#ErmiasAyele
ኢትዮጵያዊው ሮም ላይ በባዶ እግሩ ሊሮጥ ነው።
ከቀናት በኃላ (እሁድ) የ2023 የሮም ማራቶን ይካሄዳል።
በዚህም ማራቶን ታሪክ ራሱን ይደግማል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያዊው የባዶ እግር ሯጭ እንዲሁም ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ቁልፍ ሰው (ዳይሬክተር) በመሆን የሰራው የ45 ዓመቱ ኤርሚያስ አየለ ሙሉ ማራቶን በባዶ እግሩ ይሮጣል።
ኤርሚያስ አየለ ይህንን የሚያደርገው ለኢትዮጵያው ታላቅ አትሌት አበበ ቢቂላ ክብር እንዲሁም ለሀገር ገፅታ ግንባታ ሲል ነው።
" አበበ ቢቂላ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት የመጀመሪያው ጥቁር በመሆኑ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለአፍራካውያን ስኬት መሰረት ጥሏል " የሚለው ኤርሚያስ " ሆኖም ግን ለሰራው ታሪክ የሚገባውን ያህል እውቅና እንዳላገኘ ይሰማኝ ነበር " ብሏል።
ኤርሚያስ ፤ የአትሌት አበበ ቢቃላ ታሪክ ሁሌም እንደሚያነሳሳው ገልጾ ለዚህም እሱ ለአትሌቲክስ እና ለኢትዮጵያ ላደረገው ነገር ክብር እና ምስጋና ለመስጠት በተመሳሳይ ቦታ እና በተመሳሳይ መንገድ ታሪክ በሰራበት ቦታ በባዶ እግሩ እንደሚሮጥ አስረድቷል።
የሮም ውድድሩ ቀላል እንደማይሆንና ስሜታዊም የሚያደርግ እንደሆነ የገለፀው ኤርሚያስ " ይህን ትልቅ ትርጉም ያለውና ታሪካዊ ውድድር ለማድረግ ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ " ብሏል።
ኤርሚያስ ውድድሩን ከ3:30 እስከ 4:00 ባለው አጠናቅቃለሁ ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጾ የሮሙ ማራቶን በመጪዎቹ 18 ወራት ከአበበ ቢቂላ ጋር በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ግንኙነት ባላቸው በአቴንስ ፣ ቶኪዮ እና ፓሪስ ማራቶን በባዶ እግር ለሚያደርገው የማራቶን ሩጫ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግለት አመልክቷል።
የባዶ እግር የማራቶን ሩጫው አትሌት አበበ ቢቂላ ለሰራው ታሪክ ክብር ለመስጠት ከማድረግ ባለፈ ለሀገር ገፅታ ግንባታ ያለው አስታዋፆ ከፍተኛ ስለመሆኑ ገልጿል።
ኤርሚያስ ከዚህ ቀደም የታላቁ ሩጫን ሙሉውን ሁለት ጊዜ ፤ የሀዋሳ ግማሽ ማራቶን ሙሉ በባዶ እግሩ የሮጠ ሲሆን ለእሁዱ የሮም ማራቶን ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።
ኤርሚያስ አየለ በሮም ስለሚያደርገው የባዶ እግር የማራቶን ሩጫ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ያዘጋጁት ዘገባዎች ፦
https://www.aipsmedia.com/aips/pages/articles/2023/33598.html

Credit 👇
#ኤልያስመሰረት #ሀይለእግዚአብሔር_አድሃኖም
@tikvahethiopia

#ብርሃን_ባንክ
በሆቴሎች፤ በሱፐርማርኬቶች እና በቅርንጫፎቻችን በሚገኙት የፖስ ማሽኖቻችን የቪዛና ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው ግብይትዎን ያቅልሉ፡፡
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://yangx.top/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!

