TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Mekelle

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን የያዘ የልዑካን ቡድን ነገ ማክሰኞ ጥር 2/ 2015 ዓ/ም ወደ ትግራይ ክልል መዲና ፤ መቐለ እንደሚጓዝ " ኢትዮጵጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

የልዑካን ቡድኑ የሚመራው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሲሆን ወደ መቐለ የሚጓዘው የክልሉ ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት መሆኑ ተነግሯል።

ቡድኑ ወደ መቐለ ነገ ረፋድ በአውሮፕላን የሚጓዝ ሲሆን በመቐለ ከተማ የሚኖረው ቆይታ የአንድ ቀን ብቻ መሆኑን በጉዞው ላይ ተሳታፊ የሆነ አንድ አትሌት ተናግሯል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ለገሰ ለድረገፁ በሰጡት ቃል ፤ የፌዴሬሽኑ አመራሮች እና አባላት በአንድ ቀን ቢመለሱም እዚያው የሚቆዩ አትሌቶች ግን ይኖራሉ ሲሉ አረጋግጠዋል።

በዚህ ጉዞ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና የተለያዩ የስራ ክፍል አባላት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በነገ ጉዞ ከሚሳተፉ የትግራይ ክልል ተወላጅ ከሆኑ አትሌቶች መካከል ፦

- አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣
- አትሌት ጎተይቶም ገብረ ስላሴ
- አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ እንደሚገኙበት ተናግሯል።

ምንጭ፦ https://ethiopiainsder.com/2023/9310/

@tikvahethiopia
#ግሬስ

ከሆስፒታል እንደወጡ ለማገገም የት እንደሚሄዱ ግራ ገብቶታል ? የቤትዎ አለመቸት ፣ የህክምና መሳሪያ እና ባለሙያ አለመኖር እንዲሁም ያስታማሚን ችግር ለመፍታት ወደተቋቋመው ግሬስ የህሙማን እና የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ብቅ ይበሉ።

ሁሉን ነገር ባሟላ ማገገምያ ማእከላችን ልምድ ባላቸው ዶክተር እና ነርሶቻችን ቤተሰብዎን ከሆስፒታል እንደወጡ በመንከባከብ እናግዝዎታለን ፤ በነፋሻ ግቢያችን ውስጥ 24/7 የNursing Home አገልግሎት ያገኛሉ።

አድራሻ ፦ አያት አደባባይ ወደ ለገጣፎ በሚወስደው መንገድ ላይ በቀኝ በኩል በፍሬሽ ኮርነር ገባ ብሎ 2ኛ ቅያስ ወደ ቀኝ በድጋሚ 3ኛ ቅያስ ወደ ቀኝ ታጥፈው ያገኙናል።

ለበለጠ መረጃ በ0967-03-42-42 ወይም በ0954-99-11-90 ይደውሉ።
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የሚመራ ልዑካን ቡድን ዛሬ ወደ ትግራይ ክልል፣ መቐለ አምርቷል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ ያመራው የልዑካን ቡድኑ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት ያለመ ጉዞ ነው ያደረገው።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የቢሮ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና የትግራይ ክልል ተወላጅ አትሌቶች የጉዞው አካል ናቸው።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ላሊበላ ለልደት በዓል ዝግጅቷ ምን ይመስላል ? የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ታህሳስ 29/2015 የሚከበረውን የልደት በዓልን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መጠናቁቁን አሳውቋል።   የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ተስፋ ሃብቴ በሰጡት ቃል፦ - ከወትሮው በተለየ መልኩ በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማዋ የሚመጡ ዕንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት ተደርጓል።…
በዘንድሮው የልደት በዓል #በላሊበላ ምን ያህል ሰው ተገኘ ?

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት የተነሳ ባለፉት 3 ዓመታት የገና በዓል በታሪካዊቷ ላሊበላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ማክበር ሳይቻል ቀርቶ ነበር።

የዘንድሮው በዓል ግን በተፈጠረው ሰላም የተነሳ በተሳካና በሰላማዊ ሁኔታ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ታጅቦ መካሄዱ ተገልጿል።

የላልይበላ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ፤ በቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ታኅሣሥ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በተከበረው የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ላይ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ዜጎች (1,975,745) መገኘታቸውን አሳውቋል።

ለበዓሉ ከተገኙት መካከል 418ቱ የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው።

ከጦርነት በኃላ ሰላም በመስፈኑ ትልቅ ለውጥ መኖሩን የገለፀው ፅ/ቤቱ ባለፈው ሙሉ ዓመት ላሊበላን የጎበኙት 776 የውጭ ዜጎች ብቻ እንደነበሩ አስታውሶ ዘንድሮ ግን በገና በዓል ብቻ 418 የውጭ ዜጎች በዓሉን አክብረዋል።

በበዓሉ በተሳተፉ ቱሪስቶች አማካኝነት የአገልግሎት ዘርፉ #የተሻለ_ገቢ እንደተፈጠረለት ተመላክቷል።

በተለይ ሆቴሎች፣ ምግብና መጠጥ አቅራቢ ድርጅቶች እንዲሁም አስጎብኚዎች በኮቪድና በጦርነቱ ምክንያት ተዳክሞ የነበረው ሥራቸው መነቃቃት እንደፈጠረላቸው ፅ/ቤቱ ገልጿል።

ወደላልይበላ የመጡት ቱሪስቶች ከበዓሉ አከባበር ባለፈ በከተማዋ የሚገኙ ቅርሶችን ተዘዋውረው እንዲጎበኙ ጥረት ስለመደረጉ ተገልጿል።

Lalibela Communication
Photo Credit : EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ወደ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) እንደሚመጡ ተሰምቷል። የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪን ጋንግ በቅርቡ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እንደሆነ ተሰምቷል። ኪንግ ጋንግ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በአሜሪካ የቻይና አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።…
#ETHIOPIA #CHINA

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሆነ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ከምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሚኒስትሩ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ባሰራጩት አጭር ፅሁፍ ፤ " የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አሁንም ጸንቶ ቀጥሏል " ብለዋል። " የዛሬው ውይይት ይህንን እና በልማት የምንጋራውን ስልታዊ የጋራ ዓላማ፤ እንዲሁም አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን አጉልቶ አሳይቷል " ሲሉ ገልፀዋል።

የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአቶ ደመቀ ጋር በተገናኙበት ወቅት የፖለቲካ ምክክር ማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት እና ከፊል የዕደ ስረዛ ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱ የሁለቱን አገራት ጠንካራ ግንኙነትን ለማስቀጠል እና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋጋር እንደሚረዳ ተገልጿል።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሁለትዮሽ ፣ቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል አሳውቀዋል።

ቺን ጋንግ በቅርቡ ወደ ስልጣን የመጡ ሲሆን የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በ #ኢትዮጵያ እያደረጉ ናቸው።

መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia