TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የዘንድሮው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ። የዘንድሮው ኢፍጧር ስነስርዓት " ኢፍጧራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን እጅግ ከፍተኛ የሆነ ምዕመን ስነስርዓቱን ታድሟል። በሌላ በኩል ፥ የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢፍጧር ፕሮግራሙ #በሰላም_መጠናቀቁን አሳውቋል። ለፕሮግራሙ በሰላም መጠናቀቅ የከተማው ነዋሪ በተለይም የሙስሊሙ ማህበረሰብ…
ፎቶ ፦ ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወነው በኢትዮጵያ ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት ፤ ስነስርዓቱን እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ታድሞት ነበር።
የፎቶ ባለቤት ፦ ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው
#ረመዷን
@tikvahethiopia
የፎቶ ባለቤት ፦ ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው
#ረመዷን
@tikvahethiopia
" ሆሣዕና '' (የዐብይ ፆም 8ኛ ሳምንት)
እንኳን አደረሳችሁ !
ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ፆም እሁዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።
ሆሣዕና ማለት የቃሉ ትርጉም " እባክህ አሁን አድን " ማለት ነው።
ዕለቱ ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም ሽማግሌዎች እና ሕፃናት '' ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሣዕና በአርያም '' በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት ነው፡፡
ይህ ዕለት በቤተክርስቲያን ውስጥ ዘንባባ ተይዞ፣ እየተዘመረ እጅግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ይታሰባል።
በዐብይ ጾም ከሰርክ ሆሣዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡
በዚህ ጊዜ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት ካህናት መስቀል በእጃቸው አይዙም፣ አያሳልሙም ፣ ይፍቱኝ ተብሎ ወደካህን አይቀረብም፤ ይህ ሳምንት የጌታን የመጨረሻው ስቃይ የሚታሰብበት ነው።
ፎቶ ፦ ፋይል እና ከማህበራዊ ሚዲያ የተሰበሰበ

" ሆሣዕና '' (የዐብይ ፆም 8ኛ ሳምንት) እንኳን አደረሳችሁ ! ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ፆም እሁዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና ማለት የቃሉ ትርጉም " እባክህ አሁን አድን " ማለት ነው። ዕለቱ ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም ሽማግሌዎች…
#ሆሣዕና
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የ2015 ዓ.ም የሆሣዕና በዓል ምክንያት በመድረግ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ተገኝተው ቃለምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።
በዛሬው ዕለት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የ2015 ዓ,ም ሆሣዕና በዓል አስመልክተው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተገኝተው ጸሎተ ቅዳሴውን በመምራት ሰፊ ትምህርት፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።
መረጃው / ፎቶው የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ነው።

#Update
የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ፤ የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ የማደራጀት ሥራ ለሕዝብ አገልግሎት መስዋዕትነት ሲከፍሉ የነበሩ የልዩ ኃይል አባላትን ለተጨማሪ ተልእኮ ከማዘጋጀት ያለፈ ዓላማ የለውም ሲሉ ተናገሩ።
ይህንን ያሉት ክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት እየተከናወነ የሚገኘውን ሥራ አስመልክቶ የፌደራልና የክልል የጸጥታ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኃላ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ ነው።
አቶ ደሳለኝ ጣሰው ፤ የልዩ ኃይል አባላትን መልሶ ማደራጀቱ ለተጨማሪ ተልዕኮ ከማዘጋጀት ያለፈ ዓላማ የለምው ያሉ ሲሆን " ልዩ ኃይሉን መልሶ የማደራጀት ሥራው መጠራጠርን በማስቀረት ዜጎች የሚተማመኑበትን ኀይል ለመገንባት ያግዛል " ብለዋል።
የልዩ ኃይል አባላቱ እንደ የሙያቸው ሥልጠና እንደሚወስዱ ከዚያም ፍላጎታቸውን መሰረት በማድረግ ወደ ተለያዩ የጸጥታ ዘርፍ መዋቅሮች ውስጥ እንደሚገቡ አመልክተዋል።
በፌደራልና የክልል የጸጥታ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ውይይት ላይ የክልል ልዩ ኃይሎች ላይ እየተደረገ ያለው የመልሶ ማደራጀት ሥራ " ለተወለድኩበት ብሔር ነው የቆምኩት የሚለውን እሳቤ በማስተካከል " ኢትዮጵያውያን በእኩል የሚተማመኑበት የጸጥታ አካል ለመፍጠር ይረዳል ተብሏል።
" ልዩ ኀይሉ ሊበተን ነው ፤ ሊፈርስ ነው፤ ትጥቅ ሊፈታ ነው " በሚል የሚነዛው አሉባልታ ትክክል እንዳልሆነ ተነግሯል።
መንግሥት የልዩ ኃይል አባላትን መልሶ የማደራጀት እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚገኝ እየገለፀ ባለበት በዚህ ወቅት በተለይ በአማራ ክልል አካባቢዎች ሂደቱን የሚቃወሙ ነዋሪዎች መንገድ በመዝጋት፣ እንቅስቃሴ በማቆም እየተቃወሙ ይገኛሉ።
ተቃውሞው የአማራ ህዝብ የደህንነት ስጋት ባልተቀረፈበት ሁኔታ ትጥቅ ለማስፈታት የተጀመረ እንቅስቃሴ ነው ፣ ህወሓት ትጥቁን ሙሉ በሙሉ ባልፈታበት ሁኔታ የሚፈፀም ነው ፣ ይበልጥ የአማራ ክልልን ህዝብን ለጥቃት በሚያጋልጥ ሁኔታ እየተደረገ ያለ ነው ፤ ከዚህ አልፈ ሲል ሂደቱ ለምን አማራ ክልል ላይ በድብቅ እንዲጀመር ተደረገ በሚል እንደሆነ ለመስማት ተችሏል።
የፌዴራል መንግሥት ከቀናት ለፊት በሰጠው መግለጫ በሁሉም ክልል በተመሳሳይ ወቅት የልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ስራ እንደጀመረ ፣ ትጥቅ መፍታ የሚባል ነገር ከዚህ ጋር እንደማይገናኝ ሂደቱ ላይ እንቅፋት ለመሆን እየሞከሩ ያሉት ሀሰተኛ መረጃ ለህብረተሰቡ እያሰራጩ ያሉ አካላት ስለመሆናቸው ገልጿል።

