TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በሳምንታዊ የዳታ ጥቅሎቻችን በአነስተኛ ዋጋ ብዙ ይጠቀሙ!
ለወዳጆችዎ በስጦታ ያበርክቱ!

ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ሲገዙ 10% ስጦታ ያገኛሉ
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነገ መግለጫ ሰጥተዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?

- ፈተናው ከኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል።

- ፈተናውን ለመፈተን በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ ከነዚህም ውስጥ 840 ሺህ 859 ፈተናውን ውስደዋል።

- በማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና የተወሰነ የሥነ-ምግባር ችግር ጨምሮ አንዳንድ ችግሮች ተስተውለው ነበር።

- በጉዞ ሂደት ያጋጠመ የትራፊክ አደጋ፣ በሕመም ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ እና ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶችን ወደ ፈተና ጣቢያ ይዞ መግባት በመሞከር እና የሥነ ምግባር ችግሮች አጋጥመዋል።

- በፈተና ሂደቱ የጎላ ችግር አልገጠመም።

- በጎንደር ዩኒቨርሲቲ 3 ካምፓሶች ላይ (ማራኪ ፣ ፋሲል ፣ ቴዎድሮስ) ትናንት ባጋጠመ ችግር 16 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን ሳይፈተኑ ቀርተዋል። በቀጣይ በሚመቻች መርሐ-ግብር ይፈተናሉ።

- በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ኢመደበኛ ኃይሎች መከላከያው ላይ በከፈቱት ተኩስና ከዛ በኃላ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲሰጥ የነበረ አንድ ግለሰብ እና ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባሎች ተገድለዋል። አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ቆስሏል።

- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የገቡ 16 ሺህ ተማሪዎች፤ ትላንት ከሰዓትና ዛሬ ጠዋት የተሰጡትን ፈተናዎች አልወሰዱም።

- በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ካጋጠመው ችግር ውጪ በአማራ ክልል በሚገኙ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የተሰጠው ፈተና በሰላም ነው የተጠናቀቀው።

- በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይም የአውሮፕላን በረራ በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ያሉ የፈተና አስፈጻሚዎች ሁኔታው እስከሚረጋጋ ድረስ ትንሽ ቀን መጠበቅ አለባቸው።

- ጋምቤላ ላይ የተወሰኑ ተማሪዎች ባጋጠማቸው ሕመም 38 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም።

- ከአዲስ አበባ ለፈተና ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የገቡ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻቸው ተቧድነው ጸብ ፈጥረው ነበር። በዚህም በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

- በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ እና ልደታ ካምፓሶች የቡድን ጸብ ነበር ከሁሉም የከፋ የነበረው በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ነው። በዚህ ግቢ ተማሪዎች በቡድን ሆነው ተማሪዎችን ከማስፈራራት እና ከመስረቅ ባሻገር የተማሪዎችን የመኝታ ቤት በር እና መስታወት እንዲሁም የተማሪ ሎከር ሰብረዋል።

- በአዲስ አበባ ከነበሩ ተቋማት 87 ተማሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። 49 ያህሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ካምፓስ ከተፈጸመው ድርጊት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው።

- በአንጻራዊነት ሲታይ ከባለፈው ዓመት አንጻር ሲታይ የፈተና አሰጣጡ ስኬታማ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነገ መግለጫ ሰጥተዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? - ፈተናው ከኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል። - ፈተናውን ለመፈተን በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ ከነዚህም ውስጥ 840 ሺህ 859 ፈተናውን…
#ጎንደር

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለፈተና የገቡ 16 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትላንት ሰዓት እና የዛሬውን ፈተና እንዳልወሰዱ የትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

ሚኒስቴሩ ፤ በማራኪ ፣ ቴዎድሮስ ፣ ፋሲል ግቢ ለፈተና የገቡ ተማሪዎች በአካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ፈተናቸውን ሳይወስዱ እንደቀሩ አመልክቷል።

በዕለቱ በነበረ የተኩስ ልውውጥም 1 ፈታኝ / የፈተና አስፈፃሚ እና 2 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሲገደሉ ፤ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ደግሞ ቆስሏል።

በአጠቃላይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ፈተናቸውን መፈተን ያልቻሉ 16 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ በሚመቻችላቸው መርሐ ግብር ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ጎንደር ካጋጠመው ችግር ውጭ በሌሎች የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉም ፈተና ተሰጥቶ መጠናቀቁን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በትግራይ ክልል በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አጠናቀው በተፈጠረው ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች የማጠናከሪያ እና የማካካሻ ትምህርት ከተሰጣቸው በኃላ ከመስከረም 29 - ጥቅምት 2 ቀን 2016 ድረስ ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

