ማዳበሪያ . . .
" ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬዎች ማዳበሪያ ሲጨምርም / ሲጠፋ መንግስትን ትኩረት እንዲያደርግ ልትጠይቁ ይገባል " - አብራራው
(በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል - አብራራው)
" ሰላም ለእናንተ ይሁን !!
አንድ አሳሳቢ ሀገራዊ ጉዳይ አለ ፤ ነገር ግን ማንም ትኩረት ሰጥቶት ሲሰራ አላየውም ፤ እናም የሚመለከተው አካል ተመልክቶ መፍትሄ እንዲሰጥበት ይህን ጥሪ አቀርባለው።
ይህ ጉዳይ በገበሬዎች ላይ የሚያተኩር ነው። ገበሬወች ለማምረት ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ ያስፈልጋቸዋል።
በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ለማግኘት በህገወጥ ነጋዴወች በኩል በስንት መከራ በጣም በውድ እንዲገዙ እየተገደዱ ነው።
ይህ ችግር የተፈጠረው #አምና ሲሆን ዘንድሮ ይበልጥ ማዳበሪያ ሚባል ለገበሬወች አልደረሰም።
ገበሬወች እንደሚሉት ከሆነ አሁን ላይ የዘር ወቅት ስለሆነ ከአንዳንድ ነጋዴወች ላይ ኩንታል እስከ አስር ሺህ ብር እየገዛን ነው ብለዋል ፤ ይህ ማለት አንድ ገበሬ አስር ኩንታል ዳፕ ቢፈልግ መቶ ሺህ ብር ሊያወጣ ነው ማለት ነው። ካሁን በፊት የአንድ ኩንታል ዋጋ ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር በላይ ሁኖ አያውቅም።
ስለዚህ በኃላ የእህል ምርት አቅርቦት እንዳይቀንስ ከሆዲሁ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ማዳበሪያ ቢያቀርብ መልካም ነው።
ይህ ካልሆነ ግን እመኑኝ ቀጣይ አመት የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ከዘንድሮው እጥፍ ይጨምራል።
ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬውች መዳበሪያ ሲጨምርም መንግስትን ልትጠይቁ ይገባል።
በዋነኝነት መንግሥት ልዩ የሆነ ትኩረት ሰጥቶ እንዲቆጣጠሯቸው ምፈልገው የወረዳ አመራሮችን እና የቀበሌ አስተዳዳሪወችን ነው ምክንያቱም እኒህ አመራሮች ከነጋዴወች ጋር በመስማማት ሚገባውን ማዳበሪያ ቀጥታ ነጋዴወች በውድ እንዲሸጡት ይሰጥቸዋል ፤ ለገበሬው ደግሞ #ማዳበሪያ_አልገባም እያሉ የዘር ወቅት ሳያልፍ ከነጋዴ ገዝተው እንዲዘሩ ይነገሯቸዋል።
ስለዚህ ይህን ችግር ለመፍታት ትኩረት መሰጠት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ሰወች ጥናት ቢያደርጉበት መልካም ነው።
ትኩረት ለገበሬወች !! "
Via @tikvah_eth_BOT
ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ
@tikvahethiopia

ሶስት ዓመት ያለ መብራት . . .
• " የመብራት መቋረጥ የከፋ የኢኮኖሚ ችግር እየፈጠረብን ነው ፤ ስራ የነበራቸው ሁሉ ስራ ፈላጊ ሆነዋል " - ነዋሪዎች
• " ችግሩ ከወረዳው መንግስት አቅም በላይ ነው። የዞንና የክልል አመራሮች በአስቸኳይ መልስ ይስጡን " - የከለላ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ታደሰ
ለሶስት ዓመታት መብራት የተቋረጠባት የከለላ ወረዳዋ ከተማ ነዋሪዎች የመፍትሄ ያለ እያሉ ይገኛሉ።
በከለላ ወረዳ የ01 ደገር ከተማ ነዋሪዎች ባለፉት ሶስት ዓመታት የመብራት አገልግልት በመቋረጡ የከፋ ኢኮኖሚያዊ ችግር እየፈጠረባቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
የከተማ ነዋሪዎቹ አገልግሎት እየሰጠ የነበረው መብራት ከሶስት ዓመት በፊት መቋረጡን ገልጸው በዚህ ምክንያት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ማለትም ፦
- በብረታ ብረትና ጣውላ ስራ፣
- በምግብና ሻይ ቤቶች
- በጸጉር ቤቶች ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች #ስራቸውን_አቋርጠው ስራ ፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ነዋሪዎቹ እንዳሉት የመብራት አለመኖር በሚያከናውኑት የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንደፈጠረባቸውና #የኑሮ_ውድነት እንዲባባስ በማድረግ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተጽዕኖ እንዳደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡
የወረዳው መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩን እንዲፈታላቸውም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡
ይህንን በተመለከተ የከለላ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ታደሰ ፤ በከተማዋ የመብራት አገልግሎቱ መቋረጥ ለተከታታይ ሶስት ዓመታት በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ የፈጠረና በተደጋጋሚ የሚነሳ ጥያቄ ሲሆን የወረዳው መንግስትም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከዞን እስከ ክልል ድረስ በማነጋገር መፍትሄ እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል ብለዋል፡፡
" የመብራት መቆራረጡ በከተማው ነዋሪዎች እና በከተማዋ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ " ነው ያሉት ኃላፊው ችግሩ ከወረዳው መንግስት አቅም በላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው የዞን እና የክልል አመራሮች በአስቸኳይ መልስ እንዲሰጡ አቶ ሁሴን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
መረጃው ከከለላ ወረዳ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።
@tikvahethiopia @tikvah_Eth_BOT

#ethio_telecom
ኪስዎ ሳይጎዳ ወሩን ሙሉ የሚወዷቸው ጋር ደውለው ይጨዋወቱ!
ለዘመድ ለጓደኛዎ እንዲሁም ለስራ አጋርዎ ያለገደብ እንደሻዎ ወሩን ሙሉ የሚጠቀሙበት የድምፅ ጥቅል በ999 ብር ብቻ ከተጨማሪ የፅሁፍ መልዕክት ጋር በቴሌብር እና ማይ ኢትዮቴል መተግበሪያዎች አንዲሁም *999# ገዝተው ይጠቀሙ።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት . . .
ዛሬ ማክሰኞ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በ "ኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት" ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ናቸው ያላቸው ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል።
ጥናቱ ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ?
ጥናቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ምንም ማሻሻያ ሳይደረግበት መቆየቱ ተገልጿል።
ኢንስቲትዩቱ ላለፉት ሁለት / 2 ዓመታት አከራካሪ በሆኑ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች በተለይም ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች የማሻሻያ ጥናት ማድረጉን አሳውዋል።
በጥናቱም ፦
በ2000 ዓ.ም ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተዘረዘሩት 83 ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል 41 የሚሆኑት በስልታዊ የዘፈቀደ ዘዴ (systematic random sampling) ተመርጠዋል ሲል አሳውቋል።
በዚህ መሠረት የሕገ-መንግሥቱ መግቢያ ላይ ያሉ የተወሰኑ ሐሳቦች ማለትም ፦
👉 የብሔር ብሔረሰቦች ሉዓላዊነት አንቀፅ 8፣
👉 የፌዴራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ፣
👉 ብሔራዊ አርማ፣
👉 #ብሔርን መሠረት ያደረገው አስተዳደራዊ ወሰን፣
👉 #መገንጠልን የሚደነግገው አንቀፅ 39፣
👉 የፖለቲካ ፓርቲን #በብሔር_ማደራጀት
👉 #የአዲስ_አበባ_አስተዳደርን በተመለከተ መሻሻል እንዳለባቸው #ሕዝቡ_ፍላጎት እንዳለው ተመላክቷል ብሏል።
#ኢብኮ

TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት . . . ዛሬ ማክሰኞ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በ "ኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት" ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ናቸው ያላቸው ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ? ጥናቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት…
ስለ ሕገ መንግሥት ማሻሻል . . .
