይ የሚመጣ ማንኛውም የውጭ ስጋት ካለ በአግባቡ ለከላከል ዝግጁነት እንዳለ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል። ይህን ጉዳይ ያነሱት ስለ ባህር በር እና ስለ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ባነሱበት አውድ ነው። " ሶማሊያ ውስጥ የምንሞተው የእነሱ ሰላም የእኛ ሰላም ስለሆነ ነው " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ፤ " ለሶማሊያ ሰላም ሶማሊያ ውስጥ እንደ እኛ የሞተ የለም፤ መግለጫ ያወጣ ግን…
" የቀረበው ሪፖርት ከእውነት የራቀ ነው " - የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ
በትግራይ ክልል " ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀምረዋል " በሚል ፓርላማ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ሪፖርት " ከእውነት የራቀ ነው " ሲል የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወቀሰ፡፡
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጥር 28 ቀን 2016 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ተገኝተው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀምረው ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው ብለው ነበር፡፡
ይሁን እንጂ የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ፤ በክልሉ ከጦርነቱ በኋላ ስራ የጀመሩ ኢንዱስትሪዎችን በተመለከተ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበላቸው ሪፖርት በተጨባጭ መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር የተራራቀ ነው ሲል ሪፖርቱን ውድቅ አድርጓል፡፡
የቢሮው ም/ኃላፊ አቶ መሐሪ ገብረሚካኤል፤ " በአሁኑ ወቅት በክልሉ ስራ የጀመሩት ለትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃ የሚያቀርቡ 2 መቶ አነስተኛ ፣ 5 መካከለኛ እንዲሁም 12 ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ናቸው " ብለዋል።
" ነገር ግን ' 2 መቶ 17 ኢንዱስትሪዎች ሁለገብ ድጋፍ ተደርጎላቸው ስራ ጀምረዋል ' ተብሎ የተገለጸው ከእውነታው ጋር የተራራቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ከፍተኛ የብድር እና የወለድ መጠንን ጨምሮ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግር አሁንም ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች ስራ እንዳይጀምሩ ትልቅ እንቅፋት ሆኖ በቀጠለበት አግባብ ሁለገብ ድጋፍ ተደርጓል ለማለት አያስደፍርም ሲሉ ተችተዋል።
በክልሉ በነበረው ግጭት የተነሳ የኢንዱስትሪ ዘርፉ ከነበረበት ከፍተኛ ጉዳት በዘላቂነት እንዲያገግም መሬት የወረዱና ተጨባጭ ድጋፎች እንዲደረጉም ነው የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሐሪ ጥሪ ያቀረቡት፡፡
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሀዱ ነው።

" ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው " - የደቡብ ወሎ ዞን በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ "018 አለኋት" ቀበሌ በተለምዶ ቆቅ ውኃ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጥር 30/2016 ሌሊት የኦፓል ማዕድን በቁፋሮ ለማውጣት ሲሞክሩ የነበሩ ከ20 በላይ ወጣቶች የቆፈሩት አለት በመናዱ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩን የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። " በአለቱ የተዳፈኑትን ወጣቶች…
" ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ውጤት አልተገኘም "
ደቡብ ወሎ ዞን ፣ ደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ ሳሉ ዋሻ የተደረመሰባቸውን በርካታ ሰዎች ለማውጣት የሚደረገው ጥረት 4 ቀኑን እንደያዘ ተነግሯል።
የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የከበረ ማዕድን አውጪዎች ማኅበር በሰጡት ቃል ፤ በቁጥር ከ8 እስከ 30 የሚገመቱትን ሰዎች ለማውጣት የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥረት እያደረገ ቢሆንም እስካሁን ውጤት አልተገኘም።