#አሚጎስ_ብድር_እና_ቁጠባ
ንግድዎን በፍጥነት ለማሳደግ፣
በአጭር ጊዜ የሚደርስ አስቸኳይ ብድር፣
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ፡ https://yangx.top/amigossacco

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ብሊንከን ከኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተወያዩ። የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ የስራ ጉብኝት ላይ ይገኛሉ። በዚህም ጉብኝታቸው ከኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር መወያየታቸው ታውቋል። ውይይቱን በተመለከተ ዶ/ር ወርቅነህ ፤ አዲስ አበባ ውስጥ ከብሊንከን ጋር ተገናኝተው መወያያታቸውን ይኸው ውይይትም ካለፈው ዓመት የናይሮቢ ውይይት የቀጠለ…
#Update
" በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ስምምነት ላይ ተደርሷል " - የጠ/ሚ ፅ/ቤት
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ቢንከንን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ይህን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ባወጣው መረጃ ውይይቱ በተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።
በውይይቱ በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።
ኢትዮጵያ በሰላም ስምምነቱ ላይ እያስመዘገበች ያለችው ስኬት ተቀባይነት አግኝቷልም ብሏል።
በኢኮኖሚው፣ በልማት ጥረቶች፣ በተለይ በግብርናና በቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ያሉ ጉዳዮችም ትኩረት እንደተሰጠባቸው ፅ/ቤቱ አመልክቷል።

#አብን አብን የፌዴራል መንግስቱ/ገዢው ብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከንቲባን ከስልጣን እንዲያስነሳ እና ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠየቀ። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ ( #አብን ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዛሬ ለምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት አጥብቆ አውግዟል። ፓርቲው ከንቲባ አዳነች አበቤ ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ ም/ ቤት ባቀረቡት ሪፖርት " ከአንዳንድ ክልሎች የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት…
#Update
እናት፣ መኢአድ እና ኢሕአፓ ፓርቲዎች ከትላንቱ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከንቲባ አዳነች አቤቤ ሪፖርት ጋር በተያያዘ ዛሬ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።
በመግለጫቸው ላይ ፤ " ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ አልፎም በመረጡት ቦታ የመኖር መብት በሕገ መንግሥቱ ለዜጎች የተሰጣቸው መብት እንጂ አንዳንድ ባለስልጣናት ደስ ሲላቸው የሚቸሩት ካልፈለጉ ደግሞ የሚነፍጉት ጉዳይ አይደለም " ብለዋል።
ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ከተማ በሚጓዙ መንገደኞች ላይ እናቶቻችን ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት ሰበባ ሰበብ እየተፈለገ ሲፈጸም የነበረው ማዋከብ፣ እንግልትና ማጉላላት ከነገ ዛሬ መሻሻል ይታይበታል ተብሎ ተስፋ ሲደረግ ይባስ ብሎ “ከአንዳንድ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት መንግሥትን በመጣል በኃይል ስልጣን ለመቆጣጠር ያለመ ነው” በሚል የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በቀን 5/07/2015 ዓ.ም ለምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ላይ የገለጹበት መንገድ ያለፈውን ስህተት ከማረም ይልቅ የዜጎችን ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት የሚነፍግ፣ በከፍተኛ ሴራና ፍረጃ ለበለጠው የዘር ፍጅት የሚያመቻችና ዜጎችን የማሸማቀቅ አካል ነው ሲሉ ፓርቲዎቹ ገልፀዋል።
" በሌላ በኩል ፥ ትናንትና ካህን በጥፊ ሲመቱ፣ ሕጻናትንና ሴቶችን ሲያዋክቡና በማንነታቸው ሲያሸማቅቁ፣ ሲሰውሩ፣ ሲገድሉና ሲዘርፉ ለኖሩ ኃይሎች ሽፋን የመስጠትና ጥብቅና የመቆም አካል አድርገን እንወስደዋለን። " ሲሉ ፓርቲዎቹ በጋራ መግለጫቸው ገልፀዋል።
" ድርጊቱ በ ' ኦሮሚያ ብልጽግና ' በንግግርም በተግባርም በተጠናና መዋቅራዊ በሆነ ሁኔታ እንደሚፈጸም ዐቢይ ማረጋገጫና በቀጣይም ሰቆቃና ማወከቡ ቢብስ እንጂ እንደማይረግብ ጉልህ ማሳያ ነው "ም ብለዋል።
ፓርቲዎቹ ፤ " ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የሚከለከሉ ዜጎቻችን ጉዳይ የሌላ ሀገር ድንበር አቋርጠው በሕገወጥ መንገድ ለመግባት የሚሞክሩ መንገደኞች እንጂ ከሀገራቸው አንድ ክፍል አባቶቻቸው ወደአቀኑላቸው ዋና ከተማቸው የሚደረግ ሕጋዊ እንቅስቃሴ አይመስልም " ሲሉም በመግለጫው ላይ አስፍረዋል።
በሌላው ዓለም ቢሆን እጅግ መርዘኛ እና ፍጅት ቀስቃሽ ንግግሮችና ተናጋሪዎች ተገቢው እርምት በቶሎ በተሰጣቸው ነበር ያሉት ፓርቲዎቹ በእኛ ሀገር ኹኔታ ሕጋዊነት ሳይሆን ሕገ ወጥነት፣ “የእኛ” ሳይሆን “ለእኔ ብቻ” ባዮች፣ ተጠያቂነት ሳይሆን ተረኝነት የሰፈነበት በመሆኑ ለዚህ አልታደለንም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ሕግና ሥርዓት ሰፍኖ አጥፊዎች በፍትሕ አደባባይ እንዲቀርቡ የበኩሉን እንዲወጣ፣ እንዲህ ላሉ ከፋፋይ ንግግሮችም ጆሮ ባለመስጠት አንድነቱን እንዲያጸና ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
(ሙሉ መግለጫቸው ከላይ ተያይዟል)

