በጋዜጠኛ ኤልሳ አሰፋ የተፃፈው 'ስለእኛ ' የፋሽን ፣ የውበትና የአኗኗር ዘይቤ ላይ ያተኮረ መፅሐፍ ገበያ ላይ ውሏል።
መፅሀፉ በቤት ውስጥ ውበትን ለመንከባከብ የሚረዱ ተፈጥሯዊ ዘዴዎችን የሚጠቁም ፣ - ተለዋዋጭ በሆነው የፋሽን አለም ለሁኔታዎች ካለን አመለካከት ፣ከቁመና ፣ ከእድሜና ከውሏችን ጋር የተጣጣመ የአለባበስ ስታይል /ዘይቤ እንዴት መምረጥ እንደምንችል በቀላል አቀራረብና በምስል የተደገፈ ገለፃ የሚሰጥ እንዲሁም በጤናማ የአ ኗኗር ዘይቤ ላይ ያተኮረ ነው።
መፅሀፉ በ206 ገፅ በቀለም ህትመት የቀረበ ሲሆን በጃፋር መፅህፍት ፣ በተመረጡ የወንዶችና ሴቶች ውበት መጠበቂያ ማእከላትና ቡቲኮች ገበያ ላይ ውሏል።
ጋዜጠኛ ኤልሳ አሰፋ ከዚህ ቀደም በልጆች አስተዳደግ ላይ ያተኮረ መፅሀፍ ለአንባቢዎች አድርሳለች።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር " መልካም የሥራ ግንኙነት ስለመፍጠር " መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት አሳውቋል። ውይይቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ…
የሰራተኞች ጥያቄ ምንድነው ? ከሰሞኑን ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር በነበረው ውይይት ምን ጥያቃ ተነሳ ምንስ ምላሽ ተሰጠ ?
(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን - ፕሬዜዳንት ካሳሁን ፎሎ)
ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ ደሞዝ ተከፋዩ ሰራተኛ ችግር ላይ ነው ያለው። በተለይ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የሆነው ሰራተኛ እጅግ የከፋ ችግር ውስጥ ይገኛል።
ለኑሮ ውድነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኮቪድ19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ፣ ከሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ የታየው የዋጋ ንረት፣ የነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያቶች ሲሆኑ #ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ጦርነቶች እና ግጭቶች ለኑሮ ውድነት አስተዋፅኦ አድርገዋል።
የኑሮ ውድነቱን ለማቅለል እየተጠየቀ ያለው ጥያቄ ፦
- ሰራተኛው በጣም ችግር ላይ ስለሆነ የስራ ግብር ይቀነስ።
- ዝቅተኛ ደመወዝ የሚከፈላቸው ጭራሽ መኖር ወደማይችሉበት ደረጃ ላይ ስለደረሱ የገበያው ሁኔታ ታይቶ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ይወሰን።
- ለሁለት ዓመት የተቋረጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ ተመልሶ እንደገና ስራ እንዲጀምር። ይህ ቦርድ ከመንግሥት 5 ከሠራተኛ 5 ፣ ከአሰሪ 5 የሚሳተፉበት የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አፈፃፀምን እየተከታተለ አቅጣጫ የሚሰጥ ችግር ሲኖርም የሚፈታ ነው። ይህ ቦርድ ስራው በመቋረጡ የሠራተኞችን ጉዳይ ተጠያቂ የሚደረግበት ቦታ አልነበረም።
- 20/80 ተግባራዊ አልሆነም ተግባራዊ ይደረግ። ይህ ስራ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ለሚቀጥሩት ሰራተኛ ይከፍላሉ ተብሎ የወጣ መመሪያ ነው። መመሪያው የሚለው ለሰራተኛው 80% ለአስተዳደራዊ ወጪ 20% ይውሰድ የሚልነው።
- በነፃ የመደራጀት እና የመደራደር መብት ይከበር። ሰራተኞች ለመደራጀት ሲሞክሩ / ሲደራጁ በአሰሪዎቻቸው እርምጃ ይወሰድባቸዋል ፣ እርምጃዎቹ ከቦታ ቦታ ማዘዋወር፣ ከድራ ዝቅ የማደረግ፣ ከስራ ማባረር ይጨምራሉ። ስለዚህ ህግ በሚፈቅደው የመደራጀት እና የመደራደር መብታቸው ይጠበቅ ይህጉ ይፈፀመ።
- በሀገሪቱ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ሰራተኞች ላይም ጉዳት እያመጣ አንዳንድ ቦታዎች ሰራተኞች እንደሚታገቱ፣ እንደሚገደሉ፣ ስለሚታወቅ ያ ጉዳይ ተነስቶ መፍትሄ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምንድነው ?
በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዝቅተኛ ደመወዝ ወለል፣ ስራ ግብር ቅነሳ፣ ከአማካሪ ቦርድ ጋር በተያያዘ ሌሎችም ለተነሱ ጥያቄዎች ለሚመለከታቸው አካላት አቅጣጫ ሰጥተዋል።
" ጥያቄዎቹ ትክክል አይደሉም " ፤ ወይም " አይፈፀሙም " የሚል ምላሽ አልተሰጠም። በጊዜ ሂደት ምላሽ እንደሚያገኙ ተገልጿል።
ምላሽ የሚሰጡት በጥናት ላይ ተመርኩዞ በመሆኑ ይታያል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤ አቅጣጫም አስቀምጠዋል።
ወዲያው መፈፀም ያለበት የአማካሪ ቦርድ መቀጠል ላይ ቅድመ ሁኔታ የማያስፈልገው ስለሆነ እሱ እንዲቀጥል ለሚመለከታቸው አካላት አቅጣጫ ተሰጥቷል።
ሌሎችም ጥያቄዎች እንዲታዩ በሚል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

