TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከቀናት በፊት በተፈፀመባቸው ጥቃት የተገደሉት የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ እሁድ ተፈፅሟል።

የአቶ ግርማ የሽጥላ ሥርዓተ ቀብር የተፈፀመው በትውልድ ስፍራቸው መሃል ሜዳ ነው።

ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ የሽኝት ስነስርዓት ተከናውኖ ነበር።

አቶ ግርማ ባለትዳርና የ3 ሴትና የ4 ወንድ ልጆች አባት ነበሩ።

ፎቶ፦ አሚኮ

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ፥ ከሀገር ውጭ የሚገኙትን ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌውን ፣ በቅርቡ ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል የተፈጠረውን አለመግባባት በስምምነት እንደፈታ የተነገረለት የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በሀገር ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የሚዲያ ሰዎች እና በውጭ ሀገር ያሉ በርካታ የሚዲያ ሰዎችን " ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ እንዲሁም #በሽብር_ወንጀል " እፈልጋቸዋለሁ ብሏል።

ግብረ ኃይሉ በአማራ ክልል እየወሰድኩ ነው ባለው እርምጃ " ፅንፈኛ ናቸው " ላላቸው ኃይሎች የሚዲያ እና ፕሮፖጋንዳ ክንፍ በመሆን እየሰሩ ናቸው ያላቸውን አካላት ነው #በወንጀል እንደሚፈልጋቸው ያሳወቀው።

በውጭ ሀገር ያሉትን ተፈላጊ ግለሰቦች በዐለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት እንዲሁም ከሚኖሩባቸው ሀገር መንግስት የፀጥታ እና ደህንነት ተቋማት ጋር በተመሰረቱ የትብብር ማዕቀፎች ተላልፈው እንዲሰጡ እየሰራሁ ነው ብሏል።

በሌላ በኩል የፀጥታ እና ደህንነት  ግብረ ኃይሉ በአማራ ክልል " በህቡዕ አደረጃጀት " ውስጥ ሲንቀሳቀሱና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ አገኘኃቸው ያላቸውን 47 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

ከእነዚህ 47 ግለሰቦች ውስጥ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውጋቸው፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ተዳርጋ የተፈታችው መምህርት መስከረም አበራ ይገኙበታል።

ግብረ ኃይሉ የተያዙት ግለሰቦች የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን " ለመግደል፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ የክልሉን መንግሥታዊ መዋቅር በመቆጣጠር የፌደራል መንግሥትን ለመጣል " በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ ስለደረስኩባቸው ነው ብሏል።

ግብረ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙሃን ያሰራጨው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በደቡብ ኦሞ ዞን በተከሰተው ድርቅና ጎርፍ አደጋ ምክንያት የፌዴራል መንግሥቱ ለችግሩ ምላሽ እንዲሰጥ የክልሉ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች 6 ጊዜ በደብዳቤ እንዲሁም በስልክ ዕርዳታ ቢጠይቁም ምንም ዓይነት መልስ አለመሰጠቱን በምርመራ ሥራው ማረጋገጡን አሳውቋል።

ተቋሙ በኦሮሚያ፣ በደቡብና በሶማሌ ክልሎች፣ በቦረና፣ በደቡብ ኦሞና በዳዋ ዞኖች አካባቢ በድርቅና ጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረግ ሰብዓዊና ቁሳዊ ድጋፍ፣ መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥና መልሶ የማቋቋም ሥራ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ምርመራ ያካሄደ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ይህኑኑን ምርመራ ይፋ አድርጎ ነበር።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ምን አለ ?

- በሦስቱ ክልሎች በሚገኙ ሦስት ዞኖች እስካሁን በድርቅ ሳቢያ የተፈናቀሉ 243 ሺሕ ነዋሪዎች በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ።

- በድርቅና ጎርፍ የደረሰው ጉዳት ሲታይ በኦሮሚያ ቦረና ዞን 1.32 ሚሊዮን እንስሳት ሞተዋል፤ በሶማሌ ዳዋ ዞን 335 ሺሕ ገደማ እንስሳት ሞተዋል 420 ሺሕ ገደማ የሚሆኑት አደጋ ላይ ወድቀዋል። በደቡብ ኦሞ ዞን በድርቅና በጎርፍ የሞቱ እንስሳት 48 ሺሕ ናቸው።

- በደቡብ ክልል በተፈጠረው ድርቅና ጎርፍ ምክንያት የደረሰውን ሁኔታ የሚያሳይ አጠቃላይ የመረጃ ችግር ቢኖርም ደቡብ ኦሞ ዞን 338 ሺሕ የሚጠጋ ሕዝብ ለጉዳት ተዳርጓል።

በድርቅና ጎርፍ አደጋው ለተጎዱ ዜጎች በወረዳና በዞን እንዲሁም ከክልል በኩል ድጋፍ ይደረግ የነበረ ቢሆንም ለ6 ጊዜ ያህል ለፌዴራል መንግሥት ደብዳቤ ቢጻፍም የፌዴራል መንግሥት መልስ መስጠት አልቻለም።

ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥበት ለፌዴራል አደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ደብዳቤና በስልክ ንግግር ቢደረግም ይሰጥ የነበረው ምክንያት ግን የጨረታ ግዥ ጋር የተያያዘ ነበር።

ለዞኑ ይመጣ የነበረው ዕርዳታ ለማግኘት ሲሉ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ መስጠትና የአካባቢው አመራር ጭምር ዕርዳታ ለማግኘት ፍላጎት ያሳዩ እንደነበር ተረጋግጧል።

- በሦስቱም ክልሎች በሁሉም አካባቢዎች የተደራጀ መረጃ አለመኖር የድርቁንና የጎርፍ አደጋው የፈጠረውን ግልጽ ሥዕላዊ መረጃ ወጥ በሆነ መልኩ ማግኘት አልተቻለም። ይሁን እንጂ የቁጥጥር ሥራው እስከተከናወነበት ድረስ በድርቁና በጎርፍ አደጋ ምክንያት የሞተ ሰው ማግኘት አልተቻለም። የጎርፍና የድርቅን አደጋ ተከትሎ በሚመጡ በሽታዎች ሊሞቱ የሚችሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ።

- ድርቁን መቀነስ የሚቻል የነበረ ቢሆንም፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራው በተገቢው መልኩ ባለማከናወኑ ችግሩን እንዳባባሰው፣ ችግሩ ከተከሰተ ወዲህም በመንግሥትና በሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት መካከል የነበረው የኮሙዩኒኬሽንና ቅንጅታዊ አሠራር አናሳ መሆን ድርቁንም ይሁን የጎርፍ አደጋውን አባብሶታል።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
" የአዲስ አበባ ጸጥታ ቢሮ ይህን ጥያቄ ይዛችሁ አደባባይ አትወጡም አለን " - አቶ ካሳሁን ፎሎ

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) መንግስት የገቢ ግብርን እንዲቀንስ ለመጠየቅ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አቅዶ የነበር ቢሆንም መንግሥት ሰልፉን እንዳይደረግ መከልከሉን አሳውቋል።

የኮንፌደሬሽኑን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ እንዳሳወቁት ፤ ዛሬ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀን (ሜይ ዴይ)ን ተተርሶ ነበር ሰልፉ እንዲደረግ ታቅዶ የነበረው።

የሰልፉ ዋነኛ ዓላማ ፤ ሰራተኛው በኑሮ ውድነቱ መኖር ባለመቻሉ መንግሥት የገቢ ግብርን እንዲቀንስ ለመጠየቅ ሲሆን በተጨማሪም ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እንዲወሰን፣ የኤጄንሲ ሰራተኞች 20/80 ክፍያ ገቢራዊት እንዲሁም የመደራጀት መብትን ለመጠየቅ ነበር።

ነገር ግን የመንግሥት ፀጥታ ቢሮ ይሄ ሰልፍ እንዳይካሄድ መከልከሉን ኢሰማኮ አሳውቋል።

የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ፤ በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ መቶ ሽህ በላይ ሰራተኞች ይሳተፉበታል የተባለው ሰልፍ በከተማዋ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ መከልከሉ ገልጸዋል።