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ምን አሉ ?
" ሕገ መንግሥቱ #ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ክርክር እየተነሳ ይገኛል።
በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች፣ መፈናቀሎች እና ብሔር ተኮር ግጭቶች ሕገ መንግሥቱ መሰረታዊ ድጋፍ ይሰጣል የሚሉ ሃሳቦች ይደመጣሉ፡፡
በሌላ በኩል የማንነት መሰረት ነው የሚሉም አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ጥናት መሥራት አስፈልጓል።
ሕገ መንግሥቱ የሊህቃኑ ብቻ ሳይኾን የሕዝብም በመኾኑ ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ መጓዝ ይገባል። "
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ስዩም መስፍን ምን አሉ ?
" ሁሉም የሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች በተለያየ መንገድ የሚሻሻሉበት ሁኔታ አለ።
በመደበኛም ይሁን በኢመደበኛ መንገድ ሕገ መንግሥቱ ይሻሻላል።
391 አንቀጽን የያዘው የሕንድ ሕገ መንግሥት 105 ጊዜ ተሻሽሏል። በመሆኑም ሕገ መንግሥቱ ሙሉ ሊሆን አይችልም።
ምንም እንኳን ሕገመንግሥቱ አልተሻሻለም ይባል እንጂ የተለያዩ አንቀጾቹ በአዋጅ እና በትርጉም እንዲሁም በሌላ መንገድ ተሻሽለዋል።
የፌዴሬሽን ምክርቤት ለእነዚህ ሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች ዕውቅና ያልነፈገ በመሆኑ እንዲሻሻል እንደፈቀደ ይቆጠራል።
ለምሳሌ ፤ የፌዴራሉ አባል ክልሎችን የሚደነግገው አንቀጽ 47 ተሻሽሏል። በተመሳሳይ የፌዴራል እና የክልል የጋራ ገቢዎች የሚወስነው አንቀጽ 58 እንዲሁም መሬት ማሥተዳደርን በተመለከተ የሚደነግገው አንቀጽ 89 እና ሌሎች አንቀጾች ተሻሽለዋል
ሕገ መንግሥትን በተመለከተ በሀገር ደረጃ 3 ምልከታዎች አሉ።
አንደኛው ሕገ መንግሥቱ ረብ የለውም የሚል ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ በፍፁም መነካት የለበትም የሚል ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚል ይገኝበታል።
ጠቃሚው ሀሳብ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚለው ነው።
ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል እጅግ አስፈላጊ ነው። ሕገ መንግሥቱ የማይሻሻል ከሆነ ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ሕገ መንግሥቱን ሙሉ በሙሉ በኃይል የመቀየር እንቅስቃሴ እና ፍላጎት ሊያሳዩ ይችላሉ።
በሀገሪቱ ያሉ የግጭት እና የአለመግባባት ጉዳዮችን በቀላሉ ለመፍታትም እንዲያስችል ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ ቢሻሻል መልካም ነው። "
#አሚኮ

ወለንጪቲ . . .
