TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
" ... ለአንድ ሓጅ አጠቃላይ ብር 329,000 እንዲሆን ተወስኗል " - ከኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት

የዘንድሮው የሐጅ እና ዑምራ ምዝገባ ነገ ቅዳሜ ጥር 25 በይፋ የሚጀመር መሆኑ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አሳውቋል።

የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ በባለፈው ዓመት 2015 ከነበሩት 18 የምዝገባ ጣቢያዎች ላይ 9 አዳዲስ ጣቢያዎችን በመጨመር ወደ 27 ከፍ እንዲሉ መደረጉ ለማወቅ ተችሏል።

የምዝገባ ጣቢያዎች ፦
- ስቴዲያም በሚገኘው የኦሮሚያ መጅሊስ ዋና ቢሮ፣
- ጦር ሃይሎች በሚገኘው የአዲስ አበባ መጅሊስ ዋና ቢሮ፣
- በሻሸመኔ፣ በጂማ፣ በሀረር፣ በጂግጂጋ፣ በድሬዳዋ፣ በባህር ዳር፣ በደሴ፣ በሀረሪ፣ በሐዋሳ፣ በቴፒ፣ በአሶሳ፣ በሰመራ፣ በባሌ በሮቤ፤ በወራቤ፤ በጎዴ፣  በሞያሌ የሚገኙ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

የሐጅ ዋጋ ተመንም ይፋ የተደረገ ሲሆን ወቅታዊ የዓለም ዓቀፍና አገራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለአንድ ሓጅ አጠቃላይ ብር 329,000.00 (ሦሥት መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ብር) እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ይህ የዋጋ ተመን ባለበት መልኩ የሚፀናዉ የዶላር ዋጋ አሁን ባለበት የሚቀጥል አሊያም በመደበኛ የአጨማማር ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ብቻ ነው ተብሏል።

ማንኛዉም የሐጅ ተጓዥ ለምዝገባ በአካል ወደ ምዝገባ ጣቢያዎች ለምዝገባ ሲቀርብ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል ፡-

1.የመኖሪያ አካባቢያቸዉን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ
2. የታደሰ የጉዞ ሰነድ ፖስፖርት (የመጠቀሚያ ጊዜው ለመጠናቀቅ ከ11 ወራት በላይ የቀረው መሆን አለበት)
3. አንድ ጉርድ ፍቶ ግራፍ
4. የኮቪድና የቢጫ ወባ ክትባት ካርድ

በዕድሜ መግፋትና በተለያዩ አካላዊ ጉዳቶች ምክንያት እራሳቸዉን ችለው የሐጅ ስርዓቱን መፈፀም የማይችሉ ሁጃጆች አስፈላጊውን መስፈርት ከማሟላታቸው ባሻገር ሊያግዛቸው የሚችል አብሯቸው የሚጓዝ ደጋፊ ሰው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

ሁጃጆች አስፈላጊ መስፈርቶች ማሟላታቸዉ በምዝገባ ጣቢያ ኃላፊ ሲረጋገጥና የባንክ ክፊያ እንዲከፍሉ ማረጋገጫ ሲሰጣቸው ብቻ የሐጅ መስተንግዶውን ክፍያ ዲፖዚት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ቀለል ያለ ግምት በመስጠት ይሸለሙ!

ግምትዎን የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል https://yangx.top/GlobalBankEth ይስጡ!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank #GBE #ArsLiv #Arsenal #Liverpool #PremierLeague
#እቴጌጣይቱ

" ብርሃን ዘኢትዮጵያ " እየተባሉ ለሚጠሩት ስመ ጥር የሀገር ባለውለታ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በትውልድ ቦታቸውና ለቁምነገር በበቁበት በደብረታቦር ከተማ የመታሰቢያ ሀውልት ቆመላቸው።

ሀውልቱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተገንብቶ በዛሬው እለት መመረቁ ተነግሯል።

እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ነሀሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ ነበር የተወለዱት።

ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ጋር ሚያዝያ 25 ቀን 1875 ዓ.ም በአንኮበር መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ከተጋቡ በኃላ ንጉሱ ዐፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በተቀዳጁ ማግስት ጥቅምት 27/1882 ዓ.ም ወይዘሮ ጣይቱ ብጡል እቴጌ ጣይቱ ተብለው ተሰይመዋል።