" ማክሰኞ ሚያዚያ 17 የከተማ አስተዳደሩን ስለ ሰልፉ አሳውቀናል ፤ ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋርም ስንነጋገር ነው የሰነበትነው ነገር ግን ካላንደር በዘጋው ቀን ድምጻችንን እንዳናሰማ ተከልክለናል " ብለዋል።

" ሰልፉን ለማድረግ ፈቃድ አያስፈልግም፡፡ እኛ ለራሳችን ደህንነታችንን እንዲጠብቁን አሳውቀናል፡፡ የአዲስ አበባ ጸጥታ ቢሮ ይህን ጥያቄ ይዛችሁ አደባባይ አትወጡም አለን፡፡ ህግ እናስከብረለን ስላሉ ሰራተኛው እንዳይጎዳ አስቀረነው " ሲሉ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ትላንት ምሽት ባወጣው ማሳሰቢያ ደግሞ የላብ አደሮች ቀንን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ምንም አይነት የአደባባይ ኩነቶችና ሰልፍ እንዲሁም ፖሊስም ሆነ የአስተዳደር አካላት የሚያውቁት ምንም ዓይነት ስብሰባ የለም ብሏል።

መረጀውን ከአልዓይን ፣ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) እና ከአ/አ ፖሊስ የተገኘ ነው።

Via @tikvahethmagazine
#አቢሲንያ_ባንክ

አፖሎን ተጠቅመው ቪዛ ካርድ ሲያዙ በ72 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ በተመችዎት ቦታ ካርድዎን እናደርስሎታለን

መተግበሪያውን ኣውርደው ካርድዎን ይዘዙ።

https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#ቴክኖ_ሞባይል

ራሳችንን በተሻለ መንገድ ለመግለፅ የሚያስችለንን አዲሱን የቴክኖ ስፖርክ 10 ሲሪየስ እናስተዋውቆ!

ራሳችንን በተሻለ መንገድ ለመግለፅ የሚያስችለን ይህ አዲሱ የቴክኖ ስፖርክ 10 ካሜራ በማንኛውም ሰዓት እንዲሁም በማንኛውም የብርሀን መጠን 32 ሜጋ ፒክስል ካሜራን በመጠቀም ጥራት ያለውን ፎቶ ያለ እንከን ቁልጭ አድርጎ ማንሳት የሚያስችል ነው።

የዚህ ምርት ትኩረት በውጫዊ ውበት ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ይልቁንም ለወጣቱ ትውልድ በራስ የመተማመን መንፈስ እንዲኖራቸው፣ ለራሳቸው ገደብ እንዳይሰጡ፣ ስብዕናቸውን እና አመለካከታቸውን በመግለፅ ችሎታቸውን ገፍተው በመሄድ እውነተኛ ማንነታቸውን በልበ ሙሉነት እንዲያሳዮ የሚያበረታታ መልዕክት አካቶ ይዟል።

በየትኛውም የስልክ መሸጫ መደብሮቻችን ያገኙታል።
ለበለጠ መረጃ: Facebook, Instagram, Tiktok

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark10Series #TecnoMobile #Ethiopia #Spark10pro
TIKVAH-ETHIOPIA
#IOM እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መረጀ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቱርክ ዜጎችን ጨምሮ ከ3,500 በላይ ሰዎች በሱዳን ያለውን ከባድ ጦርነት ሸሽተው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ከሚያዚያ 21 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ3500 በላይ የሆኑ የ35 ሀገራት ዜጋ  ስደተኞች ተመዝግበዋል። ከተመዘገቡት አጠቃላይ ስደተኞች መካከል ከ40 በመቶ በላይ የቱርክ ዜጎች ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን 14…
" ግጭቱ ከሶሪያ እና ከሊቢያ የከፋ ሊሆን ይችላል " - አብደላ ሐምዶክ

የቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳላ ሐምዶክ በአገራቸው የተከሰተው ግጭት ከሶሪያ እና ከሊቢያ የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ውጊያው የሚቀጥል ከሆነም " ዓለምን የሚያስጨንቅ ቅዠት " ሊሆን ይችላል ብለዋል አብዳላ ሐምዶክ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ በኬንያ ዋና ከተማ በተካሄደ ጉባኤ ላይ ሁለቱን ተቀናቃኝ ጄኔራሎች ወደ ሰላም ንግግር ለማምጣት የተባበረ ዓለም አቀፍ ጥረት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

