TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ቦረና

" በቡድንም ሆነ በተናጠል ድጋፍ መሰብሰብ አይቻልም " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ድጋፍ ለማድረግ በቡድንም ሆነ በተናጠል መሰብሰብ እንደማይፈቀድ የኦሮሚያ ክልል መንግስት አሳሰበ።

የክልሉ መንግስት ፤ በክልሉ አንዳንድ ዞኖች በተለይ በቦረና ዞን በተከታታይ አምስት የዝናብ ወቅት ዝናብ አለመጣሉን ተከትሎ ድርቅ መከሰቱ አስታውሷል።

በተከሰተዉ ድርቅ ምክንያትም መንግስት ባቀረበዉ ጥሪ መሠረት ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች በተለያዩ መንገዶች በገንዘብና በዓይነት ድጋፍ እየተሰበሰበ ይገኛል ብሏል።

ከዚህ በኋላ ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ወይም ከኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ እዉቅና ዉጭ #በቡድንም ሆነ #በተናጠል ድጋፍ ማድረግ የማይፈቀድ መሆኑን አሳስቧል።

ይህም የሚሰበሰበዉን ድጋፍ በአግባቡ ለማስተዳደር፣ ፍትሓዊ በሆነና ግልፅነት ባለዉ መንገድ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ውሳኔ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ገልጿል።

#ኦቢኤን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar 15ኛው የአፋር ሱልጣን በዓለሲመት ሰኞ ይከናወናል። የፊታችን ሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ሱልጣን አህመድ አሊሚራሕ  15ተኛው የአፋር ሱልጣን በመሆን  በዓለሲመታቸው እንደሚከናወን የአፋር ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ ዘግቧል። ለዚሁ በዓለሲመት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ዛሬ አዲስ አበባ  ገብተዋል። አዲስ አበባ ሲገቡ ከፍተኛ  አመራሮች ተገኝተው  አቀባበል አድርገውላቸዋል። @tikvahethiopia
#Afar

ቀጣይ የአውሳ ሱልጣኔት አልጋወራሽ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ በዓለሲመታቸዉን ለመከወን ዛሬ  የአፋር መዲና፣ ሰመራ መግባታቸውን የአፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።
   
ሱልጣን አህመድ አልሚራህ ሰመራ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመሬሮችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች አቀባባል አድርገዉላቸዋል።

በዓለሲመቱ የሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ/ም በአውሳ ሱስለጣኔት መናገሻ በሆነችው አይሳኢታ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከናወን ይጠበቃል።

በእለቱ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከሚገኙ እና በጀቡቲና ኤርትራ የሚገኙ የአፋር ማህበረሰብ ባህላዊ መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ ሰዎች እንዲሁም የፌድራልና የክልሉ መንግስት አካላት አምባሳደሮች እንደሚገኙ ይጠበቃል ተብሏል።

#አፋብመድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፤ ምክትል ፕሬዘዳንቱ በፖሊስ ታፍነው እንደተወሰዱበት አሳወቀ። ፓርቲው ምክትል ፕሬዘዳንቱ አቶ አምሃ ዳኘው ዛሬ 10፡00 ሰዓት ላይ ሲቪል በለበሱ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል ሲል አሳውቋል። አቶ አምሃ ዳኘው የታሠሩት የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ነገ እሁድ መጋቢት 03/2015 ዓ.ም. ለማካሄድ ከአንድ ቀን ያነሰ ጊዜ በቀረበት ወቅት ነው…
" ጉባኤው በተያዘለት እቅድ መሰረት ይደረጋል " - ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ፕሬዜዳንቱ አቶ አምሀ ዳኜው መፈታታቸውን አሳውቋል።

" አቶ አምሀ ዳኘው ከነበሩበት አፈና ተለቀዋል " ሲል ፓርቲው ገልጿል።

ፓርቲው ትግሉን እንደሚቀጥል እና የነገው ጉባኤ በተያዘለት እቅድ መሰረት የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል።

የባልደራስ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አምሀ ዳኜው ዛሬ 10 ሰዓት ላይ ሲቪል በለበሱ ኃይሎች መወሰዳቸውና በላዛሪስት አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ፓርቲው መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ጤፍ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስለ #ጤፍ ...

