TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሙሴቬኒ ምን አሉ ?

የዓለም ባንክ ፤ ኡጋንዳን ለምን የ " ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚከለክል ሕግ ተግባራዊ አደርግሽ ፤ ይህ ሕግ መሰረታዊ ከሆኑ እሴቶቼ ጋር ይቃረናል " በማለት አዲስ ብድር እንደማይሰጣት አሳውቋል።

ይህ ውሳኔ በተመለከተ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ ምን አሉ ?

" ኡጋንዳ ያለ ዓለም ባንክ ብድር ማደግ ትችላለች።

የዓለም ባንክ እምነታችንን ፣ ሉዓላዊነታችንን እና ባህላችንን በገንዘብ እንድንቀይር እያስገደደን ነው።

ምዕራባዊያን አፍሪካን ዝቅ አድርገው መመልከት እና ጫና ማሳደር ይፈልጋሉ ፣ እኛ ችግራችንን እንዴት መፍታት እንዳለብን እናውቃለን፣ እነሱም የእኛ ችግሮቻችን ናቸው።

ኡጋንዳ ከዓለም ባንክ ጋር ያለባትን ችግር ለመፍታት የሚቻል ከሆነ ውይይት ለማድረግ ትቀጥላለች። " #ALAIN

ኡጋንዳ ባፀደቀችውና ተግባራዊ ባደረገችው የፀረ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ሕግ እድሜ ልክ በእስር ቤት መማቀቅን ጨምሮ ሞት ሊያስፈርድ ይችላል።

ይህን ሕግ አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት እና ተቋማት የተቃወሙ ሲሆን የዓለም ባንክ ደግሞ አዲስ ብድር አልሰጥሽም ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ የባህር ዳር ፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት ነዋሪዎች ምን አሉ ? የባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ከተማቸው በመከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝና ዛሬ ተኩስ እንዳልነበር ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። #ባህርዳር ነዋሪ 1 " ከትለንት ከግማሽ ለሊት በኃላ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። ተኩስም የለም፤ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። አንፃራዊ ሰላም አለ። መከላከያው…
የአማራ ክልል ከተሞች እንዴት ዋሉ ?

በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን ፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

#ባሕርዳር

ዛሬ  የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም።

የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው ከተማዋ ጭር ብላ ነው የዋለችው።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች እና ባጃጆች ወደ ሥራ ባለመመለሳቸው የነዋሪው እንቅስቃሴ ተገትቶ ውሏል።

ተቋርጦ የነበረው የ ' ኢትዮጵያ  አየር መንገድ በረራ ' ወደ ባሕር ዳር መጀመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ የሚወስድ ትራንስፖርት ስለሌለ ተሳፋሪዎች በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል።

አሁንም የተወሰኑ መንገዶች በትላልቅ ቋጥኖች እና ድንጋዮች እንደተዘጉ ስለሆኑ ለትራንስፖርት አስቸጋሪ ነው።

ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ባትመለስም አንዳንድ ነዋሪዎች በእግራቸው ሲንቀሳቀሱ ውለዋል።

#ደብረ_ማርቆስ

በደብረ ማርቆስ ከተማ ትራንስፖርትም ሆነ የንግድ መደብሮች ወደ ስራ እንዳልተመለሱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

" ሱቅ፣ ሆቴል ዝግ ነው። " ያሉ አንድ ነዋሪ " ምንም እንኳን በአይኔ ባላይም ጥዋት አንድ ባስ ከማርቆስ ወጥቶ ወደ አ/አ ሄዷል የሚባል ነገር አለ ፤ ከአዲስ አበባ መስመር ግን አንድ ሁለት ባሶች ማርቆስ ገብተዋል። " ሲሉ ገልጸዋል።

በደብረ ማርቆስ ወደ ጎንደር፣ ወደሌሎችም ቦታዎች የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ናቸው ፤ መደበኛ እንቅስቃሴም አልተጀመረም።

