#ሲዳማ
የ " በላይነህ ክንዴ ግሩፕ " በሲዳማ ክልል በሎካ አባያ ወረዳ 550 ሔክታር መሬት ተረክቦ በፍራፍሬ እና በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በመመደብ ልማት መጀመሩን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የእርሻ ዘርፍ አስፈጻሚ ዶ/ር አንተነህ አብዋ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።
ዶ/ር አንተነህ አብዋ ምን አሉ ?
- በሲዳማ ክልል ሎካ አባያ ወረዳ 550 ሔክታር መሬት ተረክበረን 380 ሔክታር መሬት ላይ አትክልት ከማልማት አስቀድሞ የበጋ ስንዴ እያለማን እንገኛለን ፤ ምርታችንን ለውጭ ገበያ ለማቅረብም አቅደናል።
- በሔክታር ከ30 እስከ 50 ኩንታል ለምግብ ፍጆታ የሚውል ስንዴ ለማልማትና ከዚህም በጥቂቱ ከ11,400 በላይ ኩንታል ስንዴ ለመሰብስብ ታቅዷል። ለዚህም ከ600 በላይ ኩንታል ስንዴ ለዘር ተጠቅመናል።
- ለስንዴና ማዳበሪያ ግዥ ከ300 እስከ 400 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርገናል። 400 ኩንታል ኤንቲኤስ፣ እንዲሁም 400 ኩንታል ዩሪያ መሬቱን ለማሰናዳት ማዳበሪያ ተጠቅመናል።
- የእርሻ ልማቱን ለማከናወን በአጠቃላይ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል፤ ከ20 ኪሎ ሜትር መንገድ እንዲሁም ወደ እርሻው የሚፈሰውን የወንዝ ውኃ ለመቆጣጠር 4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ግድብ ተገንብቷል።
- የአባያ ሐይቅና የብላቴ ወንዝን ለእርሻው በዋነኛነት እንጠቀማለን፤ ለዚህም ዘመናዊ ፓምፖችን ለመጠቀም ተሰናድተናል።
- በአካባቢው የዝናብ እጥረት ያለበት አካባቢ በመሆኑ ከአባያ ሐይቅ እስከ እርሻው መዳረሻ ድረስ ሦስት ኪሎ ሜትር ያለውን ርቀት በፓምፕ ስቦ ለማምጣት መሠረተ ልማት ተዘርግቷል።
- የበጋ ስንዴ ማልማቱ ሲጠናቀቅ የአትክልትና የፍራፍሬ ልማቱ ይቀጥላል ፤ አቮካዶ፣ ሙዝና ፓፓዬ ለማልማት የችግኝ ግዥ ተፈጽሞ ለመትከል ዝግጅት ላይ ነን።
- መሬቱን ከተረከብን 4 ወራት ብቻ ሲሆን አትክልትና ፍራፍሬ ማልማቱንም ለማስቀጠል ከ40 ሔክታር መሬት በላይ አቮካዶ ተተክሏል። በቀሪዎቹ ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ እንዲሁም ፓፓዬ ለማልማት ታቅዷል። በዚህ መሬት ላይ ተጨማሪ ፍራፍሬዎችን ለማሰናዳት የችግኝ ማፍላት ሥራ እየተሰራ ነው። ለጊዜው ለ200 የአካባቢው ሠራተኞች፣ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፤ ይኼም ቁጥር ወደ 500 ለማሳደግ ታቅዷል።
በሌላ በኩል ፤ በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር በአካባቢው ለምትገኘው #መራሬ_ከተማ #የውኃ እና #የኤሌክትሪክ_ኃይል ለመዘርጋት የኮንክሪትና የእንጨት ፖል ዝርጋታ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
መንግስት ከክልል ልዩ ኃይል ጋር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ዛሬም ለተከታታይ ቀን መቀጠሉ ለማውቅ ተችሏል።
ዛሬ በደሴ ከተማ ፣ በእንጅባራ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉ ለማወቅ ተችሏል።
ሰልፉ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መፍረስን የሚቃወሙ የተለያዩ መልዕክቶች የተስተጋቡበት ነበር።
በተለይም ፤ " ልዩ ኃይሉ የአማራ ህዝብ ጠባቂ ነው የአማራ ህዝብ ደህንነቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ይህ ውሳኔ መወሰኑ ተገቢ አይደለም " በሚል የሰልፉ ተካፋዮች የመንግሥትን ውሳኔ በመቃወም ሀባቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪ ሌሎች የታጠቁ አካላት ትጥቅ ሳያወርዱ የክልሉን ህዝብ ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ ይህን አይነት ውሰኔ መወሰኑ ተቀባይነት እንደሌለው ነው ያመለከቱት።
ስለዚህም መንግሥት ውሳኔውን እንዲያጤነውና እንዲቀለብሰውም ተጠይቋል።
የፌዴራል መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት ውሳኔ አሳልፎ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል።
ይህ ውሳኔ ለሀገር ሉዓላዊነት እና አብሮነት ሲባል በሁሉም ክልል በተመሳሳይ ወቅት የሚፈፀም እንደሆነም መንግሥት ገልጿል።
የአማራ ክልል መንግሥት በበኩሉ የአማራ ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ እንደሌለ በመግለፅ ክልሉ የተወሰነውን ውሳኔ ለመተግበር እየሰራ እንደሆነ አመልክቷል።
በአፈፃፀም ላይ ክፍተት እየታየ መሆኑን የሚገልፀው ክልሉ ፤ እየተነዛ ባለው ሀሰተኛ ፕሬፖጋንዳ ችግሮች መከሰታቸውን ገልጿል።
በአማራ ህዝብ ዘንድ ቅሬታን የፈጠረው ሁኔታ የመነጨው በተሟላ መንገድ ለህዝብ መረጀ ባለመድረሱ ስለመሆኑ የአማራ ክልል መንግሥት አሳውቋል።
ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

#GONDAR
በጎንደር ክልከላዎች ተጣሉ።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ክልከላዎችን አስቀመጠ።
ኮማንድ ፖስቱ ፤ ክልከላው " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል " የተቀመጠ መሆኑን ገልጿል።
የተቀመጡ ክልከላዎች ምንድናቸው ?
1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት ተከልክለዋል።
2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ ተከልክለዋል።
3. ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
4. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
5. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ ተከልክሏል።
6. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ ተከልክሏል።
7. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦
- የልዩ ኃይል ፣
- የፓሊስ ፣
- የመከላከያ ሠራዊት ፣
- የፌዴራል ፓሊስ ልብስ መልበስ በጥብቅ ተከልክሏል።
9. ያልተፈቀዱ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት ተከልክሏል።
10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።
11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስተው ወደ ከተማው የመጡ በከተማው በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንዲሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተለልፏል። ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ ተከልክሏል።
12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ ይጠየቃል።
መረጃው የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ነው።

ልክ ጎንደር እንደተደረገው በደብረብርሃን ከተማም ክልከላዎች ተጣሉ።
ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ #ህጋዊ_መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል ተብሏል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ " እንዲቻል በሚል ክልከላዎችን መጣሉን አሳውቋል።
ክልከላዎቹ ምንድናቸው ?