@tikvahethiopia

" ቲክቶክ " ኪርጊስታን ውስጥ እንዲታገድ ተወሰነ።
ኪርጊስታን " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው በሚል ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ወስናለች።
ውሳኔውን ያሳለፈው የሀገሪቱ የባህል ፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ነው።
ሚኒስቴሩ ባደረገው ግምገማ መሰረት " ቲክቶክ " ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ መቆጣጠሪያ እንደሌለው ገልጿል።
በተጨማሪም መተግበሪያው ለተጠቃሚዎቹ ትክክለኛ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎች እንደሌሉት ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ " ተጠቃሚዎችን በአጫጭር የቪዲዮ ክሊፖች ወደ ምናባዊ ግዛት ይስባል እናም እነዚህን ክሊፖች ከተመለከቱ በኋላ አንዳንድ ሰዎች ለሕይወት አስጊ የሆኑ አደጋዎችን የሚያስከትሉ ቪዲዮዎችን ለመኮረጅ ይሞክራሉ ሲል አክሏል።
እንዲህ ያለው #ሱስ የሚያስይዝ ይዘት በወጣቱ ትውልድ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በአጠቃላይም ለትውልዱ ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ የገለፀው ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ "ን ከሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ወስኗል።
ቲክቶክ ለሀገሪቱ እገዳ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።
" ቲክቶክ " በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ ሀገራት የሚደረግበት እገዳ እና ገደብ እየጨመረ መሆኑ ተነግሯል።
" ቲክቶክ " ከዚህ ቀደም በምስራቅ አፍሪካዋ ሀገር #ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ መቅረቡ ይታወሳል። በወቅቱም የፓርላማው አፈጉባኤ " ቲክቶክ በኬንያውያን በወጣቶች ዘንድ ተዘውታሪ በመሆኑ ፦ ግጭቶችን በማባባስ፣ ልቅ ወሲብን በማስፋፋት፣ የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት፣ የብልግና ቃላትን በማስፋፋት፣ አደገኛ ባሕሪያትን በማስፋፋት ለአገሪቱ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጠንቅ እየሆነ ነው " ብለው ተናግረው ነበር።
የእግዱ ጥያቄ ከቀረበ በኃላ ግን የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ከ " ቲክቶክ " ስራ አስፈፃሚ ጋር በመነጋገር በኬንያ ቲክቶክ ላይ የሚወጡ ቪዲዮች ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ስምምነት ላይ ሊደርሱ ችለዋል።
ከኬንያ በተጨማሪ ሶማሊያ የአሸባሪዎች መፈንጫ ሆኗል ፣ አሰቃቂ ቪድዮዎች ያለገደብ ይሰራጩበታል፣ ህዝቡንም አሳሳች መልዕክቶች ይዘዋወሩበታል በሚል እንዲታገድ መወሰኗ ይታወቃል።
የ " ቲክቶክ " መተግበሪያ በተለይ ፦
- ህፃናት ፣ ወጣቶች እንዲያዩትና እንዲሰሙት የማይመከሩ ቪድዮዎችን፤
- ልቅ የሆኑ የብልግና ስድቦችን ፤
- የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን፤
- ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን . . . የመሳሰሉትን በፍጥነት እንዲሁም እጅግ በቀላሉ ወደ ብዙሃን ያደርሳል ፤ ይህንን የሚቆጣጠርበት ስርዓት የለውም በሚል ይተቻል።
መተግበሪያው ለአጠቃቀም ቀላልና ማንኛውም ሰው የሚሰራው ቪድዮ በቀላሉ ለብዙሃን የሚደርስበት መንገድ ችግሩን እንዳባሰው የሚገልጹም አልጠፉም።
ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ " ቲክቶክ " በተለያዩ ሀገራት በርካታ ወጣቶች ተሠጥኦቸውን አውጥተው በቀላሉ ተደራሽ እንዳሆኑ ፣ በሚሰሯቸው ስራዎችም ክፍያዎችን እያገኙ እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲደግፉ ፣ ሀሳብ ያላቸውም ሀሳባቸውን በቀላሉ ለብዙሃን እንዲያደርሱ የሚያደርግ መተግበሪያ ነው በሚል የሚያወድሱት አሉ።

