TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#መቐለ

ዛሬ ህደር 3 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ የታክሲ አገልግሎት ተቋርጦ ውሏል።

የመቋረጡ ምክንያት የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች በአጠቃላይ አድማ ላይ በመሆናቸው ነው።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የመቐለ ታክሲ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች አጠቃላይ አድማን ተከትሎ የተፈጠረውን መስተጓጎል በአካል ተገኝቶ ቃኝቷል።

ከለሊቱ 11:30 የታክሲ ረዳቶች ጩኸት የማይለይባት የመቐለ ከተማ ያለወትሮዋ የህዝብ ታክሲ የጠፉባት ሆና ውላለች።

ከከተማዋ የተለያዩ ጫፎች ወደ መሃል ከተማ ከ20 እስከ 10 ብር በመክፈል ሰው በሰው ላይ ተደራርበው ተጨናንቀው የሚጓጓዙት ተሳፋሪዎች በመንገድ ዳር ቆመው በብዛት ታክሲ ሲጠብቁ ነበር።

ተገልጋዮች ዝር የሚል ታክሲ ሲያጡ የመክፈል አቅም ያላቸው በባጃጅ ኮንትራት ከፍለው ሲጓዙ አቅሙ የሚያጥራቸው ደግሞ በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ሪፓርተር ረፋድ አከባቢ ታክሲዎች አድማ መምታቸውን ለመገንዘብ ችሏል። 

የታክሲ አገልግሎቱ መቋረጥ አስመልክቶ ተገልጋዮች አነጋግሯል።

ወዲ ቐሺ ፣ ዘርኣያዕቆብና ሰናይት የተባሉት ተጠቃሚዎች እንደሚሉት ፤ " የታክሲዎች አድማ በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚታየው በሃይል በመጫን ፍላጎት ለማሳካት የመሻት ዝንባሌ ነው " ብለዋል።

የታክሲ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ግን የተገልጋዮቹን አስተያየት ፍፁም በመቃረን ፤ ህዝብ የመበዝበዝና የማጉላላት ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸዋል።

ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ በመሄድ ላይ የሚገኘው የኑሮ ሁኔታ ፣ የመኪና እቃ መለዋወጫ መወደድ (የመኪና 5 ሊትር ዘይት ከብር 500 በአምስት እጥፍ ጨምሮ ወደ ብር 2500 ከፍ ማለቱ እንደ ማሳያ ይጠቅሳሉ)  ፤ የሹፌርና የረዳት ክፍያን ገበያ ላይ ባለው ታሪፍ መሸፈን እጅግ እንደከበዳቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ገልፀዋል።

የታክሲ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች በማከልም አሁን ባለው 10 ብር ለአንድ ተሳፋሪ ታሪፍ ኑሮአቸውን አሸንፈው የመኪኖቻቸው ድህንነት ለመጠበቅ እንደሚቸገሩ ፤ ስለሆነም መንግስት ታሪፉ እንዲያስተካክል ከአንድ ወር በፊት በማህበራቸው በኩል ጥያቄ እንዳቀረቡ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ መንግስት ጥያቄያቸው መመለስ ትቶ አንድ ሰው ተርፍ ጭነው ከተገኙ ብር 500 መቅጣቱ አጠቃላይ የስራ የማቆም አድማ እንዲያደርጉ ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ስለ ጉዳዩ የመንግስት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም ፤ ከመንግስት የሚሰጠው ምላሽና የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች ቀጣይ እርምጃ ተከታትሎ ያቀርባል።
                                
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሶማሊያ ሶማሊያ ቲክቶክ እና ቴሌግራም እንዲሁም 1ኤክስቤት (1XBet) የተባለውን የስፖርት ውርርድ ገጽን እንዲዘጉ አዘዘች። " ቲክቶክ " እና " ቴሌግራም " የአሸባሪዎች መረጃ ማስተላለፊያ ሆነዋል ብሏል የሶማሊያ መንግሥት። መተግበሪያዎቹ " አሸባሪ ድርጅቶች እና ቡድኖች አሰቃቂ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲሁም ፎቶግራፎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ጥቅም ላይ ውለዋል " ሲል ገልጿል።…
ኔፓል ሀገሪቱ ላይ " ቲክቶክ " እንዲታገድ ወሰነች።