#ደጀን

ከተማዋ አሁን ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ሰሞኑን ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አገልግሎቶች ተስተጓጉለዋል።

የውሃ እንዲሁም መብራት አገልግሎት ከተቋረጠ ቀናት እንደተቆጠሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ፤ በብቸና መስመር ወደ ሞጣ የሚያልፍ በርካታ የመከላከያ ኃይል እንደተመለከቱ ገልጸዋል።

ብቸና ላይ ግጭት እንደነበር የሚጠርጥሩት ነዋሪው ሥፍራው ከደጀን ከ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ቢሆንም የከባድ ተኩስ ድምፅ ግን ይሰማ እንደነበር ጠቁመዋል።

#ጎንደር

ከትላንት #ረቡዕ ጀምሮ ተኩስ እንደማይሰማና አሁን ላይ ሰላም መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሰዎች በእግር ይንቀሳቀሱ እንጂ፣ ተሽከርካሪ የለም።  በብዛት ሱቆች እና ወፍጮ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

በከተማው የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከፈቱ ቢታዘዙም ሁሉም ሙሉ በሙሉ እንዳልተከፈቱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በጎንደር የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ታንኮች በተለይ ደግሞ አድማ በታኞች በስፋት እንደሚታዩ ተነግሯል።

ዛሬ ወደ ጎንደር ከተማ በረራ ይጀመራል ቢባልም ወደ ከተማው አውሮፕላን እንዳልገባ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

#ደብረብርሃን

በደብረ ብርሃን ሱቆች እና ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ባጃጅ መንቀሳቀስ መጀመሩን ጠቁመዋል። ዛሬ ደግሞ ሱቆች መከፈታቸውንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።

#ላሊበላ

" ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ባይሆንም " የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ መግባታቸው ፣ ተቋማት እና ተሽከርካሪዎች በተወሰነ ደረጃ ስራ እንደጀመሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከወትሮው የተለየ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳልታየ የገለፁት ነዋሪዎች የአውሮፕላን በረራ እንዳልተጀመረና የበረራው መጀመር እየተጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

በላሊበላ በረራ ለመጀመር ቀናት ሊፈለግ እንደሚችል ተነግሯል።

#ደብረታቦር

የከተማዋ እንቅስቃሴ በጣም ቀዝቃዛ ነው። ነዋሪው በጊዜ  ነው ወደ ቤቱ እየገባ ያለው።

አሁን ላይ በከተማዋ ፤ ምንም ዓይነት የተኩስ ድምፅ ባይሰማም  በከተማዋ የጦር መሣሪያም ሆነ ስለት ያለው ቁስ ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ መገኘት አደጋ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጻዋል። ይህን ይዞ የተገኘ ሰው እርምጃ ይወስድበታል ብለዋል።

ሆቴሎችና ባንኮች ዝግ እንደሆኑ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን በከተማው ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ቢኖርም 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስለ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ እንዳለ ፤ ይሄም ቢሆን ሱቆች አሁንም ዝግ ስለሆኑ በሰው በሰው የሚገኝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

መረጃው ከኤኤፍፒ፣ ዶቼቨለ፣ ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።

NB. የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ፦
- በባህር ዳር ፣
- በደብረ ማርቆስ፣
- በደብረ ብርሃን፣
- በላሊበላ ፣
- በጎንደር ፣
- በሸዋሮቢት ከባጃጆችና ከሞተር ሳይክሎች በስተቀር ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከነሐሴ 4 ጀምሮ ወደ ሥራ የመመለስ እና አገልግሎት የመስጠት #ግዴታ_እንደተጣለባቸው ማሳወቁ ይታወሳል።

ከዚህም በተጨማሪ ፤ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ ማዘዙ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
በአቢሲንያ ቪዛ ካርድ በካፌዎች ፣ በሆቴሎች ፣ በሱፐርማርኬቶች እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች በቀላሉ ያለ ብዙ ንክኪ ይገበያዩ ፤ ይክፈሉ።

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#contactless #nfc  #BoAVisacard  #Visa #Abyssiniabank #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #the_choice_for_all
" በጦርነትና አለመረጋጋት ምክንያት በሚፈጠረው ቀውስ የመጀመሪያ ተጠቂዎችና የመከራው ገፈት ቀማሾች ሴቶች እና ህፃናት ናችው " - በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የሴቶች ክንፍ

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ክንፍ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ልከውልናል።

በመግለጫቸው ፤ በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው አመልክተዋል።

" በወንድማማች ጦርነት አሸናፊም ሆነ ተሸናፊ ላይኖር  ነፍጥ ያነሱ ወገኖች ከሀገር መከላከያ ጋር በመዋጋት የሚመጣ መፍትሔ አይኖርም፡፡ " ብለዋል።

መንግስትም ባወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወይም በጠመንጃ ኃይል የክልሉን ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ማምጣት እንደማይችል ገልጸዋል።

በመሆኑንም ፦

- ከቀደመው የትግራይ ጦርነት በመማር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጦርነት ቆሞ ችግሮች በድርድርና ውይይት እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

- ሮጠው ማምለጥ የማይችሉት አረጋውያን፣ ሴቶች እና ህጻናት በከፍተኛ የደህንነት ስጋት ውስጥ ስለሆኑ መንግስት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያድርግላቸው አሳስበዋል።

- የሰላም ጠንቅ የሆኑ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች መነሻቸው ተፈትሾ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ የሚያስችል የጋራ መድረክ በማመቻቸት ለውይይትና ድርድር ቅድሚያ በመስጠት ከተጨማሪ ቀውስ እና ጉዳት መታደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

- በየትኛውም ሀገር በትጥቅ የታገዘ አለመግባባት እና ግጭት እጅግ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ካደረሰ በኋላ መቋጫው በሰላማዊ ውይይት እንደሆነ በተግባር በሀገራችንም ተከስቶ ስላየነው ነፍጥ ያነሱ ሁሉ ነፍጣቸውን ወደ አፎት እንዲመልሱ ተማፅነዋል።

- የሚዲያ አካላትና አክቲቪስቶች አብሮ የኖረውንና ሊለያይ የማይችልውን ህዝብ ከሚያጋጩና ለጦርነት ከሚያነሳሱ ዘገባዎች  እና ቅስቀሳዎች እንዲታቀቡ ጠይቀዋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#AmharaScholarsCouncil

በአማራ ክልል የምሁራን መማክርት ጉባኤ በላከልን መግለጫ ፤ በክልሉ ውስጥ አሁን የተፈጠረው ቀውስ በዘላቂነት የሚፈታው በውይይት መሆኑን ገልጾ መንግስትና የታጠቁ ሀይሎች ተኩስ አቁመው እንዲወያዩ ጥሪ አቅርቧል።

ጉባኤው  በመግለጫው ፤ " ሕዝባችን ባለፉት አመታት ተደጋጋሚ የሆኑ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግፎች እና በደሎች እየደረሱበት ይገኛል " ብሏል።

ይህንን ለማስቆምና መሠረታዊ ጥያቄዎቹ መልስ እንዲያገኙ በተደራጀ መልኩ መታገል እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

ይህ አይነቱ ፖለቲካዊ ትግል ዘላቂ መፍትሔ እንዲያስገኝ በ #መነጋገር እና በ #ውይይት ላይ የተመሠረተ ሊሆን እንደሚገባው አስገንዝቧል።

" በዚህ ረገድ ባለፉት አመታት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል " ሲልም ገልጿል።

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ፤ " ዛሬ ሕዝባችን ዘር የሚዘራበትና የማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ዕጥረቱን ለመቀነስ አይን አይን እያየበት ያለበት ወቅት ነው። በተጨማሪም ትላንት አብረውት ተሰልፈው የተዋደቁ ኃይሎች ዛሬ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር የሚጋጩበት ሁኔታ ሊፈጠር አይገባም። " ብሏል።