1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት ተከልክለዋል።
2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
3. በከተማ አስተዳደሩ ለጸጥታ ማስከበር ተልዕኮ ከተሠጠው የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ ተከልክሏል የልዩ ኋይል ፣ የፓሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት ፣ የፌዴራል ፓሊስ ልብስ መልበስ ተከልክሏል።
9 . ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ያልተፈቀደ ሰልፍ ማድረግ ፣ መንገድ መዝጋት ተከልክሏል።

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስተው ወደ ከተማው የገቡ በከተማው በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንዲሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተላልፏል። ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ ተከልክሏል።
12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል ተብሏል።
13. በከተማው ውስጥ ህጋዊ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል።
14. በከተማው በተፈናቃይ ካምፕ የምትገኙ ተፈናቃይዎች በማንኛውም ሰአት ወቅታዊ ሁኔታው እስከሚስተካከለ ድረስ ከካምፕ ውጭ መገኘት ፈጽሞ ተከልክለዋል።
መረጃው ደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የጸጥታው ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት ነው።

#Update ልክ ጎንደር እንደተደረገው በደብረብርሃን ከተማም ክልከላዎች ተጣሉ። ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ #ህጋዊ_መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል ተብሏል። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ " እንዲቻል በሚል ክልከላዎችን መጣሉን…
#ደሴ
የአማራ ክልል ከተሞች ተመሳሳይ / #አንድአይነት ይዘት ያላቸው ክልከላዎችን እየጣሉ ይገኛሉ።
ማምሻውን የደሴ ከተማ ኮማንድ ፖስት በጎንደር እና ደብረብርሃን የተጣሉትን አይነት ተመሳሳይ ክልከላዎች መጣሉን ገልጿል።
ኮማንድ ፖስቱ የጣላቸው ክልከላዎች ከላይ ተያይዘዋል።
በሌላ በኩል ፤ የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ ለከተማው ነዋሪዎች ባሰራጨው መልዕክት " በከተማው እየተሰራ ያለው ልማት ለደቂቃም ሊስተጓጎል አይገባም። " ብሏል።
" ህዝባችን ሰላም ፣ ልማት እንደሚፈልግ ጠንቅቀን እንረዳለን። " ያለው ኮማንድ ፖስቱ " የደሴ ህዝብ ከእንግዳህ በሴራ እየተጎዳ መቀጠል የለበትም " ሲል ገልጿል።
" ወጣቶቻችን በሆደ ሰፊነት በትዕግስት በስክነት ነገሮች እንዲፈቱ እንደሚፈልጉና ልማቱን ምንም እንቅፋት እንዲፈጠርበት እንደማይፈልጉ ጠንቅቀን እናውቃለን " ሲል የገለፀው ኮማንድ ፖስቱ " መንግስት ህግ ለማስከበር የተደራጀ ኃይል እና ዝግጅት ቢኖረውም ከተማችን ነገሮች በሰከነ መንገድ በውይይት እንደፈቱ ከመፈለግ ታግሰናል። " ብሏል።
የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ " ዋናው ችግር ከሌላ ቦታ በመጡ ኃይሎች አስተባባሪነት እንጂ በከተማው ህዝብ እንዳልሆነ ህዝባችን ልብ ሊል ይገባል " ብሏል።
የደሴ ከተማ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት " ከሌላ ቦታ መጡ " ያላቸው ኃይሎች እነማን እነድሆኑና ከየት እንደመጡ ባወጣው መግለጫ ያለው ነገር የለም / ማብራሪያም አልሰጠም።

#SpecialForce
መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት ወስኖ ወደ ተግባር መግባቱን ተከትሎ በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ካለፉት ቀናት አንስቶ ዛሬም ድረስ ቀጥሏል።
በርካቶች አደባባይ ወጥተው መንግሥት ውሳኔውን እንዲያጥፍ ጠይቀዋል።
ይህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለሰዎች ህይወት መጥፋት ፣ መቁሰል ፣ የትራንስፖርት ፣ ገበያ መስተጓጎል ምክንያት ሆኗል።
በአማራ ክልል ነዋሪዎች ዘንድ ውሳኔው ተቃውሞ የገጠመው " ልዩ ኃይሉ የአማራ ህዝብ ጠባቂ ነው ፤ የአማራ ህዝብ ደህንነቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ይህ ውሳኔ መወሰኑ ተገቢ አይደለም " በሚል ነው።
ከዚህ ባለፈ ፤ ሌሎች የታጠቁ አካላት ትጥቅ ሳያወርዱ የክልሉን ህዝብ ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ ይህን አይነት ውሰኔ መወሰኑ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለፅ ጭምር ነው ተቃውሞው የቀጠለው።
በሌላ በኩል ፥ ዛሬ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ባወጣው መግለጫ የልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ስራ በጋራ ውይይት መግባባት ላይ የተመሰረተ ነው ብሏል።
ፓርቲው ፥ " የክልል ልዩ ሀይሎችን እንደገና የማደራጀት አስፈላጊነት ልክ ያልነበረን ጉዳይ ልክ የማድረግ ውሳኔ እና ጥረት እንጂ ሌላ ምንም አመክንዮ እንደሌለው በውል ሊታወቅ ይገባል " ብሏል።
" አንዳንድ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና መሪዎቻቸው እንዲሁም ማህበራዊ አንቂዎች ነን የሚሉ ግለሰቦች ጉዳዩን አንድን ክልል ብቻ ትጥቅ የማስፈታት ጉዳይ አድርገዉ እያቀረቡ ነው " ሲል ገልጿል።
እነዚህ ፓርቲዎች ጉዳዩን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው " ማክሰም፣ ማጠፍ፣ ማፍረስ፣ መበተን… " ወዘተ የሚሉት አገላለጾች እንደሆነ የሚገልፀው ብልፅግና ፓርቲ እነዚህን አገላለፆች የሚጠቀሙበት ግባቸው ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ እና ህዝብን ለማሳሳት በመሞከር ጊዜያዊ ቅቡልነት ለማግኘት ነው ሲል ገልጿል።
ከዚህ ሀገርን ዋጋ ከሚያስከፍል ህገ ወጥ እና መርህ አልባ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ ሲል ፓርቲው አስጠንቅቋል።
ፓርቲው ልዩ ሀይልን ትጥቅ የማስፈታት ሳይሆን የተሻለ የማስታጠቅ፤ የመበተን ሳይሆን በጠንካራ መሰረት ላይ የማደራጀት ስራ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።
ከዚሁ ከክልል ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ጋር በተያያዘ ፤ የሶማሌ ክልል ካቢኔ የክልሉ ልዩ ኃይልን መልሶ የማደራጀት የትግበራ ዕቅድ ተፈፃሚ እንዲሆን ዛሬ እንደወሰነ ታውቋል።
የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ፤ የፀጥታ ኃይሎች በሀገር አቀፍ እና ክልል ደረጃ መልሶ ለማደራጀት በታቀደው ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።
አቶ ሙስጠፌ ፤ በዕቅዱ ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ የክልሉን ልዩ ኃይል በሌሎች የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ለማደራጀት የወጣው የትግበራ እቅድ ተፈጻሚነት ላይ ከመግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

#ባህርዳር
ትላንትና ከምሽቱ 1:40 ገደማ በባህር ዳር ከተማ በተለምዶ " አባይ ማዶ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ዳያስፖራ በሚወስደው አስፓልት መንገድ መገንጠያ ላይ በሚገኝ የምግብ እና መጠጥ መሸጫ የንግድ ተቋም ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ 3 ሰዎች ሲሞቱ 10 ሰዎች ቆስለዋል።