" አጠቃላይ የኑሮ ውድነቱን በተመለከተ የኛን መስሪያ ቤት #አይመለከትም " - ወ/ሮ በላይነሽ ረጋሳ (የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር)

🗣 ወ/ሮ አረጉ ጥፍጤ፦

" የጤፍ ዋጋ በጣም ጨምሯል፤ በወፍጮ ቤቶች ጤፍ የለም። በአንዳንድ ወፍጮ ቤቶች ቢገኝም እንደጤፉ ዓይነት እስከ 8 ሺ 500 መቶ ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።

25 ኪሎ ጤፍ በሁለት ሺህ ብር ገዝቻለሁ ነገር ግን ዋጋው በዚህ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ጤፍ ገዝቼ እንጀራ የምበላ አይመስለኝም።

በዜህ ዋጋ ለመግዛት እንኳን ምርቱን ማግኘት አልተቻለም ፤ ስለሆነ መንግሥት ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ ሊያየው ይገባል። "

🗣 አቶ መሀመድ ጀማል ፦

" በገበያው ላይ በቂ ጤፍ ባለመኖሩ ኅብረተሰቡ ሳያልቅ እንግዛ እየተባባለ ነው።

በወፍጮ ቤት ተቀጥሬ መስራት ከጀመርኩ አምስት ዓመት አልፎኛል። ነገር ግን የጤፍ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ምክንያት ቤተሰቤን ለማስተዳደር እንደዚህ የተቸገርኩበት ወቅት የለም።

ይህ ጉዳይ ሥር ሳይሰድ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተወካዮች ችግሩን በአስቸኳይ ሊፈቱት ይገባል።

🗣 አቶ አብርሃም ዳኜ ፦

" ኅብረተሰቡ ለዕለት ፍጆታ የሚውሉ ምርቶችን በአቅራቢያው በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያገኝ ይገባል፤ እየታየ ያለው የገበያ ዋጋ ግን የሚቀመስ አልሆነም።

በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማኅበረሰብ የዋጋ ጭማሪውን መቋቋም አልቻለም።

የዋጋ ጭማሪ ለዕለት ተዕለት በሚውሉ ምርቶች ላይ መደረግ የለበትም። የአገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን መሠረት ያደረገ አይደለም።

መንግሥት ለዕለት ተዕለት ፍጆታዎች የዋጋ ተመን አውጥቶ ሕግ የሚተላለፉ አካላት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል። "

🗣 በልደታ ክ/ከተማ የወፍጮ ቤት ባለቤት አቶ ሰለሞን ባይሳ (ስማቸው የተቀየረ) ፦

" የጤፍ አቅርቦት ችግር እና የዋጋ ጭማሪው ከኅብረተሰቡ ጋር ያለመተማመን ሁኔታ ውስጥ ከቶኛል። ወፍጮ ቤቴን ለአራት ቀን አልከፈትኩም።

ለኅብረተሰቡ የምሸጠው ጤፍ ስለሌለ ኅብረተሰቡ ጤፍ የደበቅኩ እየመሰለው ነው። ስለሆነም ከኅብረተሰቡ ጋር ላለመጋጨት ጥቂት ጤፍ ያላቸው ነጋዴዎችን ተለማምጬ ለኅብረተሰቡ ጤፍ አምጥቻለሁ።

የኅብረተሰቡ አቅም እና የገበያው ሁኔታም የሚጣጣም አይደለም። ስለዚህ መንግሥት ጉዳዩን በትኩረት ሊያስብበት ይገባል። "

🗣 የእህል በረንዳ ነጋዴ የሆኑት አቶ አማን ይሁን (ስማቸው የተቀየረ) ፦

" መንግሥት የንግድ ዘርፉን እንዲቆጣጠሩ ኃላፊነት የሰጣቸውን አካላት በዘርፉ ምን እየሠሩ እንደሆነ መመርመር ያለበት ሲሆን በኬላዎች አካባቢ እየተሠራ ያለውን ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ከሥር ነቅሎ ማጥፋት አለበት።

ወቅቱ ከፍተኛ ምርት ያለበት እና ኢትዮጵያ ሰላም የሆነችበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅት በተለየ ሁኔታ የእህል ዋጋ እንደ ሰማይ እየራቀ በመምጣቱ ዜጎችን ይበልጥ እያስጨነቀ ነው።

ስለሆነም ይህንን ጉዳይ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ መፍታት አለበት።

🗣 የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ ረጋሳ ፦

" አጠቃላይ የኑሮ ውድነቱን በተመለከተ የኛን መስሪያ ቤት #አይመለከትም። ጉዳዩ ዘርፈ ብዙ ተዋንያን ያሉት ነው።

ዋጋ ባልወጣበት ነገር ላይ ኃላፊነት መውሰድ አይቻልም።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሁን ለተፈጠረው የጤፍ ዋጋ ኃላፊነት 'ማንዴት' የለውም። የንግድ ሥርዓቱን በተመለከተ አጥንተን በቀጣይ ምላሽ የምንሰጥበት ይሆናል።