ከአዳማ ከተማ #በ33_ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ወለንጪቲ ከተማ ዛሬ በተኩስ ስትናጥ ነበር።
በከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ዛሬ ማክሰኞ ዘለግ ላለ ደቂቃ ከበድ ያለ ተኩስ ሲሰማ እንደነበር አመልክተዋል።
አንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል ፤ " ከ11:30 አካባቢ አንስቶ የከባድ መሳሪያ ተኩስ ሲሰማ ነበር " ያለ ሲሆን መልዕክቱን እስከላከበት ሰዓት (ምሽት) ድረስ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ገልጿል።
ባለው ሁኔታ " ለአዳራችን ፈርተናል " ሲል ስጋቱን ገልጿል።
አቢ የተባለ የቤተሰባችን አባል በበኩሉ ከምሽት 12:00 ጀምሮ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሲሰማ እንደነበር ጠቁሟል።
የተኩስ ልውውጡ በመንግሥት ፀጥታ አካላት እና መንግሥት " ሸኔ " እያለ በሚጠራቸው ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መካከል እንደነበር አመልክቷል።
ይኸው የቤተሰባችን አባል፥ " ከ12 ሰዓት ጀምሮ በቃ በጣም ከባድ ተኩስ ነበር፤ አሁን ላይ ተኩሱ ጋብ ብሏል። ነገር ግን አሁን ላይ አልፎ አልፎ ራቅ ብሎ ወደ ጋራ የከባድ መሳሪያ ድምፀ ይሰማል። " ሲል ሁኔታውን ገልጿል።
" አሁን ላይ ምንም አይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የለም " ያለው የቤተሰባችን አባል ማምሻውን የነበረውን ሁኔታ ለማስረዳት አጭር የድምፅ ፋይል አያይዞ ልኳል።
" በጣም ከባድ ሁኔታ ላይ ነን " ሲልም ሁኔታውን ገልጿል።
ሌላ የወልጪቲ ቤተሰባችን አባል ደግሞ ፥ " ሁኔታውን በቃላት ከምገልፀው በላይ ነው ፤ የሰዎች ህይወት አልፏል ፤ የተጎዱ ሰዎችም አሉ " ሲል አመልክቷል።
ይህ የወለንጪቲ መስመር እጅግ በጣም ወሳኝ ከሚባሉ የሀገራችን ቁልፍ የንግድ መስመሮች አንዱ ሲሆን በዚሁ መስመር በተደጋጋሚ ጊዜ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩ ፣ #ግድያን ጨምሮ ዘረፋ ፣ እገታ እጅግ የለየለት ወንጀል እንደሚፈፀም በተደጋጋሚ መጠቆሙ የሚታወቅ ነው።
ከጥቂት ቀናት በፊት በዚሁ ቀጠና ላይ ከአዳማ ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ " ወለንጪቲ " አካባቢ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ የሓንሩካ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር ለማን እና ወንድማቸውን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች መገደላቸው መነገሩ አይዘነጋም።

Photo
#Update
" የቦርዱ ውሳኔ የሰላም ሂደቱ አደጋ ውስጥ የሚከት ነው " - ህወሓት
ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አልቀበልም አለ።
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከቀናት በፊት ምርጫ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበለውም " ያለው ህወሓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እወያይበታለሁ ብሏል።
የምርጫ ቦርድም ውሳኔውን እንደገና በማጤን የፕሪቶርያ ስምምነትና ሌሎች የፌደራል ተቋማት ያስተላለፉትን ውሳኔዎች መነሻ በማድረግ እንዲያስተካክል ጠይቋል።
ህወሓት የሰላም ስምምነቱ ባለቤት ናቸው ያላቸው የድርጅቱ አባላት፣ የትግራይ ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የቦርዱ ውሳኔ የሰላም ሂደቱ ኣደጋ ውስጥ የሚከት መሆኑ በመገንዘብ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
የፌደራል መንግስትም " ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ በተጀመሩት አወንታዊ የሰላም እና የመደጋገፍ ጥረቶች ላይ ሊያሳድረው የሚችል አላስፈላጊ ጫና እንዲሁም የፌደራል መንግስቱ ህጋዊ ውሳኔዎችን እና ስምምነቶችን #በሁሉም የመንግስት ተቋማት እና አካላት እንዲከበሩ የማድረግ ኃላፊቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የቦርዱን ውሳኔ እንደገና ታይቶ ከህወሓት ህጋዊ ሰውነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ያሉትን ህጋዊና ፖለቲካዊ አማራጮች ተጠቅሞ ነገሮች ቅድመ-ጦርነት ወደ ነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ በሚያደርግ ቀና አካሄድ እንዲፈቱ እንዲያድረግና የፕሪቶርያ ስምምነት በተሟላ መንገድ ተግባራዊ እንዲደረግ እና የተጀመረውን የሰላም ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንዲያደርግ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።
(የህወሓት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#big5construct
Tomorrow it is! Ethiopia’s largest construction event - Big 5 Construct Ethiopia kicks off tomorrow. Join us tomorrow at
11:00 AM to explore the future of construction.