#CBE
ነጋዴ ነዎት?
እንግዲያውስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መርቻንት አፕ (Merchant APP) ተጠቅመው ክፍያዎትን ይቀበሉ።
==========
መርቻንት አፕ ነጋዴዎች ወይም የሽያጭ ባለሙያዎች ለሸጡት እቃ ወይም አገልግሎት ክፍያ የሚቀበሉበት የሞባይል መተግበሪያ ነው፡፡
መተግበሪያውን ከ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbebirr.merchantapp አውርደው በመጫን ባቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ይመዝገቡና መለያ ቁጥር (Till No.) ይውሰዱ ። ከዚህ በፊት መለያ ቁጥር (Till No.) ወስደው ከሆነ በቀጥታ መተግበሪያው ላይ ይመዝገቡ፡፡
አጠቃቀሙ
1. መተግበሪያውን ከፍተው የደንበኛውን ስልክ ቁጥር በማስገባት ክፍያውን ያስጀምሩ፣
2. ገዥው የነጋዴውን መለያ ቁጥር (Till No.) እና የክፍያውን መጠን የያዘ መልእክት ስልኩ ላይ ይደርሰዋል። ትክክለኛነቱን አረጋግጦ የሚስጥር ቁጥሩን (PIN) በማስገባት ክፍያውን ያከናውናል፡፡
3. የክፍያ ማረጋገጫ መልዕክት ይደርስዎታል። አለቀ፡፡

#itel_Mobile
በሚያመርታቸው የስልክ ሞዴሎች የባትሪ ጥራት የሚታወቀው አይቴል ሞባይል ለአዲሱ S23+ ሞዴል ባለ 5000 ሚሊ አምፒር ባትሪ ከ18ዋት የፍጥነት ቻርጅ የማድረግ አቅም ጋር በማጣመር ረጅም አገልግሎትን ያለ ማቋረጥ እየሰጠ ቀኑን ሙሉ ያለ ስጋት ማስጠቀም እንዲያችል ተደርጎ የተመረተ ነው ። የተለያዩ መተግበሪያዎችን ሲጠቀሙም ይሁን ጌሞችን እየተጫወቱ ሲዝናኑ የባትሪዎ ቶሎ የማለቅ አቅም የሚታሰብ አይሆንም።
አይቴል ሞባይል
#ItelMobile #ItelEthiopia #S23+
Follow Us : Facebook Instagram

#እስራኤል
ኔታኒያሁ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ከእስራኤል ለማስወጣት ለሚያዝ እቅድ ፍቃድ መስጠታቸው ተነገረ።
በትላንትናው ዕለት በቴል አቪቭ ጎዳናዎች ላይ በኤርትራዊያን ስደተኞች መካከል የተፈጠረውን አስከፊ ግጭት ተፈጥሮ ነበር።
ይህን ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ደም በተቃባው ግጭት ላይ የተሳተፉት ስደተኞች በሙሉ በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ አክለውም ሁሉም #አፍሪካዊያን ስደተኞች ከእስራኤል እንዲወጡ ለሚያዝ እቅድ ፍቃድ መስጠታቸውንም ገልጸዋል።
ትላንት ቅዳሜ የፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን አስተዳደርን በሚቃወሙ እና በሚደግፉ ኤርትራዊያን መካከል ግጭት ተነስቷል።
ተቃውሞውና ግጭቱ በእስራኤል ኤርትራ ኤምባሲ ፊት ለፊት ነው የተካሄደው። የእስራኤል የአደጋ አገልግሎት ተቋም 114 ሰዎች በግጭቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል።
የእስራኤል ፖሊሶች የግጭቱን ተሳታፊዎች ለመበተን የፕላስቲክ ቦምቦችን የተጠቀሙ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ በፖሊሶቹ ላይ ድንጋይ ወርውረዋል።
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፖሊስ ተቃዋሚዎቹ ላይ እሳት መርጨቱን የዘገበ ሲሆን በአጸፋው 27 ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል አስታውቋል።
በተያያዘ ሮይተርስ እጃቸው እና ጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች በህጻናት መጫወቻ ሜዳዎች ሲደበቁ መመልከቱን ዘግቧል።
በእስራኤል 20,000 ኤርትራዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹም በህገወጥ መንገድ በግብጽ አድርገው የመጡ ናቸው።
#ቪኦኤ #ኤኤፍፒ #ሮይተርስ