" ሱዳን የተለያዩ ሕዝቦች ያሉባት ግዙፍ አገር ናት...ግጭቱ ዓለምን እንቅልፍ የሚነሳ ቅዠት ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ሐምዶክ ተናግረዋል።

" ይህ በአገሪቱ ሠራዊት እና በትንሽ አማጺ ቡድን መካከል የሚካሄድ ጦርነት አይደለም። " ያሉት የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር " በደንብ በሰለጠኑ እና በታጠቁ ሁለት ሠራዊቶች መካከል የሚካሄድ አይነት ጦርነት ነው " ብለዋል።

አሁን ውጊያ በገጠሙት ጄኔራሎች #በመፈንቅለ_መንግሥት ከሥልጣን ከመወገዳቸው በፊት ለሁለት ዓመት ያህል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገሪቱን የመሩት አብዳላ ሐምዶክ፣ ' በሱዳን የተከሰተው ቀውስ በሶሪያ እና በሊቢያ ካጋጠመው የእርስ በርስ ጦርነት የከፋ ሊሆን ይችላል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በሱዳን ተፋላሚዎቹ ጄኔራሎች መካከል እንዲራዘም ከስምምነት የተደረሰው የተኩስ አቁም በዋና ከተማዋ ካርቱም ውስጥ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች እየተጣሰ መሆኑ ተነግሯል።

ሁለት ሳምንት የሆነው ውጊያ አስካሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን፣ አስር ሺዎችን ደግሞ ከአገራቸው እንዲሰደዱ አድርጓል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Metema

የምዕራብ ጎንደር ዞን ፥ ከ6 ሺህ በላይ የሱዳን ተፈናቃዮች በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን አስታውቋል።

ዞኑ ፥ በሱዳን በተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት የ42 ሀገራት ዜጎች  በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ነው ያመለከተው።

ወደ አካባቢው ሊገባ የሚችለውን ተፈናቃይ ለመቀበል በሚቻልበት ጉዳይ ቅድመ ዝግጅት  ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀው ዞኑ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ብቻ  ከ6 ሺህ በላይ የ42 ሀገራት  ዜጎች መግባታቸውን አመልክቷል።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ 941  #ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጿል።

ተፈናቃዮቹ የጤና ችግር እንዳይገጥማቸው የጤና ባለሙያ በመመደብ  አገልግሎት እየተሰጠ ነው ያለው ዞኑ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በኩል መካከለኛና ከፍተኛ ተሽከርካሪዎች ተመድቦ ተፈናቃዮች ወደ የሚፈልጉት አካባቢ የመሸኘት ሥራ ተሠርቷል ብሏል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበርም ውኃና ብስኩት በማቅረብ እያገዘ እንደሆነ ዞኑ ገልጿል።

በቀጣይ ችግሩ እየሰፋ የሚሄድ ከኾነ ወደ ቀጣናው ሊገባ የሚችለውን ስደተኛ ሊያስተናግድ የሚችል ቦታ የመለየት ሥራ መሰራቱን ዞኑን ማስታወቁን አሚኮ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ

እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ልኮልናል።

ፓርቲው በዚህ መግለጫው፤ መንግሥት " ኦነግ ሸኔ '' እያለ ከሚጠራው የታጠቀ ቡድን ጋር በታንዛኒያ እያደረገው ያለው ድርድር ከሴራ ፖለቲካ በፀዳ መልኩ ተከናውኖ እንዲጠናቀቅ ምኞቱን ገልጿል።

እናት ፓርቲ ፤ " ካለ ፍትሕ ሰላምን ማስፈን አስቸጋሪ መሆኑን ብናምንም ድርድሩ ከተለመደው የሴራ ፖለቲካ በጸዳ መልኩ ተከናውኖ በስቃይ ውስጥ የሚገኘውን ሕዝባችንን ሊታደግ በሚችል መልኩ እንዲቋጭ እንመኛለን፡፡ " ብሏል።

መንግስት ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ሀሳብ ካላቸው ፓርቲዎች ጋርም የጋራ መግባባትን ለማስፈን የሚያስችል ውይይት እንዲያደርግ ፓርቲው ጥሪ አስተላልፏል።

