TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Irreecha2016

በኦሮሚያ ክልል የሚዋጉ አካላት " በኢሬቻ ሥርዓት ወቅት እንቅፋት የሚሆን ተጽእኖ እንዳያደርሱ " ሲሉ አባገዳዎች ጥሪ አስተላለፉ።

አባገዳዎቹ ጥሪውን ያስተላለፉት መስከረም 26 እና 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ የሚከበረውን የኢሬቻ ሥርዓት በማስመልከት ነው ።

የጉጂ አባገዳ እና የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ሰብሳቢ አባገዳ ጂሎ ማንኦ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ፤ " እኛ አባገዳዎች ሥራችን ሰላም ነው፡፡ በኦሮሚያ የሚዋጉ ሁለቱም አካላት በኢሬቻ ስርዓታችንም ምንም አይነት እንቅፋት የሚሆን ተጽእኖ እንዳያደርሱብን ጠይቀናል፡፡ " ብለዋል።

" በሁሉም አቅጣጫ ያለው ኦሮሞ ሰላምና መግባባት ሰፍኖለት አንድነቱን እንዲያጠናክር እንፈልጋለን፡፡ " ያሉት አባገዳ ጂሎ " አገር ውስጥም ሆነ ከውጪም ያለው ኦሮሞ እንዲግባባ ነው የኛ መሻታችን፡፡ የሰላምና አንድነት አርማ በሆነው እሬቻ ስምም መጎዳዳቱ ቆሞ መግባባቱ እንዲሰፍን ነው የምንጠይቀው፡፡ ስለዚህ በዚህ በመጪው ኢሬቻችን ኦሮሞ በሙሉ ተስማምቶ በአንድ ሃሳብ እንዲግባባ ነው ፍላጎታችን። " ሲሉ ተናግረዋል።

አባገዳ ጂሎ ማንኦ ከኦሮሞም ባሻገር በመላው አገሪቱ ሰላም ሰፍኖ ወንድማማቾች መካከል ደም መፋሰሱ እንዲቀር ለማሸማገል አባገዳዎች ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

" እኛ ያላደረግነው ጥረት የለም፡፡ ከዚህ በፊት በትግራይ ጦርነት ነበር፡፡ ያንንም ለማሸማገል ከጦርነት በፊትም ሆነ ከጦርነት በኋላ ጥረናል፡፡ " ያሉ ሲሆን " አሁንም በአማራ ክልል የሚደረገውን የወንድማማች ግጭት እንዲቆም ነውና ፍላጎታችን ለሰላሙ የምንችለውን እንጥራለን፡፡ " ብለዋል።

" ተፋላሚዎች ችግራቸው ላይ እንዲነጋገሩ ነው የምንጠይቀው፡፡ ስለዚህ አሁንም በሰላሙ ጥረታችን ይቀጥላል፡፡ " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
" ምዕመናን ከጠዋቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ነጫጭ ልብስ በመልበስ ወደ በመስቀል አደባባይ መገኘት ይኖርባቸዋል " - ቤተክርስቲያን

በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅቱ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

የደመራ በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ ከቀትር ቀኋላ በመስቀል አደባባይ በመገኘት የቅድመ ዝግጅት ሥራው የደረሰበትን ደረጃ ተዛውረው የጎበኙ ሲሆን አጠቃላይ የዝግጅት ሥራው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተለይ የክብር እንግዶች የሚቀመጡበትን የመቀመጫ  መድረክ ከነ ሙሉ የድምፅ ግብዓቱ በማቅረብ ለበዓሉ ድምቀት ትብብር ላደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን እና ለከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል።

የበዓሉን አከባበር ሥነ ሥርዓትን በተመለከተ በተዘጋጀው መርሐ ግብር መሠረት በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጡ ምዕመናንም ከጠዋቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ነጫጭ ልብስ በመልበስ ወደ በመስቀል አደባባይ መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን የመንግሥት የጸጥታ አካላት በዓሉን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማክበር ሲባል ለሚያደርጉት ፍተሻ ፍጹም ክርስቲያናዊ የሆነ ትብብር እንዲያደርጉ ቤተክርስቲያን አሳስባለች።

