#INDIA #UAE
ህንድ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ዛሬ በህንድ ሰሜን ምዕራብ በምትገኘው ራጃስታን ግዛት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ መጀመራቸው ተሰምቷል።
ወታደራዊ ልምምዱ " Desert Cyclone " በሚል ለቀጣይ ሁለት ሳምንት የሚዘልቅ ሲሆን በሀገራቱ መካከል ያለውን ወታደራዊ ልምድ እንዲለዋወጡ እንደሚያስችል እና ያላቸውን ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ተነግሯል።
የተባባሩት አረብ አሜሬትስ (UAE) ፤ ህንድ ያለችበትን የBRICS አባል ሀገራት በትላንትናው ዕለት ከነ #ኢትዮጵያ ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ እና ኢራን ጋር በይፋ መቀላቀሏ ይታወሳል።
@tikvahethiopia

ℹ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ ምሽት ለግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ስልክ ደውለው ነበር።
ስልክ የደወሉላቸው አል ሲሲ ድጋሚ የግብድ ፕሬዜዳንት ሆነው በመመረጣቸው " እንኳን ደስ አልዎት " ለማለት ነው ተብሏል።
በዚህ የስልክ ውይይታቸው ፤ " በቀጠናው ያሉ የጋራ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ጥረቶችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን " በሶማሊያ መንግሥት ይፋ የተደረገው መረጃ ያሳያል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በዚህ ወቅት ስልክ መደዋወላቸው ምን ያለመልክት ይሆን ሲል አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቀጠናውን ጉዳይ የሚከታተሉ ግለሰብን ጠይቋል።
እኚሁ ግለሰብ ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ ያለ አንዳች ግጭት በሰላም የባህር በር ላግኝ ማለቷ ያናደዳቸው ፦
- ፍፁም እድገቷን ፣
- የህዝቧን ከችግር መውጣት ፣
- በኢኮኖሚና ወታደራዊ አቅም ሃያል እንድትሆን የማይፈልጉ ኃይሎች ብዙ ሊያስቡና ሊያብሩባት ስሚችሉ ቀጠናዊ ሁኔታዎችን በንቃት መከታተል ያስፈልጋል ብለዋል።
የሁለቱ ሀገራት የስልክ ውይይታቸው ምንም ይሁን ምን የኢትዮጵያ ፍትሃዊ የሆነውን የባህር በር ጥያቄ ማንሳትን እንደ ክፉ ነገር ፣ ጎረቤቶችን ለመጉዳት አድርገው የሚያዩ ኃይሎች ስላሉ ሁሉንም ነገር በከፍተኛ ጥንቃቄ መያዝ እና በአይነ ቁራኛ መከታተል ይገባል ሲሉ መክረዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የሶማሊላንድ ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ።
የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ምክትል ፕሬዜዳንት አብዲራህማን ሳይሊች የሶማሊላንድን ካቢኔ ለነገ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል።
ይኸው የተጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ በሶማሊያ መንግሥት ካቢኔ እና የፌዴራል ምክር ቤቶች ለተደረገው አስቸኳይ ስብሰባ #ምላሽ የሚሰጥ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ንግድ እና ቱሪዝም ሚኒስትር አብዲረሺድ ኢብራሂም ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ባለፈ ስብሰባው በሶማሊያ መንግሥት እየተፈፀመ ስለሚገኘው ቅስቀሳ ግልፅ በሆነ መንገድ በጥልቀት ይመከርበታል የሚል መረጃ ማግኘት ተችሏል።
አስቸኳይ ስብሰባው በፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት ነገ ጥዋት ይካሄዳል።
በሌላ በኩል፤ ዛሬ ምሽት በሶማሊላንድ ሃርጌሳ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ ወጥተው ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሲደግፉ ነበር ተብሏል።