🗣 የአዲስአበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ፦

" በከተማ አስተዳደሩ በኩል ግብረኃይል ተቋቁሟል የተደረሰበትን በቀጣይ እናሳውቃለን "

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጉባኤው በተያዘለት እቅድ መሰረት ይደረጋል " - ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ፕሬዜዳንቱ አቶ አምሀ ዳኜው መፈታታቸውን አሳውቋል። " አቶ አምሀ ዳኘው ከነበሩበት አፈና ተለቀዋል " ሲል ፓርቲው ገልጿል። ፓርቲው ትግሉን እንደሚቀጥል እና የነገው ጉባኤ በተያዘለት እቅድ መሰረት የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል። የባልደራስ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አምሀ…
#ባልደራስ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያደርግ መከልከሉ አስታውቋል።

ፓርቲው ምንም እንኳን አዲስ አበባ በሚገኘው " ጋምቤላ ሆቴል " ጉባኤ ለማድረግ ፍቃድ ቢያገኝም በፀጥታ እና ደህንነት ኃይሎች በተፈጠረ ጫና ጉባኤውን ማድረግ ሳይችል መቅረቱን ገልጿል።

ፓርቲው ለሆቴሉ ክፍያ ለመፈፀም ከከንቲባ ፅ/ቤት የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ የተፃፈ የፍቃድ ወረቀት ለሆቴሉ ቢያሳይም ቀደም ብሎ " ከኦሮሚያ ፖሊስ መጥተው ስብሰባው እዚህ እንዳይካሄድ አስፈራርተውኛል " ስትል ምክትል ስራ አስኪያጇ መናግሯን ገልጿል።

" ማስፈራራት ህጋዊ አይደለም፣ ተቀባይነትም የለውም ፤ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ህጋዊ ወረቀት አለን ፤ ከምርጫ ቦርድም ህጋዊ ወረቀት ይዘናል አስተናግዱን " በሚል ፓርቲው ለሆቴሉ ጥያቄ ቢያቀርብም ምክትል ስራ አስኪያጇ ከኦሮሚያ ፖሊስ ባለፈው የደህንነት ኃይሎችም እየመጡ እያስፈራሩኝ ስለሆነ ክፍያ መፈፀም አትችሉም የሚል ምላሽ እንደሰጠች ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወኪሎች በስፍራው ተገኝተው የነበረውን ሁኔታ መታዘባቸውን ፓርቲው ገልጿል።

ባልደራስ ፓርቲ ትላንትም ምክትል ፕሬዜዳንቱ ታስረው መለቀቃቸውን አስታውሶ ዛሬ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ የምስክር ወረቀት እንዳያገኝ ከፍተኛ ጫና ስለተደረገበት ጉባኤውን ማድረግ አለመቻሉን አሳውቋል።

ጫና ሲደረግ የነበረው ትላንትን ጨምሮ ጉባኤውን ለማድረግ በነበረው ሂደት ውስጥ እንደሆነ የገለፀው ባልደራስ " እንዲህ ታፍነን አንቀጥልም እንዲህ ያሉ አፈናዎችን ሰብረን ለመውጣት ትግላችን ይቀጥላል ፤ በዚህ ተሰናክሎ እና ተደናቅፎ የሚቀር ኃይል የለም " ብሏል።

ፓርቲው ዛሬ የተከላከለውን ጠቅላላ ጉባኤውን በመመካከር በቀጣይ ቀስ ብሎ እንደሚያደርግ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ATTENTION

በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ።

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልጉ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ይህን ያሳወቀው ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን በሰጠው ቃል ነው።

በሶማሌ ክልል ከሚገኙ 11 ዞኖች ውስጥ በዘጠኙ ላይ ድርቅ የተከሰተ ሲሆን ድርቁ በሰዎች እና እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ብሏል ኮሚሽኑ።

አሁን ላይ ድርቁን ተከትሎ በሶማሌ ክልሉ አዲሱን ጥናት ሳይጨምር ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

በክልሉ እየተካሄደ ያለው አዲስ ጥናት ሲጠናቀቅ የተረጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተመላክቷል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ያሳወቀው ኮሚሽኑ የተረጂዎች ቁጥር ከፍተኛ እና ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞም ተጨማሪ አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥቷል።