እቴጌ ጣይቱ ብጡል ፦

* በሀገር አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

* የጥቁር ህዝቦች ድል ለተሰኘውና ለዓድዋ ጦርነት ድል መሳካት ሚናቸው ከፍተኛ ነበር።

* ለአዲስ አበባ ከተማ መመስረት መሰረት ጥለዋል።

* የውጫሌ ውል ይሰረዝ ዘንድ ሞግተዋል።

* የዓድዋ ጦርነት አይቀሬ መሆኑ ሲታወቅ " ሴት ነኝ ጦርነት አልፈልግም፤ በሀገሬ ክብር ግን አልደራደርም " በማለት የአዲስ አበባን ሴቶች ሰብስበው ሎጀስቲክስ አዘጋጅተዋል። በአንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ማዕረግ (ራስ) ሆነው 5,000 ጦር በመምራት ወደ ማይቀረው ፍልሚያ ተመዋል። ... ሌሎች ብዙ ያልተዘረዘሩ ሀገራዊ ተግባርን ፈፅመዋል።

እቴጌ ጣይቱ የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ/ም ነው  ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

ፎቶ፦ የደብረ ታቦር ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

“ የፍርድ ቤት ማገጃ ጥሰው ዕቃችንን አውጥተው ሜዳ ኮብልስቶን ላይ ጣሉን ” - የቄራ ነዋሪዎች 

“ ከሳሾች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡና ይህን ቤት ለሌላ ሰው እንዳይሰጥ” - የፍርድ ቤት ደብዳቤ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ቄራ ዶሮ ተራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚገኙ “ የድሃ ድሃ ” የተባሉ የቀበሌ ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ሰዎች ፍርድ ቤት እንዳይወጡ የሚያዝ ደብዳቤ ቢጽፍላቸውም የእግዱን ውሳኔ በመጣስ የፓሊስ አባላት ከቤት አስወጥተው ሜዳ ላይ እንደጣሏቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹን ወክለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ከባለጉዳዮቹ መካከል አንዱ ፣ ቄራ ዶሮ ተራ 11 አባውራዎች እያንዳንዳቸው የቀበሌ ቤት ተከራይተው ይኖሩ እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላ ቤቱ 'የቀበሌ ነው' ተብለው ውጡ እንደተባሉ፣ ይህን ተከትሎም፣ ፍርድ ቤት ክስ መስርተው ማገጃ እንዳስመጡ፣ በዚሁ ጉዳይ ፍርድ ቤት ለሁለት ጊዜያት ያህል ቀጠሮ እንደሰጣቸው አስረድተዋል።

አክለውም፣ “ ፍርድ ቤት ሁከት ይወገድልን ብለን ክስ መስርተን ማገጃ አስመጣን። ከዚያ ‘እናንተ በተከራያችሁት ክፈሉ’ ተብለን መክፈል ጀመርን። በዚያ ሁኔታ እያለን ሳንሰማ፣ ምንም ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ መጡና ‘በሦስት ቀናት ውስጥ ውጡ’ አሉን ” ሲሉ ገልጸዋል።

እኛም ፍርድ ቤት ሂደን ማገጃ አመጣን ያሉት ቅሬታ አቅራቢው፣ “ የፍርድ ቤት ማገጃውን ጥሰው ዕቃችንን አውጥተው ሜዳ ኮብልስቶን ላይ ጣሉን። የእገዳ ወረቀት አምጥተን እራሱ ‘ማንም ኣይከለክለንም፣ እንቀበልም’ ብለው ከቤት አስወጥተው ሜዳ ላይ በትነውን፣ አሽገውት ሄዱ። ውጪ ላይ ነን ” ሲሉ አማረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የፍርድ ቤት ደብዳቤ፣ “ ለን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 06 ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በከሳሽ እነ ኤሊያስ ዘርጋና በተከሳሽ የን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 06 ቤቶች አስተዳደር ባለው ክርክር ከሳሾች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡና ይህን ቤት ለሌላ ሰው እንዳይሰጥ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ ቁጥር 154 መሠረት ይህ የእግድ ትዕዛዝ እስከ 27/05/2016 ዓ/ም ድረስ ተሰጠ ” ሲል ያረጋግጣል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቤት ያስለቀቋቸው የአዲስ አበባና የፓሊስ አባላት መሆናቸውን በገለጹት መሠረት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው አንድ የዶሮ ተራ ቀጠና ፓሊስ፣ ሰዎቹ የቀበሌ ቤት ነው ተብለው እንዲወጡ እንደተደረገ ገልጸው ተጨማሪ ማብራሪያ ከወረዳው ጠይቁ ብለዋል።

ይሁን እንጂ ከወረዳው እስከ ፓሊስ ኮሚሽን የተደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ትግራይ

የመኪና አደጋ የአባትና ልጅ ህይወት ቀጠፈ።

ሦስት ተጓዦች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

ዛሬ ጠዋት ጥር  25/2016 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ መቐለ 5 ሰዎች ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ባለቤትነቱ የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ የሆነ ትዮታ ዳብል ጋቢና መኪና ተምቤን ልዩ ቦታ " መነወ " በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ በውስጡ የነበሩ ሁሉም ተጓዦች ላይ የሞትና የጉዳት አደጋ አድርሷል።