ኔፓል ፤ ማህበራዊ መስተጋብርን የሚረብሹና የቤተሰብን መዋቅር እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያውኩ ይዘቶችን ለማጋራት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ያለችውን የቻይናውን " #ቲክቶክ " መተግበሪያ እንዲታገድ ውሳኔ አሳለፈች።

ሀገሪቱ ፤ " ቲክቶክ " በማህበራዊ መስተጋብር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ያለች ሲሆን በመተግበሪያው ላይ የሚለቀቁት ተንቀሳቃሽ ምስሎችና የሚተላለፉት መልዕክቶች ለሀገሪቱ ህዝብ ባሕል እንግዳ የሆኑና ቀድሞ በማህበረሰቡ ዘንድ የነበረውን ማህበራዊ መስተጋብር የሚሸረሸሩ ናቸው ስትል አሳውቃለች።

የመገናኛ ና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሬካ ሻርማ ፤ የቲክቶክ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ የሀገሪቱ ካቢኔ ተሰብስቦ መመክሩንና #ለማገድ ውሳኔ እንዳሳለፈ ይፋ አድርገል።

የቴሌኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ኃላፊ የሆኑት ፑሩሾታም ካናል በሰጡት ቃል ፤ በኔፓል የሚገኙ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች " ቲክቶክ " ን እንዲዘጉ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

አንዳንዶች መዝጋታቸውን ሌሎችም በቀጣይ እንደሚያደርጉት ጠቁመዋል።

" ቲክቶክ " የማህበራዊ ህይወት ላይ እያሳደረ ነው ከተባለው አሉታዊ ተፅእኖ በተጨማሪ በርካታ ከመተግበሪያው ጋር የተያያዙ የሳይበር ደኅንነት ወንጀሎች መመዝገባቸው ተመላክቷል።

የኔፓል መንግስት ተቃዋሚዎች ውሳኔው " ውጤታማነት ፣ ብስለት እና ኃላፊነት " የጎደለው ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

አንድ የእገዳው ተቃዋሚ ፤ በሌሎችም ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ብዙ የማያስፈልጉ ነገሮች እንዳሉ አንስተው መደረግ ያለበት እነሱን መቆጣጠር ነው እንጂ መገደብ አይደለም ብለዋል።

ወደ አንድ ቢሊዮን የሚጠጉ ወርሃዊ ተጠቃሚዎች አሉት የሚባለው ታዋቂው የቪዲዮ ማጋሪያ መድረክ " ቲክቶክ " መረጃን በመበርበር እና በወጣቶች ላይ ጎጂ ተፅእኖ እያመጣነው በሚል ከዚህ ቀደም በአንዳንድ ሀገራት እገዳ ገጥሞታል።

አንዳንድ ሀገራት መተግበሪያው የቻይና መንግሥት መረጃ ለመበርበር ይጠቀምበታል በሚል ይተቹታል።

የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ ንብረት የሆነው " ቲክቶክ " በቤጂንግ ቀጥተኛ ቁጥጥር ስር ነው እየተባለ የሚቀርቡበትን ክስና ትችቶችን በተደጋጋሚ #እንደማይቀበል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ ዛሬ ህዳር 3/2016 ዓ.ም በመቐለ የተካሄደው የታክሲ አገልግሎት የማቆም አድማ ከማህበራቱ እውቅና ውጪ የተፈፀመና ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ሶስት የታክሲ ማህበራት ባወጡት መግለጫ አሳወቁ።

ማህበራቱ ከሰዓት በኃላ ባሰራጩት ይፋዊ መግለጫ ፤ " ለመንግስት ያቀረብነው ጥያቄ በህጋዊ መንገድ እንዲመለስ ጥረት እያካሄድን ባለንበት ጊዜ አገልግሎት ማቋረጥ አግባብ አይደለም " ብለዋል።