#ግሎባልባንክኢትዮጵያ
ባሉበት ሆነው ጥያቄ በመመለስ ይሸለሙ! 2ኛ ዙር
የሽልማቱ ሕግጋትና ደንቦች፤
1. የሚያሸልመውን ትክክለኛ ጥያቄ ምላሽ የምንቀበለው በቴሌግራም ቻናላችን https://bit.ly/3Ti6vAJ ብቻ ነው፡፡
2. የጥያቄውን ትክክለኛ ምላሽ ለሚያገኙ ቀዳሚ 10 ተወዳዳሪዎች ሽልማቱን የምንሰጥ ይሆናል፡፡፡
4. ተወዳዳሪዎች ሽልማቶቹን ለማሸነፍ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን የቴሌግራም ገፅ ተከታይ መሆን አለባቸው፡፡
6. ከአንድ በላይ ግምት መስጠት ለሽልማት ብቁ አያደርግም፡፡
በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD
ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈጻሚ ናቸው፡፡
መልካም ዕድል!
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን
#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank

#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
አውሮፓ ህብረት ምን አለ ?
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ አጭር መግለጫን ትላንት ምሽት አውጥቶ ነበር።
በዚህ መግለጫው፤ እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያ የባህር በር አገልግሎት (በሊዝ) ማግኘት የሚያችላትን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል ብሏል።
ቀጠል አድርጎ ፦ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት ፣ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተሮችን መሰረት በማድረግ የሶማሊያን አንድነትን ፣ ሉዓላዊነትን እና የግዛት አንድነትን ማክበር አስፈላጊ መሆኑን ለማስታወስ እንፈልጋለን ብሏል።
ይህ ለመላው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላምና መረጋጋት ቁልፍ ጉዳይ ነው ሲል ገልጿል።