በመኪናው የነበሩ የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ማርኬቲንግ መምሪያ ሃላፊ ከነልጃቸው ህይወታቸው ሲያልፍ ፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 3 ተጓዦች ደግም በመቐለ ዓይደር ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

የራስ አሉላ አባነጋ የትውልድ ቦታ የሆነው " መነወ " ጠመዝማዛ ቦታና ተደጋጋሚ የመኪና አደጋ የሚከሰትበት በመሆኑ መንገዱ ትኩረት እንደሚያሻው አደጋው አስመልክተው የሚሰጡ የህዝብ አስተያየቶች ያመለክታሉ። 

የመኪና አደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ፓሊስ ትራፊክ ገልጿል።

መረጃውን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው የላከው።
                                    
@tikvahethiopia            
M-PESA

ሁለተኛና ሦስተኛ ዙር ‘ተረክ በ M-PESA’ መርሀ ግብር አሸናፊዎች መሸለማቸውን ድርጅቱ አስታወቀ።

በሁለተኛውና ሦስተኛው ዙር የ’ተርክ በ M-PESA’ ሽልማት መርሀ ግብር ከመኪናው በተጨማሪ እድለኛ ደንበኞች አራት ባጃጆች፣ 360 ስልኮችና በሺህዎች የሚቆጠሩ የአየር ሰዓት (በእያንዳንዱ ሁለቱም ዙሮች) ተሸልመዋል ተብሏል።

ሦስት መኪናዎች፣ 12 ባጃጆች፣ 1,080 ስልኮች እና በሺህዎች የሚቆጠሩ ሽልማቶች ለእድለኞች  በቀጣይ (እስከ መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም) እንደሚሰጡ ድርጅቱ ተመላክቷል።

ደንበኞች በአንድ ቀን የሚደርሳቸው ከፍተኛ የእጣ ብዛት 10 ሲሆን፣ "ይህም በየእለቱ፣ በሁለት ሳምንት አንዴ እና በወር አንዴ የሚወጡ ሽልማቶችን በሚያስገኘው እጣ አወጣጥ ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያስችላችዋል" ብሏል ድርጅቱ።

ደንበኞች፣ ወኪሎች እና ነጋዴዎች በM-PESA ለሚያደርጉት ለእያንዳንዱ የ20 ብር ግብይት አንድ እጣ በአጭር የስልክ መልእክት እንደሚላክላቸው፣ M-PESAን መጠቀም በመጀመራቸው አምስት እጣ እንደሚያገኙ ተነግራል።

M-PESA ሳፋሪኮም አሸናፊዎችን በ+251-700 700 700 ብቻ በመደወል እንዴት ሽልማታቸውን መውሰድ እንደሚችሉ ድርጅቱ አብስሯል።

እንደ ገለጻው ከሆነ፣ ደንበኞች የአየር ሰዓት ሽልማት ሲደርሳቸው ደግሞ ከተረክ በM-PESA አጭር የጽሁፍ መልእክት ይደርሳቸውና ወዲያው የአየር ሰዓታቸው የሚሞላ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#Amhara #Merawi

በአማራ ክልል ፤ በየጊዜው በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መከላከያ እና በ " ፋኖ " ታጣቂ ኃይሎች መካከል ግጭቶች ይደረጋሉ።

በእነዚህ ግጭቶችም በሁለቱም በኩል ከሚሞተው የግጭቱ ተካፋይ ባለፈ ንፁሃን ሰዎች ሰለባ እየሆኑ እንዳለ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

ምንም እንኳን #መንግሥት ፤ " ከእውነታው ያፈነገጠ እና ሚዛናዊነት የጎደለው " ብሎ ቢያጣጥለውም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮኒሽን  (#ኢሰመኮ) ይፋ አድርጎት በነበረው ሪፖርት በክልሉ ፦

- የአንድ ዓመት ከሰባት ወር #ሕፃንን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች በድሮን መገደላቸው / የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው።

- በከባድ መሣሪያ ድብደባ ምክንያት #ሲቪል_ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱ።

- በመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት #ከሕግ_ውጪ የሆኑ ግድያዎች እንደሚፈፀሙ።

- ከዚህ ቀደም ግጭቶች በተካሄደባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ሲቪል ሰዎች ውስጥ ፦
" ፋኖን ትደግፋላችሁ "
" ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ "
" መሣሪያ አምጡ "

" የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ " በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ በርካታ #ግድያዎች መፈጸማቸውን በይፋ ማሳወቁ አይዘነጋም።