ከዚህ ባለፈ የአማራ ክልል ብልጽግና ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ግድያን ተከትሎ መንግስት አሁንም " ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች" ን ትጥቅ በማስፈታት " ሰላም አስከብራለሁ " በሚል በአማራ ክልል የጀመረው እንቅስቃሴ ከሕወሓትና " ኦነግ ሸኔ " ጋር የታለፈበትንና አገርን ውድ ዋጋ ያስከፈለ አካሄድ የሚደግም ነው ብሎታል።

" መንግስት ካለፈ ስህተቱ መማር ሲገባው  ወደ ሌላ የግጭት አዙሪት አገርንና ሕዝብን የሚከት፤ የክልሉን ወጣት ለአመጽ የሚጋብዝ " ነው ያለው ፓርቲው " በዚህም ከቀደሙት መደበኛ ጦርነትና የሽምቅ ውጊያ ሂደቶች ትምህርት ያልወሰደ፣ የሚያስከትለውንም መጠነ ሰፊ ጉዳት እና መዘዝ በአግባቡ ያላገናዘበ አደገኛ የማንአለብኝነት አካሄድ እየተከተለ ነው " ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

ስለዚህ መንግሥት ከጀመረው የጅምላ እስር፣ የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ፣ የድርጅቶችን የንግድና የገንዘብ እንቅስቃሴ የማገድ ሂደት ወዘተ. በእሳት ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ አካሄዶች ራሱን አቅቦ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ሊፈቱ በሚችሉበት ሁኔታዎች ላይ ብቻ እንዲያተኩር አጽንዖት ሰጥቷል።

ከዚህ ውጭ የድርድርና የውይይት ፍኖትን ባለመሻት መንግሥት በማንአለብኝነት አካሄዱ ቀጥሎ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥፋትና ውድመት ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ እናት ፓርቲ በጽኑ እንደሚያምን ገልጿል።

እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ ፥ በአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦች መፅናናት ተመኝቶ ፤ ምርመራ ባልተካሄደበትና ጥፋተኞች በአግባቡ ባልተለዩበት ሁኔታ የሚደረጉ ፍረጃዎች የፍትህ አሰጣጡን እንደሚያዛባው ገልጿል።

(ፓርቲው የላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ከዓመታት በኃላ በትግራይ ያሉ #ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ምዝገበ እየተካሄደ ይገኛል። የትግራይ ትምህርት ቢሮ  ለዓመታት በኮቪድ-19 እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ከሚያዚያ 18 ጀምሮ ምዝገባ እንደሚከናወን እና ሚያዚያ 23 ትምህርት እንደሚጀመር ማሳወቁ የሚዘነጋ አይደለም። ተማሪዎች ያለፋቸውን ጊዜ ለማካካስ በሳምንት 3 የትምህርት…
#ትግራይ

በትግራይ ክልል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ተመለሱ።

ላለፉት ዓመታት በትግራይ ክልል አንድም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኃላም በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ትምህርት ዛሬ ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓ/ም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ትምህርት የሚጀመረው ሁሉ ነገር ተሟልቶ ፤ ችግሮች ሁሉ ተፈተው ሳይሆን ትውልድን ለማስቀጠል ሲባል መሆኑን ከዚህ ቀደም አሳውቆ ነበር።

ዛሬ ትምህርት ከተጀመረባቸው ት/ቤቶች መካከል የኤርትራ ጦር ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰበት የተነገረው " ማይመኸደን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም በእንደርታ ወረዳ የሚገኘው ሓሬና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ይጠቀሳሉ።

ምንም እንኳን በርካታ ችግሮች ያሉ ቢሆንም በተማሪዎች ሆነ በወላጆች ዘንድ ትምህርት መጀመሩ ደስታን እና ተስፋን ፈጥሯል።

በትግራይ 85 በመቶ ትምህርት ቤቶች ከባድ ወይም ከፊል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ባለው ነገር ትምህርት ቢጀምሩም አሁንም የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተፈናቃይ ዜጎችን አስጠልለው ይገኛሉ።

ፎቶ ፦ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት

#BringTigrayChildrenBacktoSchool

@tikvahethiopia