Photo
በኢትዮጵያ ምን ያህል መስማት የተሳናቸው ዜጎች ይኖራሉ?
በወቅታዊ ጥናት ላይ ተሞርክዞ የቀረበ መረጃ ባይኖርም እንደማሳያ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ፣ የዓለም የጤና ድርጅትና የዩኒሴፍ ጥናቶችን መመልከት ይቻላል፡፡
የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በ2005 ዓ.ም በሰራው ዳሰሳ ኢትዮጲያ ከህዝብ ቁጥሯ 3 በመቶ የሚሆነው አካል ጉዳተኛ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ከዚህ ውስጥም 20 በመቶ ሚሆኑት (720 ሺ) መስማት የተሳናቸው መሆናቸውን ይጠቅሳል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ በ2003 ዓ.ም ባወጡት ሪፖርት ከኢትዮጲያ ከህዝብ ቁጥሯ 15 ሚሊዮን ዜጎቿ (17.6 በመቶ) አካል ጉዳተኛ መሆናቸውን ገልጾ፤ ከዚህ ውስጥም 20 በመቶ ሚሆኑት (3.5 ሚሊዮን በላይ) መስማት የተሳናቸው ይላል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት በ2013 ዓ.ም ባወጣው ቁጥራዊ ማስረጃ (Fact Sheet on Deafness and Hearing loss) ላይ ደግሞ በኢትዮጵያ ከ5 ሚሊዮን በላይ መስማት የመስማት ችግር ያለባቸው ዜጎች መኖራቸውን ይጠቅሳል።
ዩኒሴፍ ከሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር በ2008 ዓ.ም በሰራው ዳሰሳ የአካል ጉዳተኛ ዜጎች ከአጠቃላይ የህዝብ ቁጥሩ 9.3 በመቶ (7.8 ሚሊዮን) መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ ከላይ በሁለቱም ጥናቶች የተወሰደውን ስሌት ተጠቅመን 20 በመቶዎቹ መስማት የተሳናቸው ናቸው ብንል ከ1.5 ሚሊዮን በላይ መስማት የተሳናቸው ዜጎች ይኖራሉ።
#ማስታወሻ፡ በተለያየ ጊዜያት የተሰሩትና ማግኘት የቻልናቸው የጥናት ውጤቶች ግኝት በጣም የተራራቁ ቢሆንም ለማሳያ ያክል የቀረቡ ናቸው። ቁጥራዊ መረጃዎቹ ወቅታዊ መረጃን ገላጭ አይደሉም፡፡ ተጨማሪ መረጃዎች ካሎት @RWethiopia ላይ ያካፍሉን
#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

" ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ ይቆያሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ/ም ፤ በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የላቀ ውጤት ላመጡ 273 ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የእዉቅናና ሽልማት ማበርከታቸውና በዕለቱ ለተማሪዎቹ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ…
#MoE
" የውጭ የትምህርት እድል ያገኛችሁ ተማሪዎች ወደ ተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲ ግቡ " - ትምህርት ሚኒስቴር
በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ያመጡና የውጪ ሀገር የትምህርት ዕድል /Scholarship/ የተሰጣቸው 273 ተማሪዎች ቀደም ሲል በትምህርት ሚኒስቴር ወደተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ትምህርት ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
ተማሪዎቹ የውጪ ሀገር ትምህርቱ የሚጀመረዉ ከመስከረም/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመሆኑ ቀደም ሲል ወደተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ነው ሚኒስቴሩ ያሳሰበው።
ለውጪ ሀገር ትምህርታቸው የሚያግዝ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ቀደም ሲል ከተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር የሚፈጸም መሆኑም ተገልጿል፡፡
በዚህ ጉዳይ በተናጠል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የሚመጣ ተማሪ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ ግልጿል፡፡
@tikvahuniversity

#Update " በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ስምምነት ላይ ተደርሷል " - የጠ/ሚ ፅ/ቤት ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ቢንከንን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ይህን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ባወጣው መረጃ ውይይቱ በተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊ…
#USA #ETHIOPIA
አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አደረገች።
ለሥራ ጉብኝ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አድርገዋል።
አንቶኒ ብሊንከን እንዳስታወቁት ድጋፉ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አማካኝነት የሚሸፈን ነው፡፡
ድጋፉም በተለያዩ ምክንያቶች በችግር ለተጋለጡ ወገኖች ለምግብ፣ ለመድሃኒት፣ ለንጹህ የመጠጥ ውሃ የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።
ይህም በግጭት ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ፣ በድርቅ ለተጠቁ እና ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ሕይወት አድን ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስችል ብሊንከን ማሳወቃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘገቧል።