Be a part of our Telegram group for regular updates: https://yangx.top/big5ethiopia
Register for your free pass using the link: https://bit.ly/3oI8P6L 📍 Millennium Hall, Addis Ababa 📅 18 – 20 May

#ብርሃን_ባንክ
የብርሃን ባንክ የዋና መስሪያ ቤት ህንጻ አርኪቴክቸራል ዲዛይን ውድድር የቀረቡ ዲዛይኖች ለህዝብ ዕይታ የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽን እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ኤግዚቢሽኑ የባንኩ የስራ አመራሮች በተገኙበት በይፋ የተጀመረ ሲሆን ከግንቦት 5 እስከ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ልደታ አካባቢ በሚገኘው ህንፃ ኮሌጅ ጊቢ ውስጥ ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
በመሆኑ ክቡራን ደንበኞቻችን ለሚቀጥሉት 15 ቀናት የሚቆየውን ኤግዚቢሽን እንድትመለከቱ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡
https://yangx.top/berhanbanksc

" ይህ የተለየ የቪፒኤን አይነት ነው " - ኢትዮ ቴሌኮም
ኢትዮ ቴሌኮም በሞባይል ቪ.ፒ.ኤን (VPN) ጥቅል አገልግሎቱ ላይ የዋጋ ማሻሻያ በማድረግ እንዲሁም ያለተገደበ አማራጭን አካቶ ማቅረቡን ገለፀ።
ድርጅቱ ፤ በቪ.ፒ.ኤን (VPN) አገልግሎቱ ደህንነቱ በተጠበቀ የዳታ አገልግሎት #የድርጅት አገልግሎት ማሳለጥ፣ #ቢሮዎችን እርስበእርስ ማገናኘት እንዲሁም በየትኛውም ቦታ የድርጅት መረጃ እና መሳሪያዎች በመጠቀም ቢዝነስ ማከናወን የሚያስችል ነው ብሏል።
ደንበኞቹ ፤ አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያቸው የሚገኝ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎችን መጎብኘት እንደሚችሉ ጠቁሟል።
ነገር ግን ድርጅቱ የዋጋ ማሻሻያውን በሚመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቹ ያሰራጨው መረጃ በርካቶችን ጋር ያጋባና " VPN ምንድነው ? " ብለው እንዲጠይቁ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ወራትን ካስቆጠረው የማህበራዊ ሚዲያዎች #ገደብ ጋር የሚገናኝ የመሰላቸውም ብዙ ናቸው።
ለመሆኑ ቪ.ፒ.ኤን (VPN) ምንድነው ?