አድማ የመቱ ሁሉ ችግሩ ከመባባሱ በፊት ወደ ስራ መመለስ አለባቸው ብለዋል።

ዛሬ በመቐለ የታክሲ አድማ በመመታቱ በርካቶች መጉላላት ደርሶባቸዋል ፤ ያላቸው በባጃጅ ኮንትራት እየያዙ ሲሄዱ አቅም የሚያንሳቸው ደግሞ በእግራቸው ለመጓዝ ተገደው ውለዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል በዚሁ ርእሰ ጉዳይ ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን እየተከታተለ እንደሚያቀርብ ያሳውቃል።
                          
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። መግለጫውን የሰጡት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ኃይሉ አዱኛ ሲሆኑ ታንዛኒያ ውስጥ እየተካሄደ ነው ስለተባለው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ተጠይቀው ቀጥተኛ ምላሽ ሳይሰጡ አልፈዋል። አቶ ኃይሉ ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም በክልሉ ዘላቂ ለሰላም እና ደህንነት እንዲሰፍን ፅኑ…
#Update

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል) በታንዛኒያ የሰላም ድርድር እየተደረገ ነው ሲል መግለጫ አወጣ።

ምንም እንኳን ከቀናት በፊት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በወታደራዊ አዛዦች አማካኝነት ለሰላም ድርድር መቀመጣቸውን ቢያሳውቁም እስከዛሬ ደረስ ከሁለቱም በኩል ምንም ነገር ሳይባል ቆይቷል።

በዛሬው ዕለት ግን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ድርድሩን በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ አጭር መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም መግለጫው ፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር-የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የልዑካን ቡድን በዋና አዛዥ ጃል መሮ ድሪባ እና ምክትላቸው ጃል ገመቹ አቦዬ እየተመራ ለከፍተኛ የሰላም ድርድር ታንዛኒያ መግባቱን አሳውቋል።

አመራሮቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ ከነበሩበት ኦሮሚያ ወደ ድርድሩ ቦታ ታንዛኒያ እንዲገቡ ለማድረግ ሲባል በሰዓቱ ይፋዊ መግለጫ / መረጃ እንዳልተሰጠ ጠቁሟል።

" የህዝባችንን ምኞት እውን የሚያደርግ እና የሰማዕቶቻችንን መስዋዕትነት የሚያከብር ሰላማዊ የፖለቲካ እልባት ለማግኘት በቁርጠኝነት እንቀጥላለን " ያለው ይኸው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መግለጫ የሰላም ድርድሩ ሲጠናቀቅ ተጨማሪ መረጃዎችን እንሰጣለን ብሏል።

እስካሁን በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የሰላም ድርድሩን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም። ነገር ግን ኦሮሚያ ላይ ዘላቂ ሰላምን  ለማምጣት የፌዴራሉ መንግስት የወታደራዊ እንዲሁም የፖለቲካ ሰዎች ታንዛኒያ እንደሚገኙ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ዲፕሎማቶች  ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#HoP

ነገ ማክሰኞ ጥዋት ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ ስብሰባውን የሚያካሂደው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
#እገታ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በተለይም አሰላ ከተማ ዙሪያ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እየተባባሰ የመጣዉ የእገታ ወንጀል እንዳማረራቸው ተናግረዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

-  ሰዎችን አግቶ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብን የመጠየቅ ተግባር ህብረተሰቡን አማሯል።

- ከአሰላ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ ገጠራማ ቀበሌያት፤ በተለይም ሄጦሳ ወረዳ፤ #ቂሊሳ በሚባል አከባቢ በሌሊት ሰዎችን በማገት ገንዘብ መጠየቅ እየተለመደ የመጣ ተግባር ሆኗል። ይህ ቦታ ቁሉምሳ ከሚባለው የአሰላ ከተማ መግቢያ አከባቢ እጅግ ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።

- በዶዶታም ተመሳሳይ የእገታ ተግባር በሌሊት ይፈፅማል።

- ከከተማ ውጪ ያለው የትኛውም አከባቢ መሰል ስጋት አለ፡፡

-  ሰዎች ሲታገቱ ባላቸው የኢኮኖሚ አቅም የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲከፍሉ በአጋቾቻው ይወሰንባቸዋል።

