TIKVAH-ETHIOPIA
#ጋምቤላ 10 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ቅዳሜ ዕለት ከደቡብ ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን የገቡ የ " ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች " 10 ሰዎችን ገድለው 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውን ከጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል። ታጣቂዎቹ ቅዳሜ ምሽት 3 ሰዓት ተኩል ገደማ ድንበር ጥሰው በመግባት…
#Update
ምዕመናን ለተጎጂዎች ድጋፍ በማድረግ እንዲደርሱላቸው፤ በምልጃና በፀሎትም እንዲያስቧቸው ጥሪ ቀረበ።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በምዕራብ ጋምቤላ ቤቴል ሲኖዶስ አገልግሎት ክልል ውስጥ በሚገኘው " ማታራ " ቀበሌ፣ በሲኖዶሱ የሴቶች አገልግሎት በተዘጋጀ እና ከስድስት ፕርስፒቴሪ የመጡ ወጣት ሴቶች፣ እናቶችና ልጆቻቸው በተገኙበት መንፈሳዊ ኮንፍራስ ላይ ከደቡብ ሱዳን ዘልቀው በገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በብዙዎች ላይ የሞትና ከባድ የመቁሰል አደጋ መድረሱን በመግለፅ ሀዘኗን ገልጻለች።
ቤተክርስቲያኗ ፤ ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ግንቦት 12፣ 2015 ዓ.ም 11 ሰዓት አከባቢ መሆኑን አስታውሳ ፤ የኮንፍረንሱ ተካፈይ የሆኑ ከ2,700 በላይ የሚሆኑ ሴቶች፣ እናቶችና ልጆቻቸው የቀኑን መርሀ ግብር አጠናቀው ለእራት በተቀመጡበት ወቅት ታጣቂዎቹ ልጆቻቸውን በጉልበት አፍነው ሊወስዱ ሲሞክሩ እናቶች በመከላከላቸው በከፈቱባቸው ተኩስ የተነሳ የሰው ህይወት መጥፋቱና ጉዳት መድረሱን አስረድታለች።
ከደረሰውም አሰቃቂ ጥቃት የተነሳ ማጣራቱ እስከተጠናቀቀበት ሰዓት ድረስ የሟች ምዕመናን ቁጥር 9 የደረሰ ሲሆን ከነዚያም ውስጥ የስድስት አመት ህፃን የሆነችው " ንያካካ ዊዩአል ኒኜት " እና አንዲት የምታጠባ እናት ይገኙበታል።
በተጨማሪም በጥቃቱ ቆስለው በጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በህክምና እየተረዱ ያሉ በርካታ እናቶች ሲኖሩ ከነዚህም ውስጥ የሁለቱ ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ ተገልጿል።
ቤተክርስትያኗ ፤ ለተጎጂች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንዲደርሱላቸው በምልጃ ጸሎትም እንዲያስቧቸው ለምዕመናን ጥሪ አቅርባለች።
ጥቃቱ የደረሰበት ይህ አከባቢ የልጆች አፈናና የከብት ዝርፊያ በተደጋጋሚ የሚከሰትበት እንደመሆኑ በመንግሥትና በሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት እየተደረገ ያለው ክትትልና ትኩረት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን አስተላልፋለች።
ከቀናት በፊት የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዶች ድንበር ጥሰው በመግባት በማኩዌይ ወረዳ ቢልኬች ቀበሌ እንዲሁም በዋንቱዋ ወረዳ መተሀር ከተማ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በፈፀሙት ጥቃት በአጠቃላይ 10 ሰዎችን ገድለው ፤ 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውን ማሳወቁ ይታወሳል።
ማስታወሻ ፦ https://yangx.top/tikvahethiopia/78609?single
@tikvahethiopia

Photo
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል !
ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች።
ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው።
በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ።
ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ተቀባይንት ያገኘ ሲሆን፣ ማሻሻያ እንዲደረግበት ለፓርላማው ተመልሶ ቀርቦ ነበር።
ቀደም ሲል ቀርቦ በነበረው ረቂቅ ሕግ ላይ ማንኛውም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም ከዚሁ ጋር በተያያዘው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ የሚያደርግ ነበር።
ሆኖም ግን ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ይህ ሰዎች እንዲታሰሩ እና በአካላዊ ገጽታቸው ብቻ እንዲከሰሱ ያደርጋል ሲሉ ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ረቂቅ ሕጉ እንዲሻሻል ወደ ፓርላማ መልሰውት ነበር።
በዚህ መሠረት ተሻሽሎ አሁን ላይ የቀረበው ረቂቅ ሕግ፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ወንጀልነት ወንድ ከወንድ ጋር በሚያደርገው ወሲባዊ ድርጊቶች ላይ የተወሰነ ሆኗል።
ይህንን ሕግ ተላልፈው የተገኙም እስከ እድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል።
ለከባድ ወንጀሎች ማለትም ወሲባዊ ጥቃቱ #በሕጻናት_ላይ ፣ በአካል ጉዳተኛ እንዲሁም ተጋላጭ በሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ በሚፈፀምበት ጊዜ አሊያም የጥቃት ሰለባዎቹ ለዕድሜ ልክ ህመም የሚዳረጉ ከሆነ በድርጊቱ ፈፃሚ ላይ #የሞት ቅጣትን ይደነግጋል።
ማኅበረሰቡ #በሕጻናት ወይም በሌሎች ተጋላጭ በሆኑ የሕብረተሰቡ አባላት ላይ ማንኛውንም ዓይነት የተመሳሳይ ጾታ ጥቃት በሚያዩ አልያም በሚሰሙበት ጊዜ ለባለሥልጣናት ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ቢቢሲ ዘግቧል።
በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ቀድሞም ሕገ ወጥ ተደርጎ ነው የቆየው ፤ ይህ ሕግ ከሕገ ወጥነቱ አልፎ ነገሩን ወንጀልና በተራዘመ እስር የሚያስቀጣ ያደርገዋል።
#ምዕራባውያን ሀገራትና #ተቋማት በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጉዳይ በዩጋንዳ ፓርላማ የተላለፈውን ውሳኔ ሲቃወሙና ፕሬዜዳንቱ #እንዳይፈርሙ ሲያሳስቡ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

#አቢሲንያ_ባንክ
ገንዘብ ገቢ ለማድረግ ባንክ ሊዘጋብኝ ነው ብለው አይቻኮሉ፡፡ በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛውም ቀን የኢንዱስትሪው ቀዳሚ በሆኑት፣ 24 ሰዓት በማያንቀላፉት የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን ገንዘብዎን ተቀማጭ ያድርጉ፡፡
#BankofAbyssinia #remittance #Banking #BankingService #Digital #DigitalEthiopia #DigitalPayment #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

ፀጋ በላቸው የት ናት ?
ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ፤ ነዋሪነቷ በሀዋሳ ከተማ የሆነች የዳሽን ባንክ (ዋርካ አካባቢ) ሰራተኛ እንዲሁም የአላሙራ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነች ፀጋ በላቸው የተባለች ግለሰብ በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ታፍና መወሰዷና የት እንዳለች ማወቅ እንዳልተቻለ በስፋት እየተነገረ ይገኛል።
ድርጊቱ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ/ም መፈፀሙ የተነገረ ሲሆን ድርጊቱን የፈፀመው በወቅቱ የከተማው ከንቲባ የግል ጠባቂ የሆነው " ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም " መሆኑ ቤተሰቦቿም ጉዳዩን ለህግ ቢያሳውቁም የፍርድ ቤት መጥሪም ወጥቶ ግለሰቡ በህግ ስር እንዲውል ጥረት ቢደረግም እስካሁን የተለየ ነገር እንደሌለ ገልጸዋል።
ስለ ጉዳዩ ቤተሰቦቿ ምን ይላሉ ?
አንድ የቅርብ ቤተሰብ እንደሆኑ የገለፁ የፀጋ በላቸው ቤተሰብ " ክርስቲያን ቱዩብ " ለተሰኘ የማህበራዊ መገናኛ መረብ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
" ግንቦት 15 ነው ከስራ ስትወጣ በመኪና አግቶ የወሰዳት ፤ ከዛ በኃላ አከራይዋ ደውለውን ነው ቤት አለማደሯን ስንሰማ በነጋታው ስራ ቦታ /ዳሽን ባንክ ዋርካ ብራንች ሴቶች ብቻ የሚሰሩበት/ ስንጠያይቅ አብራት የምትሰራ የስራ ባልደረባ አለች በእሷ በኩል ነው መወሰዷን ያወቅነው።
ከዛ በኃላ ለሴቶች እና ህፃናት ፣ለከተማው ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለሲዳማ ክልልም ለደቡብም ጭምር አመለከትን መጥሪያ ወሰድን ፤ ማን እንደሆነ ሲያውቁ ሂዱና እናተ ስጡት አሉ፤ / አስቡት ለከንቲባ ጋርድ አንገታችሁን ቆርጣለሁ እያለ ለሚዝትብን ሰው እኛ ሄደን መጥሪያ እንድንሰጥ / ከዛ በስንት ልመና ተኬደ ተፈለገ የለም።
ልጁ የሃገረሰላም ልጅ ነው፤ ሀገረሰላም ሲገባ ሽጉጥ ተተኩሶ የጀግና አቀባበል ነው የተደረገለት ፤ እሷን ይዞ ሲገባ፤ እዛ እንደደረሰ በስልክ GPS ተፈልጎ ተኬደ ሲኬድ ጓደኞች ዘመዶች አሉት አስመልጠውታል፤ ከንቲባው ይሄን ያወቀበት ቀን ልጁን ከስራ እንዳባረረው ትጥቁን እንዲፈታ ፣ ባለበት እንዲያዝ ደብዳቤ ፅፎ ለፖሊስ ኮሚሽን ልኳል፤ ባለሃብቶችን ፣ የቸርች መሪዎችን ሰብሰበን ሽምግልና ሞክረን ነበር ከዚህ በላይ ምንም ማድረግ እንዳማይችልን ነው ያሳወቀን።
አሁን የት እንዳለ አይታወቅም፤ ከቴሌ መረጃዎችን የሚፈልገው ፖሊስ ከኛ ነው ፤ ማክሰኞ ነው የታገተችው። አሁን የልጅቷ ህይወት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነው ያለው።
እሷ እጮ ነበራት ልታገባ እየተዘጋጀች ነበር ፤ የጋብቻ ትምህርትም ተምራ ጨርሳለች እጮኛዋም ላይ ሲዝትበት ነበር። በሀዋሳ አላሙራ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን አገልጋይም ናት ፤ በጣም የተመሰገነች ፣ ጌታን የምትወድ ፣ ድምጿ የሚያምር የሚገርም የዝማሬ ፀጋ መንፈስ በሁሉም ዘንድ የምትወደድ ልጅ ነች።
የተደረገው ነገር ለእግዚአብሔርም መንግሥት ለቸርችም ትልቅ ስድብ ነው ። "
የፀጋ በላቸው ቤተሰቦች በአሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙና ልጃቸውን ማግኘት እንዳልቻሉ ለመስማት የቻልን ሲሆን ጉዳዩን በተመለከተ ከተማው አስተዳደር መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

የምርቶች ዋጋ ...