በትግራይ ለተማሪዎች የማካካሻ እና ማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጠው በክልሉ  ውስጥ በሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች ነው።

የራያ እና የኣክሱም ዩኒቨርሲቲዎች የማካካሻ እና የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጧቸውን ተማሪዎች ባለፉት ቀናት የተቀበሉ ሲሆን ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ እና ነገ ይቀበላል።

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የሚቀበልበትን ቀን በቅርብ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ፎቶ፦ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነገ መግለጫ ሰጥተዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? - ፈተናው ከኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል። - ፈተናውን ለመፈተን በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ ከነዚህም ውስጥ 840 ሺህ 859 ፈተናውን…
#Update

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንድ መምህሩ ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አስፈታኝነት ተመድበው ባቀኑበት #ጎንደር ህይወታቸው ማለፉን ይፋ አድርጓል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት መምህር የነበሩት ታደሰ አበበ ገብረሀና (ረ/ፕ/ር) ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፈታኝነት ተመድበው በሔዱበት ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ/ም ህይወታቸው ማለፉን ተቋሙ አመልክቷል።

በ38 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት መምህር ታደሰ አበበ፤ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 2009 - 2013 ዓ.ም በእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነ-ጽሁፍ ትምህርት ክፍል በመምህርነትና በኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን ከየካቲት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ምክትል ዲን በመሆን እያገለገሉ ነበር፡፡

መምህር ታደሰ አበበ ባለትዳርና የ3 ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ። የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት 23ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር። በዚህም ስብሰባ ፤ " የሕዝብን ሠላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ " በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ መመምከሩ ተነግሯል። ምክር ቤቱ ፤ " በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን…
#State_of_Emergency

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ " አማራ ክልል " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

አመሻሹን ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና ተከለከሉ ተግባራት ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።

በዚህም ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬከተር ጄነራል የሚመራ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ መቋቋሙ ተገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ አባላት፣ መዋቅር እና አደረጃጀት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።

የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ጠቅላይ ዕዙ ተጠሪነት ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆንም ተገልጿል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎችና የተከለከሉ ተግባራት ምንድናቸው ?

- ማንኛውም ሰው በአዋጁ መሰረት የሚወጡ መመሪያዎችን፣ የሚሰጡ ትዕዛዞች እና የሚተላለፉ ውሳኔዎችን የመተግበር እና የማከበር ግዴታ አለበት ተብሏል።

- የአስቸኳይ ጊዜ ጠ/መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላማ #የሚቃረን#የሚቃወም እና በክልሉ የአመጽ እንቅስቃሴን የሚያበረታታ ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር፣ እንዲሁም የፀጥታ መደፍረሱን የሚያባብስ ንግግር፣ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ቅስቀሳ በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጭት የተከለከለ መሆኑ ተመላክቷል።

- በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ለታጣቂ ቡድኖች የገንዝብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

- ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንዲሁ ተከልክሏል።

- ከአስቸኳይ ጊዜ ጠ/መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተመላክቷል።

(ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#State_of_Emergency ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ " አማራ ክልል " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል። አመሻሹን ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና ተከለከሉ ተግባራት ዝርዝር ይፋ ተደርጓል። በዚህም ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬከተር ጄነራል የሚመራ…
" እንደአስፈላጊነቱ #በየትኛዉም የሃገሪቱ አካባቢ ተፈፃሚነት ይኖረዋል " - የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዋነኝነት በ " አማራ ክልል " ተፈፃሚ ቢሆንም እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ላይ ተፈፃሚ ይሆናል ተብሏል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 / 2015 በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስተዳደር እንዲሁም በክልሉ አስተዳደር የሕዝብን ሠላም እና ፀጥታ ለማስከበር የሚወሰድ እርምጃን ፣ በክልሉ ወይም በሃገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የፀጥታ ችግር የሚያባብስ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ወይም ሁኔታን በሚመለከት እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛዉም የሃገሪቱ አካባቢ ተፈፃሚነት እንደሚኖረው ተገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ ለስድስት (6) ወራት የፀና እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን የስድስት (6) ወር ጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዋጁ ተፈፀሚነት ቀሪ የሚሆንበትን ጊዜ ሊወስን ይችላል ተብሏል።

https://yangx.top/tikvahethiopia/80310?single

@tikvahethiopia
#Amhara

ዛሬ አርብ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በፋኖ የታጠቁ ኃይሎች መካከል ግጭቶች ሲደረጉ መዋሉን እንዲሁም በተለያዩ ከተሞች ውጥረት መኖሩን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ዛሬ ጥዋት ጎንደር ላይ ተኩስ እንደነበር ፤ ፍኖተ ሰላምና ጅጋ ላይ ከፍ ያለ ግጭት እንደነበር ፤ በተለያዩ ቦታዎች ላይም የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር፣ ተመላክቷል።

በብዙ ቦታዎች አሁንም ችግሮች እንዳሉ ነዋሪዎች አመልክተዋል።

ደብረታቦር፣ ወልድያ እንዲሁም ቆቦ ላይ መረጋጋት ያለ ቢሆንም አሁንም ውጥረት እንዳለ ተገልጿል።

በክልሉ መዲና ' ባህር ዳር ' ላይ የተሻለ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደነበር ፤ ገበያዎችም ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ያመለከተው የሬድዮ ጣቢያው ዘገባ ከባህር ዳር ከተማ ወደ ሌሎች ከተሞች ወይም ከሌሎች ከተሞች ወደ ባህር ዳር የሚያስገቡት መንገዶች በመዘጋታቸው እንቅስቃሴ የለም ብሏል።

ዛሬ ፈተናቸውን የጨረሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሄድ መንገድ በማጣታቸው በጣም መቸገራቸው ተገልጿል። ተማሪዎቹ ስልክ ስላልያዙ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት የተቸገሩ ሲሆን በቅርብ ቤተሰብ ያላቸው አንዳንድ ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸው ስማቸውን እያስጠሩ እየወሰዷቸው እንደነበር ተነግሯል።

ዩኒቨርሲቲው የመኝታም ሆነ የምግብ አቅርቦት እነድማያቋርጥ ለተማሪዎቹ አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ በዛው በባህር ዳር ከተማ ሁለት ቦታ ቦምብ መፈንዳቱ የተነገረ ሲሆን ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ አልወጣም ሲል ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው የሰጡ ነዋሪዎች የተለያየ አመለካከት ያላቸው ሲሆን አንዳንዶቹ " ችግሩን የሚያባብስ ውሳኔ ነው " የሚል አቋም አላቸው ፤ ሌሎች በበኩላቸው ውሳኔው " ችግሩን ሊቀንሰው ይችላል "  ሲሉ ገልጸዋል። ከዚህ ባለፈ ግን በርካታ አስተያየት ሰጪዎች አዋጁን ከማወጅ ይልቅ የክልሉ መንግሥት እና ፌዴራል መንግሥት መሳሪያ ታጥቀው ከሚዋጉ ኃይሎች ጋር ችግሩን በንግግር እና በድርድር መፍታት አለባቸው የሚል አቋም እንዳላቸው ለሬድዮ ጣቢያው አጋርተዋል።

በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች የኢንተርኔት ግኙነት እንደተቋረጠ ነው።

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዛሬ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ መምከራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ውይይቱ የነበረው በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ዙሪያ እንደነበር ተገልጿል።

አንቶኒ ብሊንከን ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል እና በጎራባቹ አፋር እና አማራ ክልሎች ያለውን ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ወደ ነበረበት ለመመለስ እየሰራ ያለውን ጥረት እውቅና መስጠታቸው ተመላክቷል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ የውጭ ኃይሎችን ከትግራይ ምድር ማስወጣትና አብሮም የትግራይ ኃይሎችን ትጥቅ ማስፈታት የሚለው ጨምሮ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት በአስቸኳይ ተግባራዊ ማድረግን እንዳሰመሩበት ተሰምቷል።

ብሊንከን ፤ ሀገራቸው አሜሪካ የአፍሪካ ህብረት የስምምነት አፈፃፀም የክትትል እና ማረጋገጫ ዘዴን ጨምሮ በአጠቃላይ ህብረቱ የሚመራውን ሂደት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በደቡብ አፍሪካ ፤ ' ፕሪቶሪያ ' በዘላቂነት ግጭት እንዲቆም የተፈረመው ስምምነትን ለማስፈፀም በኬንያ ኖይሮቢ በተፈረመው ስነድ ፤ የትግራይ ኃይሎች የከባድ መሳሪያ ትጥቅ አፈታት የውጭ ኃይሎችና ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ኃይሎች ከክልሉ መውጣት ጋር በአንድ ግዜ እንደሚፈፀም ይገልጻል።

@tikvahethiopia