- የታገቱት ሰዎች የተጠየቁትን ተደራድረው ከፍለው ከመውጣት ውጪ ህይወታቸውን የማቆያ ሌላ ስልት የለም።

- አጋቾቹ እነማን እንደሆኑ አይታወቅም እሱ ነው ትልቁ ችግር።

- ከፍተኛ የአርሶ አደር የኢኮኖሚ አቅም የሚስተዋልበት አከባቢ ነው በቀጣይም ለመሰል ዘረፋ ተጋላጭ እንዳኆን ስጋት አለን።

- ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው አርሶ አደሮች አከባቢውን ለቀው ወደ ከተማ በመሸሽ ላይ ሲሆኑ አቅም የሌለው ግን አከባቢው ላይ ተቀምጦ የሰቀቀን ህይወት ይመራል።

ፖሊስ ምን ይላል ?

የአርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ ከድር ፦

▸ ችግሩ ጎልቶ የሚስተዋለው ከከተማ ራቅ ባሉ ደናማ አከባቢዎች ነው፡፡ እንደሚባለው ሳይሆንም አልፎ አልፎ በአንዳንድ አከባቢዎች በደን በተሸፈኑ ገጠራማ አከባቢዎች በተለይ ወደ አኖሌ ባሉ ደናማ የዝዋይ ዱግዳ ወረዳ አዋሳኝ ነው።

▸ በተለያዩ ጊዜያት ተግባሩን ለማስቆም የሚወሰዱ ኦፕሬሽኖች በመኖራቸው እንዲህ ጎልቶ በከተማ ዙሪያ የሚፈጸም ነገር የለም፡፡

▸ በተለይ በአሰላ ከተማ ዙሪያም ሆነ በአስፓልት መንገዶች ላይ እንዲህ ያለ ነገር የለም፡፡ ወንጀሉ አልፎ አልፎ የሚስተዋለው በዶዶታ እና ሁሩታ ወረዳዎች ዳገታማ አከባቢዎች እና ከምስራቅ ሸዋ ዝዋይ ዱግዳ ጋር ከሚያዋስኑን አከባቢ ነው፡፡

▸ መሰል ተግባርን የሚፈጽሙ በውንብድና ስራ የተሰማሩ አሉ፡፡ አንዳዴ ኦነግ ሸኔ በሚል ትጥቅ አንግቦ በጫካ የሚንቀሳቀሰውን ሃይል እንደ ሽፋን በመጠቀም በዝርፊያው የተሰማሩ መኖራቸውን አረጋግጠናል፤ በዝርፊያ ላይ እያሉም ጭምር ተቆጣጥረን ለህግ ያቀረብናቸው አሉ።

• ምን ያህል ሰዎች ተያዙ ? የሚለውም ጥያቄ ላይ ዝርዝር ምላሽ ሳይሰጡ አልፈዋል።

▸ በተለያየ ጊዜ ኦፕሬሽኖችን እያካሄድን ነው ፤ ከታጣቂዎች በተጨማሪ በታጣቂዎች ስም የተደራጁ መኖራቸውን ህዝቡን እናስገነዝባለን፡፡ እነዚህ ማህበረሰቡን በስልክ ጭምር እየደወሉ የሚያስፈራሩትን ተከታትለን እየያዝን ነው፡፡

(ከዶቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃለምልልስ የተወሰደ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ዛሬ ህዳር 3/2016 ዓ.ም በመቐለ የተካሄደው የታክሲ አገልግሎት የማቆም አድማ ከማህበራቱ እውቅና ውጪ የተፈፀመና ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ሶስት የታክሲ ማህበራት ባወጡት መግለጫ አሳወቁ። ማህበራቱ ከሰዓት በኃላ ባሰራጩት ይፋዊ መግለጫ ፤ " ለመንግስት ያቀረብነው ጥያቄ በህጋዊ መንገድ እንዲመለስ ጥረት እያካሄድን ባለንበት ጊዜ አገልግሎት ማቋረጥ አግባብ አይደለም " ብለዋል። አድማ…
#Update

" የምንሰጠውን ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማው የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ላይ #ጥብቅ_እርምጃ ይወሰዳል " - ወ/ሪት ራሄል ሃይለ

የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ በመቐለ የተደረገው የታክሲ አገልግሎት ማቋረጥና አድማ " ህጋዊ አይደለም " ብሏል።

ቢሮው ከመቐለ የትራንስፓርት ፅህፈት ቤትና ፓሊስ በጋራ ' አካሄድኩት ' ባለው ግምገማ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች ቀድም ሲል አገልግሎት ለማቋረጥና አድማ ለመምታት የሚያበቃ ቅሬታና ጥያቄ አላቀረቡም ሲል ገልጿል።

የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሪት ራሄል ሃይለ ህዳር 3/2016 ዓ.ም አመሻሽ ለሚድያ በሰጡት መግለጫ ፤ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች አገልግሎት የማቋረጥና አድማ የመምታት ደርጊቱ ችላ ተብሎ የማይታለፍ ህጋዊ እርምጃና ተጠያቂነት የሚያስከትል በመሆኑ በመገንዘብ ስራቸው ይቀጥሉ ዘንድ መክረዋል።

የመንግስት ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማ የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ግን ጥብቅ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ለምለም ኪሓ ፣ ህዳሴና ሓወልቲ የተባሉ የመቐለ የታክሲ ማህበራት አመራሮች በማህተም አስደግፈው ህዳር 3/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ለሚድያዎች በላኩት መግለጫ ፤ አግልግሎት ማቋረጡና አድማው ከእውቅናቸው ወጪ የተደረገ ኢ-ህጋዊ ነው ማለታቸው መዘገባችን ይታወሳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

በመቐለ ከተማ የታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች ባደረጉት አድማ ነዋሪዎች ለእንግልት እና አላግባብ ለሆነ ወጭ ተዳርገዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ ያነጋገራቸው የታክሲ ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ በመሄድ ላይ የሚገኘው የኑሮ ሁኔታ ፣ የመኪና እቃ መለዋወጫ መወደድ የሹፌርና የረዳት ክፍያ ገበያ ላይ ባለው ታሪፍ መሸፈን እጅግ እንደከበዳቸው ፤ ያለው ታሪፍ እንዲስተካከል ከአንድ ወር በፊት መንግሥትን በማህበራቸው በኩል ቢጠይቁም ምላሽ ስላላገኙ ወደ አድማ እንደገቡ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
" . . . ፌክ ዶክሜንት አሰርተው እነርሱ አይደለም ለማስተማር ለመማር ያልቻሉ ሰዎች ገብተው ትውልዱን ሲያበላሹ እያየን ነው " - አንጋፍ እሸቱ

የአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2015 ዓ.ም ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ለተመረቁ ፣ 12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሴቶች ተማሪዎች ሽልማትና የምስክር ወረቀት፣ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ውጤታማ የሆኑ ሴቶች ተሞክሯቸውን ለሌሎች የሚያካፍሉበት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር።

በዚህም መድረክ ላይ ፤ በ2015 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል አገራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሴት ተማሪዎች የ10 ሺሕ ብር ሽልማትና የምስክር ወረቀት ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ ከኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲ ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ለተመረቁ ሴት ተመራቂዎች የ15 ሺሕ ብር ሽልማትና የምስክር ወረቀትና አበርክቷል።

ከተሸላሚዎች መካከል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አካውንቲንግ ዲፓርትመንት ከፍተኛ ውጤት (3.92) ያመጣችው ተማሪ አንጋፍ እሸቱ አንዷ ናት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪ አንጋፍ እሸቱን አነጋግሯል።

አንጋፍ እሸቱ ምን አለች ?