የወገል ጤና ከተማ አስተዳደር ፍለጋውን በማሽን ለማገዝ የአካባቢው መልከዓ ምድር ምቹ ባለመሆኑ ጥረቱን አዳጋች እንዳደረገው አሳስውቋል።
በሕጋዊ መንገድ ተሰማርተው በማዕድን ቁፋሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ናዳ የተጫናቸው ከ4 ቀናት በፊት ነበር።
ሌሎች የአካባቢው ወጣቶችም አብረው ሳይኖሩ እንዳልቀረ ተነግሯል።
አሁን ወጣቶቹ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አልተቻለም።
የወረዳው አስተዳዳር ባለፉት ቀናት ከ500 በላይ ሰዎች በነፍስ አድን ሥራው ላይ እገዛ ለማድረግ ወደ ሥፍራው ቢያቀኑም፣ ወደ ዋሻው ለማምራት የሚያስችለው መንገድ ጠባብ እና በአንድ ጊዜ ከ10 ሰዎች በላይ ማስገባት ባለመቻሉ ጥሩቱ አዝጋሚ ነው ሲል ገልጿል።
ወርቅ ዋሻ የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ፤ በናዳው ተይዘው ከሚገኙት 8ቱ የማኅበሩ አባላት ናቸው ያለ ሲሆን እስካሁን በተደረገው ጥረት 150 ሜትር ርዝማኔ ወዳለው ዋሻ ዘልቆ ለመግባት መቆፈር የተቻለው 33 ሜትር ገደማ ብቻ ነው።
" የአካባቢው ሕዝብ ሌት ተቀን ርብርብ እያደረገ ነው " ያለው ማህበሩ በመንግሥት በኩል የተቀበሩትን ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅም ሆነ ከዋሻው ለማውጣት የተደረገ ድጋፍ የለም ብሏል።
የወገል ጤና አስተዳደር ግን የከተማ እና የወረዳው አመራሮች በሥፍራው እንደሚገኙ አስታውቆ ፤ " በቂ ድጋፍ ማድረግ ያልተቻለው አማራጭ ስለሌለ ነው " ሲል ገልጿል።
" ጥረቱን በማሽን ለማገዝ አልተቻለም፤ ማዕድን አውጪዎቹም ባህላዊ ማዕድን አምራች ተብለው የተሰማሩት ቦታው ከባህላዊ ቁፋሮ ውጪ የሚቻል ባለመሆኑ ነው። ቦታው ለእግር መንገድ እንኳን ምቹ አይደለም " ብሏል አስተዳደሩ።
መረጃው የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

M-PESAን በማውረድ እና በመገበያየት ፤ አዳዲስ መኪኖች፣ ባጃጆችን፣ እንዲሁም ሌሎችም ብዙ ሽልማቶችን የማሸነፍ ዕድል እናግኝ።
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
🔗 የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ትክክለኛ ቴሌግራም ገፅችንን በዚህ ሊንክ ያገኛሉ: https://yangx.top/Safaricom_Ethiopia_PLC
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether

በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በሞባይል ስልክዎ Wegagen Mobile መተግበሪያ ከፕለይስቶር ወይም ከአፕስቶር በማውረድ ምቾትዎ ተጠብቆ ሂሳብዎን ያንቀሳቅሱ ፡፡
ወጋገን ሞባይል ደህንነቱ የተጠበቀ መተግበሪያ ሲሆን ደንበኞች የሚከተሉትን አገልግሎቶች እንዲያገኙ ያስችላል፡፡
👉 በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሆነው ገንዘብ መላክና መቀበል ፣
👉 የሞባይል ስልክ በመጠቀም የሒሳባቸውን እንቅስቃሴ መከታተል፣
👉 ግብይት መፈፀም እና ገንዘብ ማስተላለፍ ፣
👉 በአምስት የቋንቋ አማራጮች አገልግሎት ማግኘት፣
👉 ለተለያዩ ከባንኩ ጋር ለሚሰሩ የተራድኦ ድርጅቶች የገንዘብ ልገሳ ማድረግ ፣
👉 የበረራ ቲኬት መቁረጥ ፣
👉 የትምህርት ቤት፣ የውኃ እና የተለያዩ አገልግሎቶች ፍጆታ ክፍያ መፈፀም ፣
👉 ገንዘብ ቴሌብርን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ማስተላለፍ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት ያስችላል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በ866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ
#WegagenBank #WegagenMobile #MobileBanking
Follow us and get more information...
https://linktr.ee/WegagenBank

#ETHIOPIA የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል። መግለጫቸው ፤ በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያንና በፓስፊክ ሀገራት መካከል የተፈረመውንና የሳሞአ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት የተመለከተ ነው። ጉባኤው ስምምነቱ ተካተውበታል ያላቸውን ጎጂ ሀሳቦች በዝርዝር አስፍሯል። ከነዚህም መካከል ፦ - በስምምነቱ…
ስለ ግብረሰዶማዊነት እና ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ ?
ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ነው ስላላቸው ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ?
- ግብረ ሰዶማዊነት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተገለጸው ለአንድ ሀገርና ሕዝብ ከነጎረቤቶቹ መጥፋት ምክንያት የሆነ ተግባር ነው። የሰዶምና ገሞራ በመቅሰፍተ እሳት መቃጠል ከእነርሱ መቀጣትም አልፎ ላለውና ለመጪው ትውልድ አስተማሪ የሆነ ምልክት እንዲሆን ነው።
- ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ግብረ ሰዶማዊነትን የምትቃወመው ተፈጥሮዋዊ ስላልሆነ ብቻ ሳይሆን በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ትምህርት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ፣ ተቀባይነት የሌለው፣ ኃጢአት በመሆኑ ነው፡፡
- ቅድስት ቤተክርስቲያን ጾታዊ ግንኙነት ወይም የተቀደሰ ጋብቻ በተቃራኒ ጾታዎች ብቻ የሚፈጾም እንዲሆን ታስተምራለች።
- ግብረ ሰዶማዊነት የሰውን ልጅ ተፈጥሯዊ ማንነት የሚንድ፣ መሠረተ እምነትንና ቀኖናን የሚሽር፣ ማኅበራዊ ዕሴት የሚያጠፋ፣ ከሥነ ምግባር መገለጫዎች በአሉታዊ ገጽ የቆመ፣ ሕሊናን የሚያውክ ለትውልድ ጥፋት፣ ለሀገር መውደም ምክንያት የሆነ አጸያፊ ተግባር ነው፡፡
- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህን ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ወደ ንሥሓና ድኅነት እንዲመጡ፣ ከሥጋና ከመንፈስ ስብራት እንዲፈወሱ ዘወትር ጥሪ ታደርጋለች እንጅ ማንም ሰው የኃጢአቱ ወይም የርኩሰቱ ተባባሪ እንዲሆን አትፈቅድም።
- በሀገራችን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕግ የተከለከለ ነው።
- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ተግባር (የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ) በግልጥ በሕገ መንግሥታቸውና በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ድንጋጌዎቻቸው እንደ ጥሩ ነገር እንደ ፍትሐዊነትና አካታችነት በመቁጠር በይፋ የደነገጉ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት መኖራቸው ግልጽ ነው። እነዚሁ ሀገራት ያላቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም መከታ በማድረግ በእምነታቸው፣ በባሕላቸው በማኀበራዊ መገለጫቸው ይህን አጸያፊ ድርጊት ፈጽመው በማይቀበሉ የአፍሪካና የምሥራቁ ዓለም ሀገራት ላይ ቢቻል በማግባባት፣ ካልሆነም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና በማሳደር እንዲቀበሉ የጥፋት ልማዳቸውን እንዲጋሩ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉትን ድብቅና ግልጽ እንቅስቃሴዎችን እንቃወማለን።
- ይህ ግብረ ርኩሰት በዘመናችን ተቀባይነት እንዲኖረው፣ የሚደረጉ ሁለገብ ማግባባቶች ፣ተጽዕኖዎችና ተያያዥነት ያላቸው ስምምነቶች በሀገራችን መንግሥት ተቀባይነት አግኝተው እንዳይፈጸሙ በጥብቅ እናሳስባለን።
- ከመገናኛ ብዙኃንና ከሌሎችም የመረጃ ምንጮች ለማወቅ እንደተቻለው ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት የንግድ፣ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ፣የፍትሕና የሰብዓዊነት ግንኙነቶች አካል በማድረግ በቃላትና በዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አስርጎ በማስገባት አሣሪ ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ለማድረግ ያለው ሃደት በአፋጣኝ እንዲፈተሽ። የሀገራችን መንግሥት ብሎም የአፍሪካ መንግሥታት የአህጉራችንን ሃይማኖታዊ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴቶች አስጠብቀው እንዲቀጥሉ ጥብቅ ጥሪ እናቀርባለን።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

Photo
#ትግራይ
አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በዛሬው እለት በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ቃለመጠይቅ ለክልሉ ሚድያዎች ሰጥተው ነበር።
በዚህም ወቅት ፤ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ተሳትፎውበት ከፌደራል መንግስት ጋር በአዲስ አበባ ስለተካሄደው ውይይትና ውጤት አስመልክቶ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
አቶ ጌታቸው ፤ " ለፌደራል መንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፓርት አቅርበናል። በአከባቢያችን ያለው ፓለቲካዊ ሁኔታ እጅግ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ እንደ አገር የውስጥ ሰላማችን መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባ ከፌደራል መንግስት ጋር መግባባት ተደርሷል " ብለዋል።
ከፌደራል መንግስት በተካሄደው ውይይት በሃይል ስለተያዙ የትግራይ ግዛቶች መነሳቱ ያብራሩት ፕረዚደንቱ " በተለይ በምዕራባዊ ዞን በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሰፋሪዎች በሰፈሩበት፤ የፌደራል ተቋማት ዴሞግራፊ ለመቀየር በሚንቀሳቀሱበትና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ባልተመለሱበት ፤ መፍረስ የሚገባቸው ሳይፈርሱ ፤ ህዝባችን ነፃ ባልወጣበት ሁኔታ ሪፈረንደም ማድረግ አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል።
በሚቀጥለው ወር መጋቢት የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታትና የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በተገኙት የፕሪቶሪያ ስምምነት አተገባበር ላይ ያተኮረ ውይይት ይካሄዳል ያሉት አቶ ጌታቸው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለውይይቱ ስኬት የበኩሉ አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ ነው ብለዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ህወሓት መልሶ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ የመመዝገብ ጉዳይ የሚመለከት ጥያቄም ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።
በዚህም፤ ከህወሓት የፓለቲካ ፓርቲነት ምዝገባ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ የፌደራል መንግስት እንደማይደግፈው በመግለፅ ያለው የህግ ክፍተት በአስቸኳይ ታርሞ ምዝገባው እንዲፈፀም ጉዳዩ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ተመርቷል ብለዋል።
መረጃውን የትግራይ ሚድያዎችን ዋቢ አድርጎ ያዘጋጀድ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#ሜትርታክሲ #ሀይገርባስ
ገቢዎች ሚኒስቴር ስለ ሀይገር ባስ እና ሜትር ታክሲዎች ምን አለ ?
የገቢዎች ሚኒስቴር ፤ የሀይገር ባስ እና የሜትር ታክሲዎች የታክስ አከፋፈል ስርዓት ውሳኔ ሳያገኝ በእንጥልጥል ቆይቷል ብሏል።
ነገር ግን ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ በንግድና በታክስ ህጉ መሠረት ተፈጻሚ መደረግ እንዳለበት ተገልጾ ከገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ እንደተሰጠበት ገልጿል።
በዚህም ፦
1ኛ. የታክሲ ማህበራት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 17 መሰረት የሂሳብ መዝገብ መያዝ የሚጠበቅባቸው የደረጃ " ሀ " ታክስ ከፋዮች በመሆናቸው የሂሳብ መዝገብ ይዘው የሚጠበቅባቸውን ግብር አስታውቀው እንዲከፍሉ፤
2ኛ. ዓመታዊ ግብራቸውን በሂሳብ መዝገብ ካላቀረቡ በገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 እና በመመሪያ ቁጥር 138/2010 በትራንስፖርት ቁርጥ ግብር ስርአት መሰረት አመታዊ የገቢ መረጃ እየተወሰደ እንደ ድርጅት በተሸከርካሪዎቹ ዓይነትና ምርት ዘመን ግብር በሚከፈልበት ገቢ ላይ 👉 30 በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር በግምት እንዲሰላና መዝገብ ባለመያዝ በህጉ መሰረት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጠየቁ፤
3ኛ. የአክሲዮን ማህበራት በንግድ ህጉ መሠረት ለአባላት የሚከፈለው የትርፍ ድርሻ (Dividend) ግብር የሚከፈልበት ስለሆነ የሂሳብ መዝገብ ካልያዙ አመታዊ የተጣራ ትርፍ ላይ ወይም በቁርጥ ግብር የገቢ መጠን ተመስርቶ የንግድ ትርፍ ግብር ከተከፈለ ግብር ከሚከፈልበት ገቢ ላይ የተከፈለው ግብር ተቀንሶ ቀሪው መጠን ላይ ህጉን ተከትለው ካፒታላቸውን እስካላሳደጉ ድረስ የትርፍ ድርሻ ግብር 👉 10 በመቶ እንዲከፍሉ እንዲደረግ እንደተወሰነ ለግብር ከፋይ የሀይገር ባስና ሜትር ታክሲ ባለንብረቶች አሳውቋል።