#EOTC ቅዱስ ሲኖዶስ የፊታችን ረቡዕ #አስቸኳይ ጉባኤ ሊያደርግ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ረቡዕ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚካሄድ ዛሬ አሳውቋል። በዚህም በአዲስ አበባ አቅራቢያና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ አዳራሽ እንዲገኙ የቅዱስ…
#EOTC
ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሰብሰባውን ያደረገ ሲሆን ስብሰባውን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው ከዚህ ቀደም የተደረሰውን ባለ 10 ነጥብ ስምምነት ቤተክርስቲያን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በመግለጫ አረጋግጣና በሮቿን ክፍት አድርጋ ለሰላም ከፍተኛ ጥረት በምታደርግበት ወቅት ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የመጡ ቢሆንም 25ቱ ግለሰቦች ግን የሰላም ጥሪውን ከመቀበል ይልቅ እስከአሁን ድረስ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው መቀጠላቸውን አሳውቋል።
ግለሰቦቹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን እግድ በመጣስም የአህጉረ ስብከትን ጽ/ቤት እየሰበሩ በመግባት በሌላቸው ሥልጣን ክህነት በመስጠት፣ በቤተክርስቲያን መዋቅር ላይ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞችን በመመደብ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው በመቀጠል ላይ ይገኛሉ ብሏል።
በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በአዲስ አበባና በአካባቢው የሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለስብሰባ በመጥራት መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ሦስቱ የቀድሞ ብፁዓን አባቶች በአካል ቀርበው በሰጡት ቃል በተከናወነው ድርጊትና ድርጊቱን ተከትሎ በተፈጸሙት ክስተቶች ማዘናቸውንና በቀጣይ ሕገ-ወጥ ድርጊቱን እንደሚቃወሙና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶሱን መመሪያ አከብረው ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸውን በመግለጫው አመልክቷል።
ቅዱስ ሲኖዶሱም የሦስቱን የቀድሞ አባቶች ሐሳብ በመቀበል ጉዳዩን አስመልክቶ በሰፊው ከተወያየ በኋላ የሰላም ጥሪ አስተላልፏል፡፡
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#EOTC ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሰብሰባውን ያደረገ ሲሆን ስብሰባውን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው ከዚህ ቀደም የተደረሰውን ባለ 10 ነጥብ ስምምነት ቤተክርስቲያን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በመግለጫ አረጋግጣና በሮቿን ክፍት አድርጋ ለሰላም ከፍተኛ ጥረት በምታደርግበት ወቅት ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው…
#የሰላም_ጥሪ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ተከታዩን የሰላም ጥሪ አቅርቧል ፦
1. ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ በስምምነቱ መሠረት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ መጥተው በበዓታቸው ተወስነው እየኖሩ ስለሆነ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው እንዲደረግ፣
2. ሃያ አምስቱን ግለሰቦችን በሚመለከት ምንም እንኳን በሕ-ወጥ አድራጐታቸው የቀጠሉ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያኗ ለሀገሪቱ ሰላም ካላት የጸና አቋም አንጻር አሁንም በድጋሚ ለመጨረሻ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት በተደረሱት 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ከዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በጽሑፍ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉና በቤተ ክርስቲያ ቀኖና መሠረት ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቀኖናቸውን ተቀብለው እንዲፈጽሙ፣
3. የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለሰላም ስምምነቱ ላደረጉት አስተዋጽኦ ቤተ ክርስቲያኗ ምስጋናዋን ያቀረበች ሲሆን በቀጣይ በተደረሰው 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ሕገ-ወጦቹ ግለሰቦች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለሕግ ተገዥ እንዲሆኑ የበኩላቸውን መንግሥታዊ ሚና እንዲወጡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን በድጋሚ አስተላልፋለች።
4. በተደረሰው ስምምነት መሠረት በሕገ-ወጥ መንገድ አህጉረ ስብከትና መንበረ ጵጵስና ሰብረው የያዙ ግለሰቦችን በተመለከተ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት ተገቢውን የሕግ ማስከበር ሥራ በመሥራት ከቤተ ክርስቲያን ይዞታ በማስወጣት ለቤተ ክርስቲያናኗ ሕጋዊ የሥራ ኃላፊዎች በማስረከብ የቤተ ክርስቲያኒቱ የእለት ከእለት ተግባርና ሐዋርያዊ አገልግሎት ያለምንም የጸጥታ ሥጋት እንዲከናወን እንዲሁም በተደረሰው ስምምነት መሠረት እስከአሁን መፈታት ሲገባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎችና ምእመናን እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን አስተላልፋለች።
5. ሃያ አምስቱን ግለሰቦች በሚመለከት ከኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተደረገው ውይይት ርእሰ መስተዳድሩ በተደረሰው 10ሩ ስምምነት ነጥቦች መሠረት " ሃያ አምስቱንም ግለሰቦች አጠቃልዬ ወደ አዲስ አበባ አመጣቸዋለሁ " በማለት በገቡት ቃል መሠረት በአሁኑ ሰዓት ግለሰቦቹ በክልሉ መንግሥት አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ስለተሰማ የክልሉ መንግሥት በገባው ቃል መሠረት ለፈጸመው አድራጐት ቤተ ክርስቲያኗ ያመሰገናች ሲሆን ያልገቡትን ግለሰቦች በአጭር ጊዜ ውስጥ በተገባው ቃል መሠረት እንዲገቡ እንዲደረግ ቤተክርስቲያኗ ጥሪ አስተላልፋለች።
6. ውግዘቱን በሚመለከት ውግዘቱን የማንሳት ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለመጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ተጠቃለው ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲመጡ ጥሪ ተላልፏል።
ሙሉ መግለጫ ፦ https://yangx.top/tikvahethiopia/77044?single

At Jasiri, we care about ethical and value-driven entrepreneurship. Fellows are nurtured and guided to solve pressing global problems. In the long term, the Ventures they build will impact many. If you are looking to make a difference, apply today - http://jasiri.org/application