Photo
#Update
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መንግስት ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት የጀመረውን ተግባር የሚቃወሙ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ዛሬም መቀጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ዛሬ በጎንደር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን የሰልፉ ተካፋዮች " የአማራ ልዩ ኃይል ለአማራ ህዝብ የጀርባ አጥንት ነው ፤ " የእርስቶቻችን ጉዳይ ለአፍታ የምንረሳው አይደለም " የሚሉና ሌሎችም መልዕክቶችን በማስተላለፍ የመንግሥትን ተግባር ተቃውመዋል።
በላሊበላ ከተማ በተመሳሳይ " የአማራ ልዩ ኃይል የጀርባ አጥንታችን ነው፤ ከልዩ ኃይል ላይ እጃችሁን አንሱ " በሚል የመንግሥትን ውሳኔ የሚቃወሙ መልዕክቶች የተላለፉበት ሰልፍ መደረጉ ተሰምቷል።
ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያዎች

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ዛሬ እሁድ ባወጣው መግለጫ መንግሥት ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘ ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ በመግፋቱ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ መቀስቀሱን ገልጿል።
ፓርቲው እስካሁን ድረስ ለሀገራዊ አንድነት እና ሰላም ሲባል ጉዳዩን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ሲከታተል መቆየቱን ገልጾ ይሁንና መንግስት ችግሩን በሰከነ መንገድ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ከዕለት ወደ ዕለት የለየለት የኃይል ፣ የአፈና እና የማደናገር አማራጭ እየገባ መሆኑን መረዳቱን አመልክቷል።
" መንግስት ችግሩን በሰከነ መንገድ ፣ በውይይት ፣ በጋራ መግባባት እና በመተማመን የመፍታት ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም በስህተት ላይ ሌላ ስህተት እየደረበ እና ችግሩን በአፈና እና በጉልበት ለመፍታት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዛሬ ጀምሮ ለችግሩ ዘላቂ እልባት እስከሚሰጥ ድረስ መንግስት እና ግብረ-አበሮቹ በአማራ ልዩ ኃይል ፣ በፋኖ እና በአጠቃላይ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚነዟቸውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳዎች በይፋና በተከታታይ አጋልጣለሁ " ብሏል።
አብን በመግለጫው የአማራ ልዩ ኃይልን ለማፍረስ እና ትጥቅ ለማስፈታት መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ እና የሚያደርገው እንቅስቃሴ ኃላፊነት የጎደለውና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ድጋሜ አሳውቋል።
የብልፅግና ፖርቲ ሥራ አስፈፃሚ ያሰፈው ውቃኔ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ ያላገናዘበ ፣ መርኅ አልባ ፣ አድሏዊ እና አምባገነናዊ ነው ሲል ገልጾታል።
ውሳኔውና የአፈፃፀም ሂደቱ በሕግ አግባብ የተመራ ፣ መርኅ ተኮር እንደሆነ ፣ ውይይት እንደተደረገበት እና መግባባት የተደረሰበት እንደሆነ ለማስመሰል የሚቀርቡ አስተያየቶችም በአጠቃላይ ሃሰት ናቸው ብሏል።
(የአብን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)