TIKVAH-ETHIOPIA
#ሶማሌላንድ በሶማሌላንድ ግዛት በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርከታ ሰዎች ሰላም ፍለጋ ወደ #ኢትዮጵያ እየገቡ ናቸው። እስካሁን ግጭት የሸሹ ከ83 ሺ በላይ የሶማሌላንድ ነዋሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በመዝለቅ በሶማሌ ክልል መስፈራቸው ተነግሯል። የተመድ የስደተኞች ኮሚሽንን ዋቢ በማድረግ #ሪፖርተር ጋዜጣ እንዳስነበበው "ላስካኑድ" በምትባለው ከተማ በተከሰተው…
#Update
ሶማሊላንድ በግጭት እየተናጠች ትገኛለች።
በዚህ ግጭት ሳቢያ እስካሁን ወደ 100,000 የሚገመቱ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቀዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት ባለፈው አንድ ወር ብቻ 98,000 ሰዎች ከሶማሊላንድ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ማቋረጣቸውን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ " አካባቢው ድርቅ የተጫነው፣ የመሠረተ-ልማት እና ማኅበራዊ ተቋማት ጉድለት ያለበት ቢሆንም የአካባቢው ማኅበረሰብ የሶማሊላንድ ስደተኞችን በመቀበል አሳቢ መሆኑን እያስመሰከረ ነው " ሲሉ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከመድረሱም በፊት የአካባቢው ነዋሪዎች ስደተኞቹን በማስጠጋት እና ያላቸውን በማካፈል ላይ እንደሚገኙ አቶ ተስፋሁን ጨምረው ገልጸዋል።
ወደ ኢትዮጵያ ከተሻገሩት መካከል በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት የተመዘገቡት ግን 29,000 ብቻ ናቸው።
" አብዛኞቹ ሴቶች እና ሕጻናት " መሆናቸውን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ያረጋገጡት በዶሎ አዶ የድርጅቱ ተወካይ ማማዱ ዲያን ባልዴ ቁጥሩ ግን ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ እንደሚሔድ ተናግረዋል።
ተወካዩ ስደተኞቹ " መጠለያ የላቸውም። ምግብ፣ ውኃ፣ የሕክምና እገዛ ይሻሉ። እነዚህ ፍላጎቶች እጅግ አንገብጋቢ ናቸው " ብለዋል።
መረጃው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎትን ዋቢ በማድረግ የዘገበው ዶቼ ቨለ ነው።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia

" ባጃጅ ታግዷል "
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነገ የካቲት 30 ጀምሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ታገደ።
ከነገ ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ አገልግሎት መታገዱን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ " የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት እንዲያስችል አሰራር ማሻሻያ ስራዎችን በማከናወን ላይ እገኛለው " ብሏል።
የአሰራር ማሻሻያ ስራው ተጠናቆ እንዲሁም የአገልግሎቱ አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ከነገ የካቲት 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አከባቢ #ላልተወሰነ_ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል።