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መቼ ይገለፃል ? የቀጣይ አመቱ ፈተናስ በየትኛው ካሪኩለም ይሰጣል ?
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እስከ መስከረም 2016 ዓ/ም አጋማሽ ድረስ ይፋ ለማድረግ እቅድ መያዙ ታውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ በማድረግ በጥቅምት ወር የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንዲጀመር የማድረግ ዕቅድ መያዙን ከሰሞኑን መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ መገራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።
ከዚህ በተጨማሪ በ2015 ዓ.ም. በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ሲወስዱ የነበሩት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች፣ የመጨረሻዎቹን ሦስት ፈተናዎች ባለመፈተናቸው ዘንድሮ መጨረሻ ድረስ ተፈትነው እንዲያሚያጠናቅቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በጎንደር በነበረው ግጭት ወቅት ፈታናዎቹን ያልወሰዱት በአጠቃላይ ከ16 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደነበሩ የሚዘነጋ አይደለም።
በሌላ መረጃ ደግሞ ፤ በቀጣይ ዓመት 2016 ዓ/ም የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አዲሱ እና የቀድሞው ካሪኩለም ድብልቅ ፈተና እንደሆነ ታውቋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ቀጣይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሆኑ እስከ 11ኛ ክፍል የተማሩት በድሮው ካሪኩለም መሆኑን ገልጸው በቀጣይ አመት የሚማሩት ግን በአዲሱ ካሪኩለም መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህ የሽሽግር ስራ በሚሰራበት ወቅት ብሔራዊ ፈተናው ተደባልቆ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
ከታች ያሉትን በድሮው ካሪኩለም አሁን ገብተው የሚማሩትን በአዲሱ ካሪኩለም ተደርጎ ነው ፈተናው የሚዘጋጀው በዚህ ላይ ችግር አይፈጠርም ብለዋል።
በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

#ኤክሶደስ_የፊዝዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክ
በውቢቷ ባህርዳር አዲስ ቅርንጫፍ ከፍተናል ፤ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች፦
- ለአንገት፣ለትክሻ፣ለወገብ ህመም
- ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር
- ለፊት መጣመም
- ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች
- ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች
አድራሻችን፦ ቁጥር 1_ አዲስ አበባ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን ፤ ቁጥር 2_ ባህርዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል አጠገብ ስልክ ቁጥር 0979099909 / 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://yangx.top/ExodPhysioClinic

ሀዋሳ ከተማ አዲስ ከተንቲባ ተሹሞላታል።
የከተማው አስተዳደር ምክር ቤት ፤ በግምገማ ከስልጣናቸው በተነሱት ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ምትክ ዛሬ አዲስ ከንቲባ ሾሟል።
አዲሱ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ ሲሆኑ ከተማይቱን በምክትል ከንቲባ ማእረግ እንዲያስተዳድሩ ተሹመዋል።
አቶ መኩሪያ የዛሬው ሹመት እስከተሰጣቸው ጊዜ ድረስ የሲዳማ ክልል ከተማ ልማትና ካንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ ተብሏል።
ከንቲባው በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሐላ ከፈፀሙ በኃላ ካቢኔያቸው አፀድቀዋል።
ላለፉት ዓመታት ሀዋሳን ሲያስተዳድሩ የነበሩት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በቅርቡ በተደረገ የአመራሮች ግምገማ በ " ብልሹ አሰራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " በሚል ከስልጣን ተነስተው በህግ እንዲጠየቁ መወሰኑ ይታወሳል።