ስለሆነም ፦
- መንግስታዊ ተቋማት፣
- የግል ድርጅቶች፣
- አጋር አካላት፣
- ታዋቂ ሰዎች እና ዳያስፖራዎች በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን በሰጠው ቃል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
" አሁን የመሳሪያ ድምጽ ጠፍቷል፤ የህጻናቱን ድምጽ ደግሞ በትምህርት ቤቶች መስማት እንፈልጋለን " - ያንቲ ሶሪፕቶ

የተመድ የሠብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) የሰብዓዊ ምላሽ እቅድ እንደሚያመላክተው በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ገልጿል። ከዚህ ውስጥ 161.4 ሚሊዮን የሚሆነው ለትምህርት የሚያስፈልግ ድጋፍ መሆኑን ነው የገለጸው።

በኢትዮጵያ ላለፉት 2 ዓመታት የዘለቀው ጦርነት በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ነው።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በትግራይ ክልል ብቻ ከ80 - 90 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ የስደተኞች መጠለያ ሆነዋል፤ ንብረታቸው ተዘርፏል/ወድሟል።

Save the Children የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት ፕሬዚዳንት ያንቲ ሶሪፕቶ ባላፉት ቀናት በኢትዮጵያ በአፋር እንዲሁም በትግራይ ክልል ተገኝተው በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አከባቢዎች ጎብኝተዋል። ከጉብኝቱ በኋላም ፕሬዝዳንቷ በጉብኝቱ ስለነበራቸው ቆይታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቷ ፥ "በተደረገው የሰላም ስምምነት ደስተኞች ነን። አሁን የመሳሪያ ድምጽ ጠፍቷል፤ የህጻናቱን ድምጽ ደግሞ በትምህርት ቤቶች መስማት እንፈልጋለን" ሲሉ ነው የገለጹት።

አክለውም በጉብኝታቸው ወቅት የደረሰው ውድመት አንዳስደነገጣቸውና "ትምህርት ቤቶችን፤ የጤና ተቋማትን፤ የውኃ መጠጥ አገልግሎቶች በፍጥነት ተመልሰው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ መደረግ አለበት። በእነዚህ ተቋማት የሚሰሩ ሠራተኞችም ወደ ሥራቸው ተመልሰው ደሞዝ እንዲከፈላቸው ማድረግና የወደሙ ንብረቶችን መተካት በቅድሚያ መሰራት ያለባቸው ሥራዎች ናቸው" ሲሉ ገልጸዋል።

የድርጅቱ የትግራይ ክልል ምላሽ ሰጪ ቡድን አስተባባሪ አቶ አታክልቲ ገ/ዮሐንስ ለቲክቫህ በሰጡት ማብራሪያ በክልሉ በኮቪድ እንዲሁም በጦርነት ምክንያት ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ለሦስት ዓመታት የራቁ መሆናቸውን ገልጸው ተማሪዎችን ወደ ትምህርት መመለስ ርብርብ የሚጠይቅ ሥራ መሆኑን አስረድተዋል።

ድርጅታቸው ባለፉት ጊዜያት በመቐለ በሚገኙ የስደተኛ ማዕከላት ህጻናት ከትምህርት እንዳይርቁ በማሰብ 850 ህጻናትን በመንግሥት የትምህርት ሥርዓት መሰረት ከ1ኛ - 3ኛ ክፍል ሲያስተምሩ የቆዩ መሆናቸውን አስታውሰዋል።[ በማዕከላቱ ከ3ኛ ክፍል በላይ ማስተማር አይፈቀድም።]

አቶ አታክልቲ ትልቁ ሥጋት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት መመለስ ብቻ ሳይሆን መምህራንንም ወደ ሥራ መመለስ አስቸጋሪ መሆኑን ያነሳሉ። "ቀደም ብለው የነበሩት መምህራን ወደ ጦር ግንባር፤ ከነበሩበት ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሁም ወደ ሌሎች ቢዝነሶች ውስጥ ስለገቡ መምህራኑን መመለስ አስቸጋሪ ያደርገዋል" ሲሉ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ቢገለጽም ድጋፉን በቀላሉ ማግኘት ግን እንደማይቻል ከዚህ ቀደም የነበሩ ሪፖርቶች ገላጭ ናቸው። የፕሬዚዳንቷ ጉብኝትም ድርጅቱ የሚያስፈልገውን ኃብት ለማሰባሰብ ተጽኖ ለመፍጠር የታቀደ ለመሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌግራም፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ መሰል የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እስካሁን ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ #ገደብ ከተደረገባቸው አንድ ወር ሊደፍን ነው። የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ " ለምን ገደብ እንደተጣለ " እንዲሁም " ገደቡ መቼ እንደሚነሳ " በየትኛውም አካል በኩል #ለህዝቡ ማብራሪያም ሆነ ገለፃ ያደረገ የለም። ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ…
#ETHIOPIA