መንግስት በፍራንኮ ቫሉታ ከውጪ እንዲገቡ የፈቀዳቸው ምርቶች ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው #መጨመር አሣሣቢ ሆኗል ተባለ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ምርቶቹን በፍራንኮ ቫሉታ እንዲያስገቡ ከተፈቀደላቸው ነጋዴዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።
ዘይት ፣ ስኳር ፤ ሩዝና የህፃናት ወተት በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ የተፈቀዱ ምርቶች መሆናቸው ይታወሳል።
ምርቶቹ በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ በመፈቀዱ ባለፉት አስር ወራት ብቻ መንግስት በታክስ መልክ ማግኘት የነበረበትን ከ10 ቢሊየን ብር በላይ አጥቷል ተብሏል።
ነገር ግን የምርቶቹ ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው ሲጨምር እንደሚታይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ተናግረዋል።
ጭማሪው እየታየ ያለዉ በአለም ላይ ዋጋቸው #ቀንሶ ባለበት ወቅት ጭምር ነው ብለዋል።
ምርቶቹ ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ስርጭታቸውም ላይ ብዙ ግልፅነት እንደሌለ ተነግሯል።
እንደ ማሣያም ዘንድሮ በአስር ወራት ወደ ሀገር ውስጥ የገባው የምግብ ዘይት 97 ሚሊየን ሊትር እንደሆነ ተጠቅሷል። አምና በተመሣሣይ ጊዜ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ግን ከአንድ መቶ ሚሊየን ነበር ተብሏል።
እንዲያም ሆኖ በገበያው ላይ የምርት አቅርቦት ችግር የለም ተብሏል። ሁኔታው በስርጭቱ ላይ ችግር መኖሩን አመላካች እንደሆነ ተጠቅሷል።
አስመጪዎች በበኩላቸው በብርና ዶላር መካከል ያለው ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ መስፋት የምርቶቹ ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ማለታቸውን ከሬድዮ ጣቢያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፀጋ በላቸው የት ናት ? ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ፤ ነዋሪነቷ በሀዋሳ ከተማ የሆነች የዳሽን ባንክ (ዋርካ አካባቢ) ሰራተኛ እንዲሁም የአላሙራ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነች ፀጋ በላቸው የተባለች ግለሰብ በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ታፍና መወሰዷና የት እንዳለች ማወቅ እንዳልተቻለ በስፋት እየተነገረ ይገኛል። ድርጊቱ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ/ም መፈፀሙ የተነገረ ሲሆን ድርጊቱን…
ፖሊስ ስለ ወ/ሪት ፀጋ በላቸው ምን አለ ?
" ከጠለፋ ወንጀል ጋር የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር አውያለሁ " - የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ
የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በፀጋ በላቸው ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል።
ፖሊስ በመግለጫው " የከተማች ነዋሪ በሆነችው ወ/ሪት ፀጋ በላቸው ላይ የደረሰባት የጠለፋ ወንጀል ጉዳዩን አስመልክተው ቤተሰቦቿ በእለቱ ለመናኸሪያ ፖሊስ በመቅረብ አቤቱታቸውን አሰምተዋል " ብሏል።
ይህን ተከትሎ መምሪያው ተፈፀመ በተባለው ወንጀል መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።
የከተማው ፖሊስ ፤ የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ጭምር አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክቷል።
የተበዳይ ቤተሰብ በትዕግሥት እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርቧል።
የምርመራው ሂደት ምን ላይ ደርሷል ?
ፖሊስ እንዳለው ፤ የወንጀሉ ድርጊት የተፈፀመው በሀዋሳ ከተማ በመናኸሪያ ክ/ከተማ ሲሆን ወ/ሪት ፅጌ በላቸው የተባለች ግለሰብ በቀን 15/9/2015 ዓ.ም " ተጠልፋ የት እንደደረሰች አናውቅም " በማለት ቤተሰቦቿ ለመነኸሪያ ክ/ከተማ ፖሊስ ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ምርመራ ተጀምሯል ብሏል።
የምርመራው ሂደትም በቀጣይ በከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አማካይነት በቅንጅት ሊመራ መቻሉን አመልክቷል።
በኋላም የምርመራው እና ተበዳይን ለማግኘት እና ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክሉሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በቅንጅት የተመራ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
ከወ/ሪት ፅጌ በላቸው የጠለፋ ወንጀል ጋር የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ አሳውቋል።
" ጥቆማው ከተደረገበት እለት ጀምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸውና የፀጥታ አካላትና ፖሊስ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪው ሣጅን የኋላ መብራቴ እና የተጠለፈችውን ወ/ሪት ፅጌ በላቸው ይዞ ከተሰወረበት ቦታ አድኖ ለመያዝ ጥረትና ክትትል እየተደረገ ይገኛል " ሲል አሳውቋል።
ወ/ሪት ፀጋን ከነተጠርጣሪው ለመያዝ ህብረተሰቡ የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ በነዚህም የስልክ ቁጥሮች 0964504677 / 0969415272 ጥቆማ እንዲሰጥ የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።