#ሲዳማ የሲዳማ ክልል መንግሥት ፤ " የተሰጣቸውን የመንግስትና የህዝብ አደራ ወደ ጎን በመተው በሙስናና ብልሹ አሰራር ላይ ተሳትፈዋል " ባላቸው አመራሮች ላይ የፖለቲካ ውሳኔ መተለለፉን አሳወቀ። ክልሉ እኚሁ አመራሮች እንደየሥራቸው ከህግ ተጠያቂነት አያመልጡም ብሏል። የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ በሰጡት መግለጫ ፤ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ያልተወጡና በብልሹ አሰራር ላይ የተሳተፉ…
" ቅንጣት ታክል ጥፋት አልሰራሁም " - ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ
በከንቲባነት ዘመኔ ቅንጣት ታክል ጥፋት አልሰራሁም አሉ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሬፌሰር ፀጋዬ ቱኬ።
የቀድሞ ከንቲባ ይህ ያሉት ዛሬ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባወጡት ፅሁፍ ነው።
በቅርቡ በተደረገ ግምገማ በ" ብልሹ አመራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " ከስልጣናቸው የተነሱት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ በእሳቸው ምክት አዲስ ከንቲባ በተሾመበት ዕለት ባሰራጩት መልዕክት በስልጣን ዘመናቸው ቅንጣት ታክል ጥፋት እንዳልሰሩ ገልጸዋል።
የቀድሞው ከንቲባ ፤ " እኔ በፈጣሪ ፊት የምመሰክረዉ እዉነት በከንቲባነት ዘመኔ ህዝቤን የሚጎዳና የማይጠቅም የተቀመጥኩለትን አላማ የሚያጎድፍ ቅንጣት ጥፋት አልሰራሁም ብዬ አምናለሁ " ብለዋል።
" ምናልባትም የግለሰቦችን የጥቅም ፍላጎት ካለማርካት በቀር፤ እኔን ማሳደዱ የስልጣን ፍላጎትና የእዉቅና ሽሚያ ካልሆነ በስተቀር ፣ በክልሉ ይፋ ያልወጡ በህዝብ እንባና ላብ የከበሩ እንኳን ህግ ፈጣሪም ይቅር የማይለዉ ወንጀል/ጥፋት የፈጸሙ የህዝብን ሀብት በሽፋን የሚዘርፉ አካላት አሉ " ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም እነዚህ አካላት " የግዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በቅርብ ይፋ ይወጣሉ። " ብለዋል።
የቀድሞው ከንቲባ " በህዝብ እምባ እና ላብ የከበሩ " ስላሏቸው አካላት ስም አልገለፁም።
በሲዳማ ክልል ያለዉ ነባራዊ ሁኔታ በብልፅግና ፓርቲ መርህ ሕዝብን ማገልገል የሚያስቸግር ነው ያሉት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ፤ " ቡድንተኝነትና በሴራ ፓለቲካ የተተበተበ፤ በመሆኑ እኔም ሆንኩ በተሻለ አፈጻጸም ላይ የነበሩ አመራሮች የፓርቲን መርህ ባልተከተለ መልኩ ከኃላፈነት ተነሰተናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" እድል ያገኘን ቀን እዉነቱን በቅርቡ በፈጣሪ እና በህዝባችን ፊት ቆመን በመረጃና በማስረጃ እንታገላለን " ብለዋል።
አሁን ያለዉ የክልሉ የፖለቲካ ጉዞ ሁኔታ ይህንን ማድረግ የሚያስችል እንዳልሆነ የገለፁት ረ/ፕ ፀጋዬ ፤ በቤተሰባቸው ላይ ለሚደርሰዉ አንዳች እንግልትና ጉዳት ተጠያቂዉ የክልሉ መንግስት እንደሆነ ገልጸዋል።
ወደፊት ሀገራቸው በምትፈልጋቸው ቦታና ግዜ ህዝብን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።
ሀዋን ለ3 ዓመታት የመሩት የቀድሞው ከንቲባ ባሰራጩት ፅሁፍ ለአዲስ ተሿሚ አካላት መልካም የስራ ጊዜ ተመኝተዋል።
ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ በአመራሮች ግምገማ ወቅት ከስልጣን እንደተነሱ እና በህግ እንደሚጠየቁ ይፋ ከተደረገ በኃላ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን ረ/ፕ ፀጋዬ " የት እንዳሉ " እንደማያውቁ መናገራቸው ይታወሳል።
በበኃላም የቀድሞው ከንቲባ የት ሀገር እንደሚገኙ በግልፅ ሳይናገሩ በህክምና ክትትል ላይ እንዳሉና በቅርቡ በህዝብ መኃል ተገኝተው እውነታውን እንደሚያጋልጡ መግለፃቸው አይዘነጋም።
በሲዳማ ክልል ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በተለይም ወጣቶች ክልሉ በብልሹ አሰራር ፣ እንዲሁም በሙስናና በትውውቅ በሚሰሩ ስራዎች ነዋሪዎችን እያማረረ መሆኑን እና ከላይ እስከ ታች ያሉት አመራሮች እያንዳንዳቸው እንዲገመገሙና አመራራቸውም እንዲፈተሽ መጠየቃቸው ይታወሳል።