ኢትዮጵያ ውስጥ ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ መሰል የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ ገደብ ከተደረገባቸው ከአንድ ወር በላይ ተቆጥሯል።

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ " ለምን ገደብ እንደተጣለ " እንዲሁም " ገደቡ መቼ እንደሚነሳ " በየትኛውም አካል በኩል እስከ ዛሬ ድረስ ለህዝብ ማብራሪያ ሆነ ገለፃ ያደረገ የለም።

ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛዎች በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች በኩል ተገድበው የሚገኙ ሲሆን ገደቡን በVPN በማለፍ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

#ትዊተር#ኢንስታግራም መሰል የማህበራዊ መገናኛዎች ገደብ ያልተደረገባቸው ናቸው።

@tikvahethiopia
#ATTENTION

" በድርቅ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ ተጋልጠዋል " - የአማሮ ልዩ ወረዳ

• " ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ ነው " - የቡርጂ ልዩ ወረዳ

በደቡብ ክልል አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ከ136 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

#አማሮ

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የአማሮ ልዩ ወረዳን ዋቢ አድርጎ ባሰራጨው መረጃ ፤ በልዩ ወረዳው ለረጅም ጊዜ ዝናብ ባለመጣሉ በ22 ቀበሌዎች ድርቅ ተከስቷል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በልዩ ወረዳው ከ96 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

በድርቁ ከ3 ሺህ 500 በላይ የቤት እንስሳት በድርቁ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል።

በልዩ ወረዳው የተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የህብረተሰቡን ተጋላጭነት እንዳባባሱት ልዩ ወረዳው አመልክቷል።

በድርቁ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በተለያየ ጊዜ እርዳታ ቢያደርግም በልዩ ወረዳው ከከተከሰተው ጉዳት አንፃር ድጋፉ በቂ አለመሆኑን ልዩ ወረዳው አሳውቋል።

#ቡርጂ

የቡርጂ ሶያማ ልዩ ወረዳ በበኩሉ በልዩ ወረዳው በተከሰተው ድርቅ 83 ሺህ 528 ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቋል።

በልዩ ወረዳው ከ30 ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውም ተጠቁሟል።

ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ ተገልጿል።

ከክልሉ መንግስት በተጫማሪ የአካባቢው ተወላጆች እና ግለሰቦች እርዳታ ቢያደርጉም በልዩ ወረዳው ከተከሰተው ድርቅ አንፃር የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት በቂ አለመሆኑ ተመላክቷል።

በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት እና መልሶ ለማቋቋም ረጂ ድርጅቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረታቸውን ወደ ልዩ ወረዳው እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮንሶ

በኮንሶ ዞን በተከሰተ ድርቅ ከ800 ሺህ በላይ ዜጎች ለአስቸኳይ ድጋፍ መዳረጋቸውን ዞኑ አሳውቋል።

ለተከታታይ 5 ዓመት የተከሰተው የዝናብ መዘግየት እና እጥረት ባስከተለው ድርቅ ለአስቸኳይ ድጋፍ የተዳረጉት 822 ሺ 526 ዜጎቻችን ናቸው።
 
የተከሰተው ድርቅ ዜጎች ላይ አስከፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

Credit : #FBC #SRTA

@tikvahethiopia
#EOTC

ቅዱስ ሲኖዶስ የፊታችን ረቡዕ #አስቸኳይ ጉባኤ ሊያደርግ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ረቡዕ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚካሄድ ዛሬ አሳውቋል።

በዚህም በአዲስ አበባ አቅራቢያና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ አዳራሽ እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ጥሪ ማስተላለፉን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia
#ኤርትራ #ሱዳን

የጎረቤት ሀገር ሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት ጄነራል ሞሀመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄመቲ) ዛሬ ሰኞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ #ኤርትራ፣ አስመራ ማቅናታቸው ተሰምቷል።

ሄሜቲ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሁሉም መስክ ግንኙነታቸውን ማሳደግና ማጎልበት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ይፋዊ ውይይት ያደርሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia