#ጋምቤላ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የጋምቤላ ክልል አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩ የትጥቅ ግጭቶችን፣ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃቶችንና አጠቃላይ የጸጥታ ችግሮችን እና በዚህ ሳቢያ የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ተጎጂዎችን፤ የአካባቢዎቹን ነዋሪዎች እንዲሁም የክልሉን የጸጥታ እና የአስተዳደር ኃላፊዎችን በማነጋገር ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በላከልን መግለጫ አሳውቋል።
በተለይ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ላለው የጸጥታ ችግር መነሻ፣ በኢታንግ ልዩ ወረዳ በተወሰነ ነዋሪዎች መካከል የተነሳ አለመግባባት መሆነ ማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ይሄው አለመግባባት በፍጥነት ወደ ብሔርን መሠረት ያደረገ ውጥረት እንደተሸጋገረ ነዋሪዎች ያስረዳሉ።
ይህንኑም ተከትሎ የተለያየ ብሔር ታጠቂ ቡድኖች በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ጎግ ወረዳ፤ በጋምቤላ ከተማ ብሔር ብሔረሰቦች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እና በከተማው በሚገኙ ሌሎች ሰፈሮች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በርካታ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀል እና ንብረት ውድመት ደርሷል።
ኢሰኮ በጸጥታው ችግር ምክንያት ገና ወደ አካባቢዎቹ በአካል ደርሶ ምርመራ ለማድረግ ያልቻለ ቢሆንም፣ ነዋሪዎች በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ መንደሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የወደሙ መሆናቸውን አስረድተዌ።
ጋምቤላ ክልል በተደጋጋሚ ከጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን በሚመጡ ታጣቂ ቡድኖች በሚደርሱ ጥቃቶች፣ እንዲሁም አልፎ አልፎ በክልሉ በሚኖሩ ብሔሮች መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስ መሆኑ እንደሚታወቅ ኢሰመኮ በመግለጫው አመልክቷል።
ክልሉ ወደ 350 ሺህ የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን በስምንት የተለያዩ ካምፖች ያስተናግዳል።
ከሁለት ወራት በላይ ለዘለቀው የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ችግር እና በክልሉ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በመድረስ ላይ ያሉ ግጭቶች ተሳታፊዎችን በተመለከተ ተጎጂዎችም ሆነ የክልሉ የጸጥታ እና የአስተዳደር ኃላፊዎች የተለያዩ ብሔር ታጣቂ ቡድኖችን ኃላፊነት ይጠቅሳሉ።
በአንዳንድ አካባቢዎች የክልሉ ኑዌር ብሔረሰብ ታጣቂዎች፣ በሌላ አካባቢ የአኝዋ ብሔረሰብ ታጣቂዎች፣ እንዲሁም ከጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች እና በአንዳንድ የስደተኛ ካምፖች ውስጥ አንደሚኖሩ የተገለጸ ሰዎች ጭምር በግጭቶቹ ተሳታፊ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡
እነዚህ ጥቃቶች እና ግጭቶች በአብዛኛው ብሔር ተኮር ሲሆኑ በሌላ በኩል ግጭት የሚደርስባቸውን አካባቢዎች ያለ የብሔር ልዩነት ሁሉንም ነዋሪዎች አካባቢውን ሸሽቶ ለመፈናቀል፣ ለንብረት ውድመት እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ያጋለጠ ነው ሲል ኢሰመኮ አመልክቷል።
የክልሉ ጸጥታ ሁኔታ በነዋሪዎች ላይ ያደረሰው ከፍተኛ ጉዳት እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰትም የመንግሥትን ተጨማሪ ትኩረት የሚሻ መሆኑን አስገንዝቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#ሀዋሳ
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀምሌ 19 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ክብረ ንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።
ለበዓሉ ሰላማዊነት ከመምሪያውና 8ቱም ክ/ከተማ ፖሊስ ማናጀመት ፣ከ8ቱም ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች፣ ለፀጥታው አጋዥ ከሆኑ ሀይሎች ፣ ከሀይማኖት አባቶች ፣ ከሁቴል ባለቤቶች ፣ከየክፍለ ከተማ የተደራጅ ማህበራት ጋር ውይይት ተደርጓል።
ፖሊስ ከፀጥታ ኃይሉ እና ከአጋዥ ኃይሎች በተጨማሪ በከተማው በተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎች የፀጥታውን ስራ አስተማማኝ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጾ የደህንነት ካሜራዎች ተደራሽ ባልደረገባቸው ቦታዎችን ካሜራ የመግጠም ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል።
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም የበዓሉ ታዳሚያን በጠቅላላ አከባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁና የወንጀል ድርጊትም ሲመለከቱ ለፖሊስ እንዲጠቁሙ መልዕክት ተላልፏል።
በተመሳሳይ የሲዳማ ክልል የፀጥታ ግብረሃይል ፤ በዓሉ በሰላም እንዲከበር በቅ የፀጥታ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ መገባቱን እና ለፀጥታ ኃይሉ ስምሪት መሰጠቱን አሳውቋል።
ከበዓሉ ጋር በተያያዘ የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ እንዳይከሰት
ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችንም ይፋ አድርጓል።
በዚህ መነሻ ከሐምሌ 18/04/2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ፦
1. ከሎጊታ - ሱሙዳ ገብርኤል
2. ከማር ስል ቤተክርስቲያን - ሱሙዳ ገብርኤል
3. ከዋርካ አደባባይ - ሱሙዳ ገብርኤል
4. ከዳሽን- ሱሙዳ ድረስ ያሉ መንገዶች በዓሉ ተከብረው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ ይሆናሉ።
አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።
ህብረተሰቡ ማንኛውን ጥቆማ ካለው በ0462209164 እና 046 212 2468 ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም በ0462201046 ለሀዋሳ ፖሊስ መምሪያ ጥቆማ መስጠት ይችላል።
ሀዋሳ የሚከበረው የሀምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ላይ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር እጅግ በርካታ እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#ቁልቢ
ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር ወደ ስፍራው የሚመጡ ምዕመናንና እንግዶችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅት ማድረጉን ፖሊስ አሳውቋል።
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ እና የበዓሉ የጸጥታ ኮማንድ በመጪው ረቡዕ በሚከበረው ዓመታዊ የቁልቢ ንግስ በዓል ላይ ከተለያየ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ብዛት ያላቸው ምዕመናን፣ ቱሪስቶችና ሌሎችም እንግዶች ወደ ስፍራው እንደሚመጡ ይጠበቃል ብለዋል።
የምዕመናኑን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅም ከምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፣ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ ከሐረሪ ክልል እና ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከመከላከያ ሠራዊት፣ ብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ጋር በመቀናጀት ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።
የበዓሉ ታዳሚዎች የግል ንብረቶቻቸውን እንዳይሰረቅ በጥንቃቄ በመያዝና የወንጀል ድርጊት ሲመለከቱ በማጋለጥ የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ተብሏል።
በንግስ በዓሉ ላይ ሶስት ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያና ተጠርጣሪ ወንጀለኞችም ሲያዙ ውሳኔ ለመሰጠት ዐቃቤ ህግና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ተቋቁሟል።
ወደ ስፍራው በሚያመራው መንገድ አልፎ አልፎ ያለው አካባቢ የመሬቱ አቀማመጥ ዳገታማ፣ ቁልቁለታማና ጠመዝማዛ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግና ደንብ በማክበር አደጋን ለመከላከል የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል።
ከዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ባለው ዋናው የተሸከርካሪ መንገድ ላይ #ከባድ_መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑንም ተገልጿል።
ምዕመናን ወደ ንግስ ስፍራው በሚመጡበት ወቅት ተገቢነት የሌላቸው አርማና ምልክቶችን ይዘው መገኘት እንደሌለባቸውም ፖሊስ አሳስቧል። #ኢዜአ

TIKVAH-ETHIOPIA
#ቁልቢ ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር ወደ ስፍራው የሚመጡ ምዕመናንና እንግዶችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅት ማድረጉን ፖሊስ አሳውቋል። የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ እና የበዓሉ የጸጥታ ኮማንድ በመጪው ረቡዕ በሚከበረው ዓመታዊ የቁልቢ ንግስ በዓል ላይ ከተለያየ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ብዛት ያላቸው ምዕመናን፣ ቱሪስቶችና ሌሎችም እንግዶች ወደ ስፍራው እንደሚመጡ ይጠበቃል…
#እንድታውቁት
ከቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል ጋር በተያያዘ ከዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ባለው ዋናው የተሸከርካሪ መንገድ ላይ #ከባድ_መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ እና የበዓሉ የጸጥታ ኮማንድ አሳውቋል።

#COOP
ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ከታች ከተዘረዘሩት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ @coopbankoromia ቅርንጫፎች ወደ አንዱ ሲሄዱ የቀበሌ መታወቂያ፣ የመስሪያ ቤት መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ እርስዎን መግለፅ የሚችል መታወቂያ መያዝ ይጠበቅብዎታል።
ለምዝገባው ምንም አይነት ክፍያ አይፈፀምም፦
1. ፊንፊኔ ቅርንጫፍ📍አፍሪካ ጎዳና፣ ፍላሚንጎ አካባቢ
2. ቀርሳ ቅርንጫፍ📍ሜክሲኮ ስኩል ኦፍ ኮሜርስ ጀርባ
3. ኃይሌ ገብሬ ቅርንጫፍ📍 ቃሊቲ ማሰልጠኛ
4. ጀሞ ቅርንጫፍ📍ጀሞ አንድ
5. መደሮ ቅርንጫፍ📍መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል ፊትለፊት
6. አየር ጤና ቅርንጫፍ📍አየር ጤና
7. ኦዳ ቅርንጫፍ 📍ባምቢስ ሱፐርማርኬት ከመስቀል አደባባይ ወደ ኡራኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
8. መጫና ቱለማ ቅርንጫፍ 📍ልደታ አልሳም ሪል እስቴት ህንፃ ላይ

#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ሕገወጥ " እንደሆነ ገልጻ እንዲቆም ያሳሰበችው የትግራይ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተፈፀመ። " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " ዛሬ ሃምሌ 15 / 2015 ዓ.ም በአክሱም ከተማ የኤጲስ ቆጶሳት በአለ ሲመት አከናውኗል። በዚህም ፦ 1. ንቡረ ዕድ መሓሪ - አቡነ ሊባኖስ 2. ቆሞስ…
#Update
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ መግለጫው ምን አለ ?
በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. የተከናወነው ሕገወጥ ሢመተ የኤጲስ ቆጶሳት መፈጸሙ በእጅጉ እንዳሳዘነው ገልጿል።
የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰንም ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ አስተላልፏል።
የስብሰባው ቀን ሊራዘም የቻለው በውጭው ክፍለ ዓለማት ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት መገኘት ስላለባቸው የጉዞ ቀኑ እንዳያጥር እና በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ለአገልግሎት ወደ አህጉረ ስብከታቸው የሄዱ በመሆኑ ለመመለሻ የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ መሆኑን አመልክቷል።
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ክፍለ ዓለማት የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ተጠቃለው ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እዲመጡ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ታያይዟል)

Photo
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ተቋማት ገቡ።
የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ትላንት እንዲሁም ዛሬ ወደተመደቡበት የመፈተኛ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተዋል።
በነገው ዕለት ገለፃ ይደረግላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ከረቡዕ ሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 21 ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ከቀጣይ ቀናት ጀምሮ ወደየቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ።
ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ በኦንላይን ተመዝግበዋል ከተባሉ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች መካከል 503,812 የሚሆኑት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።

#NewsAlert በጋምቤላ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ቦታዎች እንዲሰጥ ተወሰነ። በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ እና በጋምቤላ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደሚሰጥ የክልሉ መንግስት አስታውቋል። የክልሉ መንግሥት ፤ " በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ብቻ ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው…
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓትን ሳያከናውን ቀርቷል።
በክልሉ ባለ የፀጥታ ችግር ምክንያት የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ በዓል መሰረዙን ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።
የምረቃ በዓሉን ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም ለማድረግ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በክልሉ በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የምረቃ ፕሮግራሙ መሰረዙን የተቋሙ ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ተናግረዋል።
"ተማሪዎቻችንን ለማስመረቅ ተዘጋጅተን ነበር፤ ይሁን እንጂ ባለው የፀጥታ ሁኔታ የምረቃ በዓሉን ማከናወኑ ትርጉም አይኖረውም" ብለዋል ኃላፊው።
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ እና አንድ መምህር ባለፈው ሳምንት ህይወታቸው ማለፉን ዩኒቨርሲው ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡
ከ650 በላይ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ትምህርታቸውን በ2015 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማጠናቀቃቸው ተገልጿል። ተመራቂዎቹ አሁን ላይ ጊዚያዊ ዲግሪ (Temporary) እየተሰጣቸው ነው።
በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው የተመደቡለትን ከ6 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ከትላንት ጀምሮ እየተቀበለ ይገኛል።
@tikvahuniversity

" ሱተን ዙሪያ ቀበሌ ድረስ ተከታትለው በመምጣት ነው የገደሉት ፤ ... ይሄን ለማን አቤት ልበል ? " - ወላጅ አባት
በኦሮሚያ ክልል፤ ደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን የትራፊክ ፖሊስ አባላት የጠየቁትን ያህል ጉቦ አልሰጥም ያለን አንድ አሽከርካሪ በጥይት ደብድበው መግደላቸውን የሟች ቤተሰቦችና የሥራ ባልደረቦች መግለፃቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
ድርጊቱ የተፈፀመው ባለፈው ዓርብ ዕለት ሲሆን በትራፊክ ፖሊስ አባላቱ በጥይት የተገደለው እና ትላንት ስርዓተ ቀብሩ ተፈፀመ የተባለው የ33 ዓመት እድሜ ያለው ሳሙኤል መረተ ነው።
ሳሙኤል መረት ነዋሪነቱ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ውስጥ ነበር፡፡
ጓደኞቹ እንዳሉት ሳሙኤል ከረጅም ጊዜ አንስተቶ የአሽከርካሪነት ሥራውን ሲያከናውን የቆየው ከአዲስ አበባ ቡታጅራ በተዘረጋው መስመር ላይ ነበር።
በመስመሩ በሰበብ አስባቡ ካልቀጣንህ የሚሉትን የትራፊክ ፖሊስ አባላት ለማባበል ዝርዝር የ " ሃምሳ ብር " ኖቶችን በእጃቸው እያስጨበጠ ማለፍ የሁልጊዜ ተግባሩ እንደነበር ጓደኞቹ ይናገራሉ።
ይህ የሃምሳ ብር ጣጣ ታዲያ " አንሷል ጨምር አልጨምርም " በሚል ከትራፊክ ፖሊስ አባላት ጋር የገባበት እሰጥ አገባ ለህይወቱ መጥፋት ምክንያት መሆኑን ነው በሥፍራው ነበርን ያሉ ገልጸዋል።
የሳሙኤል ረዳት ምን አለ ?