(ስለ ትምህርት ፖሊሲው)

" አሁን ላይ የትምህርት ፖሊሲው መቀየር አለበት ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም አሁን ባለው የትምህርት ፓሊሲ ላይ ያለውን ተማሪ እያየነው ነው።

ይሄ ሁሉ ተማሪ የወደቀው አሁን ባለው አሰራር ነው። ችግሩ ሁሉም ላይ ነው ተማሪ ላይ ብቻ አይደለም። ከመምህራኑም፣ ከአመራሩም፣ ከፓሊሲውም ነው ብዬ አምናለሁ።

ስለዚህ በመጀመሪያ ከሥር መሠረቱ ፖሊሲውን ማስተካከል፣ ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት ማስተካከል ያስፈልጋል።

መምህራን እውነት ብቁ ናቸው ወይ ለሚያስተምሩት ትምህርት የሚለውን ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል። ምክንያቱም በጣም ብዙ ነገሮችን እንሰማለን ፌክ ዶክሜንት አሰርተው እነርሱ አይደለም ለማስተማር ለመማር ያልቻሉ ሰዎች ገብተው ትውልዱን ሲያበላሹ እያየን ነው። 

ስለዚህ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች የሚያገኙት ትምህርት የተሻለ ነው? ወይ ብሎ ትኩረት ማድረግ አለበት። ' ጋርቤጅ ኢን ጋርቤጅ አውት ' የሚባል ኮንሰፕት አለ። ተማሪዎች ከጥናት በተጨማሪ ተምረው ባስገቡት ልክ ነው ፈተናቸውን የሚሰሩት።

ስለዚህ መጨረሻ ላይ ተማሪዎች ፈተና ስላላለፉ ብቻ ችግሩ ተማሪዎቹ ላይ ብቻ ነው ብዬ አላስብም። "

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-14
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoP ነገ ማክሰኞ ጥዋት ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል። ምክር ቤቱ ስብሰባውን የሚያካሂደው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሏል። @tikvahethiopia
#Update #አሁን

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትም ጥያቄዎችና አስተያየቶችን እያቀረቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ባለው ከተወካዮች ም/ ቤት አባላት ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ ?

- የኦሮሚያ እና አማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ ፣

- የሀገራዊ ትርክት ጉዳይ ፣

- የዜጎች ደህንነት ጉዳይ፣

- በየቦታው ያሉና ህዝቡን ሰላም እየነሱ ያሉ ታጣቂዎችን በተመለከተ ምን እየተሰራ እንዳለ፤

- የትምህርት ጥራት አፈፃፀም፣ የመፅሀፍት እና የቁሳቁስ እጥረት ጉዳይ፣ በተጨማሪ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች እጣፈንታ ምንድነው ?

- ከባህር በር ጉዳይ ጋር ተያይዞ እንዲሁም በአጠቃላይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ስላለው የዲፕሎማሲ ሁኔታ፤

- ሰፊ የሀብት ብክነት እና ሌብነት የሚታይባቸው እንደ መሬት አስተዳደር፣ ገቢዎች  ፣ የጉምሩክ አገልግሎት ፣ ትላልቅ ግዢዎችና ትላልቅ የኮንስትራክሽን ስራዎች ከሌብነት እና ብክነት ለማፅዳት መንግስት ስለያዘው አቋም ፤

የሚመለከቱ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ተነስተዋል።

የሚሰጡት ምላሾችን እና ሌሎች ሀሳቦችን ተከታትለን እናቀርባለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #አሁን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው። የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትም ጥያቄዎችና አስተያየቶችን እያቀረቡ ይገኛሉ። እስካሁን ባለው ከተወካዮች ም/ ቤት አባላት ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ ? - የኦሮሚያ እና አማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ ፣ …
#ጥያቄ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ወ/ሮ ከድጃ ያሲን ፦

" ... የብልሹ አሰራር ከማስወገድና የፀረ-ሌብነት ትግልን ከማጠናከር አንፃር መንግሥት በየደረጃው ተጠያቂነትን ለማስፈን ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ? በፀረ-ሌብነት ትግሉ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ምን ይጠበቃል ?

ሰፊ የሀብት ብክነት እና ሌብነት በሚታይባቸው ለምሳሌ እንደ #መሬት_አስተዳደር#ገቢዎች#የጉምሩክ_አገልግሎት ፣ ትላልቅ ግዢዎች እና የኮንስትራክሽን ዘርፍን ከሌብነት እና ከብክነት የፀዳ እንዲሆን እንደ መንግስት የተያዘው አቋም ላይ ማብራሪያ ይሰጥ። "

@tikvahethiopia