የቦምብ ፍንዳታው ከተፈፀመበት ቦታ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው የአዲስ ዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ተወካይ ዶ/ር ምትኩ ተገኝ ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥ " በትላንትናው ዕለት በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ወደ ሆስፒታላችን 15 የሚሆኑ ታካሚዎች መጥተዋል ፤ ከዚያ ውስጥ ሶስት እንደደረሱ የሞቱ ነበሩ፣ 2 ታክመው ወደቤታቸው ሄደዋል ፤ አንደኛው ሪፈር ተፅፎለታል ወደ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ሌሎቹ ግን እዚህ በእኛ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው ፤ አጠቃላይ ዘጠኝ ናቸው። " ብለዋል።
ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን የሰጡት አንድ የአይን እማኝ ፥ " ለሁለት ሃያ ጉዳይ ነው፤ እንደፈነዳ ወጣ ከዛም ስናይ ሁለት ሰው ወድቋል ፤ ልዩ ኃይል እና ፖሊስ መጥተው አነሷቸው ፤ ከዛ ውጭ እኛንም በተኑን ወደቤት ግቡ አሉን ገባን። ቦንቡን የጣለው አካል አይታወቅም ልክ ፈነዳ እዛው አካባቢ ያለው ሰውም አላወቀውም ከየትኛው አካል ይጣል የመንግስት አካል ይጣለው ፣ ግለሰብ ይጣለው አይታወቅም። ጥዋት ስንጠይቅ ጎረቤት ያሉ ሰዎችን 4 ሰው ሞቷል ሌሎች ቁስለኛ ናቸው አሉ። የወደቁ ሰዎችን የልዩ ኃይል እና ፖሊስ አባላት ናቸው መጥተው ያነሱት ፤ ሁኔታውንም ያረጋጉት " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።
በትላንትናው የቦምብ ፍንዳታ ህይወታቸው ያለፈው በሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ የነበሩ ወጣቶች እንደነበሩ የአይን እማኙ ገልጸዋል።
ከክልል ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ውሳኔ ጋር በተያያዘ በባህር ዳርም ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን ከትላንት ጀምሮ እንደ ሆስፒታል፣ ባንክ የመሰሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቀር ሌሎች የንግድ ተቋማት ስራ ማቆማቸውን ቪኦኤ ሬድዮ ከባህር ዳር ዘግቧል።
ፎቶ ፦ ፋይል

#BlueBell
ካሉበት የዓለም ክፍል ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለፋሲካ በዓል ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ!
ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲልኩ እድሉን አመቻችቷል። ከእርሶ የሚጠበቀው ደውሎ ማዘዝ ብቻ ነው! ደስታና ምርቃቱን በፎቶና በቪዲዮ እንልክሎታለን።
📞 - 0911359234 (WhatsApp NO.) / 0954882764 ወይም በቴሌግራም @yordiflower ላይ ያግኙን።
ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 https://bluebell-gifts.com/
ለበለጠ መረጃ 👉 t.me/bluebellgiftstore
አድራሻ: አዲስ አበባ፣ 22፣ ትጋት ህንጻ F2-23 - ቀድመው ለሚመዘገቡ ቅድሚያ እንሰጣለን!
ካሉበት የዓለም ክፍል ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለፋሲካ በዓል ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ!
ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲልኩ እድሉን አመቻችቷል። ከእርሶ የሚጠበቀው ደውሎ ማዘዝ ብቻ ነው! ደስታና ምርቃቱን በፎቶና በቪዲዮ እንልክሎታለን።
ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 https://bluebell-gifts.com/
ለበለጠ መረጃ 👉 t.me/bluebellgiftstore
አድራሻ: አዲስ አበባ፣ 22፣ ትጋት ህንጻ F2-23 - ቀድመው ለሚመዘገቡ ቅድሚያ እንሰጣለን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።
ፓርቲው በዛሬው መግለጫ የብልጽግና ፓርቲ ትናንት ሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ላወጣው መግለጫ ምላሽ ሰጥቷል።
ብልፅግና ትላንት ባወጣው መግለጫ የክልል ልዩ ኃይል ፖሊሶችን ' መልሶ የማደራጀት ' ውሳኔ በብዙ ጥናት፣ በጥልቅ ውይይት፣ በሰከነ ንግግር እና በጋራ መግባባት የተደረሰበት ውሳኔ መሆኑን ገልጿል።