የሳሙኤል መረተ ረዳት ሆኜ ሥሠራ ነበር የሚለው አንዱዓለም ሁሴን ፦
" መንገደኞችን አሳፍረን ከአዲስ አበባ ቡታጅራ በመጓዝ ላይ እያለን በኦሮሚያ ክልል ፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ተሬ ወረዳ ላይ ስንደርስ ሦስት ትራፊኮች ያስቆሙናል።
ሳሙኤል የመውጫ ወረቀት እና ሃምሳ ብር ሲሰጥ ከትራፊኮቹ አንዱ ሀምሳውን ቀይረህ መቶ አድርግ ሲለው ሰምቻለሁ።
ሳሙኤል አሁን የለኝም አልተዘጋጀሁም ሲለው ትራፊኩ አለበለዚያ የተሸከርካሪውን ሠሌዳ እፈታለሁ በማለት በቦክስ መታው፡፡
ይሄኔ በንዴት ተሽከርካሪውን አስነስተን ወደፊት መሄድ ስንጀምር ተከትለው መተኮስ ጀመሩ፡፡
ጥቂት እንደተጓዝን ተሸከርካሪውን በማቆም እኔም ሆንኩ ሌሎች መንገደኞች ደንግጠን ወረደን መሮጥ ጀመርን፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እሱን በጥይት መትተው ጣሉት " ሲል ቃሉን ሰጥቷል።
የሟች ሳሙኤል አባት አቶ መረተ ለማ በበኩላቸው ፤ ከትራፊክ ፖሊስ አባላቱ ጋር አለመግባባቱ የተነሳው በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ተሬ ወረዳ ላይ ቢሆንም ግድያው የተፈጸመው ግን በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ሱተን ዙሪያ ቀበሌ ድረስ ተከታትለው በመምጣት አንደሆነ ገልጸዋል።
" ይህን ለማን አቤት ልበል ? " ሲሉም ጠይቀዋል ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን የተሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ፈይሳ ደበላን ጉዳዩን በተመለከተ ከሬድዮ ጣቢያው ተጠይቀው ፤ ወንጀሉ የተፈጸመው እሳቸው ከሚመሩበት የተሬ ወረዳ አልፎ ጉራጌ ዞን ውስጥ መሆኑን በመጥቀስ " በዚህ ላይ እኔ የምለው ነገር የለም ፤ ባይሆን የደቡብ ክልል ፖሊስን ጠይቁ " ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ፤ የወንጀሉ አድራሾች በኦሮሚያ ክልል ፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኙ የትራፊክ ፖሊስ አባላት ናቸው ብለዋል።
አሁን ላይ ድርጊቱን በመፈጸም የተጠረጠሩ ሦስት የትራፊክ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል።
" የተከሰተው ነገር አሳዛኝ ነው " ያሉት ኮማንደር ጠጄ " የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች ወዲያው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ጥሩ ነገር ነው፡፡ አሁን ምርመራውን ከኦሮሚያ ክልል የሥራ ሃላፊዎች ጋር አብረን እየሠራን እንገኛለን ፡፡ ወንጀሉ የተፈጸመው በጉራጌ ዞን ውስጥ በመሆኑ ምርመራውን ወደ ዞኑ ለማዛወር በሂደት ላይ ነው ያለነው " ብለዋል፡፡
#ዶቼቨለ