በአንዳንድ የመገናኛ አውታሮች የቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት የሆኑ ከበሮ፣ ጸናጽልና መቋሚያ እንዳይገባ ተከልክሏል በማለት የሚናፈሰው ወሬም ፍጹም ሐሰት መሆኑን የገለፀችው ቅድስ ቤተክርስቲያን " በዓሉን በትርኢት ለማክበር የተፈቀደላቸው ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ኤነዚሁኑ ኔዋያተ ቅድሳት ይዘው ይገኛሉ " ብላለች።

በሌላ በኩል ፤ ወደ በዓሉ ማክበሪያ በሚደረግ ጉዞ ላይ በዓደባባዩ የሚገኙ የበዓሉ ታዳሚ ምዕመናን ያለምንም መግቢያ ባጅ ተፈትሸው ብቻ ወደ ዐደባባዩ መግባት የሚችሉ ሲሆን የመግቢያ ባጅ የሚጠየቁት የክብር እንግዶች፣ ጋዜጠኞችና ልዩልዩ የሚዲያ ተቋማት ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
እንኳን #ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ !

መልካም በዓል !

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
እንኳን ለመስቀል #ደመራ በዓል አደረሳችሁ !

መልካም በዓል !

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
" የመስቀል ደመራ በዓል ለ6ኛ ጊዜ አይከበርም " - በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት የላሃ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት " በላሃ ከተማ " የመስቀል ደመራ በዓል ለ6ኛ ጊዜ እንደማይከበር ተገልጸ።

ይህ የተገለፀው ፤ በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት የላሃ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ነው።

በዚሁ መግለጫ ፤ " በላሃ ከተማ የመስቀል ደመራ እና የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ቦታ በኃይል ከተነጠቀበት ቀን ጀምሮ ለ6ኛ ጊዜ አይከበርም " ብሏል።

ሀገረ ስብከቱ ላለው ጥያቄ ከፌዴራል እስከ ክልል መንግሥት ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ቢሰጥም በጎፋ ዞን እና በመሎ ኮዛ ወረዳ እንዲሁም የላሃ ከተማ አስተዳደር አመራር ትዕዛዙን ሳይቀበሉ በመቅረታቸው ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱን አሳውቋል።

በዚህም ቤተክርስቲያኒቷ ለጥያቄዋ ምላሽ ባለማግኘቷ የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓል ለ6ኛ ዓመት ማክበር እንደማትችል ገልጿል።

መንግሥት የቤተክርስቲያኒቷን ጥያቄ በአንክሮ ተመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቆ ምዕመናን በጸሎት ፈጣሪን በመጠየቅ ዕለቱን እንዲያሳልፉ  ጥሪ አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ምዕመናን ከጠዋቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ነጫጭ ልብስ በመልበስ ወደ በመስቀል አደባባይ መገኘት ይኖርባቸዋል " - ቤተክርስቲያን በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅቱ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳውቃለች። የደመራ በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ…
ፎቶ ፦ የመስቀል #ደመራ_በዓል በአዲስ አበባ መስቀል ዐደባባይ ፤ ብፁዓን አባቶች ፣ ምዕመናን ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ላይ እየተከበረ የሚገኘውን የመስቀል ደመራ በዓል የሚያሳዩ ፎቶዎች / ቪድዮዎችን በ @tikvahethmagazine ላይ የምንስቀምጥ ይሆናል።

የበዓሉን ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎችን / ቪድዮዎችን በእጅ ስልካችሁ እያነሳችሁ የምትገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት @tikvah_eth_BOT ላይ ከስማችሁ ጋር መላክ ትችላላችሁ።

Photo Credit - EOTC TV

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እንኳን #ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ ! መልካም በዓል ! #TikvahFamily @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ 1 ሺህ 498ኛው የመውሊድ በዓል አከባበር በታላቁ አንዋር መስጊድ እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች።

Photo Credit - ENA / DW

@tikvahethiopia