#Hawassa #ጤና
በሀዋሳ ከተማ በሚገኝ " ፓነሲያ ሆስፒታል " 2,094 የሀሞት ከረጢት ጠጠር በቀዶ ህክምና ከአንዲት 40 ዓመት ሴት በሆስፒታሉ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት በዶ/ር ፀጋዬ ቸቦና በስራ ባልደረቦቻቸው የቀዶ ህክምና ቡድን አማካኝነት ወጥቷል።
ጉዳዩን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት ዶ/ር ፀጋዬ ፤ ይህ በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ አህጉር ደረጃ በቁጥር ብዛት የመጀመሪያ የሆነና እስከዛሬ ያልተመዘገበ ከ2,094 በላይ ቁጥር ያለው የሀሞት ከረጢት ጠጠር (Symptomatic Multiple Cholelithiasis) ነው ብለዋል።
ቀዶ ህክምናው 2 ሰዓታት ከ30 ደቂቃ የፈጀ ሲሆን በተሳካ ሁኔታ ማስወገድ መቻሉን አስረድተዋል።
የሀሞት ከረጢት ጠጠሮቹ በቀዶ ህክምና ቡድን የተቆጠሩ ሲሆን ጠጠሮቹን ለመቁጠር ከ45 ደቂቃ በላይ መፍጀቱን ዶ/ር ፀጋዬ ገልጸዋል።
የ40 ዓመት እድሜ ያላት ታካሚዋ ለ3 ዓመታት የቆየ በአብዘኛው ጊዜ ቅባታማ ምግቦችን ከተመገቡ በሗላ የሚከሰት ለረጅም ሰዓታት የሚቆይ ፦
- የሆድ የላይኛው ቀኝ ክፍል የመውጋትና የማቃጠል ህመም ፣
- ምግብ ያለመፈጨት ችግሮች ፣
- የቀኝ ትከሻ እና የጀርባ ህመም ስለነበራቸው ነው ወደ ሆስፒታሉ ያቀናችው።
አስፈላጊው ምርመራ ከተደረገላት በኃላ ነው የሀሞት ከረጢት ጠጠር (Symptomatic Cholelithiasis) እንዳለባቸው በመታወቁ ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልጋት የተነገራት።
የቀዶ ህክምናው ውስብስብነት ላይ ውይይት ከተደረገና በቂ መረጃ ከተሰጣቸው በኋላ ተጨማሪ ስምምነት ፈርመው ነው ቀዶ ህክምናውን ለማደረግ የወሰኑት።
የታካሚዋ ቀዶ ህክምና ከባድና ውስብስብ ያደረገው ምንድነው ?
* በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ሶስት ጊዜ (3x) የእንቅርት ዕጢ/ካንሰር ቀዶ ህክምና የተደረገላቸው መሆኑ
* ከቀዶ ህክምናው በሗላ በታካሚዋ ላይ የነበረባቸው ተጓዳኝ የጉሮሮ ነርቭ ጉዳት ፤
* የድምፅ ለውጥ/የድምፅ ኃይል መቀነስ እና አልፎ አልፎ የነበረባቸው የአተነፋፈስ ችግሮች የድህረ- ቀዶ ህክምናው ፅኑ እንክብካቤ እና እርዳታ ውስብስብ አድርጎታል።
ምንም እንኳን ቀዶ ህክምናው ታካሚዋ በነበረባቸው ተጓዳኝ ችግሮች ውስብስብ ቢሆንም በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ቡድን ቅንጅት ቀዶ ህክምናው በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።
🔹በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳይንሳዊ መጽሔቶች እና ምርምር ሪፖርቶች ላይ ከፍተኛ ብዛት ያላቸው የሀሞት ከረጢት ጠጠር በህንድ በሪከርድነት ተይዞ ይገኛል።
🔹በአፍሪካ ጆርናሎችና ሳይንሳዊ ወረቀቶች ወስጥ በዚህ ደረጃ ብዛት ያላቸው የሀሞት ከረጢት ጠጠር ተመዝግቦ አልተገኘም። እስካሁን ባሉ መረጃዎች በኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ጆርናሎች ላይ 146 የሃሞት ጠጠር ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቦ ይገኛል።
በፓነሲያ ሆስፒታል-ሀዋሳ በቀዶ ህክምና የወጣዉ ከ2,094 በላይ ብዛት ያለው የሀሞት ከረጢት ጠጠር በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ አህጉር ደረጃ በቁጥር ብዛት በሳይንሳዊ መጽሔቶች እና ምርምር ወረቀት ሪፖርቶች ላይ አዲስ ሪከርድ ሆኖ ሊመዘገብ የሚችል መሆኑን ዶ/ር ፀጋዬ ቸቦ ተናግረዋል።
ለጥንቃቄ . . .
በአብዘኛው ጊዜ ቅባታማ ምግቦችን ከተመገቡ በሗላ የምከሰት ለረጅም ሰዓት የሚቆይ የሆድ ህመም ካላ ፦
☑️ በሆድ የላይኛው ቀኝ ክፍል ድንገተኛ የመውጋትና የማቃጠል ህመም ፣
☑️ በቀኝ ትከሻ ላይና በትከሻ መሳቢያዎች መካከል የጀርባ ህመም፣
☑️ የሆድ መነፋት ስሜት እና ምግብ ያለመፈጨት ችግሮች ካሳየና ካለዎት ፤ ይህ የሀሞት ከረጢት ጠጠር ህመም (Symptomatic Cholelithiasis) ምልክት ሊሆን ስለምችል ባፋጣኝ ወደ ሆስፒታል ማቅናት ያስፈልጋል።