ስለሆነም ክልሉ ውስጥ አሁን የተፈጠረው ቀውስ በዘላቂነት የሚፈታው በውይይት መሆኑ ታውቆ መንግስትና የታጠቁ ሀይሎች ተኩስ አቁመው እንዲወያዩ ጥሪ አቅርቧል።

በየአካባቢው ያሉ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች እና ምሁራን ሰላም እንዲሰፍን ችግሮች በውይይት እና በሰላም እንዲፈቱ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪውን አስተላልፏል።

(መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#NBE

የውጭ ምንዛሬ ክፍፍል ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ የብሄራዊ ባንክ ቦርድ መወሰኑን " ካፒታል " ጋዜጣ ዘግቧል።

በዚህም ውሳኔ መሰረት የውጭ ምንዛሬ ክፍፍሉ ቀደም ሲል ከነበረው 70/30 ወደ 50/50 እንዲስተካከል ተደርጓል።

በውሳኔው መሰረት ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ግኝታቸው 50 በመቶ ለብሄራዊ ባንክ 40 በመቶውን የውጭ ምነዛሬውን ላመነጨው አካል እንዲሁም ቀሪውን 10 በመቶ ለባንኮች እንዲከፋፈል ተወስኗል።

የብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ፤ ቦርዱ የዋጋ ግሽበትን ለመግታት በርካታ የገንዘብ እና የፊሲካል ውሰኔዎችን ማሳለፉን እንዳሳወቁ " ካፒታል " ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) በረራ ነገ ይጀምራል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን አሳውቋል። መንገደኞች የአየር መንገዱን ድረ-ገጽ (www.ethiopianairlines.com) ወይም የሞባይል መተግበሪያውን (https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian…
የላሊበላ በረራ ነገ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ የመንገደኞችን ፍላጎት በማጤን በድጋሚ ወደተከፈቱት የአገር ውስጥ መዳረሻዎች የበረራ ምልልሶችን ለመጨመር ዝግጁ መሆኑን አየር መንገዱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ ወደነበሩት ባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ደሴ (ኮምቦልቻ) ዳግም በረራ መጀመሩን ማሳወቁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NBE የውጭ ምንዛሬ ክፍፍል ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ የብሄራዊ ባንክ ቦርድ መወሰኑን " ካፒታል " ጋዜጣ ዘግቧል። በዚህም ውሳኔ መሰረት የውጭ ምንዛሬ ክፍፍሉ ቀደም ሲል ከነበረው 70/30 ወደ 50/50 እንዲስተካከል ተደርጓል። በውሳኔው መሰረት ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ግኝታቸው 50 በመቶ ለብሄራዊ ባንክ 40 በመቶውን የውጭ ምነዛሬውን ላመነጨው አካል እንዲሁም ቀሪውን 10 በመቶ ለባንኮች እንዲከፋፈል…
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፤ የዋጋ ንረትን ለማርገብ የሚያስችል የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ ወስኗል።

ይህ በተመለከተ የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫው ምን ምን ነጥቦችን አነሱ ?

- ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እያየለ የመጣውን የዋጋ ንረት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቆጣጠር የብሔራዊ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ አሳልፏል።

- ከውሳኔዎቹ መካከል ለመንግስት የሚሰጠው የቀጥታ ብድር ባለፈው አመት ከተሰጠው ከ1/3ኛ እንዳይበልጥ ይደረጋል።

- መንግስት ቅድሚያ የግምጃ ቤት ሰነድ አማራጭን አሟጦ እንዲጠቀምና አማራጭ ሳይኖር ሲቀር ብቻ የቀጥታ ብድር ይጠቀማል።

- በ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ሰኔ መጨረሻ የሃገር ውስጥ ብድር ዕድገት በ14 በመቶ ጣሪያ ይገደባል። ሁሉም ንግድ ባንኮች የብድር ዕድገት ዕቅዳቸውን በዚህ የብድር ጣሪያ መሰረት እንዲያስተካክሉ ይደረጋል።

- ባንኮች የገንዘብ እጥረት ሲገጥማቸው ከብሄራዊ ባንክ ከሚወስዱት ብድር የብድር ፋሲሊቲ ላይ የሚከፍሉት ወለድ ከ16 በመቶ ወደ 18 በመቶ ከፍ እንዲል ይደረጋል።

- ቁልፍ የሆኑ የወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዘርፎች በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ላኪዎችን ለማበረታታት ከዚህ ቀደም የነበረው የውጭ ምንዛሬ የማስተላለፍ ግዴታ ከ70/30 ወደ 50/50 እንዲሻሻል ይደረጋል። ላኪዎች 50 በመቶውን ለብሄራዊ ባንክ እንዲያስገቡ፣ 10 በመቶውን አብረው ለሚሰሩት ባንክ እንዲሰጡ እና 40 በመቶውን ለራሳቸው እንዲጠቀሙ ተወስኗል።

- በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ የዋጋ ንረቱ ከ20 በመቶ በታች እንዲሆንና በ2017 በጀት ዓመት ደግሞ ከ10 በመቶ በታች ለማውረድ ይሰራል።

ህብረተሰቡ ውሳኔውን በመደገፍ የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን እርምጃ እንዲደግፍ ጥሪ ቀርቧል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እስራኤል ዜጎቿን ከአማራ ክልል ወደ #ትግራይ ክልል ማስወጣቷን " ጄሩሳሌም ፖስት " ዘግቧል። እስራኤል በአማራ ክልል ውስጥ ያለውን ግጭትና የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቅርበት እየተከታተለችው መሆኑ ተነግሯል። ባለፈው ሰኞ ከአካባቢው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመሆን ተጓዥ ዜጎቿን ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ እንዲወጡ ማድረጓ ተገልጿል። ዘገባው ተካሂዷል ባለው የእስራኤል ዜጎችን ከግጭት ቀጠና…
#Update

እስራኤል ዜጎቿን ከአማራ ክልል አስወጣች።

በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ትዕዛዝ ከ200 በላይ እስራኤላውያን ከባሕር ዳር እና ጎንደር መውጣታቸው ተዘግቧል።

በርካታ ቤተ እስራኤላውያን በሚገኙበት የአማራ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ ፦
- የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣
- በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ፣
- የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣
- የእስራኤል የደኅንነት ም/ቤት
- የአይሁዳውያን ተቋም በጋር ሆነው ዜጎቻቸው ከክልሉ እንዲወጡ አድርገዋል።

በዚህም ከጎንደር ከተማ 174 ከባሕር ዳር ደግሞ 30 ቤተ እስራኤላውያን ትላንት እንዲወጡ ተድረገዋል።

እስራኤላውያኑ እንዴት ወጡ ?

ረቡዕ ምሽት ላይ ካሉባቸው ከተሞች እንዲወጡ ለማስቻል በተመቻቹላቸው የመሰባሰቢያ ቦታዎች ላይ እንዲገኙ ከተደርገ በኋላ ወደ ጎንደር እና ባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያዎች ተወስደዋል።

በአየር ማረፊያዎቹም ቀድመው በተዘጋጁ ልዩ በረራዎች አማካይነት እንዲጓጓዙ ተደርገው አዲስ አበባ ሐሙስ ዕለት ገብተዋል።

እስራኤላውያኑን ከአማራ ክልል የማስወጣት ተልዕኮ በእስራኤል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ባለ የመከታተያ ክፍል (ሲችዌሽን ሩም) እገዛ የተደረገለት ሲሆን ዲፕሎማቶች፣ የአይሁዳውያን ተቋም ሠራተኞች እና አማርኛ የሚችሉ የእስራኤል ሠራዊት አባላት በቡድኑ ውስጥ ነበሩበት ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት እንዳለው ዜጎቹ ወደ አስራኤል ለመመለስ አስኪወስኑ ድረስ በአዲስ አበባ ውስጥ ይቆያሉ።

ኔትያንያሁ ምን አሉ ?

ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ፤ " እስራኤል ዜጎቿን ባሉበት ቦታ ሁሉ ጥበቃ ታደርጋለች " ያሉ ሲሆን " ባለፉት ቀናት ግጭት ባለበት የኢትዮጵያ አካባቢ ዜጎቻቻን ነበሩ። ከዚያ እንዲወጡ እንዲደረግ አዝዣለሁ " ብለዋል። አገራቸው ዜጎቿን በደስታ እንደምትቀበልም መግለፃቸውን #ቢቢሲ_አማርኛ ዘግቧል።

እስራኤል ከቀናት በፊት ጥቂት ዜጎቿን ከአማራ ክልል ደባርቅ ወደ ትግራይ ሽረ ከተማ ማስወጣቷ ይወሳል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የእስራኤል ጠ/ሚ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
#Update

- የአውስትራሊያ ፣
- የጃፓን ፣
- የኒውዚላንድ፣
- የእንግሊዝ እና የዩናይትድ ስቴትስ መንግስታት በቅርቡ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሰላማዊ ዜጎች ሞት እና አለመረጋጋት ያስከተለው ግጭት እንዳሳሰባቸው ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ሀገራቱ ፤ ሁሉም ወገኖች ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ እና የሚያጋጩ ውስብስብ ጉዳዮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተባብረው እንዲሰሩ አበረታተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ድጋፉን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል ፦
- የአውሮፓ ህብረት ልዑክ በኢትዮጵያ
- የኦስትሪያ ፣
- የቤልጂየም ፣
- የቼክ ሪፖብሊክ ፣
- የዴንማርክ ፣
- የፊንላንድ ፣
- የፈረንሳይ ፣
- የጀርመን ፣
- የሃንጋሪ ፣
- የአየርላንድ ፣
- የኢጣሊያ ፣
- የሉክሰምበርግ ፣
- የማልታ ፣
- የኔዘርላንድስ ፣
- የሮማኒያ ፣
- የፖላንድ ፣
- የፖርቹጋል ፣
- የስሎቬንያ ፣
- የስፔን እና የስዊድን ኤምባሲዎች በጋር ባወጡት መግለጫ ሰሞኑን በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ሁከትና የዜጎች ሞትና አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ሀገራቱ ፤ " ሁሉም ወገኖች ሲቪሎችን እንዲጠብቁ ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ህዝቦች የተሟላ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀጣይነት ያለው ሰብአዊ ተደራሽነት እንዲረጋገጥ፣ የውጭ ዜጎች ከግጭቱ አካባቢ ለቅቀው እንዲወጡ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲተላለፉ እንዲፈቀድ፤ የሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም በሚቀጥልበት ጊዜ ውስብስብ ጉዳዮችን በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት በጋራ መስራት፣ እና ግጭቱ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ተዛምቶ ብጥብጥ እንዳይፈጠር ተገቢው መከላከል እንዲደረግ እናበረታታለን " ብለዋን።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የረዥም ጊዜ የመረጋጋት ግብ ድጋፉን ይቀጥላል ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት አካውንትዎን ያለማንም እርዳታ በኢ-ኬር ድረ-ገጽ ያስተዳድሩ!

✔️ የአገልግሎት መረጃዎን ማየት እና ማስተዳደር
✔️ ወርሀዊ የድሕረ-ክፍያ ቢል እና የአጠቃቀም ዝርዝር መረጃ ለማግኘት
✔️አገልግሎት መቋረጥ/ብልሽት ሪፖርት ለማድረግ እና ለመከታተል
✔️የአገልግሎት (የጥሪ፣ መልዕክት፣ ዳታ) አጠቃቀም ዝርዝር ለማግኘት
✔️ፒን እና ፒዩኬ ለማግኘት

እነዚህንና ሌሎች በርካታ እገልግሎቶችን በኢ-ኬር  ለማግኘት በቀጣዩ ሊንክ
https://www.ecare.ethiotelecom.et ይመዝገቡ፤ ይጠቀሙ!