(ኢትዮ ቴሌኮም)
ቪ.ፒኤ.ን (VPN) ማለት የግል እና የመንግስት ተቋማት ከተለያዩ ቅርንጫፎቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ ነው።
ተቋማቱ የራሳቸውን የግል ኔትወርክ እንዲያደራጁ ያስችላቸዋል፤ መረጃን ለማጋራት እንዲሁም በቅርንጫፎች ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓቶችን በመደበኛ ወይም በተንቀሻቃሽ አማራጮች መተግበር ያስችላል።
አገልግሎቱ የሞባይል ኔትዎርክ ሽፋን ተደራሽ በሆነባቸው እና የዳታ አገልግሎትን በሚሰጡ በሁሉም ኢትዮጵያ ክፍሎች ይገኛል።
ኢትዮ-ቴሌኮም የቪፒኤን አገልግሎቶች በሁለት አማራጭ የሚያቀርብ ሲሆን እነዚህም " የሞባይል ብሮድባንድ ቪፒኤን " እና " የፊክስድ ብሮድባንድ ቪፒኤን " ናቸዉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ " ይህ የተለየ የቪፒኤን አይነት ነው። " ያለ ሲሆን " የተንቀሳቃሽ ስልክ ኔትዎርክ ሽፋን ባለባቸው አካባቢዎች ነገርግን ግን መደበኛ ባለገመድ መስመር ተደራሽነት ባሌለባቸው አካባቢዎች ልክ እንደ #ባንክ ያሉ የድርጅት ደንበኞች ቅርንጫፎቻቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማገናኘት የሚረዳ የግል መዳረሻ አውታር ሆኖ እንደ አማራጭ የቀረበ ነው። " ሲል አስረድቷል
የሞባይል ቪፒኤን / VPN / ጥቅል ዋጋ ማሻሻያ የሚመለከተውም ይሄን ነው ብሏል።
Credit : #EthioTelecom

ማዳበሪያ . . . " ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬዎች ማዳበሪያ ሲጨምርም / ሲጠፋ መንግስትን ትኩረት እንዲያደርግ ልትጠይቁ ይገባል " - አብራራው (በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል - አብራራው) " ሰላም ለእናንተ ይሁን !! አንድ አሳሳቢ ሀገራዊ ጉዳይ አለ ፤ ነገር ግን ማንም ትኩረት ሰጥቶት ሲሰራ አላየውም ፤ እናም የሚመለከተው አካል ተመልክቶ መፍትሄ…
ማዳበሪያ . . .
አርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያ ባለማግኘታቸው ያዘጋጁትን የእርሻ መሬት በዘር ለመሸፈን መቸገራቸውን እያሳወቁ ይገኛሉ።
ለአብነት ቃላቸውን የሰጡ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፤ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች በቂ የአፈር ማዳበሪያ ባለማግኘታቸው ያዘጋጁትን የእርሻ መሬት በዘር ለመሸፈን ተቸግረዋል።
ቄስ ተበባል መኮነን ፤ 2 ነጥብ 5 ሄክታር የእርሻ መሬታቸውን በበቆሎ ፣ በስንዴ ፣ በበርበሬና በጤፍ የሰብል አይይነቶች ለመሸፈን በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጽዋል።
ላዘጋጁት የእርሻ መሬትም 6 ኩንታል ዳፕና 4 ኩንታል ዩሪያ በአጠቃላይ 10 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ማዳበሪያ አለማግኘታቸውን አመልክተዋል።
የችግሩን አሳሳቢነት ለሚመለከታቸው ተቋማት ቢያሳውቁም ጠብቁ ከማለት ውጭ ምንም ተስፋ የለውም ብለዋል።
የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ማቅረብ ካልቻለ የጥራጥሬ ሰብሎች የዘር ወቅት የሚያልፍባቸው መሆኑንና የሚፈልጉትን ያህል ምርት ማግኘት የማይችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሌላው የዚህ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ምስጋነው ስንሻው ያላቸውን 7 ጥማድ መሬት በቆሎ ፣ በስንዴ ፤ በበርበሬና በጤፍ የሰብል አይነቶች ከፋፍለው ለመዝራት እቅድ ይዘው ማሳቸውን ደጋግመው በማረስና በማለስለስ በዘር ለመሸፈን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
የጥራጥሬ ሰብላቸውን ወቅቱ ሳያልፍ ለመዝራት ቢዘጋጁም የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገልፀው መሬታቸው ያለ አፈር ማዳበሪያ ማብቀል ስለማይችል በወቅቱ የአፈር ማዳበሪያ የማይቀርብላቸው ከሆነ ከራሳቸው የምግብ ፍጆታ አልፎ ገበያ ላይ የሚቀርብ ምርት ስለሚጠፋ በመንግስት በኩል ትኩረት ተሰጥቶት በአፋጣኝ ሊቀርብልን ይገባል ብለዋል።
የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ምን አለ ?
ያንብቡ : https://telegra.ph/West-Gojjam-05-17