#አስቸኳይ
አስቸኳይ የነፍስ አድን እርዳታ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ።
የቡርጂ ልዩ ወረዳ ተከስቶ ባለው ድርቅ ምክንያት በመኖ እጥረት 4496 ዳልጋ/የቀንድ ከብቶች እና በርካታ የጋማ ከብቶች እንዲሁም ፍየልና በጎች እየሞቱ መሆኑ ተገልጿል።
አሁን ላይ በህይወት ያሉት እንስሳትም ከተኙበት መነሳት የማይችሉ የደከሙ እንደሆኑ ተገልጿል።
በወረዳው ዓመቱን ሙሉ ይፈሱ የነበሩ ወንዞች በመድረቃቸው እንስሳቱ ውሃ ፍለጋ ረጅም ኪሎ ሜትር ተጉዘው ከጠጡ በኋላ ደክመው መመለስ ሳይችሉ በዚያው በየመንገዱ እየሞቱ እንዳሉም ተነግሯራ።
በበሬ አርሶ የሚኖረው ህብረተሠብ በሬዎቹን በሞት በማጣቱ ለከፋ ረሀብ መጋለጡ ተጠቁሟል።
ክልቾ በተባለችው ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ይርጋለም ጮታ ከ30 የዳልጋ ከብቶች ውስጥ 23ቱ ሞተው 7ቱ በህይወት ያሉ ቢሆንም እነሱም ደክመው ለመሞት መቃረባቸውን አመልክተዋል።
እኚሁ አርሶ አደር ከነቤተሠባቸው በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሌሎችም አርሶ አደሮች ያሏቸውን ከብቶች በድርቁ እያጡ በመሆኑ ለአስከፊ ድህነትና ረሃብ እየተጋለጡ መሆኑን አስረድተዋል።
በወረዳው በህይወት ያሉትን እንስሳት ሽፈራውና ሌሎችም ቅጠሎች እየተቆረጠ የነፍስ ማቆያ ቢሆንም ከዚህ በኋላ ግን አስቸኳይ የመኖ እና የመድኃኒት ድጋፍ ካልተደረገ ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆን ወረዳው ገልጿል።
ሁሉም አካላት በድርቁ ለተጎዳው የቡርጂ ህዝብ የቻለውን ያህል እርዳታ በማድረግ የህይወት አድን ስራ እንዲሰራ ይፋዊ ጥሪ ከወረዳው ቀርቧል።
መረጃው ከቡርጂ ልዩ ወረዳ የተገኘ ነው።

" ተጥሎ የነበረው የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት እግድ ተነስቷል " - ዶ/ር ቀንኣ ያደታ
በአዲስ አበባ ከተማ ተጥሎ የነበረው የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት እግድ መነሳቱን የከተማዋ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ቀንአ ያደታ ፤ የመሬትና መሬት ነክ መረጃዎችን ለማጥራት ሲባል በጊዜያዊነት ተጥሎት የነበረው የአገልግሎት እግድ ተነስቷል ብለዋል።
እግዱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከትናትን የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱን ሃላፊው ተናግረዋል።
የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ባለጉዳዮችም አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ ከሚመለከተው አካል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
በመዲናዋ የመሬት ወረራንና ሕገወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሲባል የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት ከጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜያዊነት ታግዶ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
#ኤፍቢሲ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Apply now at Jasiri.org/application. Applications close April 5, 2023.
#ብርሃን_ባንክ
በሆቴሎች፤ በሱፐርማርኬቶች እና በቅርንጫፎቻችን በሚገኙት የፖስ ማሽኖቻችን የቪዛና ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው ግብይትዎን ያቅልሉ፡፡
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://yangx.top/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!

#Mekelle
የኢፌዴሪ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የባለድርሻ እና አጋር አካላት የውይይት መድረክ #በመቐለ ለመጀመርያ ጊዜ ይካሄዳል።
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ የባለድርሻ እና አጋር አካላት መድረክ ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በመቐለ እንዲደረግ የተወሰነበት ምክንያት ከሰላም ስምምነቱ ብኋላ ክልሉ ላይ አንፃራዊ መረጋጋት መፈጠሩ እና በሁለቱም ተስማሚ ወገኖች የመተማመን ጉዳዩ መጎልበቱን ማሰያ ነው ብሏል።
በመድረኩ ለመሳተፍ የተለያዮ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ከፌዴራል መንግስት የተላከ የልኡኳን ቡድን በአምባሳደር ተሾመ ቶጋ መሪነት ዛሬ መቐለ ገብቷል።
የፌደራል መንግስቱ ልኡኳን ብድኑ ከጠቅላይ ሚኒስተር ፅህፈት ቤት፣ የሰላም ሚኒስቴር ፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የሰቪክ ማህበራት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ከንግድ ሚኒስቴር እና የተለያዮ ክልሎች ተወካዮች ያካተተ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
#ድምፂወያነ

#EOTC
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፤ የ " ቤተክርስቲያን ችግሮች እና ዘለቄታዊ መፍትሔ ጥናትና ትግበራ ኮሚቴ " በሚል ስያሜ እንደተቋቋመ የገለፀችውና ከሁሉም የሞያ ዘርፎች የተውጣጡ የቤተክርስቲያኗን ልጆች ያቀፈው ቡድን ወደ ትግበራ ሊገባ መሆኑን አስታወቀች።
ኮሚቴው የጥናታዊ ጽሑፍ በማቅረብ አላማውን እና የአሰራር ሂደቱን ያብራራ ሲሆን ሰፊ ውይይት አካሂዷል ተባቧል።
በቅድስት ቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ #ከዶግማ_በስተቀር ከላይ ጀምሮ እስከ ታች ድረስ ያሉ ችግሮችን ለማስተካከል እንደሠራም ተገልጿል።
ውጤቱን በተመለከተ ቤተክርስቲያን የራሷ #መንፈሳዊ_ፍርድ_ቤት እንዲኖራት ማድረግን ጨምሮ 25 ዝርዝር ነጥቦች ላይ ማተኮሩ ተመላክቷል።
#ከ90_በላይ አባላትን በጥናት ያሳተፈው ኮሚቴ በ14 ቡድኖች ተዋቅሮ ስራውን #በቅርቡ እንደሚጀምር ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።
#EOTC_TV

#AddisAbaba
" የቤት ኪራይ ዋጋ አከራዮች እስክ ሰኔ #እንዳይጨምሩ ተወስኗል "
የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ 2ኛ አመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
ካቢኔው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ፦
1. የመኖሪያ ቤቶችን በመንግስትና የግል አጋርነት በ70/30 አሰራር መቶ ሺህ የሚደርሱ ቤቶችን ለመገንባት የተዘጋጀውን 35 ሄክታር መሬት ላይ ተወያይቶ ወስኗል።
2. ሃገራዊ ፋይዳ ያላቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች እና የስራ እድል የሚፈጥሩ የ373 ፕሮጀክቶች የመሬት ጥያቄ እነሱም ፦
2.1. ለኢንዱስትሪ ልማት
2.2 ሆቴሎችና ሞሎች ፣
2.3 የሀይማኖት ተቋማት ፣
2.4 ቀደም ሲል በካቢኔ ተወስነው የመሬት ለውጥ የቀረበባቸው ቦታዎች ፣ ለተለያዩ የግንባታ ግባዓት ማስቀመጫ የሚሆኑ ጊዜያዊ መጠቀሚያ ቦታዎች ናቸው።
3. ወቅታዊ የኑሮ ውድነትና የገበያ መረጋጋት የዋጋ መናር መነሻ በማድረግ በአስቸኳይ ምርት ወደ ከተማ እንዲገባና እንዲሰራጭ ግብረ ኃይል አቋቁሟል።
4. ለተማሪዎች ምገባ የሚያቀርቡ እናቶች በአሁኑ ዋጋ ማቅረብ መቸገራቸውን መነሻ በማድረግ ለተማሪዎች ምገባ በወር 54,000,000 ብር (ሀምሳ አራት ሚሊየን) በዓመት 540,000,000 ብር (አምስት መቶ አርባ ሚሊየን) ተጨማሪ በጀት አጽድቋል፤ ይህ ማለት ለአንድ ተማሪ በቀን ሃያ ብር የነበረው ወደ የሀያ ሶስት ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል።
5. ከወቅቱ ዋጋ መናር እና የገበያ አለመረጋጋት ጋራ ተያይዞ የነበረው የቤት ኪራይ ዋጋ አከራዮች እስክ ሰኔ እንዳይጨምሩ ተውስኗል።
(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር)
@tikvahwthiopia