ልዩ ኃይልን ትጥቅ የማስፈታት ሳይሆን የተሻለ የማስታጠቅ ፤ የመበተን ሳይሆን በጠንካራ መሰረት ላይ የማደራጀት ሥራ ላይ መሆኑን ብልፅግና ገልጿል።
የልዩ ኃይል አባላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የተለየ አክብሮት እና ፍቅር እንዳለው፤ ውሳኔው በአማራ ክልል ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተመሳሳይ የጊዜ መስመር የሚተገበር መሆኑን በትላንት መግለጫው አሳውቋል።
አብን ፤ የብልጽግና ፓርቲ ያወጣው መግለጫ እውነታን የካደ እና አሁንም ገዥው ፓርቲ ለመፍትሄው ዝግጁ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው ብሎታል።
ገዥው ፓርቲ ውሳኔው በአማራ ክልል ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተመሳሳይ የጊዜ መስመር የሚተገበር ነው ቢልም ከአማራ ክልል በቀር በየትኛውም ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላትን ትጥቅ የማስፈታት ወይም በገዥው ፓርቲ አነጋገር “መልሶ የማደራጀት” እንቅስቃሴ አልተደረገም ሲል ገልጿል።
አብን " ገዥው ፓርቲ ሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የተስማሙበት ውሳኔ ነው እያለ ቢሰነብትም ፣ የአማራ ክልልን ጨምሮ የየትኛውም ክልል ካቢኔ ወይም ምክር ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ ያደረገው ውይይት ሆነ ያሳለፈው ሕጋዊ ውሳኔ የለም " ብሏል።
ለዚህም ፓርቲው ማስረጃዎች ያላቸውን እንደሚከተለው አቅርቧል ፦
- የማስፈጸሚያ እቅድ ነው የተባለው ሰነድ በፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ደረጃ ውይይት የተደረገበት በቀን 30/07/2015 ዓ.ም ነው።
- የሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈው በቀን 02/08/2015 ዓ.ም መሆኑ መገለጹ፣ ገዥው ፓርቲ ያወጣው መግለጫ እውነትነት የራቀው መሆኑን የሚያጸና ነው ብሏል።
ገዥው ፓርቲ የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የተለየ አክብሮት እና ፍቅር እንዳለው ቢገልጽም በአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ላይ የተደረገው እና የሆነው ግን የመግለጫውን ቃል ከምጸት የሚያስቆጥረው ነው ብሎታል።
አብን የአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላት ከፍተኛ አመራሮች ፣ የብርጌድ እና የክፍለጦር አዛዦች በድንገት ከሥራ ውጭ መደረጋቸውን ፤ የልዩ ኃይሉ የእዝ ሰንሰለት እንዲፈርስ መደረጉን፣ የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት ስንቅ ፣ ሎጂስቲክ እና ደሞዝ ተነፍገው ለርሃብ እና ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸው እና ከካምፕና ከግዳጅ ምድብ ቦታቸው እህል ውሃ ወደሚያገኙበት ቦታ ለመድረስ በርካታ መቶ ኪሎሜትሮችን በእግራቸው ለመጓዝ የተገደዱበት ሁኔታ መስተዋሉን ገልጿል።
አብን ፓርቲ፤ የገዥውን ብልፅግና ፓርቲ ውሳኔ በመቃወም የክልሉ ሕዝብ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተቃዉሞ እያሰማ መሆኑን አመልክቷል።
በብልፅግና የተሳሳተ ውሳኔ ምክንያትም ላለፉት በርካታ ቀናት በአማራ ክልል ፦
- መደበኛ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለዋል
- በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ የጸጥታ መደፍረስ የሰው ህይወት አልፏል
- የክልሉ ዋና ዋና ከተሞች የቀውስ አስተዳደር ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ተገደዋል ሲል አሳውቋል።
አብን ፓርቲ የፌደራል መንግስት እና የአማራ ክልል መንግስት የክልሉ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ያቀረበውን ጥያቄ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)