ℹ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ ምሽት ለግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ስልክ ደውለው ነበር። ስልክ የደወሉላቸው አል ሲሲ ድጋሚ የግብድ ፕሬዜዳንት ሆነው በመመረጣቸው " እንኳን ደስ አልዎት " ለማለት ነው ተብሏል። በዚህ የስልክ ውይይታቸው ፤ " በቀጠናው ያሉ የጋራ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ጥረቶችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ…
ℹ️ ግብፅ በፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ቃል አቀባይ በኩል ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት ገልጻለች።
የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሼክ ሀሰን ሞሀሙድ ፤ ትላንት ምሽት ወደ አል ሲሲ ስልክ ደውለው #ከሁለት_ሳምንት በፊት ላሸነፉት ምርጫ " እንኳን ደስ አልዎት " ብለዋል።
የስልክ ውይይቱን ተከትሎ የግብፅ ፕሬዜዳንት ቃል አቀባይ ሁለቱ መሪዎች ፦
- የሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን፤
- ታሪካዊ ግንኙነታቸውን መሰረት በማድረግ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የጋራ ትብብርን ለማጎልበት መወያየታቸውን ገልጸዋል።
አል ሲሲ ፤ ግብፅ ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት መግለፃቸው ተነግሯል።
የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ከአል ሲሲ በተጨማሪ ለኳታር ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ስልክ ደውለው ነበር።
ከኳታሩ ኤሚር ጋር ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችሉ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የጋራ ጥቅሞችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተሰምቷል።
ትላንት ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የቀጠናውን ጉዳይ የሚከታተሉ ምሁር ፤ የግብፅ እና ሶማሊያ የስልክ ውይይት ምንም ይሁን ምን የኢትዮጵያ #ፍትሃዊ የሆነውን የባህር በር ጥያቄ ማንሳትን እንደ ክፉ ነገር ፣ ጎረቤቶችን ለመጉዳት አድርገው የሚያዩ ኃይሎች ስላሉ ሁሉንም ነገር በከፍተኛ ጥንቃቄ መያዝ በአይነ ቁራኛ መከታተል ይገባል ሲሉ አሳስበው ነበር።

#Tigray
በትግራይ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መሰጠት ተጀመረ።
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር በሚያስተዳድራቸው 76 ወረዳዎች በሚገኙ 1114 ትምህርት ቤቶች 60 ሺህ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክላሊው ፈተና ለመውሰድ መቅረባቸው የክልሉ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ አስታውቋል።
ኤጀንሲው ፤ ከጦርነቱ በኋላ በ2012 ዓ.ም መፈተን ሲገባቸው ሰኔ 2015 ዓ.ም ላይ ከተፈተኑ ተማሪዎች 98 በመቶ ማለፋቸው አስታውሷል።
የአሁኑም ፈተና ያለውን ችግር በመቋቋም በተደረገው ጥረትና ዝግጅት የተሻለ ውጤት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል።
የዚህ ዓመት የ8ኛ ክፍል ፈተና በቴክኖሎጂ ተደግፎና ታግዞ በቶሎ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
ፎቶ፦ TG TV

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።
በመግለጫው ምን አለ ?
አገልግሎቱ ለተገልጋዮች አዲስ አሰራርን ወደ ስራ ማስገባቱን አሳውቋል።
በበይነ መረብ አማካኝነት ፦
- የትምህርት መረጃ ማጣራት፣
- የትምህርት ማስረጃ ለሌላ ተቋማት መላክ ፣
- ድጋሚ የትምህርት ማስረጃ መውሰድ፣
- የትምህርት ማስረጃን ማረጋገጥ
- በምዝገባ ወቅት የሚያጋጥምን የስም ፊደላትን ጉድለት ማስተካከል ይቻላል ብሏል።
አገልግሎቱን ለማግኘት ተገልጋዮች በቴሌ ብር እና ንግድ ባንክ በኩል ክፍያ መፈፀም እንደሚኖርባቸው አመልክቷል።
ከዚህ በኋላ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ቅርንጫፎች እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ180 ሀገራት፣ በአካል እንዲሁም በውክልና ማግኘት እንደሚቻልም ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ #ከቀጣይ_ወር ጀምሮ ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ምዝገባ እንደሚጀመርም ይፋ ተደርጓል።
#ኤፍቢሲ

#ጅግጅጋ
የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።
ፕሬዜዳንቱና ልኡካቸው ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት ሲደርሱ የሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሁለቱም በኩል ያሉ ባለስልጣናት የንግድ ትብብርን በተመለከተና በድንበር #የፀጥታ እና #ደህንነት ጉዳዮች (በሶማሌ ክልል እና በሶማሌላንድ) ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።
የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ከተማ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን እውን ያደርጋል የተባለለንትን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው አይዘነጋም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤስአርቲቪ ሶማሊኛ ክፍል ነው ያገኘው።