ከሰሞኑን ዳግሞ በሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል፣ ሰኞ ጥር 20/2016 ዓ/ም የነበረውን ውጊያ ተከትሎ በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ገለጻ ፤ በሰሞኑ ተኩስ እሳቸው የሚያውቋቸው ብቻ 15 ወጣቶች መገደላቸውን ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ ግን ፤ " የሟቾቹን ቁጥር በዚህ ወቅት ለመግለጽ መሞከር የጥቃቱን አድማስ ያሳንዋል እንጂ አይገለጸውም" ብለዋል።

እኚሁ ነዋሪ በግፍ የተገደሉ ንጹሐን ሰዎችን ቁጥር በሂደት እንጂ አሁን ሁሉንም ማወቅ እንደማይቻል ገልጸው ፤ " የዚህ ህዝብ ጭፋጨፋ ግን መቼ ነው የሚያበቃው? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች፣ የሆስፒታል ሰዎችና የአይን እማኞች በከተማው ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

አብዛኞቹ ነዋሪዎች ግድያው የተፈጸመው በቤታቸው እና በመንገድ ላይ በተገኙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

አንድ የህክምና ባለሙያ 13ት ሰዎች ከአስፓልት ዳር መገደላቸውን እንደሚያውቁ ተናግረው በአጠቃላይ በከተማዋ በዚያ ዕለት 85 ሰዎች መገደላቸውን አመልክተዋል።

አንድ የአይን እማኝ በርካታ ቀብሮች ላይ መገኘታቸውን ጠቅሰው የሟቾችን ቁጥር " ከ100 በላይ ነው " ብለዋል። ጥቃቱ በተፈጸመ ማግስት ጠዋት ላይ 48 አስከሬን መቆጠራቸውን ተናግረው ፤ " ከማርዘነብ ሆቴል እስከ በረድ ወንዝ ድረስ ግራ እና ቀኝ አስከሬን ብቻ ነበር " ብለዋል።

የሟቾችን ቁጥር 115 ገደማ የሚያደርሱ አንድ የዐይን እማኝ ደግሞ መከላከያ ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ስታዲየም እና ጤና ጣቢያ በተባሉ ሰፈሮች " ከ6 ዓመት ህጻን እስከ 75 ዓመት አዛውንት " ድረስ ግድያ ተፈጽሟል ብለዋል።

የሆስፒታል ሠራተኛ የሆኑት የዐይን እማኝ በከተማዋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ6 ወር ነፍሰ ጡርን ጨምሮ 25 ሰዎች ቆስለው መጥተው " የተረፈ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" 24ቱ ሆስፒታል የመጡት ሞተው ነው። አንዲት የ6 ወር ነፍሰ ጡር ሴት ከነ ነፍሷ መጥታ ሆስፒታል እንደደረሰች አርፋለች። አጠቃላይ 25 ነበር የመጡት " ብለዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፤ #በመርዓዊ_አስተዳደር ህንጻ ውስጥ በነበሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፋኖ ታጣቂዎች ሰኞ ጠዋት ድንገተኛ ጥቃት ፈፀመው እንደነበርና ለዚህ ምላሽ " የበቀል እርምጃ " በመወሰዱ ነው ለበርካታ ሰዎች ግድያ ምክንያት የሆነው ብለዋል።

ስለ ግድያው ምን ምላሽ እንዳለቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ  መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)፣ " ስብሰባ ላይ ነኝ መልሸ ልደውል " ብለዋል።

መንገሻ (ዶ/ር) ይህን ያሉት እንዲያብራሩ የተፈለገውን ጥያቄ በዝርዝር ከሰሙ በኋላ ሲሆን፣ በድጋሚም ስልክ ሲደወል ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

እንዲሁም፣ " እባክዎ ስልክዎን ያንሱና በኮሚዩኒኬሽን በኩል ያለውን የመርዓዊ ጉዳይ ማብራሪያ በመስጠት ኃላፊነትዎን ይወጡ " የሚል የፅሑፍ መልዕክት (SMS) ቢላክላቸውም ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
* የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ምክትል፣
* የክልሉና የሰሜን ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት፣
* የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ስለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳለቸው ለማወቅ እና ሃሳባቸውን ለማካተት ስልክ ቢደውልም ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ፤ " መረጃው ደርሶናል (የመርዓዊ ጉዳይ) ። እያረጋገጥን ነው " ብለዋል።

አክለው ፣ "የጸጥታ ጉዳይ ስለሆነ ትንሽ መንቀሳቀስና መረጃ መሰብሰብ አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ሊዘገይ ይችላል። ግን እያጣራን ነው" ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia